Telegram Web Link
ሐላል ሪዝቅ ፍለጋ ወገብህን ይሰብረው ይሆናል፤ ግን ራስህን ቀና አድርገህ እንድትሄድ ያደርግሃል።💜❤️‍🩹

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ ዙልም አይነቶች

-------------------------

ኡስታዝ ሙሀመድ ኸድር

۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
ሁዳ መልቲሚዲያ
-------------
አላህ سبحان وتعالى
ሰባት ነገሮችን ይወዳል

①☞ተውበት  “አላህ (ከኃጢኣት) ተመላሾችን ይወዳል”
አል በቀራህ ☞2:222

②☞ ጦሀራ ☞“አላህ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው፡፡”
☞አል በቀራህ 2:222

③ ☞ተቅዋ  ❥አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡” ☞አተ ተውባ 9:4

④ ☞ኢህሳን  ❥ “አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡”
☞አል ኢምራን 3:134

⑤ ☞ተወኩል ❥“አላህ በርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”
❥ ☞አል ኢምራን 3:159

⑥ዐድል ❥ “አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና፡፡”
☞አል ማዒዳህ 5:42

⑦ ☞ሶብር ☞”አላህም ትዕግስተኞችን ይወዳል፡፡
☞”አል ኢምራን3:146

#ሼር_የድርጉ
“ጥንብ ነችና ተዋት!”
~
ዘረኝነት በነብዩ ﷺ አንደበት “ጥንብ” እንደሆነ ተገልጿል። ጥንብ ላይ የሚያንዣብበው ጥንብ አንሳ ነው! ሰው ሁን። ከጥንብ ራቅ። በተቅዋ ከፍ በል። “ከናተ በላጫችሁ ይበልጥ አላህን የሚፈራው ነው” ብሎናል ጌታችን። [ሑጁራት፡ 13] ሐበሻው፣ ጥቁሩ፣ ባሪያው ቢላል፤ ከዐረቡ፣ ከቁረይሺዩ፣ ከነብዩ ﷺ አጎት አቡ ለሀብ የበለጠው በተቀዋው እንጂ በምንም አልነበረም። ሞኝ አትሁን። ከእምነትህ ዘርህን አታስቀድም። አታይምንዴ አላህ ዐረቡን፣ ቁረይሺዩን፣ የነብዩን ﷺ አጎት አቡ ለሀብን ከሀበሻው ጥቁር ባሪያ በታች ሲያደርገው?! መቼም አቡ ለሀብን የሚያወግዝ አንድ የቁርኣን ምእራፍ እንደወረደ የምትዘነጋው አይመስለኝም። ቢላል ግን በኢማኑ ስንቶች የሚቋምጡበትን ማእረግ ነው የታደለው። የነብዩ ﷺ ቅርብ ሰው ነበር። የነብዩ ﷺ ሙአዚን መሆን ምንኛ መታደል ነው?! እርግጠኛ ነኝ ዛሬም ድረስ ቢላል በሙስሊሞች ልቦና ውስጥ ያለው ቦታ ታላቅ እንደሆነ እስክነግርህ አትጠብቀኝም።
የትኛውንም ቋንቋ ስለተናገርክ ከማንም በላይ አይደለህም። ከየትኛውም ብሄር ስለመጣህም ከማንም በታች አይደለህም። ከሁሉ በፊት አንተ ለራስህ ትክክለኛ ቦታህን ስጥ። ሰዎች ስለሰቀሉህ አትሰቀልም። ሰዎች ስላወረዱህም አትወርድም። ለሆሳሱ ሁሉ ስላንተ እየመሰለህ አትሳቀቅ። ለቃላት መጥፎ ትርጉም እየሰጠህ አትሸማቀቅ። በትንሽ በትልቁ ውስጥህ አይደፍርስ። ጥቂት ከጠረጠርክ ሸይጧን ብዙ ያመሳስልብሃል። በዘሩ ሊኮፈስብህም የሚሻ ካለ፣ በማንነትህ ሊንቅህ ከዳዳው በተቅዋ ብለጠው። እሱ ጥንብ ቢያነሳ አንተም ጥንብ ታነሳለህንዴ?!
ሀላፊነት ይሰማህ። ቂል የዘረኝነት እሳት ሲያቀጣጥል አንተ ጋዝ አታርከፍክፍ። ቂል ትከተላለህንዴ? የአረሕማን ባሪያዎች ማለት ቂሎች በቂልኛ ሲያናግሯቸው በነገር ሲተነኩሷቸው ነገር እንዲበርድ የሚያደርጉ፣ ሠላም እንዲሰፍን የሚጥሩ ናቸው። ታዲያ አንተ የማን ባሪያ ነህና?! እርግጠኛ ነኝ “የሸይጧን ነኝ” አትለኝም! የዘረኛ ዘረኝነት ዘረኛ አያድርግህ። የጥንብ አንሳው ጥንብ ማንሳት ጥንብ እንደማያስነሳህ ሁሉ። ሞኝ አትሁን! የሱ ዘረኝነት ላንተ ይቅርታ አይሆንም፡፡ እሱን ሸይጧን ቢጋልበው አንተም ጀርባህን ትሰጣለህ እንዴ? ግን የሸይጧን ፈረስ የሆነ ሰው ምንኛ አስቀያሚ ነው?!
እናም እልሃለሁ ዘረኛው በቆሻሻ ዘረኝነት ውስጥ ሲዋኝ ብታየው ከቻልክ “አላህን ፍራ” በለው። በጥንብ እየተጨማለቀ እንደሆነም አስረዳው። ካልሆነልህ እሱ የያዘውን ጥንብ ለመንጠቅ እንዳትሞክር፤ ወይም ጥንብ ላይ እንዳትሻማ። ዘረኝነትን በዘረኝነት እንዳትመልስ ማለቴ ነው። ሸይጧን ከፊት ሲስብህ፣ ከኋላም ሲገፋህ ዝም ብለህ አትነዳ። “አላህን ፍራ” ማለት ካቃተህ አላህን መፍራት ግን አያቅትህ። ሂሳብ ስራ። ፈሪ ሁን! አዎ! አንድየውን፣ ሁሉን አዋቂ፣ ሁሉን ተመልካች፣ የፍርዱ ቀን ዳኛ… የሆነውን ጌታ የምትፈራ ሁን። አስተውል! “ፈሪ” እባላለሁ ብለህ አትጨነቅ። የፈራሀው አላህን እንጂ ሰው አይደለም! ቀድሞ ነገር አላህን እንደሚፈራ ሰው ጀግና አለና ወይ? በጭራሽ! ነብዩስ ﷺ “ጀግና ማለት በንዴት ጊዜ ቁጣውን የሚቆጣጠር ነው” አላሉምንዴ? ታዲያ ትእዛዛቸውን እናክብራ! ወዳጅ ያምፃልንዴ?!
የሌላውን ብሄር፣ ቋንቋ፣… ከማንቋሸሽ ራቅ። በሌላው ብሄር ላይ ከመሳለቅ ከመቀለድ ተጠንቀቅ። በሌላው ላይ ሲቀለድም አትሳቅ። ለራስህ የማትወደውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። ይሄ ብዙዎቻችን የተለከፍንበት ገዳይ በሽታ ነው አላህ የጠበቀው ሲቀር። ምናልባት አንተ ስለራስህ ደንታ ቢስ ሆነህ ሊሆን ይችላል። ግን ሁሉ እንዳንተ እንዳልሆነ አትርሳ።
አትጠራጠር! ዘረኝነት የጃሂሊያ ስራ የመሀይሞች መታወቂያ እንደሆነ ታማኙ የአላህ መልእተኛ ነግረውሃል። ልብ በል! በምትናገረው ቋንቋ ከማንም በታች እንዳልሆንክ ሁሉ ከማንም በላይም አይደለህም! ከፍም ዝቅም የሚያደርግህ ስራህ እንጂ ዘርህ አይደለም። “ስራው ያስቀረውን ዘሩ አያስቀድመውም!” አይደል ያሉን ነብያችን ﷺ? ነብዩኮ ልጃቸው እንኳ “የነብይ ልጅ ነኝ” ብላ እንዳትሸወድ ይልቁንም በርትታ ሰርታ እራሷን እንድታተርፍ ነው አደራ ያሏት። ከፍ ማለት ከፈለግክ በኢስላም ከፍ በል፣ በተውሒድ ከፍ በል፣ በሱና ከፍ በል። ከዚህ በራቅክ ቁጥር እየወረደክ፣ እየዘቀጥክ፣ ቁልቁል እየተምዘገዝግክ እንደሆነ ነጋሪ እስኪነግርህ አትጠብቅ።
ጥሪየ ማንነትህን እንድትጥል፣ ማንም በመታወቂያህ ሲረማመድ ዝም እንድትል አይደለም። ይልቁንም ጥሪየ አላህን እንድትፈራ ሚዛንህ እንድትጠብቅ ብቻ ነው። እናም የራስህን አስጠብቅ፣ ከሌሎች አትድረስ። ዘርህን ከእምነትህ ያስቀደምክ እለት ግን አትጠራጠር ታመሃል፡፡ እንዲህ እየገዘገዘህ ህመሙ ካልተሰማህማ ጭራሽ ቫይረሱ አናትህ ላይ ወጥቷል፡፡ ጓደኛህ ይህን ህመምህን እያየ፣ ጥምብ ስታጨማልቅ እየተመለከተህ ዝም ካለህ፤ ወይ እንደ ተናካሽ ውሻ ያገኘኸውን ስለምትነክስ ፈርቶሃል፣ ወይ ደግሞ እሱም እንዳንተው ጥንብ አንሳ ነው ማለት ነው!
አደራ ግን እኔ ይሄን ሁሉ ስለቀልቅ ከችግሩ ነፃ ነኝ እያልኩ አይደለም፡፡ እኔ ቀርቶ ስንት ታላላቆች የሚወድቁበት ችግር እኮ ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ታላቅ ሰው ማለት ፍፁም የማይሳሳት ነውንዴ? ከስህተቱ የሚመለስ ነው እንጂ!!! እናም ቫይረሱ ጋር ላለመድረስ ስንሳሳትም ለመመለስ እንጣር፡፡ እንዲህም እንበል፡ “አላሁመ ኣቲ ነፍሲ ተቅዋሃ፣ ወዘኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘካሃ፣ አንተ ወሊዩሃ ወመውላሃ!” “ጌታዬ ሆይ አንተ ለነፍሴ ተቅዋዋን ስጣት፡፡ አጥራትም፤ አንተ ከሚያጠራት ሁሉ በላጭ ነህና፡፡ አንተ ረዳቷም ተንከባካቢዋም ነህ”
=
ኢብኑ ሙነወር
(ሚያዚያ 15/2009)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://www.tg-me.com/IbnuMunewor
የሸዋል ፆም ካልፆምን መፆሙን አንዘንጋ! የአመት ምንዳ እንዳያልፈን!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿صِيامُ شهْرِ رمضانَ بِعشْرَةِ أشْهُرٍ، وصِيامُ سِتَّةِ أيّامٍ بَعدَهُ بِشهْرَيْنِ، فذلِكَ صِيامُ السَّنةِ﴾

“የረመዳን ወር ፆም እንደ አስር ወር ነው የሚታሰበው። ከዛ በኋላ የሚፆመው ስድስት ቀናት ፆም ደግሞ እንደ ሁለት ወር ነው የሚታሰበው። በዚህም አመት እንደመፆም ተደርጎ ነው የሚታሰበው።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 3851

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
እህቴ ግትርነትን ተጠንቀቂ መልካም ትዳርን ያናጋል !

🌱 ለስላላሳ ፀባይን ተላበሽ ቁጣን ያበርዳል ፍቅርን ይጨምራል !!💜💗


http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
በአላህ ላይ እውነተኛ መመካትን እንመካ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لو أنَّكم توَكَّلتم على اللهِ حقَّ توَكُّلِهِ، لرزقَكم كما يرزقُ الطَّيرَ، تغدو خماصًا، وتروحُ بطانًا.﴾

“እናንተ በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነ መመካትን ብትመኩ ኖሮ ወፎችን እንደሚመግበው ይመግባችሁ ነበር። ሆዷ ባዶ ሆኖ ጠዋት ትወጣና ከሰዐት በኋላ ሆዷን ሞልታ ትመለሳለች።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 2344

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
◇5ቱ የስኬት መንገዶች

~ፈጅር
~ዙሁር
~አሱር
~መግሪብ
~ኢሻ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Surat Al-Kahf - Mishary Rashed Alafasy الشيخ مشاري راشد العفاسي سورة الكهف

ከጁመዓ ቀን ሱናዎች

↩️ ‏سنن يوم الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት


📌((قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين))

👉የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል))

📚 صحيح الجامع - رقم : (6470)

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
ሸይጣን ያልቅሳል!

ረሱል (ﷺ🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿إِذَا قَرَأَ ابْنُ آدَمَ السَّجْدَةَ، فَسَجَدَ اعْتَزَلَ الشَّيْطَانُ يَبْكِي يَقُولُ: يَا وَيْلِي، أُمِرَ ابْنُ آدَمَ بِالسُّجُودِ، فَسَجَدَ، فَلَهُ الْجَنَّةُ، وَأُمِرْتُ بِالسُّجُودِ، فَأَبَيْتُ، فَلِي النَّارُ﴾

“የአደም ልጅ ሱጁድ ሲያደርግ ሸይጣን እያለቀሰ ይሄዳል። እንዲህም ይላል፦ ወይኔ! እሱ ሱጁድ እንዲያደርግ ታዘዘ ሱጁድ አደረገ፤ በመሆኑም ጀነት የሱ ሆነች። እኔ ግን ሱጁድ እንዳደርግ ታዘዝኩ እምቢ አልኩ ስለሆነም ጀሀነም እጣፋንታዬ ሆነ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 81

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
تلاوة من سورة الروم القارئ : ناصر العمري

🌸 የምሽት ስንቅ 🌸

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
ጠቃሚ ምክሮች❗️

ወደ አላህ ተጠጋ፤ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነውና!

ለሁሉም ነገር አትቸኩል፤ ችኮላ የሸይጧን ነውና!

የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ፤ እርሱ ካንተ ጋር ነውና!

የበደለህን ይቅር በል፤ አላህ ይቅር ባዮችን ይወዳልና!

በሁሉም ነገር ላይ ታገስ፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና!

ድሆችን እርዳ፤ ሰደቃ/ ምጽዋት ወንጀልን ታብሳለችና!

ባጣኸው ነገር አትበሳጭ፤ የተሻለውን ረበና ይሰጥኋልና!

አትበሳጭ! ብስጭት የሰይጣንን በር ትከፍታለችና!

በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ፤ ካጣኸው በኃላ ይቆጭኋልና!


የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ፤ ያስታውስኋልና!

ባለህ ነገር አመስግን፤ አላህ ይጨምርልኋልና!

ሰዎች ላይ አትመቀኝ፤ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለችና!

ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን፤ ሁሉን ማድረግ የሚችል ፈጣሪ ነውና!

በወንድምህ ውድቀት አትደሰት፤ በሌላ ቀን ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና!

ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም፤ ውሳኔው የፈጣሪ ነውና!

ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ፈጣሪህን አመስግን፤ እርሱ አመስጋኞችን ይወዳልና!
#የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ የተጠላ ማለት ደረቅ ፤ ሙጉት የሚያበዛ ሰው ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
☆ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና።☆

አል-ዓንከቡት [29:45]

http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
http://www.tg-me.com/+TOuxbrki5gY2iIpt
2024/05/20 22:07:25
Back to Top
HTML Embed Code: