Channel name was changed to «የአዲብ ግጥሞች እና እይታዎች»
ልብ ያልላልኩት )

አረግሽኝ እንጂ
የከውኑ የአለሙ አዲስ እንግዳ
ጀባሽኝ እንጂ
ሩጬ ማልሸሸው ማኣት ዱብዳ

አፍዝዞ ያደናገረኝ
አክላቁን ውሉን የሳትኩት
ድሮንስ ይሄን አልነበር
ደግሜ ደግሜ የኖርኩት

ሁሉንም አውቃቸዋለሁ
አኳኳን አከራረመሙን
ሰው ከሰው ይሰማል እንጂ
መለያ መጠሪያ ስሙን

መራቅሽ ያንሰፈሰፈኝ
ናፍቆትሽ ያንገበገበኝ
የማጀት የእልፍኜን ዝቆ
ለራቤ እስኪመግበኝ

አላውቅም የራሴ እንደሆን
ይህ ሁሉ የኔ እንደነበር
በልክሽ አቁሜ ስኖር
በሩሄ በጅስሜ ማገር

ቃላባይ ልብሽን አይቶ
መሄድሽ ጠልቆ ነገርኝ
ለነገ መንገድ ሚሆን
ብዙ ስንቅ እንደነበረኝ

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ዝም ብላ ምትስቀው
ልቤን እስክትሰርቀው
ያወራሁት ወሬ
ሚገርማት አስሬ

ስሜን በየቦታው
[ ሺ ግዜ ምትፈታው ]

ምጥን ንግግሯ
ቃሏ ሚጣፍጠው
ዝም ያለ አንደበቴን
ማብራሪያ ምትሰጠው

ህልሜን ከእውኔ ጋር
አይኔን ልትገልጠው
በቄንጥ ተራምዳ
መርጣ ምትረግጠው

ፀጉራ ሲዘናፈል
ሽንጧ ሲውረገረግ
ከአለም ነጥላ
ከስሯ ለማድረግ

እስካልቆጥር እድሜ
የሆነችኝ ህልሜ
ከ'ናት በላይ ቀርባኝ
ሆዴን ምታባባኝ

ዜማ ወረብ ሳቋን
የመኖር ሲር ሀቋን
አሳይታኝ ልትበር
ከጎኔ ያረፈችው
እስክወዳት ነበር

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
https://vm.tiktok.com/ZMY7JgLj1/

ቲክቶክ አካውንቴን ፎሎ በማድረግ ግጥሞቼን በምስል ታገኛላቹህማ 🙏
ናቆት ሲበጣኝ
ቀን ሲያስቆጥረኝ
እሸሸግበት ጥግ ባይኖረኝ

ከራሴ ጠፋሁ
ከአለሜ ሸሸሁ
ራኳት ብዬ ማለዳ መሸሁ

ስሜን አጣሁት
ሞገሴ ራቀኝ
በሷ ነበረ አለም ያወቀኝ

ምን አለው አለም
መንገዱ ራሱ እሷን አላለም

ቆሌ ርቆታል አድባሩ ቀየው
እሷን እያለ ደርቷል እዬዬው

ሁሉም ለምዶታል ፌሽታ ለዛዋን
ባዶ አረገችው ምድር ታዛዋን
እሷ ሳትኖር ህይወት ይኖራል ?
እውነት ያስፈራል

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ሌላ ስትለምጂ
ሌላ ስትወጂ
በላዬ ላይ ሂጂ

ሀሴት ከሚርቅሽ
ሌላ ሰው ይናፍቅሽ

ሌላ ሰው ፈልጊ 
በእንቅፋቴ ርጊ
ቀኔን አደብዝዢው
መውደዴን ገንዢው

ይደክርት መንፈሴ
ይጨልም በርኖሴ

ከእኩዮቼ ልነስ
ገድ ይሁነኝ ማልቀስ

ከአቅሜ ስገዳደር ከራሴ ስታበይ
እኔ መሳቅ ስሻ አንቺ ፈገግ በይ

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
#አንሶላ_እንዴት_ናቀው?

ከታምራት በላይ
በታምር አድርጎ እኛን ሲከልቀን
አለም ትደምቃለች ለሰከንድ ስቀን
አናኮርፍም እንጂ
እኛ ካኮረፍን ያውም ለአንድ ቀን
ፉጡራን በመሉ
ተጠናውቶት ያድራል እልፍ አዕላፍ ሰቀቀን

ከንጋት ከምሽት
ኩርፊያና ሳቃችን እንዲ እያስደነቀ
እኛን እያፀና ዘመኑ ካለቀ
የኛ መፈቃቀር
ንፁ ሆኖ ሳለ በነገር ያልሸሸ
ተኝተን ስነቃ
ለምንድነው ?ታዲያ አሶላው ቆሸሸ

የነካን ይቅርና ያየን በፀደቀው
ንፁ ፍቅራችንን አንሶላ እንዴት ናቀው?

አዲብ

አልባሌ ነገር አታስቡ አሏቹ ደግሞ 😝

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ልክ እንደመሻትህ
እንደፈለክ አርገኝ
ሲሩን ግለጥልኝ
ከከውኑ ሸሽገኝ

አይወስነኝ ቦታ
አይገድበኝ ሰአት
ንፋስ ሆኜ ልዝለቅ
ከደጃፍህ በአት

ሰው አይተዘበኝ
አይሻኝ ጠበቃ
በስምህ ልብቃቃ
ካንተ ጋራ ልንቃ

የለም እስከምባል
ከእይታ ሰውረኝ
ጎንህ ባልሆን እንኳን
ከስርህ አኑረኝ

ከልቤ ከሆነ
የዘይኔን ፊት ልየው
አጥብቀኝ ጠብቀኝ
ከይምሰል እዬዬው

ፊትህ ሞቆሚያውን
ባላገኝም ፅናት
አትከለክለኝም
በስምህ መፅናናት

አትንሳኝ እምባዬን
ለጠፋብኝ ሚሆን
ልቤን አራራልኝ
ብቻዬንም ስሆን

ከአጣሁት የሚልቅ
ከማገኘው በላይ
ወድጄ ይሁና
የቆምኩት በርህ ላይ

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ፍጥረተ አለም
ተጓዥ ጠፍቶት
በቀረበት መንገድ በኩል
እኔ እዛ አለሁ
ለጋ እድሜዬን ስኮሎኩል

ልብ ደክሞት 
ተጓዥ ርቦት
ወቶ ሲቀር
መንገድ ሰልቦት

ለብቻዬ ተጉዣለሁ
ለብቻዬ ደርሻለሁ
እኮ ለምን ?
አንቺን ብቻ ስለማምን

አዲብ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
2024/05/03 07:01:46
Back to Top
HTML Embed Code: