#ኅዳር_7
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን #የቅዱስ_ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት ቅዳሴ ቤቱ፣ ከእስክንድርያ አገር የሆነ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው፣ #አባ_ናህርው በሰማዕትነት አረፈ፣ #የአባ_ሚናስ_ዘተመይ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፣ #ቅዱሳን_ዘኖቢስ እና እናቱ #ቅድስት_ዘኖብያ እንዲሁም #ቅዱስ_ሐዲስ_መርቆሬዎስ እና ወንድሙ #ቅዱስ_ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕት
ኅዳር ሰባት በዚህችም ቀን የልዳ ሀገር የሆነ የሰማዕታት አለቃ የታላቁ መስተጋድል የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት ነው ዳግመኛም #ጌታችን በውስጧ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ይህም እንዲህ ነው በውስጧ ድንቆች ተአምራት እንደሚሠሩ ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስ በሰማ ጊዜ ሊአፈርሳት አሰበ ስሙ አውህዮስ የሚባለውንም መኰንን ከብዙ ሠራዊት ጋር ላከው፤ ያም መኰንን በደረሰ ጊዜ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ወዳለበት አዳራሽ በትዕቢት ሆኖ ገባ። በሥዕሉም ፊት በብርጭቆ መቅረዝ መብራት ነበረ በቤተ ክርስቲያኒቱና በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ እየዘበተ በእጁ በያዘው በትር የመብራቱን መቅረዝ መትቶ ሰበረው የመቅረዙም ስባሪ ወደ ከሀዲው ራስ ደርሶ መታው ራሱንም ታመመ ፍርሃትና እንቅጥቅጥም መጣበት ወድቆም ተዘረረ ባልንጀሮቹም ወደ አገሩ ሊወስዱት ተሸከሙት በክፉ አሟሟትም ተጐሳቊሎ ሞተ ወስደውም ከባሕር ጣሉት ወገኖቹም ወደ ሀገራቸው አፍረው ተመለሱ።
ከሀዲ ዲዮቅልጥያኖስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ በልዳ ሀገር ያለች የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን ያፈርሳት ዘንድ ራሱ ተነሥቶ ሔደ በዚያንም ጊዜ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መታው ሰባት ዓመት ያህልም ዐይኖቹ ታውረው አእምሮውንም አጥቶ ቁራሽ እንጀራም እየለመነ ኑሮ ሞተ።
ክብር ይግባውና #ጌታችንም የቤተ መንግሥቱን ሰዎች አስነሣበት እርሱን አስወግደው ጻድቅ ሰው ቁስጠንጢኖስን በ #እግዚአብሔር ፈቃድ አነገሡት እርሱም በአዋጅ የጣዖታትን ቤቶች ዘግቶ አብያተ ክርስቲያናትን ከፈተ ለክርስቲያን ወገኖችም በሁሉ ዓለም ተድላ ደስታ ሆነ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_እስክንድርያ
በዚህች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ።
የዚህም ቅዱስ አባቱ በእስክንድርያ አገር በንግድ ሥራ የሚኖር ነው ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ #እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው #ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት።
የዚህም ልጅ እናቱ ለእስክንድርያ አስተዳዳሪ ለአርማንዮስ እኅቱ ናት ከዚህም በኋላ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም አንዲት ብቻዋን ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ።
የአባቷ እኅት ልጅ የሆነ ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ትርጓሜውንና ጥቅሙን ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ።
ወደ አባቷም አርማንዮስ በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች።
ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት የእኅትህ ልጅ ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ሰምቶ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይተው ቅድስት ራሱን በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።
በዚያም ሳሙኤል የሚባል ዲያቆን ነበር የቅዱስ ጊዮርጊስንም ሥጋ አንሥቶ ወደ ሀገረ መኑፍ ወሰደው። የአርማንዮስም ሚስት በአወቀች ጊዜ መልእክተኞችን ልካ አስመጣችው ከልጅዋም ሥጋ ጋር በአንድነት በእስክንድርያ አገር አደረገችው።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ
ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ገብረ እንድርያስ ዘወለቃ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው። የትውልድ ሀገራቸው ወሎ ቦረና ጋስጫ ነው፡፡ አባታቸው ተንሥአ #ክርስቶስ እናታቸው አርሴማ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዕድሜአቸው ለትምህርት ሲደርስ ለመምህር ሰጧቸው፡፡ መምህሩም ጸጋ #እግዚአብሔር እንዳደረባቸው ዐውቀው ‹‹ብዙዎችን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍትንም ትርጓሜ በሚገባ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሌም ይባል የነበረውን ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው፡፡
ጻድቁ በአቡነ ዮሐንስ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፡፡ አባታችን ሙታንን በማስነሣትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ ብዙ አባቶች ሱባኤ ይይዙበት በነበረው በሰኮሩ #ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑራኤል በወርቅ ጽዋ ሰማያዊ ወይንና ኅብስት መግቧቸዋል፡፡ #እመቤታችንም ሦስት ጽዋ ማየ ሕይወት ሰጥታቸው በእርሱ ብዙ ሕሙማንን ፈውሰውበታል፡፡
ጻድቁ በስማቸው የፈለቀው ጸበል እጅግ አስገራሚ ነው፡፡ ጸበሉ ውስጥ እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት ነጭ መቁጠሪያ ሆኖ ይወጣል፡፡ ይህም እስከዛሬ ድረስ በግልጽ ይታያል፡፡ ጸበሉ ውስጥ ማታ የነከሩትን እንጨት ጠዋት ላይ መቁጠሪያ ሆኖ ያገኙታል፡፡ እጅግ አስገራሚ ነው በእውነት! መቁጠሪያውም ለእንቅርትና ለልዩ ልዩ ሕመሞች መድኃኒት ነው፡፡ ነገር ግን ጸበሉ ያለበት አካባቢው በመርዛማና አደገኛ እባቦች የተሞላ ነው፡፡ ሆኖም ግን እባቦቹ የጻድቁ ግዝት ስላለባቸው በገዳሙ ውስጥ ብቻ ማንንም አይነኩም፡፡ ጸበሉ ደግሞ የሚገኘው ከገዳሙ የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ርቀት ላይ ነው፡፡
አባታችን #እግዚአብሔር ኃጥአንን እንድምርላቸው ጣቀት ወንዝ ከተባለው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሸከሙ ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህ ይጸልዩበት ከነበረው ወንዝ ውስጥ ነው በተዓምራት መቁጠሪያ የሚሠራው ጸበል የፈለቀላቸው፡፡ ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የሚገኘው አቡነ ገብረ እንድርያስ ገዳም ከአባ ጽጌ ድንግል ገዳም በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ያስኬዳል፡፡
ጻድቁ አቡነ ገብረ እንድርያስ ዓርብ ዓርብ የ #ጌታችንን_ቅዱስ_ሥጋውንና #ክቡር_ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በትልቅ ድንጋይ ላይ እንደ ደመና ተጭነው ነበር፡፡

👍1
ጻድቁ በአየር ላይ ሲጓዙ ድንጋዩን እንደ ሠረገላ ዋርካውን እንደ ጥላ ይጠቀሙበት ነበረ፡፡ ያ እንደ ሠረገላ ሆኖ ያገለግላቸው የነበረው ትልቅ ድንጋይ ዛሬም ድረስ በገዳማቸው ውስጥ ይገኛል፡፡ ታሪኩም በቅዱስ ገድላቸው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአቡነ እንድርያስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ናህርው
በዚህችም ቀን ዳግመኛ ከግብፅ አገር ከፍዩም መንደር አባ ናህርው በሰማዕትነት አረፈ። ይህም ቅዱስ #እግዚአብሔርን እጅግ የሚፈራው ነው በእስክንድርያ ሀገር የሚሠቃዩ የሰማዕታትን ዜና በሰማ ጊዜ ክብር ይግባውና ስለ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ስለ ስሙ ሊሞት ወደደ በራእይም ወደ አንጾኪያ ሀገር ሒደህ በዚያ ትሞት ዘንድ አለህ አለው።
ወደዚያ መድረስ እንዴት ይቻለኛል በማለት የሚያስብ ሆነ ሊሳፈርም መርከብን ፈለገ በዚያን ጊዜ #እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ሚካኤልን ላከለት በክንፎቹም ተሸክሞ ወደ አንጾኪያ ሀገር አደረሰው።
በዲዮቅልጥያኖስም ፊት ቀርቦ በ #እግዚአብሔር ታመነ ንጉሡም ስሙንና አገሩን ጠየቀው እርሱም ከግብጽ አገር እንደሆነ አስረዳው ንጉሡም ቃሉን ሰምቶ ለጣዖታቱ ቢሠዋለት ብዙ ገንዘብና የግምጃ ልብሶችን ሊሰጠው ማለለት እርሱ ግን ቃሉን አልሰማም ንጉሱም እኔ ታላቅ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ የሚል ቃልን ደግሞ ተናገረው ከሥቃዩም የተነሳ አልፈራም ትእዛዙንም አልሰማም።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ናህርውን በብዙ አይነት ስቃይ እንዲአሰቃዩት ንጉሱ አዘዘ አንድ ጊዜ ለአንበሶች ጣሉት አልነኩትም አንድ ጊዜ ከእሳት ጨመሩት አልተቃጠለም ሌላ ጊዜም በወጭት ቀቀሉት ከማሠቃየትም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ ንጉሡ አዘዘ።
ይህ አባ ናህርውም በግብጽ አገር በሰማዕትነት ስለሞቱ ስለ አንጾኪያ አገር ሰማዕታት ፈንታ በአንጾኪያ አገር በሰማዕትነት አረፈ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ሰማዕት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አባ_ሚናስ_ዘተመይ
በዚህችም ቀን ከገምኑዲ አውራጃ የሀገረ ተመይ ኤጲስቆጶስ የአባ ሚናስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ደጎች #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ዜናቸውም በቅዱሳን አባቶች ዘንድ እስከ ተሰማ ድረስ በጾማቸው በጸሎታቸው በገድል በመጸመዳቸው የመነኰሳትን ሥራ የሚሠሩ ናቸው።
እነርሱም ያለ ፈቃዱ ልጃቸውን ሚስትን አጋቡት ሙሽራዪቱም ወዳለችበት የጫጒላ ቤት ገባ ድንግልናቸውንም ሳያጠፉ ሥጋቸውን በንጽሕና ይጠብቁ ዘንድ ከእርሷ ጋር ተስማሙ ሁለቱም በበጎ ተጋድሎ እየተጋደሉ በአንድነት ኖሩ።
ከዚህም በኋላ ቅዱስ ሚናስ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ወዶ ሚስቱን እንዲህ አላት በዓለም እያለን የምንኲስና ሥራ ልንሠራ ለእኛ አግባብ አይደለም እነርሱ ከልብሳቸው ውስጥ ማቅ በመልበስ በ #እግዚአብሔር_መንፈስ የተደረሱ መጻሕፍትን በማንበብና ለጸሎት በመትጋት ሌሊቱን ሁሉ ይቆሙ ነበርና ከዚህም በኋላ ሰላምታ ሰጥታ ሸኘችው አሰናበተችውም።
እርሱም ወደ አባ እንጦንዮስ ገዳም ሔደ ከወላጆቹ ሊርቅ ወዶአልና እነርሱ ወደ ሚስቱ ይመልሱት ዘንድ በንጉሥ ትእዛዝ በቦታ ሁሉ እየፈለጉት ነበርና #እግዚአብሔር ሠውሮታልና ከቶ አላገኙትም በዚያም ገዳም በገድል ተጠምዶ ብዙ ጊዜ ኖረ በእስክንድርያም ሊቀ ጳጳሳት የሆነው አባ ሚካኤል ከእርሱ ጋር በምንኵስና ነበር።
ከዚህም በኋላ ሁለቱ ብሩሃን ከዋክብት አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ በነበሩበት ወራት ከነበረበት ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ። ይህ ቅዱስ አባ ሚናስም ተወዳጅ ልጅን ሆናቸው ከእርሳቸውም ዘንድ በበዓታቸው የሚኖርና የሚያገለግላቸው ሆነ የምንኲስናንም ሥራ ጨመረ ከእርሳቸውም ትምህርታቸውን ተጋድሏቸውን በመማር ከብዙዎች በተጋድሎውና በአምልኮቱ ከፍ ከፍ አለ አባ አብርሃምና አባ ገዓርጊ ሌሎችም አባቶች ከእርሱ ተጋድሎ የተነሣ ያደነቁ ነበር።
ሰይጣን ግን በእርሱ ቀንቶ በታላቅ አመታት እግሮቹን መታው ሁለት ወርም በምድር ላይ ወድቆ ኖረ ። ከዚህም በኋላ #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ያለ ጥፋት በጤና አሥነሣው።
ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኤጲስቆጶስ ይሆን ዘንድ መርጦ ጠራው የሊቀ ጳጳሳቱም መልእክተኞች ወደርሱ መጡ ከመነኰሳት የሚለይ በመሆኑ ታላቅ ኀዘንን አዘነ ቅዱሳን አባቶችም ይህ ሥራ ከ #እግዚአብሔር ነው አትዘን አሉት።
እርሱም ለ #እግዚአብሔር ትእዛዝ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከሊቀ ጳጳሱ መልክተኞች ጋር አብሮ ሔደ ሊቀ ጳጳሱም ተመይ በሚባል አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾመው ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሆነ በሽታ ያለባቸውም ሁሉ ወደርሱ ይመጣሉ እርሱም ክብር ይግባውና ወደ #እግዚአብሔር በመጸለይ ይፈውሳቸዋል።
ሁለተኛም የተሠወረውን የማወቅ ሀብተ ጸጋ #እግዚአብሔር ሰጠው በሰው ልቡና የታሰበውንም የሚያውቅ ሆነ ኤጲስቆጶሳቱም ሁሉ ከየሀገሮቻቸው በመምጣት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚታዘዙለትና ትምህርቱን የሚቀበሉ ሆኑ አሕዛብም ሁሉ ትምህርቱን ይሰሙ ዘንድ ይመጡ ነበር እርሱም ለአራት ሊቃነ ጳጳሳት አባት ሆነ። በሚሾሙ ጊዜ እጁን በላያቸው ጭኖአልና እሊህም በእስክንድርያ አገር ሊቃነ ጳጳሳት የሆኑ እለእስክንድሮስ፣ ቆዝሞስ፣ ቴዎድሮስ፣ ሚካኤል ናቸው።
ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ሊለየው በፈቀደ ጊዜ የሚለይበትን ቀን በ #መንፈስ_ቅዱስ አውቆ በሀገረ ስብከቱ ያሉትን ሕዝቡን ሁሉ ልኮ አስመጣቸው። በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ የከበረ የወንጌልንም ትእዛዝ እንዲጠብቁ አዘዛቸው ከዚህም በኋላ ለእውነተኛው ጠባቂያቸው ለ #ጌታችንና_ለመድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሰጣቸውና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ተለይቶ ወደ ወደደው #ክርስቶስ ሔደ ሕዝቡም አለቀሱለት ቸር ጠባቂያቸውም ከእርሳቸው በመለየቱ እጅግ አዘኑ እንደሚገባም ገንዘው እርሱ ራሱ በአዘዛቸው ቦታ አኖሩት።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_ዘኖቢስና_እናቱ_ዘኖብያ
በዚህችም ቀን ቅዱሳን ዘኖቢስና እናቱ ዘኖብያ በሰማዕትነት አረፉ እሊህም ቅዱሳን ተበይስ ከምትባል አገር ከታላላቆቿ ናቸው። እነርሱ ክርስቲያን እንደሆኑ በንጉሥ ዘንድ ወነጀሏቸው ንጉሥም ወደርሱ እንዲአቀርቧቸው አዘዘና ሲቀርቡ እንዲህ አላቸው የምትጠበቁት ከምንድን ነው አገራችሁስ ወዴት ነው እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት እኛ ጣዖታትን ከማምለክ እንጠበቃለን እምነታችንም በ #ክርስቶስ ነው ሀገራችንም ተበይስ ይባላል።
መኰንኑም ለአማልክት ሠዉ አላቸው ቅዱሳንም እኛ ለ #ኢየሱስ_ክርስቶስ እንሠዋለን እንጂ ለጣዖታት አንሠዋም አሉት መኰንኑም ተቆጣ ልብሳቸውንም ገፈው በራሳቸው ጠጒር ሰቅለው ይደበድቧቸው ዘንድ አዘዘ ወደ #እግዚአብሔርም ጸለዩ በዚያንም ጊዜ ማሠሪያቸው ተፈታ የብርሃንንም ልብሶች ለብሰው ሕዝቡ አዩአቸው መኰንኑም ወንበሩን ተሸክሞ በኋላቸው ሲከተል ነበር ። ሕዝቡም ይህን በአዩ ጊዜ እንዲህ እያሉ ጩኸው አመሰገኑ ልዩ ጽኑዕ ምስጉን አሸናፊ #እግዚአብሔር የጌትነትህ ክብር በሰማይና በምድር የመላ የ #ክርስቲያን_አምላክ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ኃይልህ ታላቅ ነው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ተቆጣ እርስበርሳቸው እንዲተያዩ አድርገው በሁለት መስቀሎች እንዲሰቅሏቸው አዘዘ ያን ጊዜም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው በማግሥቱም የ #እግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምሩ መኰንኑ አገኛቸው ሕዝቡም አይተው እኛ በክርስቲያኖች አምላክ እናምናለን እርሱ ታላቅ ነውና እያሉ በአንድ ቃል ጮኹ።
ሁለተኛም እንዲህ ብሎ አዘዘ ሁለት ወንበሮችን እንዲሠሩ በውስጣቸውም ብረቶችን እንዲተክሉ እሊህንም ቅዱሳን በላዩ አስተኝተው ከእሳት ምድጃ ውስጥ እንዲጨምሩአቸው አዘዘ #ጌታችን_ኢየሱስም አዳናቸው በእነዚያ ወንበሮችም ላይ ተቀምጠው ሕዝቡን ሲያስተምሩ አገኙአቸው።
መኰንኑም በአየ ጊዜ ቁጣን ተመላ ቁመቱና ጐኑ ሃያ ሃያ ክንድ የሆነ ጒድጓድን ቆፍረው እሳትን እንዲአነዱበትና በውስጡ እንዲጨምሩአቸው አዘዘ ወደ #እግዚአብሔርም በጸለዩ ጊዜ ያ እሳት ጠፋ ጒድጓዱም እንደተሸለመ ቤት ሆነላቸው።
መኰንኑም የውሽባ ቤት ጠባቂውን ጠርቶ እሳትን እንዲያነድ አዘዘው ቅዱሳኑንም ከውስጡ እንዲጨምሩአቸው። ወደ #እግዚአብሔርም በጸለዩ ጊዜ የውሽባ ቤቱ ውኃ ሆነ መኰንኑም ውኃ የተመላበትን ጋን ተሸክሞ ነበር ይህንንም ድንቅ ሥራ ሕዝቡ በአዩ ጊዜ #እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ በሚሠራው ሥራ የተደነቀ ነው እያሉ #እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
መኰንኑም ምን እንደሚያደርጋቸው በተቸገረ ጊዜ እንዲገድሏቸውና እስከ ነገ ድረስ በድናቸውን ጠብቀው በእሳት እንዲአቃጥሏቸው በነፋስም ውስጥ እንዲበትኑአቸው አዘዘ። በገደሏቸውም ጊዜ ነጐድጓድ መብረቅ ንውጽውጽታና ዝናም ሆነ በዚያ ንውጽውጽታም ብዙዎች ኃምሣ አራት ያህል ሰዎች ሞቱ በሌሊትም ምእመናን መጥተው በሥውር ሥጋቸውን ወስደው ቀበሩአቸው።
በማግሥቱም መኰንኑ በድናቸውን በፈለገ ጊዜ የሆነውን ሁሉ ተአምር ነገሩት ያም መኰንን አደነቀ በ #ጌታችንም አምኖ ክርስቲያን ሆነ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱሳን_መርቆሬዎስና_ዮሐንስ
በዚህችም ቀን ቅዱሳን ሐዲስ መርቆሬዎስና ወንድሙ ዮሐንስ በሰማዕትነት አረፉ። እነዚህ ቅዱሳን #እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያመልኩ ክርስቲያኖች ሰዎች ልጆች ናቸው የታላቁም ስሙ "መናሂ" ነበር የምንኲስና ልብስ በለበሰ ጊዜ መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት የታናሹም ስሙ "አቡፈረዥ "ነበር እርሱንም በሚመነኲስ ጊዜ ዮሐንስ ብለው ሰየሙት።
በአደጉም ጊዜ ወደ ሊቀ ሰራዊት ቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም ሔዱ በዚያም #እግዚአብሔርን ለሚያገለግል አረጋዊ ጻድቅ ሰው የሚታዘዙ ሁነው ኖሩ ለገዳሙ በሚአሻው ስራ መነኰሳቱንም በማገልገል የክረምቱን ቅዝቃዜና የበጋ ቃጠሎ ታግሠው የምድሩን ፍሬዎች የሚሰበስቡና ወደዚያች ገዳም የሚያመጡ ሆኑ።
ለራሳቸው ግን በዓለም ውስጥ ምንም ምን ጥሪትን አላደረጉም ዳግመኛም በዓለም ውስጥ ጣዕም ካላቸው ከመብል ከመጠጥ ከእንቅልፍ የራቁ ናቸው በየሁለትና በየሶስት ቀን ይጾማሉ። ዳግመኛም በቅብጢና በዓረብ ቋንቋ ጽሕፈት ተማሩ የምንኲስናንም ሕግና ሥርዓት ፈጸሙ።
በአንዲት ቀንም በአንድነት እያሉ ከ #እግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ወደ እነርሳቸው መጥቶ እነርሱ ወደ ምስክርነት አደባባይ እንደሚደርሱ ነገራቸው ያን ጊዜ ደስ አላቸው በ #መንፈስ_ቅዱስም በረቱ ተነሥተውም በችኰላ ተጒዘው ወደ አገራቸው ደረሱ። የአገራቸውም ሰዎች በአገሩ ገዥ ዘንድ ወነጀሏቸው እርሱም ለብህንሳው ገዥ አሳልፎ ሰጣቸው እርሱም በውኑ እናንተ ጣዖትን የምታመልኩ ናችሁን ብሎ ጠየቃቸው ። ቅዱሳን ግን ይህ በእኛ የሚነገር አይደለም እኛ በግልጥ ክርስቲያን የሆን የረከሱ ጣዖታትን የማናመልክ ነንና እውነተኛውን #አምላክ_ጌታችንን_ኢየሱስ_ክርስቶስን እናመልከዋለን እንጂ አሉት።
መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ ቊጣን ተመላ በአንገቶቻቸውም ሰንሰለት አስገብተው ከተማውን ሁሉ አዙረው ከዚያ በኋላ በወህኒ ቤት እንዲአስሩአቸው አዘዘ በዚያም ሳሉ የ #እግዚአብሔር መልአክ ብዙ ጊዜ የሚጐበኛቸው ሆነ።
ከአምስትም ወር በኋላ መኰንኑ ከእስር ቤት አውጥቶ በፊቱ አቆማቸውና ሃይማኖታችሁን ተዉ አላቸው። አይሆንም በአሉትም ጊዜ ሥጋችሁን በእሳት አቃጥላለሁ ብሎ አስፈራራቸው እነርሱ ግን ምንም አልፈሩትም የልባቸውን ጥንክርና አይቶ ወደ ወህኒ ቤት መለሳቸው።
ከብዙ ወራት በኋላ ሌላ መኰንን መጣ እርሱም ሊአድናቸውና ሊተዋቸው ወደደ የአገር ሰዎች ግን ተቃወሙት እነዚህን ካልገደልካቸው በንጉሥ ዘንድ እንከስሃለን አሉት ያንጊዜም ሊአስፈራራቸው እሳትን ያነዱ ዘንድ አዘዘ እነርሱ ግን ወደ እሳቱ ለመግባት ተደፋፈሩ ዳግመኛም ራርቶላቸው ወደ ወህኒ ቤት መለሳቸው ሁለተኛም አምጥተው በተሳሉ ሰይፎች ያስፈራሩአቸው ዘንድ አዘዘ የእዚህ ቅዱሳን ልብ ግን አልደከመም ቃላቸውም አልተለወጠም።
ከዚህም በኋላ ህዝቡን ከመፍራት የተነሳ ራሳቸውን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በመጀመሪያም የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ያን ጊዜም ራሱ ከሥጋዋ ላይ ዘለለች ከእርሷም እንደ ደስታ ቃል ያለ የሰሙ ሁሉ እስኪያደንቁ ድረስ ታላቅ ድምፅ ወጣ።
ዳግመኛም የቅዱስ መርቆሬዎስን ራስ ቆረጡ ሥጋቸውንም ከእሳት ውስጥ ጨመሩ በዚያንም ጊዜ እሳቱ ጠፋ ሥጋቸውንም ልብሳቸውንም አልነካም መኰንኑም በአየ ጊዜ ክርስቲያኖች እንዳይሰርቋቸው ጠብቁ ብሎ አዘዘ በማግስቱም የዐዘቅት ውኃ በአገኙ ጊዜ ከውስጧ ጨመሩአቸው ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_7 እና #ከገድላት_አንደበት)

"በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።
እንኳን #ለዘመነ_አስተምህ(ሕ)ሮ_የመጀመርያ_ሳምንት ለዕለተ እሑድ #እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
#የዚህ_ሳምንት_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፰ " #ኢትዘኪሮ_አበሳነ ዚአነ ፍጹመ ኢኀደገነ ፍጹመ ንማስን #ኄር_እግዚአብሔር_አዘዞሙ_ሙሴ ለሕዝብ ያክብሩ ሰንበተ ጽድቅ"። ትርጉም፦ #ቸር_እግዚአብሔር በደላችንን ሳያስብ ፈጽሞ እንጠፋ ዘንድ አልተወንም፤ በእውነት ሕዝብህ #ሰንበትን_ያክብሩ_ብሎ_ሙሴን አዘዘው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
#ዘመነ_አስተምሕሮ፦ ይህ ዘመን አስተምሕሮ ከኅዳር ፮ (6) እስከ ታኅሣሥ 7 (13) ፯ (፲፫) ያለው ወቅት ሲሆን አስተምሕሮ ማለት ኹለት ትርጉም አለው፤ ይኸውም በመሐሩ "ሐ" (አስተምሕሮ) በሚለው ከተጻፈ ምሕላ፣ ምልጃና፣ ልመና፣ ይቅርታ ማለት ነው። ይህም "መሐሪ" ይቅር አለ በደልን ተወ፤ ወይም አስተምሕሮ ስለ #እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ የምንመሰክርበት እርሱ በደላችንን ሁሉ ይቅር ብሎ ሊታረቀን በሰማይ መውረዱን ከድንግል #ማርያም መወለዱን የምናዘክርበት እንዲሁም እርሱ ይቅር እንዳለን ተገንዝበን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ወቅት ነው። በተለይ ይህ ዘመነ አስተምሕሮ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ምልጃ የምታቀርብበት ምዕመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት ዘመን ነው።
#በሃሌታው "ሀ" (አስተምህሮ) በሚለው ከተጻፈ ትምህርት ሥርዓት ማለት ነው፤ አስተምህሮ የሚለው ቃል "መሀረ" አስተማረ፣ መከረ፣ ዘከረ ከሚለው ሥርወ ግሥ የተገኘ ነው ይኸውም የ #እግዚአብሔር ቸርነት፣ ርኅራኄ፣ ትዕግሥትና የማዳን ሥራው በቤተ ክርስቲያን በስፋት የሚሰበክበት ጊዜ ስለኾነ ወቅቱ ዘመነ አስተምህሮ ተብሏል የሥርዓትና የትምህርት ወቅት ማለት ነው። "ፊደል አይቀነስም" ብለው ሊቃውንቱ የሚሟገቱት ከዚህ የተነሣ ነው፤ እነዚህ ተመሳሳይ ድምጽ ያላቸው ፊደላት በአገባባቸው ሰፊ የትርጉም ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉና። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ዘመነ አከፋፈል መሠረት ከኅዳር ፮ (6) እስከ ታኅሣሥ 7 (13) ፯ (፲፫) ቀን ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምሕሮ ተብሎ ይጠራል።
#በዘመነ_አስተምሕሮ የ #እግዚአብሔርን ቸርነት፣ ታጋሽነት፣ ይቅር ባይነት በየጊዜው የሰዎችን በደል ሳይመለከት የቸርነቱን ሥራ መሥራቱን፣ ለሰዎች የዕረፍት ቀን እንዲሆን ሰንበትን መቀደሱ ይታሰባል። በተለይ ደግሞ ቅዱሳን ነቢያት ስለ #ክርስቶስ መምጣት የቆጠሩት ሱባኤ፣ የመሰሉት ምሳሌ፣ የተናገሩት ትንቢት፣ የጸለዩት ጸሎት የጾሙት ጾም የሚዘከርበት ሰሞን ነው።

ከ #ኅዳር_6 እስከ #ታኅሣሥ_7 ወይም 13 አስተምህሮ ይትበሃል። 1ኛ መዝሙር ዘአስተምህሮ ኢተዘኪሮ።
#የኅዳር_7_ግጻዌ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሮሜ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤
¹¹ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።
¹² ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤
¹³ ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም፤
¹⁴ ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና።
¹⁵ ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን እንደዚያው አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎቹ ሞተዋልና፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋና በአንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።
¹⁶ አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።
¹⁷ በአንዱም በደል ሞት በአንዱ በኩል ከነገሠ፥ ይልቁን የጸጋን ብዛትና የጽድቅን ስጦታ ብዛት የሚቀበሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሕይወት ይነግሣሉ።
¹⁸ እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።
¹⁹ በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
²⁰-²¹ በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ፤ ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ፥ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ፥ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
² እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።
³ ትእዛዛቱንም ብንጠብቅ በዚህ እንዳወቅነው እናውቃለን።
⁴ አውቄዋለሁ የሚል ትእዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም።
⁵ ቃሉን ግን የሚጠብቅ ሁሉ በእርሱ የእግዚአብሔር ፍቅር በእውነት ተፈጽሞአል። በእርሱ እንዳለን በዚህ እናውቃለን፤
⁶ በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል።
⁷ ወንድሞች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረቻችሁ አሮጌ ትእዛዝ እንጂ የምጽፍላችሁ አዲስ ትእዛዝ አይደለችም፤ አሮጌይቱ ትእዛዝ የሰማችኋት ቃል ናት።
⁸ ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤ ጨለማው ያልፋልና እውነተኛውም ብርሃን አሁን ይበራል።
⁹ በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።
¹⁰ ወንድሙንም የሚወድ በብርሃን ይኖራል ማሰናከያም የለበትም፤
¹¹ ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።
¹² ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
¹³ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
¹⁴ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።
¹⁵-¹⁶ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።
¹⁷ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እናንተ ወንድሞች አባቶችም፥ አሁን ለእናንተ ነገሬን ስገልጥ ስሙኝ።
² በዕብራይስጥም ቋንቋ ሲናገር በሰሙ ጊዜ ከፊት ይልቅ ዝም አሉ። እርሱም አለ፦
³ እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።
⁴ ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰርሁ ወደ ወኅኒም አሳልፌ እየሰጠሁ ይህን መንገድ እስከ ሞት ድረስ አሳደድሁ።
⁵ እንዲህም ሊቀ ካህናቱ ደግሞ ሽማግሌዎቹም ሁሉ ይመሰክሩልኛል፤ ከእነርሱ ደግሞ መልእክትን ለወንድሞቻቸው ተቀብዬ፥ በደማስቆ ያሉትን ደግሞ ታስረው እንዲቀጡ ወደ ኢየሩሳሌም ላመጣ ወደዚያ እሄድ ነበር።
⁶ ስሄድም ወደ ደማስቆ በቀረብሁ ጊዜ፥ ቀትር ሲሆን ድንገት ከሰማይ ታላቅ ብርሃን በዙሪያዬ አንጸባረቀ፤
⁷ በምድርም ላይ ወድቄ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።
⁸ እኔም መልሼ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? አልሁ። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ እኔ ነኝ አለኝ።
⁹ ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አይተው ፈሩ፥ የሚናገረኝን የእርሱን ድምፅ ግን አልሰሙም።
¹⁰ ጌታ ሆይ፥ ምን ላድርግ? አልሁት። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ደማስቆ ሂድና ታደርገው ዘንድ ስለ ታዘዘው ሁሉን በዚያ ይነግሩሃል አለኝ።
¹¹ ከዚያ ብርሃንም ክብር የተነሣ ማየት ባይሆንልኝ ከእኔ ጋር የነበሩት ሰዎች እጄን ይዘው እየመሩኝ ወደ ደማስቆ ደረስሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ኢትዝክር ለነ አበሳነ ዘትካት። ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ። እስመ ተመንደበነ ፈድፋደ"። መዝ.78÷8
#ትርጉም፦ “የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።” መዝ.78÷8
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኀዳር_7_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 6
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

⁶ አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
⁷ አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።
⁸ ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።
⁹ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥
¹⁰ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤
¹¹ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤
¹² እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤
¹³ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
¹⁴ ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤
¹⁵ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም በዓልና ዕለተ ሰንበት ለሁላችንም ይሁንልንተ

#ኅዳር_8
#አንድ_አምላክ_በሆነ_በአብ_በወልድ_በመንፈስ_ቅዱስ ስም
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_አፍኒን የተሾመበት ነው፣ #ለንጉሥ_ቈስጠንጢኖስም መስቀል የተገለጸበት ነው፣ የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ #ቅዱስ_አባ_ቅፍሮንያ ያረፈበት ቀን ነው።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አርባዕቱ_እንስሳ
ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የቅዱሳን የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።
እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የ #እግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ #እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ #እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ #እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ #እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በ #እግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በ #እግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አፍኒን_ሊቀ_መላእክት
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ሊቀ መላእክት ቅዱስ አፍኒን የተሾመበት ዓመታዊ በዓሉ ነው፡፡ ይህም ከቅዱሳን ሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው፡፡ ስለዚህም ክቡር መልአክ ሄኖክ እንዲህ አለ፡- "…ያንን ቤት ሱራፌልና አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል፣ እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፉ ናቸው፡፡" ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ "በ #እግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን አየሁ" (ራዕ 8፥2) እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቁጥር 7 ናቸው፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱስ ሩፋኤል፣ ቅዱስ ራጉኤል፣ ቅዱስ ዑራኤል፣ ቅዱስ ፋኑኤልና ኅዳር 8 ቀን የተሾመበትን ዓመታዊ በዓሉን የምናከብርለት ቅዱስ አፍኒን ናቸው፡፡
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ አፍኒን አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ታላቁ_ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ
በዚህችም ቀን ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስም #መስቀል ተገለጸለት።
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያህል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም። ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ።
ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር። ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ። ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ። ሚሊየኖች በግፍ አለቁ።
የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም። ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ #እግዚአብሔር አስቁሞ ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው፣ ብዙ ሥርዓት የተሠራው፣ ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና።
ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል። በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለች፡ በኃይለ #መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል።
ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ #መስቀልን የተመለከተባት ናት። መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጓዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን #መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል።
ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል። እርሱም በጋሻው፣ በጦሩ፣ በሰይፉ፣ በፈረሱ ላይ የ #መስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል። እኛንም በሞገሰ #መስቀሉ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ቅዱስ_አባ_ቅፍሮንያ
በዚህችም ቀን የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ አባ ቅፍሮንያ አረፈ። ከዕለታትም በአንዲቱ ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል መነኰስ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም ወደ ሀገሩ መጣ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገረ።

ከጥቂት ወራትም በኋላ ገዳማትን ሊያጠፋ ምርኮንም ሊማርክ ሠራዊቱን ሰብሰቦ ወደ ግብጽ አገር ዘመተ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም በደረሰ ጊዜ አበ ምኔቱ ወደርሱ ወጥቶ እኔ ነኝ አለው ቅፍሮንያም ሰምቶ አበምኔቱን ለብቻው አግልሎ እንዲአጠምቀውና የምንኵስናንም ልብስ እንዲአለብሰው ለመነው አበ ምኔቱም እሺ በጎ አለው።
ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ ብቻውን ቀረ በዚያንም ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ለበሰ ተጋድሎውንም በመጾምና በመጸለይ ጀመረ። ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ ነገረ ሠሪ አስነሣበት በመኳንንቱም ዘንድ ወነጀለው እነርሱም አገራችንን ያጠፋ የመኰንን ልጅ ከዚህ አለ ብለው ገዳሙን ከበቡ #እግዚአብሔርም ሠወረው በአጡትም ጊዜ ነገረ ሠሪውን ገደሉት።
ይህም ቅዱስ በገድል ተጠምዶ ኖረ በየሰባት ቀንም ይጾማል ያለ መራራ አደንጓሬ አይመገብም። በዚያም ወራት የምድር አውሬ እንስሶቻቸውን እየገደለ በገዳሙ ላይ ጥፋትን አደረሰ አባ ቅፍሮንያም ወደርሱ መጥቶ እንደ በግ ይዞ አሠረው ዐሥር ዓመትም ቆይቶ ሞተ።
ቅዱስ ቅፍሮንያም የ #እግዚአብሔር መልአክ እየመራው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በአንዲትም ቀን ደረሰ በዚያም ታላቅ ምሥጢርን አየ ከከበሩ ቦታዎችም ተባርኮ ወደ መኖሪያው ተመልሶ በሰላም አረፈ።
#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል፣ በቅዱሳን መላዕክት እና ሰማዕታት አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_8፣ #ከዲያቆን_ዮርዳኖስ_አበበ እና #ከገድላት_አንደበት)

#የኅዳር_8_ግጻዌ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_8_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ጢሞቴዎስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።
²² በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፥ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።
²³ ስለ ሆድህና ስለ በሽታህ ብዛት ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ፥ ወደ ፊት ውኃ ብቻ አትጠጣ።
²⁴ የአንዳንዶች ሰዎች ኃጢአት የተገለጠ ነው ፍርድንም ያመለክታል፥ ሌሎችን ግን ይከተላቸዋል፤
ወይም👇
1ኛ ቆሮንቶስ 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።
²⁵ ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።
²⁶ የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤
²⁷ ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን፦ ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው።
²⁸ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።
²⁹ እንዲያማ ካልሆነ፥ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ምን ያደርጋሉ? ሙታንስ ከቶ የማይነሡ ከሆነ፥ ስለ እነርሱ የሚጠመቁ ስለ ምንድር ነው?
³⁰ እኛስ ዘወትር በሚያስፈራ ኑሮ የምንኖር ስለ ምንድር ነው?
³¹ በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ዕለት ዕለት እሞታለሁ።
³² እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ።
³³ አትሳቱ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል።
³⁴ በጽድቅ ንቁ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ።
³⁵ ነገር ግን ሰው፦ ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።
³⁶ አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ራእይ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁶ በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዓይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
⁷ ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፥ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፥ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፥ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።
⁸ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።
⁹ እንስሶቹም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው ከዘላለምም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴ ምስጋናም በሰጡት ጊዜ፥
¹⁰-¹¹ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ፦ ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።
ወይም👇
1ኛ ጴጥሮስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥
¹⁹ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤
²⁰ ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ፥ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቈየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም።
²¹ ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፥ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፥ ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ፥ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ነው፤
²² እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
³⁰ እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤
³¹ ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
³² እኛም ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፥ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ምስክር ነው።
³³ እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቈጡ ሊገድሉአቸውም አሰቡ።
³⁴ ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የከበረ የሕግ መምህር ገማልያል የሚሉት አንድ ፈሪሳዊ በሸንጎ ተነሥቶ ሐዋርያትን ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጉአቸው አዘዘ፥
³⁵ እንዲህም አላቸው፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ስለ እነዚህ ሰዎች ምን እንደምታደርጉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
³⁶ ከዚህ ወራት አስቀድሞ ቴዎዳስ፦ እኔ ታላቅ ነኝ ብሎ ተነሥቶ ነበርና፥ አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎችም ከእርሱ ጋር ተባበሩ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበተኑ እንደ ምናምንም ሆኑ።
³⁷ ከዚህ በኋላ ሰዎች በተጻፉበት ዘመን የገሊላው ይሁዳ ተነሣ ብዙ ሰዎችንም አሸፍቶ አስከተለ፤ እርሱም ጠፋ የሰሙትም ሁሉ ተበታተኑ።
³⁸ አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤
³⁹ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።
⁴⁰ ሰሙትም፥ ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው።
⁴¹ እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_7_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ተፅዕነ ላዕለ #ኪሩቤል ወሠረረ። ወሠረረ በክነፈ ነፋስ። ወረሰየ ጽልመተ ምሥዋው። መዝ.17÷10
#ትርጉም፦ " #በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ። መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ"። መዝ.17÷10
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ኅዳር_7_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ማቴዎስ 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።
¹¹ የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና።
¹² ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን?

¹³ ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።
¹⁴ እንደዚሁ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ በሰማያት ያለው አባታችሁ ፈቃድ አይደለም።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️ የሚቀደሰው ቅዳሴ የ #ሠለስቱ_ምዕት ወይም የ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ_ቅዳሴ ነው። መልካም የአርባእቱ እንስሳ(ቅዱሳን ኪሩቤል በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።