Telegram Web Link
በ90 ቀናት ለሚከናወነው የንቅናቄ ስራዎች እቅድ ላይ የባለስልጣኑ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተወያዩ፡፡
(ሰኔ 10 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ዳዊት ለቀጣይ 90ቀናት የሚከናወነው እቅድ ዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ዕቅዱ በ90ቀናት ውስጥ የሚተገበሩ የተለያዩ ግቦችን የያዘ እና ተግባራቱ የሚተገበሩበት ጊዜ እና ዝርዝር አፈጻጸሞችን የያዘ ሲሆን የ90 ቀናቱ ግቦች የተሳኩ እንዲሆን አብይ ኮሚቴ እና ንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡
በእቅዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚተገበሩትን ግቦች ካስኬድ በማድረግ እንዲሰሩ እና ለተግባራቱ የሚያስፈልጉትን ሀብቶች እንዲያሰባስቡ የሚያመላክት ነው፡፡
በውይይቱ የተገኙት የስራ ኃላፊዎች እንደገለፁት ተግባራቱ የሚከናወኑት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆኑ በተለይ የሀብት ማሰባሰብ የሚያስፈልጋቸው ግቦች ከወዲሁ ከትምህርት ተቋማት ጋር በመወያየት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
እንዲሁም እቅዱን በተቀመጠው ጊዜ እና ጥራት ተጠያቂነት በሠፈነበት አሠራርን በመፍጠር በቁርጠኝነት በትብብር መንፈስ ከተሠራ እቅዱ መሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በቀረበው እቅድ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ዛሬ "በአፍሪካ ጥራት ያለውና አካታች የሆነ የህጻናት እድገትን ለማረጋገጥ የጋራ ትብብርን ማጠናከር" በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ የህፃናት ክብካቤ እና ጥበቃን የተመለከተ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እያካሄድን ነዉ።

ኮንፍረንሱ አዲስ አበባ እንዲካሄድ የተመረጠዉ ከተማዋ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ህጻናት በአዕምሮ፣ በአካል እና በስነልቦና የተሟላ ዕድገት እንዲጎናጸፉ ለማስቻል የሰራችዉ የተቀናጀ እና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም አፍሪካውያን ትምህርት የሚወሰዱበት ውጤታማ ስራ በመሆኑ ጭምር ነው።

እኛም አፍሪካዊያን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለተሻለ ነገ ከልብ እንድንሰራ ጥሪ በማቅረብ እስካሁን በከተማችን የሰራናቸዉን ስራዎች ልምድ አጋርተናል።

መድረኩን ያዘጋጀውን የአፍሪካ ህብረት የጤና፣ የሰብዓዊ ጉዳዮችና ማህበራዊ ልማት ኮሚሽንን እያመሰገንኩ፤ ኮንፈረንሱን ለመታደም ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጣችሁ ሚንስትሮች ፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ የዘርፉ ባለሞያዎች እና ተመራማሪዎች በከተማችሁ አዲስ አበባ ያላችሁ ቆይታ ያማረ እና የተሳካ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሙያ ብቃት ምዘና ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ እና ብቁ እና ተወዳደሪ ዜጎችን ለማፍራት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
(ሰኔ 11 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአዲስ ከተማ እና ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የቴክኒከና ሙያ ብቃት ምዘና አገልግሎት ዝግጅትና አሰጣጥ ዳይሬክቶሬት የ11 ወር የስራ አፈፃፀም በመገምገም እና በቀጣይ በትኩረት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ፡፡
አቶ አንዋር አብዲ የአዲስ ከተማ እና ልደታ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ በውይይት መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ለሚነሱ ጥያቄዎች በምዘና ሂደቱ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በመለየት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በመድረኩም ስለ አዲሱ (ሆልስቲክ) ምዘና አፈፃፀም፣ስለአጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች እና ከመዛኝ ስነ-ምግባር እና ብልሹ አሰራርን በተመለከተ ከመድረክ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡የተቋማት ባለቤቶችና አመራሮች በአዲሱ የሙያ ደረጃ መሰረት እየተሰጠ ስላለው የቴ/ሙ/ብ ምዘና የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከመድረኩ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን የጋራ ግንዛቤ መያዝ ተችሏል፡፡
(ሰኔ 13 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 በካቢኔ በቅርቡ መጽደቁ ይታወቃል ፡፡ባለስልጣኑ በፀደቀው ደንብ ዙሪያም መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡በመሆኑም የክፍያ ጭማሪው የተገለጸው የዋጋ ጣሪያ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ትምህርት ቤቶች ወላጆችን በመጥራት ማወያየት ይገባቸዋል፡፡
ወላጆችና ት/ቤቶች በጋራ በሀሳቡ ላይ በመወያየትና በመመካከር የሚወስኑ ሲሆን በቀረበው የክፍያ ጭማሪ ላይ ወላጆች ት/ቤቱ ባቀረበው ፕሮፖዛል መሰረት መግባባት ላይ መድረስ ካልችሉ ወደ ባለስልጣኑ ሪፖርቱን የሚያመጡ ይሆንና ባለስልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል፡፡በመሆኑም ትምህርት ቤቶች ወላጆችን በክፍያ ጭማሪ ዙሪያ ለማወያየት ሲጠሩ ወላጆች በመገኘትና በብስለት በመወያየት ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ባለስልጣኑ ያሳስባል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
2025/07/02 00:39:47
Back to Top
HTML Embed Code: