TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ " በአንጋፋዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ላይ ግድያ እና ስቃይ መፈጸሙን የሰማነው በታላቅ ድንጋጤና ሀዘን ነው " አለ። መሰል ተግባራት በተለያዩ ወቅቶች ሲፈጸም እንደነበር አስታውሷል። ጉባኤው የቤተክርስቲያኗን " የዛሬውን የሀዘን መግለጫ ተመልክቻለሁ " ብሏል። " በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ፦…
" በጥቃቱ የተወሰኑ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ህይወት ጠፍቷል " - ጠቅላይ ምክር ቤቱ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ዛሬ አርብ ምሽት የሀዘን መግለጫ አውጥቷል።
በተፈጸመው ጥቃት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በተጨማሪ የእስልምና እምነት ተከታዮችም መገደላቸውን አመልክቷል።
ም/ቤቱ ምን አለ ?
" በአርሲ ዞን ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ጥቅምት 14 ለ15 2018 እንዲሁም ጥቅምት 18 ለ 19 /2018 ወገኖቻችን በተኙበት ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ካወጧቸው መግለጫዎች ለመረዳት ችለናል " ብሏል።
" በዚሁ አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት ሳቢያ የተወሰኑ የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችንም ህይወት መጥፋቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ ለማወቅ ችለናል " ሲል ገልጿል።
ሟቾችን ምን ያህል እንደሆኑ በዝርዝር አላመለከተም።
ጠቅላይ ም/ቤቱ " በደረሰው አሳዛኝ ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች መፅናናትን ፤ ለሙስሊም ወንድሞቻችንንም አሏህ ጀነተል ፊርደውስ እንዲወፍቃቸው እና ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን " ብሏል።
" መንግስት የሰው ልጅን በዚህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረጉ አካላትን በመከታተል ለህግ ያቅርብ " ሲል ምክር ቤቱ አሳስቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
@tikvahethiopia

😭1.52K❤1.03K😡435🤔160💔71🕊60🙏41😢27👏26😱12🥰7
Mesirat Mahber is a dedicated space for Ethiopian entrepreneurs who need more than just motivation:
Expert-built resources: In-depth PDFs on business development, finance, legal, investment, and marketing — all tailored to the local context
Practical toolkits to help you manage and scale your business
A supportive community of people who’ve been where you are
Events and resources designed to help you move forward strategically
👉 Access these resources and grow your business, join today: https://mahber.mesirat.org/wp-login.php?redirect_to=https%3A%2F%2Fmahber.mesirat.org%2F&bp-auth=1&action=bpnoaccess

❤116💔4😭4😢1
በታንዛኒያ በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የወቅቱ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን 98% ድምፅ አግኝተው ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አሳውቋል።
ምርጫውን በርካቶች የይስሙላ እና ፉክክር አልባ ነው በማለት ተችተውታል።
ሁከት እና ተቃውሞም ቀስቅሷል።
የፕሬዜዳንቷ ቀንደኛ ተቀናቃኝ የሆኑ 2 ተቃዋሚዎች በምርጫ ባለመሳተፋቸው ነው አለመረጋጋት የተቀሰቀሰው።
አንደኛው ዋነኛ ተቃዋሚ ሲታሰሩ ሌላኛው ተቃዋሚ ከምርጫው ታግደው ነው ምርጫ የተደረገው።
የሀገሪቱ መንግሥት ኢንተርኔት ጠርቅሟል። የሰዓት እላፊ አውጇል።
ምርጫውን ተከትሎ በተነሳው ሁከት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። የተቃዋሚ ኃይሎች ቢያንስ 700 ሰዎች መገደላቸውን ለሚዲያዎች አመልክተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ከ16 ትንንሽ ድምፅ ካላቸው ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወዳድረው ምርጫውን 98% ድምጽ አግኘተው ማሸነፋቸው ዛሬ ተነግሯል።

😭307❤283🤔32💔19😡18🙏9😢5🕊3🥰1😱1
የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?
➡️ በከፊል ኃይድሮጂኔሽን ሂደት የተለወጠ ስብ የያዘን ምግብ ማምረት ወይም ወደ ሀገር ማስገባት ሙሉ ለሙሉ ይከለክላል።
በሀገራችን ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች በየዓመቱ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚጠቁ እና በየአመቱ ከሚሞተው ሰው 43 በመቶ የሚሆነው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ምክንያት እንደሆነ የኢትዮጵያ ሥነ-ምግብ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ገልጿል።
ይህን ታሳቢ ያደረገ የታሸጉ ምግቦችን ለመቆጣጠር የሚረዳ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ምክክር ምክክር እየተደረገበት እንደሚገኝ ተገልጿል።
ለመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ምን ይዟል ?
ረቂቅ አዋጁ ሙሉ ለሙሉ የታሸጉ ምግቦችን አልከለከለም። ነገር ግን ከተቀመጠላቸው መጠን በላይ ጨው፣ ስኳር፣ ሳቹሬትድ ስብ ወይም በፋብሪካ ሂደት የተለወጠ ስብ እንዲሁም ስኳር ያልሆነ ማጣፈጪያ የያዙት ላይ ነው ክልከላዎችን አስቀምጧል።
በረቂቅ አዋጁ በከፊል ኃይድሮጂኔሽን ሂደት የተለወጠ ስብ የያዘን ምግብ ማምረት ወይም ወደ ሀገር ማስገባት፣ ማከፋፈል ወይም ለምግብ አገልግሎት ማቅረብ ሙሉ ለሙሉ ይከለክላል።
ከመጠን ያለፈ ንጥረ-ነገር እንዳለው የሚቆጠረው እንዴት ነው ?
- በምግብ ውስጥ ያለው የሶዲየም መጠን በሚሊግራም ከአጠቃላይ የኃይል መጠን (ኪሎ ካሎሪ) ጋር እኩል ወይም የሚበልጥ ከሆነ፤
- በረቂቅ አዋጁ 1 ግራም ስኳር 4 ኪሎ ካሎሪ ኃይል እንደሚሰጥ ይቆጠራል ይላል። በዚህም መሰረት ምግቡ ጠጣር ከሆነ ከምግቡ ከሚገኝ 10% ኃይል ወይም ከዛ በላይ ሲሆን፤
- ምግቡ በስኳር የጣፈጠ ፈሳሽ ከሆነ ከምግቡ ከሚገኝ 5% ኃይል ወይም ከዛ በላይ ሲሆን፤
- በረቂቅ አዋጁ 1 ግራም ሳቹሬትድ ስብ 9 ኪሎ ካሎሪ ኃይል እንደሚሰጥ ይቆጠራል ይላል። በዚህም መሰረት ምግቡ ከሚሰጠው አጠቃላይ ኃይል ውስጥ 10% ወይም ከዚያ በላይ ኃይል ከሳቹሬትድ ስብ የሚያገኝ ከሆነ ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር የሚደረግበት ተብሎ ይለያል።
ከመጠን ያለፈ ቁጥጥር የሚደረግበት ንጥረ ነገር የያዙ ምግቦች ላይ ምን ክልከላ ተቀመጠ ?
የተለዩ ምግቦች ወይም መጠጦች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው፣ ጥንካሬ እንደሚሰጥ ወይም "ምርጥ"፣ "ጥራት ያለው"፣ "ኦርጂናል" እንዳለው መግለጽ ከልክሏል።
ልጆችን የሚስብ ታዋቂ ገጸ-ባህሪን፣ የልጆች አገላለጽን ወይም ቋንቋን፤ የልጆች ስዕል ወይም ፎቶ በማሸጊያው ላይ ማስቀመጥ ከልክሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ቁጥጥር የሚደረግባቸውን ንጥረ-ነገሮች የያዙ ምግቦች/መጠጦች የጤና ማስጠንቀቂያ ምልክት በፊምግቦችት ለፊት ማሸጊያቸው ላይ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል። በመግለጫቸውም ፥ " ከመጠን ያለፈ ስኳር ያለው " የሚሉ አገላለጾችን እንዲያስቀምጡ ያስገድዳል።
ምርታቸውን፣ የንግድ ስማቸውን፣ አርማቸውንና ሎጓቸውን በማኅበራዊ ሚዲያና ቢልቦርድን ጨምሮ በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ማስተዋወቅ እንዳይችሉ ይከለክላል።
በየአካባቢው ባሉ ሱቆች ላይ የታሸጉ ምግቦችን ፊት ለፊት አንዳያዩት ማድረግ ግድ ሲል፣ ፊት ለፊት በሚያስቀምጡ ነጋዴዎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ ይጠቅሳል።
ረቂቅ አዋጁ በዘርፉ ያለውን ቁጥጥር ያሳድጋል ሲባል ኢንዱስትሪዎች በተጠቀሱሱት መጠኖች ምርታቸውን እንዲያቀርቡ አልያም ተፈጻሚ የሚሆኑ አስገዳች ሁኔታዎችን እንዲተገብሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በተጨማሪም ይህንን በማይፈጽሙ ላይ ከአስተዳደራዊ የገንዘብ መቀጮ እስከ አምስት ዓመት እስራት ድረስ የሚዘልቅ መቀጮን ያካተተ ነው።
ℹ️ ከፊል ኃይድሮጂኔሽን በአርቴፊሻል መልኩ የተለወጠ ስብ የሚፈጠርበት ሂደት ሲሆን ፈሳሽ ዘይትን ወደ ከፊል-ጠጣር ቅባቶች (semi-solid fats) ለመቀየር ይውላል። አርቴፊሻል መባሉም በተፈጥሮ ከሚገኘው በተለየ በማቀነባበር ሂደት የሚፈጠር በመሆኑ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.02K👏190🙏49😭19😡12🤔9🥰8😢4
#Chapa 🤝 #EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻፖ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ የባንክ ኤቲ ኤም(ATM) ካርድ መለያ ቁጥርን በመጠቀም የበረራ ትኬትን መግዛት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋታቸዉን ይፋ አድርገዋል፡፡
እስካሁን በዚህ አገልግሎት አምስት ባንኮች፥ ሕብረት ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ቡና ባንክ አገልግሎቱን የተቀላቀሉ ሲሆን
የቻፓ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናኤል ኃይለማርያም አሁን ላይ አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ ገንዘብ መጠቀም የሚያስችል እንደሆነ ገልጸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ገንዘቦችን ግዢ መፈጸም ይጀምራል ብለዋል።
አክለውም፥ “ይህ አጋርነት ለሀገራችን የዲጅታል ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ዕድገት አዲስ እና ተጨማሪ መሠረት ከመጣል አልፎ በክፍያና ገንዘብ ዝዉዉር ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ካለው አስትዋጽዖ ባሻገር ራዕያችንን እዉን ለማድረግ የሚያስችለን ከፍተኛ ምዕራፍ ነዉ" በማለት ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየርመንገድ ኦንላይን/በይነ መረብ እና ተንቀሳቃሽ ስልካቸዉን (ሞባይል) ተጠቅመዉ የበረራ ትኬት ግዥዎችን ያለምንም ዉጣ ዉረድ በቀላሉ መፈጸም የሚያስችል የዲጂታል ፋይናንሻል ቴክኖሎጂዉን የበለጠ ያዘመነ ነው ተብሏል።
ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያለ ዉጣ ዉረድ ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ የገንዘብ ክፍያ እና ዝዉዉር መፈጸም የሚያስችል የቴክኖሎጂ አገልግሎትን ለገበያያስተዋወቀ ግንባር ቀደም የዲጅታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።
#FlightMeetsFintech
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻፖ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ የባንክ ኤቲ ኤም(ATM) ካርድ መለያ ቁጥርን በመጠቀም የበረራ ትኬትን መግዛት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋታቸዉን ይፋ አድርገዋል፡፡
እስካሁን በዚህ አገልግሎት አምስት ባንኮች፥ ሕብረት ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ቡና ባንክ አገልግሎቱን የተቀላቀሉ ሲሆን
ሌሎች ባንኮችም በመንገድ ላይ ናቸው ተብሏል።የቻፓ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናኤል ኃይለማርያም አሁን ላይ አገልግሎቱ በሀገር ውስጥ ገንዘብ መጠቀም የሚያስችል እንደሆነ ገልጸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ገንዘቦችን ግዢ መፈጸም ይጀምራል ብለዋል።
አክለውም፥ “ይህ አጋርነት ለሀገራችን የዲጅታል ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ዕድገት አዲስ እና ተጨማሪ መሠረት ከመጣል አልፎ በክፍያና ገንዘብ ዝዉዉር ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ካለው አስትዋጽዖ ባሻገር ራዕያችንን እዉን ለማድረግ የሚያስችለን ከፍተኛ ምዕራፍ ነዉ" በማለት ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየርመንገድ ኦንላይን/በይነ መረብ እና ተንቀሳቃሽ ስልካቸዉን (ሞባይል) ተጠቅመዉ የበረራ ትኬት ግዥዎችን ያለምንም ዉጣ ዉረድ በቀላሉ መፈጸም የሚያስችል የዲጂታል ፋይናንሻል ቴክኖሎጂዉን የበለጠ ያዘመነ ነው ተብሏል።
ቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂስ አ.ማ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያለ ዉጣ ዉረድ ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ የገንዘብ ክፍያ እና ዝዉዉር መፈጸም የሚያስችል የቴክኖሎጂ አገልግሎትን ለገበያያስተዋወቀ ግንባር ቀደም የዲጅታል ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።
#FlightMeetsFintech
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤225🙏9😡7👏6
#SafaricomEthiopia
2ቀን ብቻ ቀረው! ቀጣይ ሚሊየነር ማን ይሆን ?🏆💚 ዛሬዉኑ የበሽ ጥቅልን ይግዙ፤ ሚሊየነር የመሆን እድሎን ያስፉ!
📲 የM-PESA መተግበሪያን አሁኑኑ ያውርዱ፡ https://onelink.to/ewsb22
የቴሌግራም ቦታችን: https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot
ወደ *777*0# ይደውሉ ወይም በM-PESA የበሽ ጥቅል ይግዙ!
#MPESASafaricom
#furtheraheadtogether
#Besh

❤34😡2
" የሱስ ችግር በጣም እየሰፋ መጥቷል። አሁን ሱስ የሚጀምሩበት እድሜም ወደ ህፃናት ደረጃ ወርዷል " - የአማኑኤል ሆስፒታል ዳይሬክተር
የሱስ ተጠቃሚዎችና ታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑና መከላከል ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት አማኑኤል የአዕምሮ ህሙማን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
የሆስፒታሉ የተሃዲሶ ህክምና ክፍል ቡድን መሪ አቶ እንዳለ ማሞ ምን አሉ ?
" የሚገቡትና የሚወጡት ህሙማን ቁጥር ተለዋዋጭ ስለሆነ መናገር ቢያስቸግርም የሱስ ተመላላሽ ታካሚዎች ቁጥር ግን ከአምናው አንፃር ከፍተኛ ነው።
መንስኤው ሰዎች የሚመርጧቸው መዝናኛ አማራጮች ስለሰፉ ነው፡፡ አማራጩ ሰፊ ስለሆነ ሰዎች ሳያስቡት በሱስ ይጠመዳሉ ለዚህም የቴክኖሎጅና የሱስ አስያዥ ነገሮች መስፋፋትና መብዛት ነው።
በእኛ ሀገር ያልተለመዱ የሱስ አይነቶች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው አዳዲስ ሱስ እየተፈጠረ ነው። ለምሳሌ ለህክምና የሚሰጡ መድኃኒቶችን ወደ ሱስ የመቀየር ፣ ኢንተርኔት የስልክ አጠቃቀም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ኃይሌ ምን አሉ ?
" የሱስ ችግር በጣም እየሰፋ መጥቷል። አሁን ላይ ሱስ የሚጀምሩበት እድሜም በጣም ወደ ህፃናት ደረጃ ወርዷል።
ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ የሱስ አይነቶች እየመጡ ነው፤ ለምሳሌ ካናቢስ የሚባለው ብዙም የተለመደ አልነበረም፤ አሁን ግን በየስርቻው ሊገኝ እንደሚችልነው የምሰማው።
ብዙ ህፃናት በዚሁ የሱስ ችግር እንደተጠመዱ መሆኑን፥ የጎዳና ልጆች የሚጠቀሙባቸው የሱሶች አይነቶችም አሉ። በጤና ባለሙያዎችም እየተበራከተ የመጣ አነቃቂ መድኃኒት አላግባብ የመጠቀም ሁኔታ አለ፤ በታብሌት የሚወሰዱትን በመርፌ እስከሚሰጡ ድረስ።
ከሌላ ሀገር ጉዞ የሚያደርጉና አዲስ አበባን አቋርጠው በሚያልፉ ዜጎች ደግሞ አደገኛ አደንዛዥ እፆች እየገቡ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የተለመዱትን እንደጫት አይነት እፆችን ጨምሮ ስርጭቱ ጨምሯል። በሰሜን በኩል አልነበረም አሁን ግን ጫፍ እስከ ጫፍ ይገኛል፡፡ በምሥራቅና ደቡብምዕራብ አካባቢ የነበረው ተስፋፍቶ አሁን የሌለበት ቦታ የለም።
አልኮልም ከጠዋት ጀምሮ የሚጠጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ በጣም እየጨመረ ያለ ችግር ነው፡፡ የአዕምሮ ጤና ችግር ሀኪም ብቻውን የሚፈታው አይደለም " ሲሉ ነግረውናል።
መፍትሄውን በተመለከተ ዶክተር ክብሮም ምን አሉ?
" ወጣቱ አማራጭ ማግኘት አለበት፣ ህፃናት ላይ መሰራት አለበት፤ ሱስን መከላከል የሚቻለው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው።
Demand Reduction (ሰዎች ወደ እፅ መጠቀም የሚሄዱበትን መንገድ ማስቀረት እንኳ ባይቻል መቀነስ)፣ Supply Reduction (ሰዎች እጾችን እንዳያገኙት ማድረግ) ይገባል።
ይህ ፕሮግራም በሀገር ደረጃ መሰራት አለበት። ግን ትኩረት እየተሰጠው አይደለም " ነው ያሉት።

3❤657😢112🙏60😭37💔31👏12🕊12🤔10🥰8😱7😡7