Telegram Web Link
Forwarded from Orthodox Patristic Writings. (Esdros)
ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ የተወለደው በኩዋርቱም ኤፍራጥስ 451 ዓ/ም ነው። በኤዴሳ ትምህርት ቤትም ገብቶ የነገረ-መለኮት፣የፍልስፍና እና የነገረ-ድርሳን ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን፥ የመጀመሪያ ሥራውን የሀያ አመት ወጣት ሳለ "The chariot of Ezekiel" የተባለ ድርሳን የደረሰ ሲሆን፥ በኋላም በምንኩስና ሕይወት ተወስኖ መኖር ጀምሯል።

በጳጳሳቱ ዘንድ በግጥም ችሎታው በጣም ተወዳጅነትን ያገኘም ነበር፤የቅስና ሹመትን አግኝቶ በሐውራ ከተማም ለአገልግሎት ተጠራ። በኤፍራጥስ፥ በመላው ሶርያ በመመላለስ ሐዋርያዊ ድርሻውን በመወጣቱ በምእመናን ዘንድ መወደድን በመነኮሳቱ ዘንድ በእውቀቱ እና በመንፈሳዊ ሕይወቱ ምክንያት ሞገስን አግኝቷል። ስለሆነም፥ለስሩግ ሀገረስብከት ጵጵስና በመጨረሻው የዕድሜ ዘመኑ በ519 ዓ/ም ተሾመ። የመጨረሻ ሥራውም "Golgotha" የሚል ሲሆነ በእረፍቱ ምክንያት አልጨረሰውም ነበር።

በሀገረ ስብከቱም፦ አንድ ዓመት ከአስራ አንድ ወራት አገልግሎ፣በመልካም እርግና በሰባ ዓመቱ በታኅሣሥ 3 ቀን አርፋል። ቅዱስ አካሉም በዲያርባኪር ይገኛል።
በርካታ ድርሳናትን ያዘጋጀ አባት ሲሆን! በተለይም የሚታወቀው ግጥማዊ በሆኑ ጽሑፎቹ ነው። ከጻፋቸው መጽሐፍት ውስጥ፦
Homily on Nativity
Homily on Epiphany
Homily on Good Friday
Homily on resurrection
Homily on Hexaemeron
Homily on Lord's prayer
Homily on the partaking of holy mysteries
Homily concerninig on red heifer and crucifixion ሲገኙበት ሌሎች ያልጠቀስናቸው ብዙ መጽሐፍት ያሉት አባት ነው።
ስርአተ አምልኮአዊ(Liturgical books) የሆኑ መጽሐፍት፥ወደ 43 የሚጠጉ ደብዳቤዎችም አሉት። ከብዙ ሥራው የተነሳ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ እንዚራ፣የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በገና፣የአበው አክሊል በመባል ይጠራል።

                #Reference
H.H Ignatius Aphram I Barsoum(2003),The scattered pearls: The history of Syriac literature: New Jersey,Gorgias press. Page 255-261
Forwarded from Orthodox Patristic Writings. (Esdros)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Orthodox Patristic Writings. (Esdros)
Jacob of serug homily on crucifixion of our lord .pdf
1.4 MB
መጽሐፉን ልታነቡ፣የምትሹ ሁሉ...እነሆ!
የራስ ቅል በሚሉት
ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
👇👇👇
https://youtu.be/05KBlwiCSmI
https://youtu.be/05KBlwiCSmI
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በእጅ ባልተሰራች መቅደስ ለኃጢአት ሥርየት የኢየሱስ ደም ፈሰሰ

የሮማውያን መስቀል የእግዚአብሔር መቅደስ ሆነ። እነርሱ በእጃቸው የሰሩት መስቀልን ነው እግዚአብሔር ግን ያን መስቀል መቅደስ አድርጎ አዘጋጀው። የመስቀል መቅደስነት በእጅ የተሰራ ሳይሆን በእግዚአብሔር የተዘጋጀ ነው። በዚህ መቅደስ ሊቀካህናታችን የገዛ ደሙን ይዞ ገባ ስለ ሁላችንም ታየልን። በደሙም የተደረገ የኃጢአታችንን ሥርየት አገኘን።
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
ውዳሴ ትንሣኤ |በዘማሪት ወርቅነሽ ኃይሉ!
https://youtu.be/ua2_FUMuJD0
https://youtu.be/ua2_FUMuJD0
https://www.tg-me.com/orthodox_melse_alat

ኦርቶዶክስ መልስ አላት

በመጨረሻም ኦርቶዶክስ መልስ አላት እሚለውን Application develop አድርገን ጨርሰን በ ቴሌግራም ቻናላችን ለቀንላችሁአል ገብታችሁ download ያድርጉና ከመናፍቃን ለሚነሱ ጥያቂወች መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ  Appliction በውስጡ የያዛቸው file

➡️  ከ 30 በላይ እሚሆኑ የድምፅ ትምህርቶች
➡️  መፅሀፍት

➡️  መፅሀፍ ቅዱስ ትርጓሜ



➡️  ሙሉ በሙሉ offline

download ለማድረግ 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/orthodox_melse_alat
📌በደንብ በደንብ ይነበብ📌

ይሄ እንደ መጀመርያ መልሳችን ነው። በዚህ ጥያቄ ላይ ብቻ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያነሳን ማሳየት ይቻላል። ደግሞም በሌሎችም ጥያቄዎች እንዲሁ🙌
ይቀጥላል🙏
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
📌 በደንብ ይነበብ 📌
ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ያማልዳሉ☑️

ማስረጃ 2 ይቀጥላል🙌
ብዙዎች ጋር እንዲደርስ share እናድርግ🙏
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
Forwarded from Orthodoxy eLibrary
ሰላም እንዴት ናችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች 😊
ዛሬ ደግሞ በሌላ አንድ መጽሐፍ ተገናኝተናል (MUST READ ከምላቸው ውስጥ ነው)... የነገረ መለኮት ጥናት ጋር በተያያዘ መሠረታዊ እውቀት ከየት ላግኝ የምትሉ ይሄን መጽሐፍ ብትመለከቱ ሰፊ የሆነ እይታ (perspective) ይሰጣችኋል፤ ተጋበዙልኝ። 😉

📖 መጽሐፉ የነገረ መለኮት መግቢያ ይሰኛል
✍🏻 ጸሐፊው መምህር ግርማ ባቱ ናቸው።

የመጽሐፉን መቅድም ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ውብ በሆነ አገላለጽ የጻፉት ሲሆን መጽሐፉን ለማንበብ ጥሩ Inspiration የሚሆን ነው።
መጽሐፉ በመግቢያው ላይ የተለያዩ የክርስትና ዲኖሚኔሽንስ ለነገረ መለኮት ያላቸውን አቀራረብ (Theological approach) በማብራራት ይጀምራል። ኦርቶዶክሳዊውን የነገረ መለኮት አቀራረ ተማሕልሎአዊ ነገረ መለኮት ይለዋል፤ ለነገሩ ተማሕልሎአዊ ነገረ መለኮት ምን ማለት ነው?😁 መጽሐፉ ላይ ታገኙታላችሁ። 😌

በመጀመርያው ምዕራፍ የነገረ መለኮት መሠረቶችን የሚናገር ሲሆን፤ ስለ አማኒነት እና ኢ-ታማኒነት እንዲሁም ኢ-ታዋቂነት(ትርጉሙን መጽሐፉ ላይ) ማብራርያ ይሰጣል። በዚሁ ምዕራፍ ስለ ነገረ መለኮት አረዳድ እንዲሁም እግዚአብሔርን ስለማየትና እግዚአብሔርን ስለማወቅም ያትታል። ከላይ በተነሱት ርእሶች ውስጥ ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

ምዕራፍ ሁለት ላይ የነገረ መለኮት ምንጮችን የሚዳስስ ምዕራፍ ሲሆን አጠቃላይ መገለጥና ልዩ መገለጥን በአግባቡ ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ ትውፊት፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ነገረ አበውና የዓለም አቀፍ ጉባኤያት ውሳኔዎች የነገረ መለኮት ምንጮች እንደሆኑ ከጥሩ ማብራርያ ጋር ያስቀምጣል። በነገራችን ላይ ሥርዓተ አምልኮ እና ምሥጢራትም የነገረ መለኮት ምንጮች ናቸው!

ምዕራፍ ሦስት ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሰብእ በሚል ርእስ ሥር ስለ ሰው ምንነት በሳይንስ፣ በፍልስፍና እንዲሁም በነገረ መለኮት መነጽር ይመረምራል፤ በሰው ያለውንም የእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ይዘክራል። የአምላክ ሰው መሆንንም በዚህ ምዕራፍ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ክብር ጋር በማገናኘት ያትታል። በዚሁ ምዕራፍ ምክንያተ ድኂን ድንግል ማርያምንም በዚሁ ምዕራፍ ከእናታችን ሔዋን ጋር እያነጻጸረ የሰው ልጅ ክብርን እንዴት እንዳስመለሰችለት ያብራራልናል። በመጨረሻም በዚህ ምዕራፍ ከተጠቀሱት ክብሮቹ የሰው ልጅ ተሳትፎ የሚኖረው በምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሆኑን አዝገንዝቦ ምዕራፉን ይዘጋል።

መጽሐፉ በመጨረሻ ምዕራፉ ከላይ ጀምሮ ሲዳስሰው የቆየውን የሰው እና የእግዚአብሔር ግንኙነት በማኅበራዊና በአካባቢያዊ ዘርፎች ላይ ያለውን ተጽዕኖ ይናገራል። ነገር መለኮትም እዚህ ላይ ቀላል የማይባል ድርሻ እንዳለው ድንቅ በሆነ አገላለጽ ያስቀምጣል። በአጠቃላይ ነገረ መለኮት ሰፊና የሰው ልጅ ሕይወትን ሙሉ ለሙሉ የሚቃኝ እንደሆነ ልብ ያስብላል።

"በተማህልሎአዊ ነገረ መለኮት ሰው ኾኖ ለሰዎች መኖር እግዚአብሔር ይርዳን!"
ከመጽሐፉ የተወሰደ

መልካም ንባብ! 🤗

https://www.tg-me.com/Orthodoxy_eLibrary/2067
ያህዋህ ማነው? ዲ/ን መኳንንት

https://vm.tiktok.com/ZMSS7Ngk3/
Forwarded from ስለ ቁርባን chat
ማታ 3 ሰዓት
ስለ ቁርባን እንማማራለን
-በመጽሐፍ ቅዱስ
-ከወጣቶች ህይወት አንጻር
-በማህበረሰባችን ላይ ያለብን ሃላፊነት
ሌሎችም.
.
.
-ጥያቄዎችን እንቀበላለን

https://www.tg-me.com/sle_kurban
2025/06/27 15:14:21
Back to Top
HTML Embed Code: