Telegram Web Link
https://www.tg-me.com/orthodox_melse_alat

ኦርቶዶክስ መልስ አላት

በመጨረሻም ኦርቶዶክስ መልስ አላት እሚለውን Application develop አድርገን ጨርሰን በ ቴሌግራም ቻናላችን ለቀንላችሁአል ገብታችሁ download ያድርጉና ከመናፍቃን ለሚነሱ ጥያቂወች መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ  Appliction በውስጡ የያዛቸው file

➡️  ከ 30 በላይ እሚሆኑ የድምፅ ትምህርቶች
➡️  መፅሀፍት

➡️  መፅሀፍ ቅዱስ ትርጓሜ



➡️  ሙሉ በሙሉ offline

download ለማድረግ 👇👇👇👇👇
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/orthodox_melse_alat
👏40👍1312🥰8👎1
📌በደንብ በደንብ ይነበብ📌

ይሄ እንደ መጀመርያ መልሳችን ነው። በዚህ ጥያቄ ላይ ብቻ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያነሳን ማሳየት ይቻላል። ደግሞም በሌሎችም ጥያቄዎች እንዲሁ🙌
ይቀጥላል🙏
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
👍3619👏4🎉2🙏21
📌 በደንብ ይነበብ 📌
ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ ያማልዳሉ☑️

ማስረጃ 2 ይቀጥላል🙌
ብዙዎች ጋር እንዲደርስ share እናድርግ🙏
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
https://www.tg-me.com/KM_thoughts
52👍8👏3🤔1👌1
Forwarded from Orthodoxy eLibrary
ሰላም እንዴት ናችሁ እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች 😊
ዛሬ ደግሞ በሌላ አንድ መጽሐፍ ተገናኝተናል (MUST READ ከምላቸው ውስጥ ነው)... የነገረ መለኮት ጥናት ጋር በተያያዘ መሠረታዊ እውቀት ከየት ላግኝ የምትሉ ይሄን መጽሐፍ ብትመለከቱ ሰፊ የሆነ እይታ (perspective) ይሰጣችኋል፤ ተጋበዙልኝ። 😉

📖 መጽሐፉ የነገረ መለኮት መግቢያ ይሰኛል
✍🏻 ጸሐፊው መምህር ግርማ ባቱ ናቸው።

የመጽሐፉን መቅድም ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ውብ በሆነ አገላለጽ የጻፉት ሲሆን መጽሐፉን ለማንበብ ጥሩ Inspiration የሚሆን ነው።
መጽሐፉ በመግቢያው ላይ የተለያዩ የክርስትና ዲኖሚኔሽንስ ለነገረ መለኮት ያላቸውን አቀራረብ (Theological approach) በማብራራት ይጀምራል። ኦርቶዶክሳዊውን የነገረ መለኮት አቀራረ ተማሕልሎአዊ ነገረ መለኮት ይለዋል፤ ለነገሩ ተማሕልሎአዊ ነገረ መለኮት ምን ማለት ነው?😁 መጽሐፉ ላይ ታገኙታላችሁ። 😌

በመጀመርያው ምዕራፍ የነገረ መለኮት መሠረቶችን የሚናገር ሲሆን፤ ስለ አማኒነት እና ኢ-ታማኒነት እንዲሁም ኢ-ታዋቂነት(ትርጉሙን መጽሐፉ ላይ) ማብራርያ ይሰጣል። በዚሁ ምዕራፍ ስለ ነገረ መለኮት አረዳድ እንዲሁም እግዚአብሔርን ስለማየትና እግዚአብሔርን ስለማወቅም ያትታል። ከላይ በተነሱት ርእሶች ውስጥ ስለ ሀልዎተ እግዚአብሔር ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

ምዕራፍ ሁለት ላይ የነገረ መለኮት ምንጮችን የሚዳስስ ምዕራፍ ሲሆን አጠቃላይ መገለጥና ልዩ መገለጥን በአግባቡ ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ ትውፊት፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ነገረ አበውና የዓለም አቀፍ ጉባኤያት ውሳኔዎች የነገረ መለኮት ምንጮች እንደሆኑ ከጥሩ ማብራርያ ጋር ያስቀምጣል። በነገራችን ላይ ሥርዓተ አምልኮ እና ምሥጢራትም የነገረ መለኮት ምንጮች ናቸው!

ምዕራፍ ሦስት ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሰብእ በሚል ርእስ ሥር ስለ ሰው ምንነት በሳይንስ፣ በፍልስፍና እንዲሁም በነገረ መለኮት መነጽር ይመረምራል፤ በሰው ያለውንም የእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ይዘክራል። የአምላክ ሰው መሆንንም በዚህ ምዕራፍ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ክብር ጋር በማገናኘት ያትታል። በዚሁ ምዕራፍ ምክንያተ ድኂን ድንግል ማርያምንም በዚሁ ምዕራፍ ከእናታችን ሔዋን ጋር እያነጻጸረ የሰው ልጅ ክብርን እንዴት እንዳስመለሰችለት ያብራራልናል። በመጨረሻም በዚህ ምዕራፍ ከተጠቀሱት ክብሮቹ የሰው ልጅ ተሳትፎ የሚኖረው በምሥጢራተ ቤተክርስቲያን መሆኑን አዝገንዝቦ ምዕራፉን ይዘጋል።

መጽሐፉ በመጨረሻ ምዕራፉ ከላይ ጀምሮ ሲዳስሰው የቆየውን የሰው እና የእግዚአብሔር ግንኙነት በማኅበራዊና በአካባቢያዊ ዘርፎች ላይ ያለውን ተጽዕኖ ይናገራል። ነገር መለኮትም እዚህ ላይ ቀላል የማይባል ድርሻ እንዳለው ድንቅ በሆነ አገላለጽ ያስቀምጣል። በአጠቃላይ ነገረ መለኮት ሰፊና የሰው ልጅ ሕይወትን ሙሉ ለሙሉ የሚቃኝ እንደሆነ ልብ ያስብላል።

"በተማህልሎአዊ ነገረ መለኮት ሰው ኾኖ ለሰዎች መኖር እግዚአብሔር ይርዳን!"
ከመጽሐፉ የተወሰደ

መልካም ንባብ! 🤗

https://www.tg-me.com/Orthodoxy_eLibrary/2067
56👍19🥰6🤷‍♂2👎2
ያህዋህ ማነው? ዲ/ን መኳንንት

https://vm.tiktok.com/ZMSS7Ngk3/
52👏1
Forwarded from ስለ ቁርባን chat
ማታ 3 ሰዓት
ስለ ቁርባን እንማማራለን
-በመጽሐፍ ቅዱስ
-ከወጣቶች ህይወት አንጻር
-በማህበረሰባችን ላይ ያለብን ሃላፊነት
ሌሎችም.
.
.
-ጥያቄዎችን እንቀበላለን

https://www.tg-me.com/sle_kurban
58🙏13👍1🔥1
✝️✝️✝️✝️
ለኪዳነ ምህረት ወዳጆች የቀረበ የበረከት ጥሪ
በየአመቱ ለምናቀርበው ጥሪ ዘንድሮም እንደአምናው ተሳተፉ

በሐዋሳ የኪዳነ ምህረት ጽዋ ማኅበር የተዘጋጀ  ለነሐሴ 16/2017 ዓ.ም ለኪዳነ ምህረት ዓመታዊ ዝክር

በዚኛው መርሃግብራችን ሁለት ቦታ የምናረግ ሲሆን 1ኛ አቅም የሌላቸውን ህጻናት እና 2ኛ በወይኒ ቤት ያሉ እህት ወንድሞቻችን ጾም እናስፈታለን ነሐሴ 16 አርብ ስለሚውል በ 17 የምናስፈታ ይሆናል

የነድያን ምገባ የሚያስፈልጉ ዝርዝር

አይነት            ብዛት       ዋጋ

እንጀራ.........200.........5000
ዘይት............ 8Lit........2700
በርበሬ.......... 3kg........4500
ሥጋ.............. 10kg....12000
ሽንኩርት........45kg.......4050
ምስር..........     3kg .... 600
ድንች............ 10kg...... 400
ካሮት  ......... 3kg...        210
ቃርያ ..........  1kg     .....   70
እንጨት.........        ........ 800
ነጭ ሽንኩር....2kg.........500
ቅመማቅም ...................300
   #አጠቃላይ  ____                  31,130ብር

ከነዚህ መካከል አቅማችሁ የፈቀደውን አንዱን በመቻል የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ በኪዳነ ምህረት ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን

   1000265320396
    መአዛ ቢሰጥ


  📞phone no
0985124428
0967955989

ለተጨማሪ መረጃ በዚህ ያውሩ
  @Shbin1
41👍1😁1
2025/10/31 08:36:09
Back to Top
HTML Embed Code: