እውነት ነው አስችሎሻል አልፈለግሽኝም
ከቀናቶች በኋላ..........
🚶🚶🚶🚶🏃🏃🏃🏃🏃🏃

ተጓዥ ነን እና ተጠርተንም ሳንጠራ እየሄድን ነው። እስካሁን በመጣንበት መንገድ ብዙ ነገሮችን አልፈናል...በሁላችንም መንገድ ላይ የማይቀሩ ነገሮች አሉ....ማግኘት እና ማጣት። ግን ደግሞ ስናገኝም ስናጣም ከጎናችን የነበሩ፣ ያገኘነወን ፍለጋ ያልመጡ፣ ያጣነውን ተከትለው ያልሄዱ ልዩ ሰዎች ህይወታችን ውስጥ አሉ። ጌታ እነኚን ሰዎች ይጠብቅ🙏 ለዛሬ ለዝችም ቦታ የደረስነው በ እኛ መሻት ብቻ ሳይሆን ከጎናችን ባሉ ጥሩ ሰዎች ምክንያት እና በ እግዜር ምህረት የተነሳ ነው። ምስጋና ለ እርሱ ከዛም ለነሱ.....።

አቤኔዘር 🤒
@ABEN_E 💐 🌘 30/07/2013 (ሀሙስ)🌑
የኔን አለም የሚወዱት እኔን የሚመስሉ ብቻ ናቸው። ልክ ነህ የሚሉኝም እኔ ን የሚመስሉ ብቻ ናቸው። ልክ ነኝ ሰክሬም፣ አልሰከርክም ብትሰክርም አልተንገዳገድክም፤ ብትወድቅም ስለሰከርክ ሳይሆን መሬት ስለጣለችህ ነው፤....... ብታብድም ጤነኛ ስለሆንክ ነው የሚሉኝ እኔን የሚመስሉ ስሜቴ የገባቸው ብቻ ናቸው።

#እኔ_ነኝ_አቤኔዘር 🤒
Forwarded from  (Λβ㉫ŋ㉫)
ከ ሰው ጋር ተላምዶ መለያየት ይከብዳል አይደል? መልስሽ አዎ እንደሆነ አውቃለው። አብረን ለሰከርንባቸው እና ላበድንባቸው 23 ቀናት በእኔ ና በ ሰካራም ጓደኞቼ ስም አመሰግናለው። ደግሞ እንደምትናፍቂኝ አትርሺ! ብቻሽን እየሰከርሽ ወይም ደግሞ እያበድሽ አስታውሺኝ……እሺ!

😘😞😞😞😞😞😞😞😞😞😘

ከኔ ላንቺ አሁን ሄደሽ ነገ ለምትመጪው
ሁሉም እንዳስቀመጥሽው አይደለም።
እግዜር ይመስገን*******🙏

መሽቶ ነበር እግዜር ይመስገን እኛም አረቄ ቤት ነበርን.....እየጠጣን የሞቀ ጨዋታ ላይም ነበርን.....ስለ ሚጠሉን ሳይሆን ስለምንወዳቸው እያወራን.....እግዜር ይመስገን ሰዉ ሲተኛ እኛ አረቄ ቤት ነበርን......በተፈጠረንበት ሳይሆን በፈጠርነው አለም ውስጥ ሆነን ሁሉም የሆነውን ሲሆን እግዜር ይመስገን የዛች ቀን ምሽት እኛ አረቄ ቤት ነበርን።

#አቤኔዘር
Forwarded from  (Λβ㉫ŋ㉫)
የፈሲካ ዋዜማ…

የዛሬው ምሽት እንደሌሎቹ ምሽቶች አይደለም። ይሄኛው ይለያል። እንደወትሮ የጎዳና መብራቶች አልጠፉም…ዛሬ በርተዋል። ዝናቡም መዝነብ ጀምሯል። አረቄዬን ይዤ እየሮጥኩ ወደ ቤቴ ገባው። ለምን እንደሆነ እኔንጃ ግን ውጪ የነበረውን ድባብ ወድጄዋለው… መስኮቴንም ከፍቼ ወደ ውጪ ማየት ጀመርኩ።…

ዛሬ ዝናቡን የፈራ የለም፤ ሁሉም ሰው አልተጠለለም። ብዙዎቹ እየረጠቡ ፣ እየተንቦራጨቁ እየሄዱ ነው። አንዳንዶች ግን ዣንጥላ ይዘዋል። መብረቁም ድምፁን እያሰማ ብልጭ ድርግም ይላል።

ዛሬ የፋሲካ ዋዜማ ነውና… እናቶች የገዙትን ዶሮ ይዘው በየሱቁ ተጠልለዋል። ያልተጠለሉም በዝናብ ውስጥ ወደቤታቸው እየሄዱ ነው። ልጆች በደስታ ዝናብ ውስጥ ይሯሯጣሉ። አባቶችም የገዙትን በግ ይዘው እየጎተቱ ቤታቸው ለመድረስ በችኮላ እየተራመዱ ነው…

እኔ መስኮቴ ጋ ቆሜ አረቄዬን እየጠጣው ነው። እየመሸ ሲመጣ እንቅስቃሴውም መቀነስ ጀመረ። አሁን ሁሉም ቤት ሞቅ ሞቅ ብሏል እናቶች የገዙትን ዶሮ እየሰሩ ነው። እኔ ቤት ግን እንደዚ አይነት ነገር የለም… ምክንያቱም ያው!! ዱርዬ፣ ሰካራም እና እብድ ስለሆንኩ ሚስት የለኝማ……

አረቄዬን ከነጠርሙሱ እንደያዝኩ ከመስኮቴ ፊት ለፊት ካለው ወንበር ላይ ሄጄ ቁጭ አልኩ…ሸለብም አረገኝ። ከሰዓታት በኋላ ስነቃ ለካ ወንበር ላይ ነው ያደርኩት፤ አይኖቼንም ጠራርጌ ተነሳው… ፀሀዩአም ድምቅ ብላለች… መንገዱም ነጫጭ ልብስ በለበሱ ሰዎች ተሞልቷል።… አራጆችም፤ አራጅ አራጅ አራጅ እያሉ ይጣራሉ…

መስኮቴንም ዘጋው…ቤቴንም አፀዳው። ጀምሬ ያልጨረስኳቸውን ደብዳቤዎቼንም ለይቼ አስቀመጥኩ… የገነፈሉ እስኪብርቶዎቼንም አውጥቼ ጣልኩ። ከቁምሳጥኔም ውስጥ ንፁህ እና ነጭ የባህል ልብስ አውጥቼ፤ ለብሼ ፋሲካን ለማክበር ከቤቴ ወጣው።

ጌታ ምትወዱትን ህይወት ይስጣችሁ!!! መልካም የፋሲካ በዓል።

በ አቤኔዘር
10/08/2012
ቅዳሜ⛅️

🌹◉◉◉የአቤኔዘር ደብዳቤዎች◎◎🌹
✥-- @ABEN_E --✥
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከእለታት የሆነ ቀን ሀገሬ ሰላም ነበረች!!!🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🌿 ዒድ ሙባረክ 💝 Eid Mubarak 🌿

እንኳን ለ1442ኛው ለዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ 💐💐

🥀መልካም በአል🥀

🍃Happy Eid AL Fitr 🍃

🍂 @Red_ii 🍂

🍂 @ABEN_E 🍂
ነገ እንደዛሬ አይሆንም እግዜር ካለ ብዙ ነገሮች ይቀየራሉ.......

🤒🤕🤒🤕🤒🤕🤒🤕🤒🤕🤒🤕
የግጥም ቤት
ለአስተያየት.ለጥያቄ እና ግጥሞትን ማጋራት ከፈለጉ @meqdicatho

ቻናላችን ይኸው ሊንኩ@gttem
https://www.tg-me.com/gttem
እብደት ሲጀማምር.....🏃‍♂🏃‍♂🚶‍♂🚶‍♂

ብናጎነብስም ከወደቁት ቀና ስላልን ብቻ አልሞቱም ተብለን አለን። ሞተናል?...... አልሞትንም እየተነፈስን ነው። ምንኖረውም እየኖሩ ነው ሳይሆን አልሞቱም እንዲባል ከሆነ ቆየ......ለነገሩ ባዮቹስ ምን ያድርጉ ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች የሆነን ሰው አልሞተም ከማለት ውጪ ሌላ ምን ይበሉት? ምንም!

🤒 #አቤኔዘር (29/09/13) 🤕
@ITSmeABENI_23
አውቃለው እንዲ የሆንሽው ፈልገሽ አይደለም......አንድ ቀን መቀየርሽ አይቀርም ግን እንዳታረፍጂ ፣ ከረፈደ እንዳትቀየሪ እፈራለው።

#አቤኔዘር 🕓
Forwarded from  (Λβ㉫ŋ㉫)
ይሄ የመጨረሻው ከኔ ላንቺ የተፃፈ ደብዳቤ ነው ሲጀምርም ሲጨርስም እንታረቅ ይላል። ሌላ ስፅፍልሽ እነግርሻው ግን ይሄንም መች እንደማነብልሽ አላቅም።

እና🎙 #አቤኔዘር
✏️ @ABEN_E 💌
Channel name was changed to «»
2024/05/08 20:14:45
Back to Top
HTML Embed Code: