በኃብት ስጦታ አንፃር ስንመለከት ኢትዮጵያ ለሁሉም የሚበቃ ኃብት እንዳላት እናውቃለን። በባሌ ዞን ከተለያዩ አመራሮች ጋር ያደረግነው ጉብኝት የመጨረሻ መዳረሻ አስደማሚው የፊንጫ ሀበራ ፏፏቴ ሆኗል። በግርማ የሚወርደው ፏፏቴ ወደ ሶፍኡመር የዋሻ ሥርዓት የሚደመረውን የወይብ ወንዝ የሚቀላቀል ነው። የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ የሚገኝበት ይኽ አስደናቂ ከባቢ ድንቅ የአዕዋፍ መገኛና በቅርቡ የዋሻ መስህብ የተገኘበት እንዲሁም የራፉ ውብ የዐለት ደን አቅራብያ የሚገኝ ነው። በቅርቡ በአካባቢው የሚገነባው ማረፊያ ሲጠናቀቅም ለጎብኝዎች የበለጠ ሳቢ እና ምቹ ይሆናል።
ባለፉት ሶስት ቀናት በጉብኝቱ የተሳተፉ የቀድሞ እና በሥራ ላይ ያሉ ኃላፊዎች በጉብኝቱ የተመለከቱት የተፈጥሮ፣ የባሕል እና የሰው ኃብት ከፍ ያለ መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል። የጋራ ሥራችን እነዚህን ኃብቶቻችንን መግለጥ፣ ማሳደግ፣ በኃብቶቹ ላይ በመጨመር ቀጣዩ ትውልድ ችቦውን ተረክቦ እንዲቀጥል መሠረት መጣል ነው። ኢትዮጵያ በርግጥም የተትረፈረፈ ኃብት ምድር ናት። እንሰባሰብ። ለማለም እንድፈር። የጋራ ነጋችንን በጋራ እንገንባ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል።
ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን።
ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ።

ዛሬ የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ የጀመርነው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመጎብኝት ነው። ፕሮጀክቱ ባለፈው ከነበረኝ ጉብኝት በኋላ የሚለካ የሥራ እድገትም ታይቶበታል። የግድቡ ከፍታ 128 ሜትር የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የሲቪል ሥራው 70 ከመቶ ደርሷል። ይኽ ስኬት ለኃይል ምንጭ ዋስትናችን ላለን ያላሰለሰ ጽኑ ጥረት ምስክር የሚሆን ነው።
Today, we begin the Council of Ministers’ macroeconomic evaluation for the first 100-days of the Ethiopian calendar year 2018 with a visit to the Koysha Hydroelectric Power Project. Since my last review, the project has shown remarkable progress, now standing 128 meters high and reaching 70% completion of civil works. This milestone stands as a testament to our continued commitment to achieving energy security.