Telegram Web Link
በኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በርካታ ህዝብ የሚታደምበት እና አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ትኩረት ሰጥተው ወደ ተግባር በመግባት እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጾ በተለይ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተከበሩ ኃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ወሳኝ ስራ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሶ የዘንድሮው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሠላም እንዲከበር የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ በፀጥታ አካላት ስም ጥሪውን  አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ፦
፨ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ሜክሲኮ፣
፨ ከወሎ ሠፈር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ፣
፨ ከቄራ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ ቡልጋሪያ፣
፨ ከመርካቶ በአቡነ ተ/ኃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ የሚወስደው መንገድ አቡነ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ፣
፨ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣
፨ ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
፨ ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣
፨ ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣
፨ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣
፨ ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
፨ ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣
፨ ከሐራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት፣
፨ ከአዲሱ ገበያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮዲሮማ፣
፨ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ  ቤተ መንግስት አጠገብ፣
፨ ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
፨ ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ
ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የሸገር ከተማ አካባቢዎች በርካታ ህዝብ በዓሉን ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ ወደ ከተማችን የሚገባ በመሆኑ መላው ህብረተሰብ ተገቢውን አክብሮት በመስጠት የእንግዳ ተቀባይነት እሴታችንን አጉልቶ ሊያሳይ እንደሚገባ ፖሊስ አስታውሶ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
*
BREAKING : በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል። ጠሚ አቢይ

በተመሳሳይም በአመት 1.33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር አስጀምረናል። ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ከሁሉም በላይ ፕሮጄክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም። ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል። ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ-ማይኒንግ ሥራዎቻችን አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርብልናል። ዛሬ በሶማሌ ክልል የጀመርናቸው ከተያያዥ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ። የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግመሉ ጉዞ በውሾች ጩኸት አይቆምም።
በ አዲስ አመት አዲስ ነገር  ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ

20% ቅድመ ክፍያ

#ለ 8 ቀድመው ለመጡ ብልህ እድለኞች ብቻ በማስታወቂያ ዋጋ እናስተናግዳለን

📍መስቀል ፍላወር 70% የተገነባ

☎️
+251929261190

👉 1,127,000 ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

➣ Studio 49 ካሬ ጠቅላላ ዋጋ 5,635,000 ብር
➣ 2 መኝታ 95 ካሬ ጠቅላላ ዋጋ 9,405,000 ብር
➣ ፔንታ ሀውስ 259 ካሬ ጠቅላላ ዋጋ 25,641,500 ብር

ልብ ይበሉ ለ 8 እድለኞች ብቻ የወጣ የማስታወቂያ ዋጋ ነው

ለበለጠ መረጃ
         👇
☎️
+251929261190
“ ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ትልልቅ መኪኖች (ትራክ) ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት የተከለከለ ነው “ - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት ባሰሙት ዘለግ ያለ ንግግር ፕሮጀክቱ ለሃይል ማመንጫ እና ለክሪፕቶ ማይኒንግ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ጭምር የሚያቀርብ መሆኑን ጠቁመዋል።

“ ቢበዛ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 2 ሺ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ ባሶች አሁን ከሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ እንቀይራለን “ ሲሉ የተደመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም የትራንስፖርት ወጪ በ 50 በመቶ የሚቀንስ መሆኑን አስረድተዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምርቃቱ ወቅት ባሰሙት ንግግር ምን አሉ?

“ በእዚህ አመት ቢበዛ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ 2 ሺህ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ከተማ እና ወደ ክልል የሚሄዱ ባሶች አሁን ከሚጠቀሙት ነዳጅ ወደ ጋዝ እንቀይራለን።

እነዚህ 2 ሺህ መኪኖች ሲቀየሩ የትራንስፖርት ዋጋ ቢበዛ ወይም ቢያንስ አሁን ካለው በ 50 በመቶ በሚቀጥለው አመት እንቀንሳለን።

በከተሞቻችን ያለው ዋናው ችግር የ ሊቪንግ ኮስት ችግር ነው የሊቪንግ ኮስት አንደኛው ምክንያት ቤት ነው።

ከ1.5 ሚሊየን በላይ ቤቶችን እንገነባለን ያልነው የዜጎቻችን የሊቪንግ ኮስት ጫና የሚያስከትለውን አንዱን ችግር እንቀርፋለን ለማለት ነው።

ሁለተኛው ትራንስፖርት ነው በከተማ ትራንስፖርት 50 በመቶ አሁን ያለውን ኮስት ቀነስን ማለት በአነስተኛ ገቢ ወጥተው የሚገቡ ሰርተው የሚውሉ ዜጎች በእጅጉ ኑሯቸውን ለማገዝ የሚጠቅም ነው።

ሦስተኛ ኢነርጂ ስናመርት ለክሪፕቶ ብቻ ሳይሆን ለብርሃንም ጭምር ስለሆነ ጋዝ ምግባችን፣ ጋዝ ትራንስፖርታችን፣ ጋዝ ለኢነርጂ ማምረቻ የሚውል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው።

ትላልቅ መኪና ወይም ትራክ ወደ ኢትዮጵያ ስታስገቡ የነበራቹ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ልክ ለትናንሽ መኪኖች ከኤሌክትሪክ መኪና ውጪ ማስገበት ታግዶ እንደቆየው ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ትራክ ወደ ኢትዮጵያ መስገባት የተከለከለ ነው።

በአንጻሩ ማንኛውም የግል ባለሃብት ጋዝ የሚጠቀሙ ትራኮች የሚያስገባ ከሆነ ከቀረጥ ነጻን(Duty free) ጨምሮ አስተማማኝ ድጋፍ የሚደረግላቹ ሲሆን እንደሃገር እያወጣን ያለነውን ከፍተኛ ወጪ ለመቀነስ ፣ የሎጅስቲክስ ኮስት ለመቀነስ፣ ትራንስፖርት ለማሳለጥ የግሉ ሴክተር ከእዚህ ቀን በኋላ በጋዝ የሚጠቀሙ ትራኮች በማስገባት የሃገሩን የኢኮኖሚ እድገት እንዲያፋጥን ከአደራ ጭምር ላሳስብ እወዳለሁ “ ብለዋል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“ክቡርነትዎ፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ዛሬ የምነግርዎት አንድ ነገር፣ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ መላው አፍሪካውያን በእርስዎ እንደምንኮራ ነው” - አሊኮ ዳንጎቴ
2025/11/02 04:52:04
Back to Top
HTML Embed Code: