🌹 #የኅዳር_3_ግጻዌ 🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጢሞቴዎስ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ ስለዚህ ወንድሞችን ብታሳስብ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃል የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።
⁷ ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ።
⁸ ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።
⁹ ይህ ቃል የታመነ ሁሉም እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤
¹⁰ ይህን ለማግኘት እንደክማለንና፥ ስለዚህም እንሰደባለን፤ ይህም ሰውን ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።
¹¹-¹² ይህን እዘዝና አስተምር። በቃልና በኑሮ በፍቅርም በእምነትም በንጽሕናም ለሚያምኑቱ ምሳሌ ሁን እንጂ፥ ማንም ታናሽነትህን አይናቀው።
¹³ እስክመጣ ድረስ ለማንበብና ለመምከር ለማስተማርም ተጠንቀቅ።
¹⁴ በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።
¹⁵ ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር።
¹⁶ ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵-¹⁶ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።
¹⁷ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።
¹⁸ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
¹⁹ ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።
²⁰ እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።
²¹ እውነትን የምታውቁ ስለ ሆናችሁ፥ ውሸትም ሁሉ ከእውነት እንዳልሆነ ስለምታውቁ እንጂ እውነትን ስለማታውቁ አልጽፍላችሁም።
²² #ሎቱ_ስብሐት ክርስቶስ አይደለም ብሎ ኢየሱስን ከሚክድ በቀር ውሸተኛው ማን ነው? አብንና ወልድን የሚክድ ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 19
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁸ ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።
⁹ አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር።
¹⁰ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲህ ሆነ።
¹¹ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_3_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ወዘሕጎ ያነብብ መዓልተ ወሌሊተ። ወከውን ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ኀበ ሙኃዘ ማይ። እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ"። መዝ.1፥2-3።
#ትርጉም፦ "ነገር ግን በ #እግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል"።መዝ.1፥2-3።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_3_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ከዚያም አልፎ ወደ ምኩራባቸው ገባ።
¹⁰ እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ። በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት።
¹¹ እርሱ ግን፦ ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት፥ ይዞ የማያወጣው ሰው ማን ነው?
¹² እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዶአል አላቸው።
¹³ ከዚያም በኋላ ሰውየውን፦ እጅህን ዘርጋ አለው። ዘረጋትም፥ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹
የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የ #ማርያም_ቅዳሴ ነው። መልካም የጻድቁ ንጉሥ የቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ከሞት የተሰወረበት (የስዋሬ) በዓል፣ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ፣ የአቡነ ፍሬ ካህን፣ የአቡነ ዓምደ ሚካኤል የዕረፍታቸውና የጾም ጊዜ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። 🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️

👍2
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በማን እጅ ነው የመነኮሱት?
Anonymous Quiz
38%
በአቡነ ኢየሱስ ሞዓ
13%
በአቡነ ዮሐኒ
38%
በአቡነ ተክለ ሐይማኖት
13%
በአቡነ አረጋዊ
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ካመነኮሱዋቸው ልጆች መካከል ያልሆነቱ ማን ናቸው?
Anonymous Quiz
10%
አቡነ ሳሙኤል ዘዌልድባ
14%
አቡነ ሳሙኤል ዘቆይጻ
31%
አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ
45%
አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኮሳቱ "ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ ያደረጉት አባት ማን ይባላሉ?
Anonymous Quiz
19%
አቡነ አሮን
56%
አቡነ ፍሬ ካህን
17%
አቡነ አሞኒ
9%
አቡነ አበይዶ
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
ከአረፈበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሥጋው አልተለወጠም ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ ሁሉ ያዩታል እነርሱም በቅርብ ጊዜ እንዳረፈ ያስባሉ እርሱ ግን ያረፈው ለአኖሬዎስና ለአርቃዴዎስ አባታቸው በሆነ በታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው። ይህ አባት ማነው?
Anonymous Quiz
42%
አባ ኪርያቆስ
10%
አባ ጴጥሮስ
21%
አባ ቄርሎስ
27%
አባ አብሳዲ
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
ከሃዲውን ንጉሥ ማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ዕራቁታቸውን ከጉድጓድ ጨመራቸው በላያቸውም የጒድጓዱን አፍ ዘጋ በውስጧም ነፍሳቸውን አሳለፉ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ። እኚህ ሰማዕታት እነማን ናቸው?
Anonymous Quiz
13%
አባ አትናቴዎስና ቅድስት ሙስያ
9%
አባ ገብርኤልና ቅድስት ኢራኢ
43%
አባ አትናቴዎስና ቅድስት ኢራኢ
36%
አባ እንዲራኒቆስና ቅድስት አትናስያ
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ገላውዴዎስ የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ ይልቁንም በሃይማኖትና በበጎ ሥራ የበለጸጉ ናቸው። ይህንንም ቅዱስ በቅዱሳን አርባዕቱ እንስሳ በዓል ወለዱት ስሙንም ማን ብለው ሰየሙት?
Anonymous Quiz
8%
ቅዱስ በእደ ማርያም
29%
ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል
51%
ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ
12%
ቅዱስ እስክንድር
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
ውኃ ይቀዳላቸው የነበረውን አህያቸውን አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን 7ዓመት ለገዳማቸው ውኃ ያስቀዱት ታላቁ አባት ማን ይባላሉ?
Anonymous Quiz
16%
አቡነ መልከ ጸዴቅ
16%
አቡነ ሊባኖስ
13%
አቡነ ተክለ አልፋ
54%
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ
#ኅዳር_4
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም ኅዳር አራት
በዚህችም ቀን የደማስቆው #ቅዱስ_ቶማስ አረፈ፣ #ቅዱስ_ያዕቆብና_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ፣ #ቅዱሳን_አቢማኮስና_አዛርያኖስ በሰማዕትነት አረፉ፣ የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር የሆኑት #አቡነ_አበይዶ ዕረፍታቸው ነው፡፡
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ቶማስ_ዘደማስቆ
ኅዳር አራት በዚህችም ቀን የደማስቆ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ቶማስ በግብጽና በሶርያ እስላ*ሞች በነገሡ ጊዜ በሰማዕትነት አረፈ።
ቅዱስ ቶማስ በ7ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዶ ያደገ ሶርያዊ ክርስቲያን ነው። ከልጅነቱ እንደሚገባ መጻሕፍትን ተምሮ ለዲቁና፣ ለቅስና፣ ከዚያም ለዽዽስና በቅቷል። በወቅቱ የሶርያ ዋና ከተማ በሆነችው ደማስቆ ላይ ተሹሞ ያገለግልም ነበር።
ታዲያ ዘመኑ በየቦታው ደም የሚፈስበት ነበርና የ #ክርስቶስን መንጋ መጠበቁ ቀላልና የዋዛ ሥራ አልነበረም። በዘመኑ የክርስቲያኖችን ደም ያፈሱ የነበሩት ደግሞ ተንባላት (የመሐ*መድ ተከታዮች) ናቸው። 7ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲደርስም ተንባላት ግብጽንና ሶርያን በቁጥጥር ሥር በማድረጋቸው ክርስቲያኖች ተቸገሩ።
በወቅቱም ቅዱስ ቶማስ ሲያስተምር የሰማው አንድ መሐ*መዳዊ "እንከራከር" አለው። ቅዱሱም ሊቅ ነበርና ስለ መሐ*መድ ሐሰተኛነት ስለ #ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ካስረዳው በኋላ ንጹሕና ሰማያዊ ሕግ ቅዱስ ወንጌል እንጂ ቁርዓን እንዳልሆነ ነገረው።
በአደባባይ በመረታቱ ያፈረው መሐመ*ዳዊም በብሽቀት ሒዶ ለደማስቆው ገዢ ከሰሰው። ቅዱስ ቶማስም ተይዞ ቀረበ። "እንዴት እምነታችን እስል*ምናን ትሳደ**ባለህ?" ቢለው ቅዱሱ "እውነቱን ተናገርኩ እንጂ አልተሳደብኩም" ሲል መለሰለት።
መኮንኑም "እሺ! #ክርስቶስ ማን ነው? ስለ ወንጌልና ቁርዓ**ንስ ምን ትላለህ?" ሲል የተሳለ ሰይፍ አውጥቶ ጠየቀው። የቀናችው እምነት ክርስትና ክብርነቷ በሰማይ ነውና መጨከንን ትጠይቃለች።
ቅዱስ ቶማስ ምንም ሳይፈራ "ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ የሰማይና የምድር ፈጣሪና አምላክ ነው።
ቅዱስ ወንጌል ሰማያዊና የሕይወት ሕግ ሲሆን ቁርዓን ደግሞ የመሐመድ የፈጠራ መጽሐፍ ነው።" ይህንን የሰማው መኮንን በቁጣ አንገቱን እንዲመቱት አዘዘ። ቅዱስ ቶማስም በዚህች ቀን ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አንገቱን ሰጠ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቶማስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ያዕቆብ_ወዮሐንስ
ዳግመኛ በዚህችም ቀን የቅዱሳን ያዕቆብና የሀገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ ዮሐንስ የሐርመዝ ልጅ በሆነ በፋርስ ንጉሥ በሳቦር እጅ በሰማዕትነት አረፉ።
አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር። እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን) በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው። ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው።
ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ። ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው። ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል።
በኋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም። የ #ክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ እያናዘዙ ጠበቁላት። ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው።
በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው። ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ። አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት።
ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው። ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ።
"አምላክ አንድ #እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው። እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_አቢማኮስ_ወአዛርያኖስ
ዳግመኛ በዚህች ቀን ከሮሜ አገር ቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ በሰማዕትነት አረፉ።
አሁን ደግሞ ወደ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ወደ ዋናው ዘመነ ሰማዕታት እንመለስ። በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩ ቅዱሳን ሰማዕታት 2ቱ ቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ ናቸው። አውሬዎቹ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ዓለምን ለ2 ተካፍለው በክርስቲያኖች ላይ ግፍን ሲሰሩ 2ቱ ቅዱሳን በሮም ግዛት ሥር ይኖሩ ነበር።
በዘመኑ እንኳን ቤተ ክርስቲያን ማነጸ መዘመር እምነትን መግለጥ ይቅርና ሲያማትቡ መታየት እንኩዋ ያስገድል ነበር። ነገሥታቱ የሾሟቸው ተከታዮቻቸው ክርስቲያኖችን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበትም አላውል አሉ።
ታላቅ ግፍ ሰቆቃና ጭንቅ በሆነበት በዚያ ወራት የሞተው ሙቶ እኩሉ ሲሰደድ ቅዱሳን አቢማኮስና አዛርያኖስ ግን በከተማ መሐል ተረጋግተው #ክርስቶስን ያመልኩ ነበር። ይህም ተደርሶባቸው ተከሰሱና ተይዘው ቀረቡ።
መኮንኑ 2ቱን ክርስቲያን ወጣቶች ሲመለከታቸው ምንም የፍርሃት ምልክት አልተመለከተባቸውምና ተገረመ። "ማንን ታመልካላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስን!" ሲሉ መለሱለት።
" #ክርስቶስን ትክዳላችሁ ወይስ ትሞታላችሁ?" ቢላቸው "ሰነፍ!" ሲሉ በአደባባይ ገሰጹት። "የፈጠረ፣ ያከበረ፣ #ቅዱስ_ሥጋውን #ክቡር_ደሙን የሰጠ #ጌታ እንዴት ይካዳል?!" ሲሉም እቅጩን ነገሩት። በድፍረታቸው የደነገጠው መኮንኑም በዚያች ሰዓት ሞትን አዘዘባቸው። በዚህች ቀንም አንገታቸውን ተሰይፈው ለክብረ ሰማዕት በቅተዋል።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_አበይዶ
ዳግመኛም በዚህች ቀን የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር የሆኑት የኢትዮጵያዊው አቡነ አበይዶ ዕረፍታቸው ነው፡፡ የታላቁ አባት የአባ ዮሐኒ ደቀ መዝሙር ናቸው፡፡ አባ ዮሐኒ ዕረፍታቸው ኅዳር 5 ስለሆነና የአቡነ አበይዶም ታሪክ ከአባ ዮሐኒ ጋር የተገናኘ ስለሆነ በዚሁ ዕለት አንድ ላይ እናየዋለን፡፡ ኅዳር 4 ቀን ግን የአቡነ አበይዶ ዕረፍታቸው መሆኑን ብቻ ጠቅሰን እናልፋለን፡፡ ስንክሳሩም ስማቸውን ብቻ ጠቅሶት ያልፋል፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_4 እና #ከገድላት_አንደበት)

🌹 #የኅዳር_4_ግጻዌ 🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_4_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
2ኛ ቆሮ 11
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልሰናከልምን?
³⁰ ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ።
³¹ ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።
³² በደማስቆ አርስጦስዮስ ከተባለ ንጉሥ በታች የሆነ የሕዝብ ገዥ ሊይዘኝ እየወደደ የደማስቆ ሰዎችን ከተማ ያስጠብቅ ነበር፥
³³ በቅጥሩም ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝና ከእጁ አመለጥሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጴጥሮስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
¹⁰ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።
¹¹ ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
¹² እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።
¹³ ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
¹⁴ በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፥ በደማስቆም ለተቀመጡት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደ ሆነ አስረድቶ መልስ ያሳጣቸው ነበር።
²³ ብዙ ቀንም ሲሞላ አይሁድ ሊገድሉት ተማከሩ፤
²⁴ ሳውል ግን አሳባቸውን አወቀ። ይገድሉትም ዘንድ በሌሊትና በቀን የከተማይቱን በር ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤
²⁵ ደቀ መዛሙርት ግን በሌሊት ወስደው በቅጥር ላይ አሳልፈው በቅርጫት አወረዱት።
²⁶ ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከደቀ መዛሙርት ጋር ይተባበር ዘንድ ሞከረ፤ ሁሉም ደቀ መዝሙር እንደ ሆነ ስላላመኑ ፈሩት።
²⁷ በርናባስ ግን ወስዶ ወደ ሐዋርያት አገባውና ጌታን በመንገድ እንዴት እንዳየውና እንደ ተናገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እንዴት እንደ ነገረ ተረከላቸው።
²⁸ በጌታም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እየተናገረ በኢየሩሳሌም ሲወጣና ሲገባ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_4_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኵሎ፡አሚረ። ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ። ንቃሕ እግዚኦ ለምንት ትነውም"። መዝ 43(44)፥22-23።
#ትርጉም፦ "ስለ አንተ ሁልጊዜም ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል። አቤቱ፥ ንቃ፤ ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፥ ለዘወትርም አትጣለን"።መዝ. 43(44)፥22-23።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_4_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇🌹
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤
³³ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።
³⁴ በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።
³⁵ ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤
³⁶ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል።
³⁷ ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤
³⁸ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
³⁹ ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል።
⁴⁰ እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
⁴¹ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ 🌹
# ኅዳር_4_ቀን የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ቶማስ ዘደማስቆ፣ የቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ፣ የቅዱሳን አቢማኮስና ወአዛርያኖስ፣ ለታላቁ አባት ዘካርያስ፣ ለጉባኤ ቅዱሳን ሰማዕታት እንዲሁም ለአባ አበይዶ የዕረፍት በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።

#የንስሐ_ሂደትና_አፈጻጸም
#ንስሐ ሦስት የአፈጻጸም ደረጃዎች አሉት
1ኛ, የ #ንስሐ የመጀመሪያ ደረጃ
የ #ንስሐ የመጀመሪያ ደረጃ ኃጢያትን መተው ብቻ ሳይሆን #ንስሐ ለመግባት ማሰብ ወይም መፈለግ ነው። ይህ ኃጢያትን ከመተው የሚቀድም ነው። ሰዎች #ንስሐ ለመግባት ባላሰቡና ባልፈለጉ መጠን በኃጢያት እየተደሰቱ ኃጢያት እየሰሩ ይኖራሉ። በእነርሱ አመለካከትም የያዙት የኃጢያት ኑሮአቸው መልካም ስለሚመስላቸው አይለወጡም። ስለዚህ #ንስሐ ለመግባት ማሰብና መፈለግ የ#ንስሐ የመጀመሪያው ደረጃ ነው።
2ኛ, ሁለተኛው ደረጃ
የ #ንስሐ ሂደት ሁለተኛ ደረጃ ኃጢያትን መተው ነው። ኃጢያትን መተው ሲባልም ኃጢያትን ከኅሊናና ከልቡና ጨርሶ በፍጹም ማጥፋት ነው። ይህም ኃጢያትን ከማሰብ መለየት ማለት ነው። ምክንያቱም ሰው በተግባር ኃጢያትን ሳይፈጽምና በልቡ ግን የኃጢያት ፍቅር ቢኖር ኃጢያትም በልቡናው የሚመላለስ ከሆነ ይህ ሰው #ንስሐ ገብቷል ለማለት አይቻልም። የዚህ ዓይነቱ ሰው ኃጢያትን የተወው ወይም ኃጢያት ከመስራት የተቆጠበው የ #እግዚአብሔርን ሕግ ለመጠበቅ ብሎ ነው እንጂ ኃጢያትን ጠልቶ አይደለምና በልቡናው የኃጢያት ፍቅር ቅሬት እያለ ኃጢያትን ትቷልና #ንስሐ ገብቷል ሊባል አይችልም። ስለዚህ ፀፀቱ ወይም #ንስሐው ልቡናው ከኃጢያት እስኪያነጻ ድረስ መሆን አለበት። ከዚህ አንጻር ኃጢያትን መተው የ #ንስሐ ሁለተኛ ደረጃ ነው።
3ኛ, ሦስተኛው ደረጃ
የ #ንስሐ የመጨረሻ(ሦስተኛ) ደረጃ ኃጢያትን መጥላት ነው። ይህም ኃጢያትን በፍጹም ልብ መጥላት፣ አለማሰብና ባሕርይን ለኃጢያት አለማስገዛት ማለት ነው። ይህ ደግሞ የፍጹምነት ደረጃ ነው። ሰው ኃጢያትን ከልቡ ካስወገደና ፍጹም ካላሰባት ከፍጹምነት ደረጃ ደርሷልና ንጹሕ ነው ይባላል። ሰው በመንፈሳዊ ሕይወቱ ውስጥ ከፍተኛውንና ዋነኛውን ኃጢያት ለመተው የሚችለው በክርስትና ሕይወቱ የዕለት ተዕለት ብስለት የሚገለጡትን ረቂቃን ኃጢያቶች በመተው ነው። #እግዛአብሔር የሰው ልጆችን ሁሉ የሚወደን ስለሆነ በኃጢያታችን ብዛት ተስፋ ቆርጠን እንዳንጠፋ ሲል ኃጢያታችንን የሚገልጥልን ቀስ በቀስ ነው። በየጊዜው በሚያጋጥሙን መንፈሳዊ ክስተቶች ውስጥ፣ በምናነባቸው ቅዱሳት መጽሐፍት በምናያቸው የተለያዩ ነገሮችና....ወዘተ ውስጥ ሊስተካከሉ የሚገባቸውን የተሰወሩ ኃጢአቶቻችንንና መንፈሳዊ ድክመቶቻችንን ይገልጥልናል። እነዚህን ኃጢያቶቻችንንና ድክመቶቻችንን የምናስወግድበት መንፈሳዊ መሣሪያ #ንስሐ እንደሚያስፈልገንም እንረዳለን። ከዚህ የተነሣም በክርስትና ሕይወታችን ሁሉ እስከ መጨረሻ አብሮን የሚዘልቀውን የ #ንስሐ ሕይወት እንጀምራለን ምክንያቱም ዛሬ በአንዱ ኃጢያት የተሸነፈ ሰይጣን ነገ በሌላ ኃጢያት ሊፈትነን ይመጣልና ጦርነቱ አይቋረጥም በጦርነቱ መውደቅ መነሣት ስላለ #ንስሐም ማብቂያ የሌለው የመላ ሕይወት ባለእንጀራ ነው።
ክፉ መሥራት ብቻ ሳይሆን መልካምን ለመሥራት አለመቻልም(አለመሥራት) #ንስሐ የሚያስፈልገው ኃጢያት ነው። ሰው ለ #ንስሐ የሚገባ ፍሬ ማፍራት ይጠበቅበታል። በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል "እንግዲህ ለ #ንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ" ተብሏልና ማቴ.3÷8። ለ #ንስሐ የሚገባ ፍሬ ያደረገ ደግሞ በገላትያ 5÷22 የተዘረዘሩትን የመንፈስ ፍሬዎች ያፈራል። እንግዲህ መንፈሳዊ ፍሬ ሊያፈራ ሲገባ ፍሬ የሌለው የሆነ ሰው ሊያደርግ የሚገባውን ባለማድረጉ ኃጢያተኛ ስለሆነ #ንስሐ መግባት አለበት። ምክንያቱም በመጽሐፍ "በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢያት ነው" ተብሏልና። ያዕ.4÷17
ስለዚህ #ንስሐ አንዴ ፈጽመን የምናልፈውና የምንዘነጋው ሳይሆን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ከእኛ ጋር የሚኖር ነው። ከሰው ወገን ከ #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በስተቀር በምድር ላይ አንድ ቀን እንኳ ቢኖር ከኃጢያት ነጻ የሆነ የለም። ሁላችን ኃጢያተኞች ስለሆንን ለሁላችን #ንስሐ ያስፈልገናል። በየዕለቱ ከሥጋዊ ባሕርያችን ከኃጢያት የማንነጻ ከሆነ #ንስሐ መግባት ለክርስቲያኖች ሁሉ የዕለት ተግባራችን መሆኑ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ "ኃጢያት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም በማለት ይህን አረጋግጦልናል። 1ኛዮሐ.1÷8