Telegram Web Link
(ሰኔ 13 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለትምህርት ተቋማት የተሰራ የመደበኛ የኢንስፔክሽን ደረጃ መረጃ እና በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ የሚያደርጉ ት/ቤቶች መረጃ የሚከተለውን ይመስላል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ባለስልጣኑ አዲስ ባለማው ሲስተም በስራ ሂደቱ ዙሪያ ለአመራሮች ስልጠና ሰጠ፡፡
(ሰኔ 13 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አዲስ ባበለጸገው ሲስተም በስራ ሂደቱ እና በአተገባበሩ ዙሪያ ለማእከል አመራሮች እና ለቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የባለስልጣኑ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታምራት እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ሲስተም ተጠቃሚ ለሆኑ ባለሙያዎች ስልጠናው መሰጠቱን ጠቅሰው በዛሬው ዕለትም ለባለስልጣኑ አመራሮች እና ለ9ኙ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተግባር ተኮር ስልጠና ከኢኖቬሽን ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ስልጠናው የተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው ሲስተሙ ጥራቱን የጠበቀ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ስለሚያስችል እንዲሁም ሲስተሙን ተግባራዊ ለማድረግና ለመከታተል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ስልጠናው መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ባለስልጣኑ በትምህርት አገልግሎት ክፍያ ዙሪያ ተቋማት ከተማሪ ወላጆች ጋር በሚያደርጉት ውይይት ላይ በታዛቢነት ለሚገኙ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡
(ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በትምህርት አገልግሎት ክፍያ ዙሪያ ተቋማት ከተማሪ ወላጆች ጋር ነገ ማለትም ሰኔ 14 ቀን ለሚጀመረው ውይይት በታዛቢነት ለሚገኙ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡
ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥራት ዘርፍ ሀላፊ በመርሀ-ግብሩ ላይ በመገኘት እንደገለጹት በሚካሄደው ውይይት ላይ እንደ ታዛቢ የሚገኙ ባለሙያዎች ከታዛቢ የሚጠበቀውን ሀላፊነትና ተግባር በገለልተኝነት ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 በቅርቡ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የጸደቀ ሲሆን ይህንንም መሰረት በማድረግ የትምህርት ተቋማት በትምህርት አገልግሎት ክፍያ ዙሪያ ከተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት የሚደረግ ሲሆን ኦረንቴሽኑም ከባለስልጣኑ እና ከትምህርት ቢሮ ለተውጣጡ ታዛቢ ባለሙያዎች የተሰጠ መሆኑ ታውቋል፡፡
ትምህርት ተቋማት ከተማሪ ወላጆች ጋር በዋጋ ጭማሪ ዙሪያ ባቀረቡት የመነሻ ሃሳብ ላይ ተወያዩ፡፡
(ሰኔ 14 ቀን 2017ዓ.ም) በዛሬው ዕለት የተማሪ ወላጆች በዋጋ ጭማሪ ዙሪያ ውይይት ካደረጉት የትምህርት ተቋማት መካከል ካየናቸው ት/ቤቶች በአራዳ ክ/ከተማ የሚገኘው የራዲካል አካዳሚ ት/ቤት እና ወላጆች ባደረጉት ውይይት ት/ቤቱ የክፍያ ጭማሪ ፕሮፖዛሉን እና የክፍያ መጠኑን ለቤቱ በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ወላጆችም ሰፊ ሃሳቦችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡

በዚህም ተቋሙ ጭማሪውን ያደረገበትን ዋና ዋና ሃሳብ ሲያስቀምጥ ለግብዓት ማሟያ፣የትምህርት ጥራት ስታንዳርዱን ለማጠበቅ፣ስቴሽሪ እቃዎችን ለማሟላት፣አስተዳደራዊ ወጪዎችን ለመሸፈን፣የመምህራን ደመወዝን ጭማሪ ለማድረግ፣የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ለመጠቀም እንዲሁም ሌሎችንም በመዘርዘር ያቀረቡ ሲሆን ወላጆች በቀረበው የመነሻ ሃሳብ ላይ እንደተናገሩት እንደዚህ አይነት የውይይት መድረክ መኖሩ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው የነገ አገር ተረካቢ ልጆችን የምናስተምርበት ተቋም የተሻለ ቢሆንና የተሻለ ውጤት ቢኖረው የሚመኙ መሆናቸውን ጠቅሰው የዋጋ ጭማሪው ላይ ግን በተቋሙ ፕሮፖዛል ላይ የተቀመጠው ዝርዝር ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወላጆች አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚኘው የሊንደን ውድ አካዳሚ ላይ ተገኝተን ባደረግነው ምልከታ ወላጆች ትምህርት ቤቱ ባቀረበው ፕሮፖዛል መነሻነት በመወያየትና የራሳቸውንም ሃሳብ በማንጸባረቅ ከተወያዩና ድምጽ ከሰጡ በኋላ በመግባባት ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥራት ዘርፍ ሃላፊ በውይይት መደረኮቹ ላይ በመገኘት ወላጆች ለሚያነሷቸው ግልጽነት ለሚስፈልጋቸው ሃሳቦች ግልጽነትን የፈጠሩና ሃሳቦችን ያብራሩ ሲሆን ወላጆችና የትምህርት ተቋማት በሚያደርጉት ውይይት መግባባት ላይ መድረስ ካልቻሉ ልዩነቱን ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በማምጣት የመፍትሄ ውሳኔ ባለስልጣኑ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ነገ እንዲሁም በቀጣይ ሳምንታት በሚኖሩ ውይይቶች በሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚገኙ ወላጆች በውይይቱ ላይ በመገኘትና የነቃ ተሳትፎና የበሰለ ውይይት በማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በተገኘንባቸው መድረኮች ላይ የባለስልጣኑ እና የቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣መድረኩን በታዛቢነት የሚከታተሉ ተወካዮች እንዲሁም የወተመህ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በነገው ዕለትም በሌሎች ተቋማት ላይ ውይይቱ የሚደረግ ይሆናል፡፡


#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
2025/06/28 20:35:58
Back to Top
HTML Embed Code: