Channel created
Channel photo updated
ከ120,000 በላይ አባላት ባለው የመረጃ ቻነል ምርት እና አገልግሎቶን በማስተተዋወቅ ትርፋማ ይሁኑ@Moe_Ethiopia በዚህ ቻናል ላይ ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ?• ቻናል• ሽያጮች (ልብስ, ጫማ, Electronics..)• ድርጅት / ሱቅ• ሙዚቃ• የፀጉር, የፊት, የፂም ማሳደጊያ ትሪትመንቶች • የConsultancy companys• እንዲሁም ማስተዋወቅ ሚፈልጉትን ሁሉ ማስተዋወቅ ይችላሉ ; ያናግሩን 👇 @Adis_Pro
ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዝቅተኛ መሆን ምክንያቶች ተጠንተው ይቅረቡ - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትየትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገብ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በጥናት ለይቶ እንዲያቀርብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠየቀ።በምክር ቤቱ የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ሚኒስቴርን የ2016 እቅድና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ገምግሟል።በዚሁ ጊዜ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ቀደም ሲል ሲሰጡ የነበሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤቶች የተማሪዎችን ትክክለኛ ችሎታ ያሳዩ አልነበሩም ብለዋል።የፈተና አሰጣጡን በመቀየር የተመዘገበው የተማሪዎች ውጤት በዘርፉ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች ማሳያ መሆናቸውን ጠቁመው ለዚህም ከወላጆች ጀምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጸዋል።@Moe_Ethiopia@Moe_Ethiopia
የኦነግ ሸኔ እገታ እንደቀጠለ ነውየመንግስት ሰራተኞች፣ ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች፣ የውጭ ዜጎች፣ ለሥራ ጉዳይ እና ለጉብኝት ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ የሚዘዋወሩ ሰዎች የዚሁ እገታ ሰለባ ሆነዋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ባሰራጨው ዘገባ እንዳመለከተው ከሆነ ይሄው ቡድን የአርሶ አደሮችን ቤተሰዎችን ሳይቀር አፍኖ በመውሰድ ጥሬ ገንዘብን እየጠየቀ ይገኛል፡፡ በዚህም አርሶ አደሮች የቤተሰብ አባሎቻቸውን ለማስለቀቅ ሲሉም የእርሻ በሪያቸውን ሳይቀር ለመሸጥ እየተገደዱ መሆኑን ዘገባው አክሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ እገታው ከምንዜውም በላይ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ከሰሞኑ 30 የኮንስተራክሽን ባለሙያዎች በዚሁ ሀይል ታግተው ሴቶቹ በነፃ ሲለቀቁ ሌሎች ወንድ ታጋቾች ግን ለ20 ቀናት ቆይተው 2 ሚሊዮን ብር የማስለቂያ ገንዘብ ከከፈሉ በኋላ ሀይወታቸውን ማትረፍ ግድ ያላቸው መሆኑን ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡@Moe_Ethiopia@Moe_Ethiopia
የትምህርት ሚኒስቴር ፤ በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጄና አማካኝነት ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ለማድረግ እንዲቻል ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች መረጃ በአስቸኳይ እንዲላክለት ጠይቋል።ሚኒስቴሩ ፤ ተቋማት መረጃው እጅግ ቢዘገይ እስከ ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲልኩ ያሳሰበ ሲሆን የማያሳውቅ ዩኒቨርሲቲ ; ተፈታኝ ተማሪ የለውም ; በሚል ተይዞ የሚታቀድ መሆኑን በጥብቅ አስገንዝቧል።በ2015 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰጠው የመውጫ ፈተና በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፉት 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ መሆናቸው አይዘነጋም።በግል ተቋማት ደግሞ ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተው ያለፉት 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ ብቻ ነበሩ።በድምሩ ከአጠቃላይ 150,184 የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 61,054 ብቻ ወይም 40.65 በመቶ ናቸው።የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና አስተዳደር መመሪያ እንደሚያሳየው ከሆነ ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ ይሰጣል። የመጀመሪያው በአመቱ መጨረሻ ሲሆን ሁለተኛ በአመቱ አጋማሽ ነው።የመጀመሪያውን የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች በዚህ አመት አጋማሽ ላይ በሚዘጋጀው ሌላ ፈተና መፈተን የሚችሉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ስርዓት እንደሚዘረጋ መግለፁ አይዘነጋም (በዚህ ጉዳይ ወደፊት የሚወጣ መረጃ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን)።@Moe_Ethiopia@Moe_Ethiopia
«በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ተበራክቷል›› - የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንበከተማ አስተዳደሩ በህገወጥ መንገድ በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ መስፋፋቱን በፌዴራል የስነ- ምግባር;ና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ- ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ ተናግረዋል።ምክትል ኮሚሽነሩ ይሄን ያሉት ኮሚሽኑ ባዘጋቸው የውይይት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡የከተማ አስተዳደሩ ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የፌዴራል ስነምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ያቀረበውን መረጃ አጠናክረው በመናገር;ና የመረጃውን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ለመከላከል እና ለማስተካከል በቅንጅት እየሰሩ ስለመሆናቸው አመላክተዋል።በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚታየው ህገ ወጥ የመሬት ወረራ ብሎም በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ መስጠትን ጨምሮ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮች መነሻቸው የአዳዲስ መመሪያዎች መበራከት እና በመረጃ አያያዙ በኩል ዘመኑን የዋጀ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት አለመቻሉ ስለመሆኑም ገልፀዋል።በሌላ በኩል ከከተማዋ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ገበሬዎች መኖራቸውን በማስታወስ ለገበሬዎች ካሳ የመስጠት አሰራር ሂደት ላይ የባለይዞታው ቤተሰብ በመምሰል ስማቸውን በመቀየርና መታወቂያ በማሰራት እንዲሁም ከደላሎች ጋር በመመሳጠር በአንድ ይዞታ ላይ በካርታ ላይ ካርታ ደርቦ የመያዝና በይዞታ ላይ ይዞታ የማረጋገጥ ህገ ወጥ ተግባር እንደሚከናወንም አክለው አመላክተዋል።በተመሳሳይ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከመሬት ጋር በተገናኘ ለሚስተዋለው ብልሹ አሰራር ብሎም ‹ አይን ያወጣ › ሙስና እንደምክንያት የተነሳው የመረጃ አያያዝ እና ስራን በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ አለመከወንና የመሬት አደረጃጀት ጉድለት መኖሩን ነው። @Moe_Ethiopia@Moe_Ethiopia
ውጤት 1 ሰአት ላይ ይወጣል ቢባልም ተማሪዎች ውጤታቸውን ማየት እንደተቸገሩ ገልፀዋልተማሪዎች ውጤታችሁን በትዕግስት እንድትጠብቁ እያሳሰብን ውጤት ሲለቀቅ በዚሁ @Moe_Ethiopia ቻነል በፍጥነት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።@Moe_Ethiopia@Moe_Ethiopia
2024/05/21 17:05:02
Back to Top
HTML Embed Code: