Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ወረዳ 8 ውስጥ የሚገኙ 2 የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች ቤቶች ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ሙሉ በሙሉ እንደገና በመገንባት ለባለቤቶቹ አስረከበ፡፡
(ሰኔ 6/2017ዓ.ም)በክፍለ ከተማው አስተዳደር እና የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በቀረበልን ጥያቄ መሰረት የቅ/ጽ/ቤቱ ጥራት የብልጽግና ህብረት ከቅ/ጽ/ቤቱ ጠቅላላ ካውንስል ጋር ተልዕኮውን በመረከብ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሚገኙት የግል ት/ቤቶች ውስጥ 10 በጎ አድራጊ ት/ተቋማትን በመለየትና በማስተባበር በጠቅላላው ከ7 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ2 አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን መኖሪያ ቤቶችን እንደገና በመገንባትና የቤት እቃ በማቅረብ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና፣ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮሐንስ ለገሰ የቅ/ጽ/ቤቱ ስ/አስኪያጅ አቶ አብርሃም ምትኩ እና ሌሎችም የክ/ከተማውና ወረዳ 8 አመራሮች የቅ/ጽ/ቤታችን ጠቅላላ ካውንስል አባላት፣ የቤቶችን ግንባታ ስራ በገንዘብ ድጋፍ አድርገው ያሰሩት በጎ አድራጊ ት/ቤቶች ባለቤቶች በተገኙበት በማስመረቅ ነዋሪዎቹ ተረክበዋል፡፡

የቅ/ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ምትኩ ይህንን የበጎ ፍቃድ ስራ በማስተባባር ላስፈጸሙት የጠቅላላ ካውንስል አባላት፣ የክፍለ ከተማውና የወራ 8 ህብተረሰብ ተሳፎ ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በዋናነት ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን በማቀናጀት እና በአካል በቦታው በመገኘት ተከታትለው የጎደለውን እያሟሉ ስራውን እንዲሰራ ላደረጉት የ10 ት/ቤቶች ባለቤቶች ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የቤቶቹን ባለቤቶችም እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና በእለቱ ግንባታውን ተጠናቆ ለነዋሪዎቹ የተላለፉትን ቤቶች ምረቃ ካደረጉ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ መርህ በሆነው ቃልን በተግባር ቤቶችን በ2 ወራት ባልሞላ ጊዜያት ሙሉ በሙሉ እንደገና ተገንብቶ ማስረከብ በመቻሉ ፓርቲውና አስተዳደሩ ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው የቤት ባለቤቶችን እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን የቤቶቹን ግንባታ ሙሉ ወጪ በመሸፈን ያሰሩትን 10 የግል ት/ቤቶች ባለቤቶች እና ስራውን በማስተባባር እንዲሰራ ላደረገው የባለስልጣኑ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ጠቅላላ ካውንስል ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የቤቶችም ባለቤቶች በጣም ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውና ለቀሪው ህይወታቸው ምቹ መኖሪያ ስለተገነባላቸው ለሁሉም በጎ አድራጊዎችና ለአስተባባሪዎችም ጭምር ምስጋናቸውን አቅርበው አባታዊና እናታዊ ምርቃታውን ለግሰዋል፡፡
ምንጭ፡- አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለቀጣይ 90 ቀናት በሚከናወነው ልዩ የንቅናቄ አጀንዳ ዙሪያ ለመላው አመራር የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
ይህ የልዩ ተልዕኮ አጀንዳ ከሰኔ 5 እስከ ጳጉሜ 5 ባሉ 90 ቀናት የሚከናወን ሲሆን 18 ዋና ዋና ተግባራትን አካትቶ ይዟል፡፡ ከነዚህ የንቅናቄ አጀንዳዎች መካከል የከተማ ግብርናን ማስፋፋት፣የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን ማሳካት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች፣ የኑሮ ውድነትን መቆጣጠር፣ ሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማትን ማጠናቀቅ፣የትምህርት ለትውልድ ኢኒሼቲቭ፣ ገቢን ማሳደግ፣ እየተገነቡ የሚገኙ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን(Mega Projects) አጠናቅቆ ለህዝብ ክፍት ማድረግ፣ ስራ ዕድል ፈጠራ እና ፍትሃዊ አገልግሎትን ለህዝባችን ተደራሽ ማድረግ አንኳሮቹ ናቸው፡፡
እነዚህንና ተያያዥ የለውጥ የንቅናቄ ተግባራትን ለማሳካት አመራሩ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ በመንቀሳቀስ የህዝባችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባዋል ያሉት ከንቲባዋ የዚህ ልዩ ተልዕኮ ዋነኛው ፈጻሚ ሀይል ደግሞ ከከተማ ማዕከል ጀምሮ እስከ ወረዳ ያሉ ተቋሞችና የአስተዳደር አካላት ይሆናሉ ብለዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም ተቋማት ምን ያህል"ሰራተኛን የልማት አቅም ማድረግ ችለናል?"የሚለው ዋነኛ መመዘኛችን ይሆናል ያሉት ከንቲባ አዳነች ትልቁ የልማታችን ሞተር የሆነው የህዝባችንን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጥብቅ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት እያንዳንዱን የንቅናቄ አጀንዳ ስኬታማነት ኦዲት እያደረግን እንሄዳለን ብለዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ በበኩላቸው የአዲስ አበባ አመራር ግዙፍ የሆኑ የልማት ስራዎችን በጥራት እና በአጠረ ጊዜ የማሳካት ቅንጅታዊ ብቃቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በማንሳት ይህ የክረምት ንቅናቄ አጀንዳም የፓርቲ እና የመንግስት አቅሞችን በማስተባበር ማሳካት ይቻላል ብለዋል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ጀርመን አደባባይ አካባቢ በመንግስት በጀት በመገንባት ላይ የሚገኙት የመኖሪያ ቤቶች የደረሱበትን ደረጃ ገምግመናል።

ከተጀመረ 9 ወር የሆነዉ ይህ ግንባታ በጥራት እና በፍጥነት ወደ ማጠናቀቂያዉ ላይ በመሆኑ ቀሪ ስራዎችን በመጨረስ ተጨማሪ የቤት አቅርቦት የመጨመር ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

በአሁኑ ሰአት ያለዉ የቤት ፍላጐት በመንግስት ብቻ ሊመለስ የሚችል ባለመሆኑ በቤት ግንባታ ስራ ላይ የተሰማራችሁ የግል አልሚዎችም የቤት አቅርቦትን መጨመር የከተማችን ትልቁ ትኩረት መሆኑን በመገንዘብ እና መንግስት እንዲህ በአጭር ጊዜ መገንባት ከቻለ ከግሉ ዘርፍ ከዚህ በላይ ስለሚጠበቅ የጀመራቹሃቸውን ግንባታዎች በፍጥነት እና በጥራት እንድታጠናቅቁ እንዲሁም መሬት አጥራችሁ ግንባታ ያልጀመራችሁም በፍጥነት ጀምራችሁ በማጠናቀቅ ለቤት ፈላጊዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አብራችሁን እንድትሰሩ ጥሪዬን እያቀረብኩ የከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊዉን ድጋፍ የሚሰጣችሁ መሆኑንን በድጋሚ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2025/07/14 02:50:58
Back to Top
HTML Embed Code: