Telegram Web Link
ቅዳሴ ላይ ኢየሱስ ይገኛል.. ማለት ሊገኝ ይችላል አይደለም.. በቃ የምርም ኢየሱስ እዛ ጋር ይገኛል.. ክርስቶስን ብዬ ልምል ነበር ግን መማል ማቆም አለብኝ በተለይ በጌታ ስም..

ዮው ክርስቶስን ልናገኘው ነው ዛሬ ምንሄደው ይሄንን እያሰብን እንሂድ.. ብንችል ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ከእርሱ እንካፈላለን.. ምናልባት ዛሬ ካልቻላችሁ እንደኔ በቃ ሄደን ከሩቁም ቢሆን አግኝተነው እንመጣለን

ይህ ሁሉ በጌታ ምህረት እና ቸርነት ብቻ ሆነ
ቅዳሴ ላይ የራሳችንን የግል ጸሎት የምንጸልይ ሰዎች ግን ምናችንን ነው ሚያመን..??

https://vm.tiktok.com/ZMBvUY4k7/
ትናንት በጊዜ ተኝቼ ነበር እና ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ ስነሳ መልእክቶች አየሁ እና “ዮኒ ማኛ” ጋር ና እና አንዳንድ ፕሮቴስታንት ወንድሞችን በቴስታ በልልን የሚል ዓይነት ነበር.. እና ከነጋ ከቅዳሴ በኋላ ስሰማ ለካ ቀውጢ ጭቅጭቅ ነበር ሎል..

በእርግጥ እኔ ብኖርም በአንዳንድ ምክንያቶች እንደነዚህ ዓይነት ቤቶች አልገባም.. ጭቅጭቁንም አልፈልገውም ግን ቀለል ያለ ነገር ስለሆነ ዛሬ ላይቭ ላይ ትንሽ ነገር እሄድበታለሁ.. ቪዲዮም እሰራላችኋለሁ ማታ ላይ
ፕሮቴስታንቶች የኢየሱስን የአለም ቤዛነት እንደማይቀበሉ ማስረጃዎች ከራሳቸው አንደበት.. ከሃገር ውስጥም ከውጭ ሃገርም..

https://vm.tiktok.com/ZMBvXHa6x/

———-
የእለቱ ወደ ቲቶ መልእክት ንባባችን:

ምእራፍ - 3

- ለምድራዊ ገዦችም እንኳን መታዘዝ እንደሚገባ(ያው ክርስትናን የሚገፋ ነገር እስካልሆነ ድረስ)

- እኛ ራሳችን አስቀድመን የሃጢአት ባሪያ እንደነበርን እና አሁን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት ከእኛ ሳይሆን ከእርሱ እንደ ምህረቱ መጠን ዳግም እንደተወለድን.. መንፈስ ቅዱስንም እንደሰጠን

- እንዲህ የሆንን እኛ ደግሞ በመልካም ሥራ ልንጸና እንደሚገባ እና ከከንቱ ክርክሮች ራሳችንን እንድናርቅ

- መለያየትን(ምንፍቅናን) ከሚያደርግ ሰው መራቅ እንደሚገባ

- የመልእክቱ ማጠቃለያ እና ስንብት

መልካም ውሎ

@Apostolic_Answers
አንዲት ጓደኛዬ የሰሞኑን የፕሮቴስታንቶች ሁኔታ አይታ ታዝባ የጻፈችልኝ😁😁

[እኛ እመቤታችንን ቤዛ ስንል ቃሉን ተጠቀምነው እንጂ ከጌታ ጋር እያጋራናት አይደለም ቃላት ብዙ ትርጉም አላቸው ብለን በግልጽ እየነገርናቸውም ይከራከሩናል.. እዛው ከአጠገባቸው ከሌሎች ፕሮቴስታንቶች ግን “ኢየሱስ የዓለም ቤዛ አይደለም” ሲባል እየሰሙ ምንም አይመስላቸውም እንደውም ድነዋል እነርሱም ምናምን ነው የሚሉት.. እና ለቤተ ክርስቲያን ያላቸውን ጥላቻ ብቻ ነው ሚያሳየው]

@Apostolic_Answers
ኢየሱስ በመምጣቱ እውነተኛውን አምላካችንን ማወቅ ተመለሰልን.. ጌታ ይመስገን የምር.. ፈጣሪን ማወቅና ለእርሱ ብቻ መገዛት የዘላለም ሕይወት ነው.. እርሱ ባይመጣ ኖሮ ይሄኔ ጣዖቴን እያመለኩ ለእሱ ደም እያፈሰስኩ ነበር..

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“መጽሐፍቶቻችን ጥራት ያስፈልጋቸዋል” - ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

እነዚህ መጽሐፍት ላይ ከተሠራ እሺ አሁን የኛ ሃገር ፕሮቴስታንቶች ምን መስበክ ሊጀምሩ ነው..??😭😭 ፕሮቴስታንቶች የምር መጽሐፍቱ ምንም እንዳይነኩ ጸልዩ.. አሁን ላይ ኦርቶዶክስን በሱ ማጭበርበር ቢከብድም ቢያንስ ግን ፕሮቴስታንቶች ወደ ጌታ ቤተ ክርስቲያን እንዳይመጡ በሱ ነበር ምታዘናጓቸው..
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🤣🤣 ኧረ በቅዱስ ሚካኤል..
በጠዋቱ ልከው ያስቁኛል
“ያመኑትን ነው የሚያድናቸው” የሚለውን አባባል ይዘው አንዳንድ ፕሮቴስታንቶች ይህንን ካልቪኒዝም ነው ሲሉ እንደመስማት የሚያስቅ ነገር የለም..

1. ካልቪኒዝም ላይ ለመዳን ማመን ሳይሆን ለማመን መዳንን ያስቀድማሉ..

2. ኢየሱስ የሞተው እግዚአብሔር አስቀድሞ እገሌ እገሌ ብሎ ለመረጣቸውና ለወሰነባቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው ይላሉ😭😭

3. እኛ ግን ኢየሱስ ለሰው ዘር ሁሉ ሞቷል ግን ያንን ማዳኑን የሚያገኙት የሚያምኑ ናቸው እንጂ እንዲሁ የማያምኑትን አያድናቸውም እንላለን👍👍

ስለዚህ በክርስቶስ በኩል ለሰው ዘር ሁሉ ደም ፈስሷል.. ሥጋዌውም የሰውን ዘር ከመዋሐዱ አንጻር ልዩነት ሳያደርግ የሁላችን መድኃኒት ነው.. በእኛ በኩል ግን ይህንን መዳን ለማግኘት ማመን መጠመቅ አለብን ነው..

#ኢየሱስ_የሰው_ዘር_ሁሉ_ቤዛ_ነው

@Apostolic_Answers
ከኢየሱስ ጋር አብረን(አዳብለን) “ቤዛ” ብለን ምንጠራው አለን እንዴ..??

ኢየሱስ ቤዛ ሲባል አብሮ ቤዛ የሚባል አለ..?? የለም።።።።።

ወላዲተ አምላክ ቤዛ ስትባል “አብራ ቤዛ” (co-redemptrix) እያልናት አይደለም.. ካቶሊኮች የፈጠሩት የመጨቃጨቂያ ቃላት እኛም ጋር እንዳይመጣ.. እኛ እመቤታችንን “ቤዛ” ስንል በሌላ ትርጉም ስለሆነ “አብሮ ቤዛ” አንልም።

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኧረ እነዚህን ሰዎች ፈራዋቸው.. ቀስ ብለው ወንጌል ስለ አክሊል ብቻ ነው እንዳይሉ.. ሎል
የሆኑ “ካህናት” ተሰብስበው.. “ብጹእ አቡነ ገብርኤል ከተነኩብን መስዋእትነት እንከፍላለን” ሲሉ ስሰማ ሽምቅቅ ነው ያልኩላችሁ ወንድም እና እህቶቼ.. ጠላታችሁ እንዲህ አይሸማቀቅ..
ዮው እንምረጥና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን እንግባ ኧረ..

የአሁኑ መጽሐፍ ከብሉይ ይሁን ወይስ ከሐዲስ..??
ወንድማችን በጋሻው ሰሞኑን ደግሞ ተነስቶበታል.. እስቲ ደግሞ እንደፈረደብኝ ትንሽ ቦታ ቦታ ላስይዘው😆😆 ሎል

ለ3 ደቂቃ የሚቆይ ፖስት
ጭራሽ በፕሮቴስታንቶች(ሪፎርምድ) ውስጥ እግዚአብሔር አንዳንድ ሰዎችን ሲፈጥር ለገሃነም ወስኖ የፈጠራቸው እንዳሉ እንደሚያስተምሩስ ያውቁ ኖሯል..??


https://vm.tiktok.com/ZMBTYt6Ay/
ክርስቲያኖች ያለ ኢየሱስ ምንም ልታደርጉ አትችሉም

ፕሮቴስታንቶችም በእውነት ያለ “ዮኒ ማኛ” ምንም ልታደርጉ አትችሉም.. ሎል🤭🤭
ጌታ ኢየሱስ ድካማችንን ያውቀዋል ሁኔታችንን ይረዳዋል ምናምን.. ማለትም በወደቅን ቁጥር በቁጣ እየተንበለበለ ለማባረር የሚቸኩል አይደለም..

እንዲያውም ድካማችንን አይቶ ይራራልናል.. መጽሐፍም እንደተናገረ: “በድካማችን የማይራራልን ሊቀ ካህናት የለንም” ስለዚህም አባ ጊዮርጊስም እንዳለው: “የተራበ ሆድ ለምግብ እንደሚቸኩል ክርስቶስም ይቅር ለማለት ይቸኩላል” ከዛም ደግሞ ያግዘናልም..

ወደዚህ ጌታ በመጠጋት ከብዙ ነገር ልንርቅ ይገባል.. አልያ ግን ይኸው ጌታ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ሊፈርድብን ይችላል..

ጌታ ግን ሁሌም በምህረቱ ያስበን..

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄንን ቪዲዮ ያየች አንድ እህቴ ምን አለችኝ:

“ቅዱስ ጴጥሮስ ቢኖርና እንዲህ ሲል ቢሰማው ግን ጆሮውን አይሰይፈውም ትላለህ..??”

😁😁
2025/07/01 20:55:12
Back to Top
HTML Embed Code: