#PHENOMENAL_picture

#የፍጥረት_ናፍቆት
"#እነሆኝ_የጌታ_ባርያ_እንደቃልህ_ይደረግልኝ"

በምድር ላይ ብዙ የማይረሱ ታሪካዊ ንግግሮችን ያደረጉ ታላላቅ ሰዎች አሉ:: ድንግሊቱ የተናገረችውን ይህን አንድ ዐረፍተ ነገር ያህል ግን የሰው ልጅን ታሪክ የለወጠ ቃል የለም::

ይህ ቃል እንደዋዛ ከሌሎች ቃላት ተርታ መፃፍ እንዴት ያስጨንቃል? በዚህ ቃል ምክንያት የሆነልንን ካሰብነው እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ ዐረፍተ ነገር #በወርቅ_ቀለም መፃፍ የሚገባው ቃል ነው:: ይህ ቃል #በብርሃናዊ ብዕር #በቅዱሳን_እጅ ብቻ ሊፃፍ የሚገባው ቃል ነበረ::

ሰማይንና ምድርን ያገናኘ ይሔ ቃል እንዴት እንዲሁ አንብበን እናልፈዋለን?? ይህ ዐረፍተ ነገር በሐዲስ ኪዳን ለተፃፉት ለሌሎች ቃላት ሁሉ መነሻ ነበር:: ይህ ዐረፍተ ነገር የሰው ልጆችም እግዚአብሔርም ተጠባብቀው የሰሙት ድንቅ ቃል ነው::

#የዚህን_ዓረፍተ_ነገር_ያህል_የሰው_ልጅን_ታሪክ_የለወጠ_ቃል_ከፍጡር_እንደበት_ተሰምቶ አይታወቅም::

ብዙ ከማትናገረዋ የዓስራ አምስት ዓመት ብላቴና ድንግል ማርያም አፍ የወጡት እነዚህ ውድ ቃላት በመነገራቸው ያስከተሉት ነገር ፍጥረታትን ሁሉ ለዘመናት ሲናገሩ ውለው ቢያድሩ ሊያመጡት የማይችሉት ነገር ነው::

ይህ ቃል #እግዚአብሔር_ወልድን_ከዙፋኑ_ሰው_ለመሆን የጠራ ቃል ነው::
ይህ ቃል #የገነት_በርን_ያስከፈተ #የኪሩቤልን_ሰይፍ_ያስጣለ_ቃል_ነበር::
ይህ ቃል #የፍጥረትን_ናፍቆት የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ መገለጥ የወጠነ #የምህረት_ዘመንን ያስጀመረ
#ዘመን_ለማቆጠርለት አምላክ ዘመን እንዲቆጠርለት የማስጀመሪያ ቃል ነበር::

#እመቤቴ_ሆይ የአንቺ 'ይሁንልኝ' የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ::

ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔስ #ሰው_የምታደርጊኝ_መች_ይሆን??🥺🥺

አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሽዋ ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን 'ይሁን' የምትይው መቼ ይሆን? 'በርታ ሰውም ሁን' የሚለው ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢያት ሰልጥኖብኝ 'ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንድሚጠፋው እንስሳት መሰለ' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ እንደቃሉ መሆን ላቃተኝ ለኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ...
'ይህ ሐጢያተኛ ባሪያህ እንደቃልህ ይሁንልኝ' ብለሽ እኔንም እንደቃሉ የምታደርጊኝ መቼ ይሆን??

መልካም የልደት በዓል😍😍😍

#የብርሃን_እናት
ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ


አብይ የማርይም ልጅ ነኝ

ለንባብ እንዲመች አድርጌ አቀረብኩት
#street_photography
#ጃን_ያሬድ #አእላፋት_ዝማሬ
@henok.haile እናመሰግናለን 😍🙏🙏😍
#ምን_አይነት_ቀን_ነበር😍😍🙏🙏🙏🥺😢😍😍😍

#best #awesome #timing

#photoshoot

#our #lovely😍 #ethiopia🇪🇹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰባቱ ሰዎች
በስታቲሺያን በሀይሉ ገብረመድህን
ታህሳስ 3
ምሽት 1:00
በ "ሐዋዝ ሀሳብ ቲዩብ" ይለቀቃል
ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ።

እነሆ ሊንካችን 👇

https://www.youtube.com/channel/UCgK1RJHl2dQDQdLlJFUExfQ
ሠላም ለእናንተ ይሁን ውድ ቤተሠቦቻችን
በታላቅ ጉጉት የምንጠብቀው ፤ ከእናንተ ጋር የማይረሳ የቤተሠብ ጊዜ የምናሳልፍበት የወርሃዊ ቡና ጠጡ ፕሮግራማችን ጊዜውን ጠብቆ ተዘጋጅቷል። እሁድ ፣ ጥር 05 ፣ 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በመምጣት ከልጆቻችን ጋር ድንቅ ጊዜን ያሳልፉ ዘንድ
ከነቤተሰብዎ ተጋብዘዋል።
Phenomenal picture

ደረሰ ደረሰ ደረሰ
" ፍቅርና መስዋዕትነት " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መታሠቢያነቱን ለ128 ኛው አድዋ በዓል ያደረገው የየካቲት ወር የቡና ጠጡ ዝግጅት እያዝናኑ ቁምነገር የሚያስጨብጡ ፕሮግራሞችን ይዞ ሊቀርብ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል
የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችን አዘጋጅተን እንጠብቆታለን
እርስዎስ ከቤተሠብዎ ጋር ይህን የድል ወር ከልጆቻችን ጋር ለማሳለፍ ተዘጋጅተዋል ?
እንግዲያውስ ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ በሚገኘው ግቢያችን የካቲት 3 ከቀኑ 8 ሰዐት እንገናኝ
AB PHOTOGRAPHY
ይሰማል ይሰማል ወይ ይህ የነፃነት ቀን ሳይሆን የድል ቀን ነው ይሰማል ወይ
አድዋ የአፍሪካውያን ኩራት
እምየ ምንሊክ ጀግናው
እንኳን አደረሳቹ
@ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD @ABPGD
2024/05/17 03:08:40
Back to Top
HTML Embed Code: