Telegram Web Link
ነፊ በረከተ።
ሀዘንን አወጆ፣ቀድሞ የሚያስነባ፡
ያሸልም ይመስል፦
ሁሉ ፈጥኖ ይነፋል፣ዲጂታል ጥሩንባ።
ደሞ ሌላው ይሮጣል፣
ችኩል የነፋውን፣ቀድሞ ሊያስተጋባ።

@Adnakotkifle
የማያቋርጥ ተከታታይ የግጥም ውድድር ሊጀመር ነው።👌ከዚህ በፊት ባሉት ዙሮች አሸናፊ እና ተሸላሚ የነበራችሁ፦

የአንደኛው ዙር አሸናፊ፦ልደቱ
የሁለተኛው ዙር አሸናፊ፦ግሩም ታደሰ
የሶስተኛው ዙር አሸናፊ፦ቃል(ፀሀፊዋ)
የአራተኛው ዙር አሸናፊ፦ቬንሲያ
የአምስተኛው ዙር አሸናፊ፦ፍሊሞን
ለስድስተኛው ዙር ከአሁን ሰአት ጀምሮ እስከ ሰኞ ማታ ሁለት ሰአት መላክ ትችላላችሁ።👌


ግጥሞን ለመላክ👇
@Adnakot
@Adnakot
ማሳሰቢያ የቀድሞ ዙር አሸናፊዎች አሪፍ ስራ ማዘጋጀት እንዳትረሱ፡፡አስረኛው ዙር ሲጠናቀቅ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ይጠብቃችኋል፡፡👌

ለብዙ ሰው እንዲደርስ share🙏
ወድድሩ የሚካሄድበት የቴሌግራም ቻናል👇
https://www.tg-me.com/Adnakotkifle
ወዛሙ ከንፈሬ፣ቀጭን የማያውቀው፡
ዘንድሮ ተረታ፣ብርድ አጎሳቆለው።😢
ሀኪም ጋ፣ባመራም አጣሁኝ ማርከሻ፡
ወዴት አገኝ ይሆን?፣ቆንጆ ሴት ወጌሻ።😔

አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን
@Adnakotkifle
ግጥማችሁን ያላካችሁ እስከ ማታ ሁለት ሰአት👇
@Adnakot
ነገ ሁለት ሰአት ግጥማችሁ ይለጠፋል።👌 እሰከዛው ያላካችሁ ተወዳዳሪዎች ላኩ።
@Adnakot
666 subscriber ላይ ስደርስ ከዚህ ማህበር ጎትታችሁ አውጡኝ አልኩ፤አወጣችሁኝ።🙏 አሁን ደሞ 888 ደርሼ ከዚህ ውብ መፅሐፍ ርዕስ ጋር የሰብስክራይበሬ ቁጥር ምን ያገናኘው ይሆን የሚል የሞኚ ምርምር ይዣለው።😔በሉ እንደተለመደው 'share' በማድረግ የሰብስክራይበሩን ቁጥር አሳድጋችሁ ከሞኚ ምርምሬ አውጡኝ።🙏
link👇
https://youtu.be/lF9fXts4pm8
"Hi,Hi kongo,Hey"እና የመሳሰሉትን መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚልኩ ጎረምሶች አስቸግረውሻል? እንግዲያውስ የሀገራችን ሳይንቲስቶችን ከፍተኛ ምርምር ሳልጠብቅ ያገኘሁትን መፍትሔ እነሆ፦

"Hi ቆንጆዋ" ሲልሽ፣ብትየው "Hi bro"፡
ዳግም ላይመለስ፣ይሰወራል በሮ።👌

ለተመሳሳይ የመፍትሔ ሀሳቦች Adnakot Tube ብለው ዩቱዩብ ላይ subscribe👌
@Adnakotkifle
ሞተ፤ተነሳ ሲል፣ሟርተኛ ሲያወራ፡
ዛሬ ግን ጨከነ፣ሄደ አሊ ብራ።😢
ነፍስ ይማር🙏
@Adnakotkifle
የሰው መኪና ላይ፣በድብቅ ሆነ እንጂ፡
ፎቶው ቆንጆ ነበር፣ልጁም ጎበዝ ነጂ።😂
https://youtu.be/fEzoPA8KbYA
"ድንግሉ" ፊልም ላይ የአለማየሁ ታደሰን መሳሪያ ለማቆም ብርቱ ትግል የሚያደርጉት እኝህ ድንቅ ተዋናይ አሁን ደ'ሞ የእኔን ብዕር ለመፃፍ እንዲቆም ለማነሳሳት እንደዚህ አይነት 'comment' በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጋሽ አሴ ከልብ አመሰግናለው።🙏
በዚሁ አጋጣሚ you tube ቻናሌን ተጋበዙልኝ።Adnakot tube👇
https://youtu.be/E6Zm7DPADfk
የግጥም ጅረት ፦ከአድናቆት
👸 አቶ፡እንቺ ሰላምታ 👱 ወ/ሮ፡በምን ታ 👸አቶ፡በሰፈር 👱ወ/ሮ:ምን አለ በሰፈር? 👸አቶ ፡ከኤርታሌ የሚግል አጀብ!ያንቺስ ከንፈር፡ ------------------------------------------------------- 👸 ወ/ሮ፡እንካ ሰላምታ 👱 አቶ፡በምን ታ 👸ወ/ሮ፡በሀገር ሰው 👱አቶ:ምን አለ በሀገር ሰው? 👸ወ/ሮ ፡በረዶ ከንፈሬን አንተ ነህ ያጋልከው፡፡ Join and share @Adnakotkifle
ታይታን የሚወድ፡
ዝናን የሚያሳድድ፡፡
ስራው እርባና ቢስ፡
ከአንጀት የማይደርስ፡፡
ቢናገር አፉ 'ሬት፡
ፍሬ የሌለበት፡፡
በሀገሩ ጉዳይ፡
የሆነ ቃል አባይ።
አንድነት የሚያመው፡
ክፍፍል 'ሚያክመው።

"የእነዚህን በሀሪ፣ተቃራኒ የያዘ፡
አንድ ሰው ፈልጉ?"፤ሲል መምህሩ አዘዘ?"

ተጠያቂዎቹም አውርደው አውጥተው፡
ምርቱን ከገለባ፣በደንብ ለይተው፡
አንድ ስም በጋራ፣ጮኸው አስተጋቡ፡
"እሸቱ መለሰ፣ባለ ትልቅ ልቡ"፡
ይህ አልበቃ ብሎም፣መመስከር ጀመሩ፡
ተራ እየጠበቁ እንዲህ ተናገሩ።

ምስክር አንድ፦
ከሬዲዮ ድራማ፡
አሁን እስካለበት፣የእውቅና ማማ፡
ጋራጅ ከመቀጠር፤
የራሱን ድርጅት እሰከማስተዳደር፤
የደረሰ ወጣት፣ብሩህ ባለተስፋ፡
ከተማ ከገጠር፣ስራው የተንሰራፋ።

ምስክር ሁለት፦
"ይህቺ ናት ኢትዮጵያ፣ይህቺ ናት ሀገሬ፡"
የተሰኘ ስራው፣ያቃጭልብኛል እንደትላንት ዛሬ፡፡
በሱ ውስጥ የማያት፣እምዬ ኢትዮጵያ፡
በሁሉ የሰመረች፣የሌላት አምሳያ።"
ምስክር ሶስት
"ገደለው፣ቆረጠው፣ካላሉ በስተቀር፡
'ሚገኝ 'ማይመስላቸው፣የዩቲዩብ ዶላር፡
በእርቃን ወተው፣ካልሸመቱ ዝና፣
ወይ ካላሰራጩ፣ፍፁም የሀሰት ዜና፡
'ሚገኝ 'ማይመስላቸው፣በሚዲያው ስኬት፣
እሸቱ መለሰ፣ማሳያ ምልክት።"

ምስክር አራት
"ፅሑፍ ላይ የሚራቀቅ፡
ምናቡ የሚደንቅ፡
ቀልዱ የተዋዛ፡
በማሳቅ ባህር ውሰጥ፣ቁም ነገሩ የበዛ፡፡"

እኔ፦
የእሸቱ ሰውን ማክበር፡
አህያዋ ትናገር።😄
ከህዝብ ፍቅር ተለገሰ፡
የተሰጠውን፣እሸቱም መለሰ።👌

በእርግጥ ይህቺን ሞነጨርክ ብለው"አሽቃባጭ" የሚሉኝ ብዙ እንደሚሆኑ እገምታለው።ምክንያቱም እንኳን እኔ ሰው በጎ ሰራ ብዬ ያመሰገንኩትን ቀርቶ በጎ የሰራውንም ሰው ራሱ በፈለጉት መንገድ እየተረጎሙ የሚዘልፉ ጥቂቶች ስላልሆኑ።
በመጨረሻም እሸቱ መለሰ(እሼ) በብዙ መንገድ አርአያ የምትሆን ነህና ክብር ይገባሃል።🙏👌

@Adnakotkifle
ደስ ብሎኛል።🙏
ከዩቱዩብ መመዘኛዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን 1000 ሰብስክራይበር አሟላሁ።💪"አንድ ሺህ ሰው ብርቅ ነው እንዴ ትሉ ይሆናል?"አዎ ብርቅ ነው።ግጥም እና ትምህርትን ብቻ ብለው፤ስድብን ጥለው የመጡ 1000 ሰብስክራይበር ማግኘት ብርቅ ነው።አዎ በቅርቡ ትልቅ ቦታ ለሚደርስ ጀማሪ ቻናል ዛሬ አንድ ሺ መድረስ ብርቅ ነው።
አቤት ጉራ እንደው 1000 ሰው ብቻዬን ጎትቼ ያመጣው አልመስልም? የእናንተ አሁን ስማችሁ ብጠራ ሰአት የማይበቃኝ ቅን ሰዎች ቀናነት ባይኖር እዚህ እደርስ ነበር? አልደርስም።ስለዚህ ሁላችሁም በያላችሁበት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።🙏

አሁን ባለሀብት ነህ ጋብዘኛ የሚል አይጠፋም እኮ።😂ባላሀብት ለመሆን 1000 ሰብስክራይበር ብቻ አይበቃም።😔4000 watch hour ሞልቶ ለባለሀብትነት መመዝገብ ይጠይቃል።😔ምንም እንኳን ቻናሌ ለትርፍ የተቋቋመ ባይሆንም።😜
እና እንዴት Watch hour እንሙላ አላችሁ? ቪዲዮቹን ገብታችሁ ማየት ነዋ።ከዛ like+comment😄 ግን ቻናሉ ውስጥ ገብታችሁ የሚጠቅም ወይም ፍሬ ያለው ነገር ካጣችሁ የመቆየት ግዴታ የለባችሁም።👌የሚስተካከል ነገር ካለ ግን ወንድማዊ ግዴታ አለባችሁ።🙏
ስለሁሉም አመሰግናለው።
#share
https://youtu.be/yVLk3WHkgn0
የአለም ዋንጫ ክስተቶች እና ትዝታዎች
የሻባላላ መክፈቻ ጎል፡
የስዋሬዝ የእጅ ኳስ፣ጋናን ሲጥል፡
ብራዚል ላይ ሲወርድባት፣የጎል ናዳ፡
በስዋሬዝ ንክሻ፣ቺሊኒ ሲጎዳ፡
አየር ላይ ተንሳፎ፣ቫን ፔርሲ ሲያገባ፡
የላምፓርድ ጎል ሲሻር፣ደጋፊው ሲያነባ፡
የቮሊ ድንቅ ግብ፣በጆምስ ሮድርጌዝ፡
የዚነዲን ቴስታ፣ልብ ሲገዘግዝ፡
'Waka Waka' ስትል፣ሽንጣሟ ሻኪራ፡
በደቡብ አፍሪካ፣አፍሪካ ስትኮራ፡፡


ስንቱን አሳለፍነው፣በቲቪያችን መስኮት፡
በቆሎ እየጋጥን፣በቀዝቃዛው ክረምት።
ከወራቶች በፊት እየገዛን ማውጫ፡
ቀድመን ስንተነብይ፣የሀያላን ፍጥጫ።
ደስ ይል ነበር መቼም፣ልዩ ነው ስሜቱ፣
በአራት አመት አንዴ፣ኳስን መመልከቱ።

አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን
https://youtu.be/FWPpU2mO2Ts
የመጀመሪያ የግጥም አልበሜን😄 በ linku በመግባት ወይም Adnakot tube ብላችሁ በመግባት ተጋበዙልኝ።
እንደተለመደው ከቅንነት የመነጨ አስታየታችሁን፣ከመርካት ብቻ የመነጨ ላይካችሁን😄፣ከቤተሰብነት የመነጨ ሰብስክራይብ እና ሼር ማድረጋችሁን፣እጠብቃለው😄🙏
አክባሪያችሁ ሞንጫሪ አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን
https://youtu.be/O8A6WrWJnmo
ስራ ለመቀጠር፣"ኤክሴል ይችላሉ"
"ፍጥነቶስ እንዴት ነው፣ሲፅፉ ሲባሉ":
በልበ ሙሉነት፣አዎ እንዲሆን መልስዎ፡
አድናቆት ቲዩቡ ላይ፣መፍትሔው እነሆ።👌😄👇

ከ100 በላይ ወሳኝ የኤክስል 'ሾርተ ከቶችን' ከበቂ ማብራሪያ ጋር ላቀርብላችሁ ሞክሪያለው።እናንተም የምታውቁትን እኔ ያልጠቀስኩት ካለ ቪዲዮ ስር በኮመንት አስቀምጡልኝ።🙏
https://youtu.be/cbHzk5BsYKU
(ፖለቲከኛው የጭንቅላቴ ክፍል)

መንጃ ፍቃድ ለማሳደስ መግባት ከነበሩብኝ ቢሮዎች ውስጥ አንዱ አሽከርካሪዎች ቅጣት ይኑርባቸው፤አይኑርባቸው የሚረጋገጥበት ክፍል ነበር።ፋይሌ ከተገላበጠ በኋላ ምንም ቅጣት እንደሌለብኝ ያስተዋለችው ባለሙያ"የትራፊክ አደጋ በበዛበት በዚህ ዘመን አንተ ላይ ምንም ሪከርድ አለመኖሩ የሚደንቅ ነው።በዚሁ ቀጥል አለችኝ"(መንጃ ፍቃዱን ካወጣሁ ነድቼም አላውቅ።😄)  እሷ እንደዛ ባለችኝ ቅፅበት ፖለቲካ ለመተንተን የምጠቀምበት ተንኮለኛው እና ነገረኛው የጭንቅላት ክፍል"እንዴት በዚሁ ቀጥል ትልሀለች?፤መኪና አለመያዙን እኮ ቀጥልበት እያለችህ ነው፤በጥቅሉ አንተንም፣የመጣህበት ማህበረሰብንም መሪ መጨበጥ አትችሉም እያለች ነው።"መኪና ቶሎ ያዝና፤ሙሉ ነጭ ለብሳ ፤ፍቅረኛዋ ጋ ለመሄድ ተቻኩላ ስትሮጥ አስፓልት ላይ የተኛ፣ የደፈረስ ውሀ ረጭተህባት የቅጣት ሪከርድህን በሷ ጀምር"አለኝ።
እኔም ፖለቲከኛው የጭንቅላቴ ክፍል የሚልኝ ነገር "ትክክል ይሆን? አይሆን? እያልኩ ሳመነታ፦"እሷ በፈግታ ተሞልታ "መቶ ብር ክፍል" አለችኝ።
"አየህ ነጭ ጥርሷን ፈልቅቃ እያሳየችህ፤ ምንም የማታውቅ ነጭ ነህ ስትልህ" አለኝ።እያመንኩት መጣሁ።
ጉዳዬን ጨርሼ ልወጣ ስል"ፈገግታዋ ሳይከስም፤"መልካም ቀን"አለችኝ።
"ጉድ! ያሁኑ ይባስ።ከቀን የዘለለ ዕድሜ የለህም እያለችህ እኮ ነው።ስታሟርትብህ መቼም ዝም አትላት።"አለኝ በድጋሜ ፖለቲከኛው የጭንቅላቴ ክፍል።

እኔም ወረቀቴን ተቀብዬ መቼና በምን ሁኔታ ጭንቅላቴ የመከረኝን ተግባራዊ እንደማደርግ እያሰላሰልኩ ወደ ቀጣዩ ክፍል አመራሁ።🚶‍♂
አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን

https://youtu.be/O8A6WrWJnmo
ሀገሬ ኢትዮጵያ፦
በሰላም በተድላ፣በፍቅር እንድትኖሪ፣
የብሔር ቀን ትተሽ፣የሰው ቀን አክብሪ።👌

@Adnakotkifle
2024/05/29 08:47:06
Back to Top
HTML Embed Code: