Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
የ እንዳናደርግ የመለኮትን መውረድ ለትስብእት ቆጠረው ። እነሆ በዚህም የትስብእት ከመለኮት ጋራ መተካከል ተገለጠ። ዮሐ 3፤13 ፣6፤41 (ሊቁ ቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ ሚስጢር)
▶️ፊል 2:7-11፤ነገር፡ግን፥የባሪያን፡መልክ፡ይዞ፡በሰውም፡ምሳሌ፡ኾኖ፡ራሱን፡ባዶ፡አደረገ፥
8፤በምስሉም፡እንደ፡ሰው፡ተገኝቶ፡ራሱን፡አዋረደ፥ለሞትም፡ይኸውም፡የመስቀል፡ሞት፡እንኳ፡የታዘዘ፡ኾነ።በዚህ ፡ምክንያት፡ደግሞ፡እግዚአብሔር፡ያለልክ፡ከፍ፡ከፍ፡አደረገው፥ከስምም፡ዅሉ፡በላይ፡ያለውን፡ስም፡ሰጠው፤ይህም ፡በሰማይና፡በምድር፡ከምድርም፡በታች፡ያሉት፡ዅሉ፡በኢየሱስ፡ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ምላስም ፡ዅሉ፡ለእግዚአብሔር፡አብ፡ክብር፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጌታ፡እንደ፡ኾነ፡ይመሰክር፡ዘንድ፡ነው።

®ወዳጄ ልጠይቅህ እስኪ እግዚአብሔር ያለልክ ከፍ ከፍ አደረገው የተባለው ለቃል ነውን ወይስ ለሥጋ ንገረኝ እስኪ ለቃል ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከነበረው ክብር የተጨመረለት ክብር አለን መቼም አለ አትለኝም ታድያ ለማነው ብዬ ስጠይቅህ ለሥጋ እንደምትለኝ እርግጠኛ ለኝ ታድያ ሥጋን ወደዬት ነው ከፍ ከፍ ያደረገው ያልከኝ እንደው ወደአምላክነት ነው ብዬ እመልስልሃለው ታድያ ሥጋ አምላክ ከሆነ ድንግል የወለደችው አምላክ እንደሆነ ገባኽን ኧረ ሌላም ልጠይቅህ ከስም ኹሉ የሚበልጠውን ስም ሰጠው የተባለው ለማነው ለሥጋ ነው ወይስ ለቃል መቼም ለቃል ኤልሻዳይ ፣አዶናይ ፣ኤል ፣አልፋና ኦሜጋ ፣ፊተኛው እና ኃለኛው እና ያህዊ ከመሳሰለት የበለጠ ስም አለውን እስኪ ንገረኝ መቼም ለቃል ነው አትለኝም ታድያ ለማነው ካልከኝ ለሥጋ ነው ኢየሱስ የሚል ስም ከቃል ጋር ተዋሕዶ ተሰጠው ፍጥረት ሁሉን የሚያድን ስም ከቃል ጋር በመዋሀዱ አገኘ ለዚህ
ስም በሰማይም በምድርም ከምድርም በታች ያሉት ኹሉ ይንበረከክ ዘንድ ለዚህ ሥጋ ሁሉም ፍጥረት ይገዛ ዘንድ ወዳጄ ድንግል የወለደችውስ አምላክ ባይሆን ኑሮ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደኾነ ይመሰክር ዘንድ ብሎ ባልተው ነበር እርሱ እራሱ ይሰግዳል ባለ ነበር እምላክ ካልኾነ እርሱም ይመሰክር እና ይገዛ ይስግድ ነበር እንጅ። ወዳጄ መለኮቱም ዓለም ሳይፈጠር አስቅድሞ እግዚአብሔር ነው ፍጥረት ኹሉ ይገዛለታል ስለሥጋው እንድኽ ተባለ እንጅ
ወዳጄ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት እንደኾነች ብዙ መረጃ አቀረብንልኽ ስለዚህ ካሁን በኃላ የአምላክ እናት እንደሆነች አምነኽ ተቀበል ካለኽበትም ጨለማ ውጣ
*⃣ክፍል አራት ይቀጥል የምትሉ ከሆነ ይቀጥላል ይብቃ የምትሉ ከሆነ በሌላ ዕርስ እንገናኝ

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
➡️ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሳምን⁉️⬅️
*⃣ክፍል አንድ
▶️ዘዳ 18:15፤16፤አምላክኽን፡እግዚአብሔርን፡በኰሬብ ፡ስብሰባ፡ተደርጎ፡በነበረበት፡ቀን ፦ እንዳልሞት ፡የአምላኬን፡የእግዚአብሔርን ፡ድምፅ፡ደግሞ፡አልስማ፥ይህችን፡ታላቅ፡እሳት፡ደግሞ፡አልይ፡ብለኽ፡እንደ፡ለመንኸው፡ዅሉ ፥አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ከአንተ፡መካከል፡ከወንድሞችኽ፡እንደ፡እኔ፡ያለ፡ነቢይ፡ያስነሣልኻል ፤ርሱንም፡ታደምጣለኽ።
®ሙሴ እንግድህ ይሄን ቃል ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንደርሱ ያለ ነብይ ከወንድሞቹ መኃል እንደሚያስነሳለት ተናገር በሐዋሪያት ሥራ መጽሐፍም እንድህ ተብሎ ተጻፈ ሐዋ 3:22፤ሙሴም፡ለአባቶች፦ጌታ፡አምላክ፡እኔን፡እንዳስነሣኝ፡ነቢይን፡ከወንድሞቻችኹ ያስነሣላችዃል ፤በሚነግራችኹ፡ዅሉ፡ርሱን፡ስሙት።
23፤ያንም፡ነቢይ፡የማትሰማው፡ነፍስ፡ዅሉ፡ከሕዝብ፡ተለይታ፡ትጠፋለች፡አለ።ሐዋ 7:37፤ይህ፡ሰው፡ለእስራኤል፡ልጆች፦እግዚአብሔር፡ከወንድሞቻችኹ፡እንደ፡እኔ፡ያለ፡ነቢይ፡
ያስነሣላችዃል፤ርሱን፡ስሙት፡ያላቸው፡ሙሴ፡ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስም ስለዚህ ሲናገር እንድህ አለ
ዮሐ 5:46፤ሙሴንስ፡ብታምኑት፡እኔን፡ባመናችኹ፡ነበር፤ርሱ፡ስለ፡እኔ፡ጽፏልና። በማለት ሙሴ ስለእርሱ የጻፈውን ባለመቀበላቸው እንደው እርሱን ያላመኑት ተናገር መናፍቃን ሆይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰው ዘር ካልሆነ እንዴት ሙሴ እንደኔ ያለ ነብይ ከወንድሞቻችሁ መኻል ያስነሣላችኋል አለ እንዴት ኢየሱስ ወንድማቸው ሆነ ከነሱ መኃል ተቆጥሮ
▶️ዕብ 2:16-27፤የአብርሃምን፡ዘር፡ይዟል፡እንጂ፡የያዘው፡የመላእክትን፡አይደለም፤ ስለዚህ፥የሕዝብን፡ኀጢአት፡ለማስተስረይ፥ለእግዚአብሔር፡በኾነው፡ነገር፡ዅሉ፡የሚምርና፡የታመነ፡ሊቀ፡ካህናት፡እንዲኾን፥በነገር፡ዅሉ፡ወንድሞቹን፡ሊመስል፡ተገባው።
®ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ስለርሱ ሲናገር የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጅ የመላእክትን አይደለም በማለት ኢየሱስን ለአብርሃም ዘሩ ያደርገዋል አስቀጥሎም በሁሉ ነገር ወንድሞችን ሊመስል ተገባው ብሎ ይነግረናል ወንድሞች የተባሉት እንድህ ሰዎች ካልሆኑ እነማን ናቸው? ለአብርሃም ዘር መሆንስ በምንድነው በሥጋ ካልሆነ
▶️ዘፍ 21:12፤እግዚአብሔርም፡አብርሃምን፡አለው፦ስለ፡ባሪያኽና፡ስለ፡ብላቴናው፡አትዘን፤ሳራም፡የምትነግ ርኽን፡ቃል፡ዅሉ፡ስማ፤በይሥሐቅ፡ዘር፡ይጠራልኻልና።
®ለአብርሃም እግዚአብሔር ቃል ኪዳን እንደገባለት እና ተስፋ እንደሰጠው እናይ አለን በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስ የይስሐቅ ዘር ነውና ስለዚህም ብርሃን ዓለም ጳውሎስ እንድህ በማለት ይነግረናል ይሄ የስፋ ቃል እንደተፈጸመ ገላ 3:16፤ለአብርሃምና፡ለዘሩም፡የተስፋው፡ቃል፡ተነገረ።ስለ፡ብዙዎች፡እንደሚነገር፦ለዘሮቹም፡አይልም፤ስለ፡አንድ ፡እንደሚነገር፡ግን፦ለዘርኽም፡ይላል፥ርሱም፡ክርስቶስ። በማለት ለአብርሃም የገባለት ቃል ኪዳን በይስሐቅ ዘር የተባለው ክስርቶስ እንደው ስለ ብዙዎች እንደሚነገር ለዘሮቹም አይልም ስለ አንድ እንደሚነገር ግን ለዘርኽም ይላል ርሱም ክርስቶስ ነው በማለት አሰረው እንጅ። መናፍቁ አይሕን ለአብርሃም የገባለት ቃል ኪዳን ክርስቶስ እንደው እና በክርስቶስ እንደተፈጸመ
▶️ዘፍ 3:22፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡አለ፦እንሆ፥አዳም፡መልካምንና፡ክፉን፡ለማወቅ፡ከእኛ፡እንደ፡አንዱ ፡ኾነ
®እግዚአብሔር እንግድህ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ኾነ አለ እንጅ እንደ ሱራፌል እና ኪሩቤል አላለም እነሱ ፍጡር ናቸውና ነገር ግን ከእኛ እንዴ አንዱ ሆነ አለ እንጅ የአዳም እንደ እግዚአብሔር መኾን ምንድነው የዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ካልሆነ በቀር በዚህም ቃል ሥጋን ተዋሕዶ የአዳምን ሥጋ አምላክ እንዳደረገው ታወቀ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን አልነሣም የምትሉ እፈሩ
መዝ 131:11፤እግዚአብሔር፡ለዳዊት፡በእውነት፡ማለ፥አይጸጸትምም፥እንዲህ፡ብሎ፦ከሆድኽ፡ፍሬ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡አስቀምጣለኹ።
®የሆድ ፍሬ የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ የሥጋን ዘርን እንደሆነ በብዙ ጥቅሶች ማየት እንችላለን ዘዳ 28:53፤ጠላቶችኽም፡ከበ፟ው፡ባስጨነቁኽና፡መከራ፡ባሳዩኽ፡ጊዜ፡አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡የሚሰጥኽን፡ #የሆድኽን፡ፍሬ ፡የወንዶችና፡የሴቶች፡ልጆችኽን፡ሥጋ፡ትበላለኽ። እዚህ ጋ እንደምናዬው የሆድ ፍሬ የተባሉት የሥጋ ልጆቹን እንደሆነ ይነግረናል እንድሁም ዳዊት በመዝሙሩ እንድህ ይለናል መዝ 127:3፤እንሆ፥ልጆች፡የእግዚአብሔር፡ስጦታ፡ናቸው፥ #የሆድም፡ፍሬ፡የርሱ፡ዋጋ፡ነው።
4፤በኀያል፡እጅ፡እንዳሉ፡ፍላጻዎች፥የጐልማስነት፡ልጆች፡እንዲሁ፡ናቸው። በማለት ዳዊት ልጆች የእግዚአብሔር እንደሆኑ የሆድ ፍሬ የሆኑ ልጆች የርሱ ዋጋ እንደሆኑ ይነግረናል ኢሳያስም በትንቢቱ እንድህ በማለት ጽፏል ት.ኢሳ 48:19፤ዘርኽም፡እንደ፡አሸዋ፡ #የሆድኽም፡ትውልድ፡እንደምድር፡ትቢያ፡በኾነ፡ነበር፥ስሙም፡ከፊቴ፡ባልጠፋና፡
ባልፈረሰ፡ነበር። እንግድህ የሆድህ ትውልድ የተባሉት ልጆች እንደሆኑ እርግጥ ነው እንግድህ የሆድ ፍሬ የተባሉት የሥጋ ዘር እንደሆኑ ካየን ከላይ በመዝሙር ከሆድኽ፡ፍሬ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡አስቀምጣለኹ።የተባለው ስለኢየሱስ ክርስቶስ እንደው የታወቀ ነው ስለዚህ ኢየሱስ የዳዊት የሆዱ ፍሬ መሆኑ ታወቀ ይኸውም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከዳዊት ዘር መሆኑ ታወቀ
እንደሁም በዘፍጥረት መጽሐፍ እንድህ የሚል ቃል አለ ዘፍ 30:1-2፤ራሔልም፡ለያዕቆብ፡ልጆችን፡እንዳልወለደች፡ባየች፡ጊዜ፡በእኅቷ፡ቀናችባት፤ያዕቆብንም፦ልጅ ፡ስጠኝ፤ይህስ፡ካልኾነ፡እሞታለኹ፡አለችው።፤ያዕቆብም፡ ራሔልን፡ተቈጥቶ፦በእውኑ፡እኔ፡ #የሆድን፡ፍሬ፡በነሣሽ፡በእግዚአብሔር፡ቦታ፡ነኝን ፧አላት።3፤ርሷም፡ባሪያዬ፡ባላ ፥እንሆ ፥አለች ፤ድረስባት፤በእኔም፡ጭን፡ላይ፡ትውለድ፥የርሷም፡ልጆች፡ለ እኔ፡ደግሞ፡ይኹኑልኝ፡አለች። እንግድህ ተወዳጆች ሆይ ያዕቆብ ራሔልን ተቆጥቶ በእውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሁ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን በማለት የተናገው ስለሥጋ ልጆች አይደለምን የሆድ ፍሬ በማለት የተናገረው ስለዚህ መናፍቁ እፈር እና ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሥጋን እንደነሣ ተቀበል የዳዊት የሆዱ ፍሬ እንደው የድንግል ማርያምም የማህጸኗ ፍሬ እንደው ተቀበል ሉቃ 1:42፤በታላቅ፡ድምፅም፡ጮኻ፡እንዲህ፡አለች፦አንቺ፡ከሴቶች፡መካከል፡የተባረክሽ፡ነሽ፥የማሕፀንሽም፡ፍሬ፡
የተባረከ፡ነው። በማለት ቅድስት ኤልሳቤጥ የማሕፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው እንዳለቻት እይ ለዚያውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ እንደው እወቅ መናፍቁ እንግድህ ፍሬ የሚለው የሥጋን ዘር እንደው ከላይ ብዙ መረጃ አቀረብንልህ እንግድህ የማሕጸን ፍሬ መሆን ምንድነው ሥጋዋ ካልሆነ የማሕጸኗ ፍሬ ስለዚኽም ኢየሱስ የማሕጸኗ ፍሬ እንደሆነ ሥጋን ከሷ እንደነሳ ታወቀ
*⃣ክፍል ሁለት ይቀጥላል ሼር አድርጉ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን ⁉️
*⃣ክፍል ሁለት
▶️ ዕብ 7:14፤ጌታችን፡ከይሁዳ፡ነገድ፡እንደ፡ወጣ፡የተገለጠ፡ነውና፥ስለዚህም፡ነገድ፡ሙሴ፡ምንም፡እንኳ፡ስለ፡ክህነት፡አልተናገረም።
®ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ሥጋን ከድንግል ካልነሰ በጠንካራ ቃላት ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነው ማለት ለምን አስፈለገው ነገድ የሚቆጠረው በሥጋ ዘር እንደው ይታወቃል ጳውሎስ ስለክህነት እየተናገረ ነው ሙሴ ክህነት ከሌዌ ነገድ እንደሆነ ተናገረ እንጅ ስለይሁዳ ነገድ አልተናገረም የይሁዳ ነገድ በንግሥናው ነው እንጅ የሚታወቁት በክህነት አልተሰጣቸው ለዚህ አገልግሎት የተለዩት የሌዊ ነገድ ናቸው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ዘዳ 10:8፤በዚያን፡ጊዜ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ይሸከም፡ዘንድ፥ርሱንም፡ለማገልገል፡በእግዚአብሔር፡
ፊት፡ይቆም፡ዘንድ፥በስሙም፡ይባርክ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የሌዊን፡ነገድ፡ለየ።
እንድሁም ክህነት ለሌዊ ነገድ ርስት ሁኖ የተሰጠ ነው ዘኁ 18:22-24፤ከዚህም፡በዃላ፡ኀጢአትን፡እንዳይሸከሙ፡እንዳይሞቱም፥የእስራኤል፡ልጆች፡ወደመገናኛው፡ድንኳን፡አይቅረቡ።ሌዋውያን፡ግን፡የመገናኛውን፡ድንኳን፡አገልግሎት፡ይሥሩ፥እነርሱም፡ኀጢአታቸውን፡ይሸከማሉ፤ለልጅ ለእግዚአብሔር፡የማንሣት፡ቍርባን፡የሚያቀርቡትን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ዓሥራት፡ለሌዋውያን፡ #ርስት፡አድርጌ፡ሰጥቻለኹ በማለት ይናገራል ታድያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የይሁዳ ነገድ ሲሆን ካህን እንደሆነ ጻውሎስ ይነግረናል ርስት ደግሞ የሚጸናው በአባታ በኩል ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ዘኁ 36:12፤ከዮሴፍ፡ልጅ፡ከምናሴ፡ልጆች፡ወገኖች፡ባሎቻቸውን፡አገቡ፥ርስታቸውም፡በአባታቸው፡ነገድ፡ጸና። ስለዚህ ድንግል ማርያም በአባቷ በኩል ከይሁዳ ነገድ ስለሆነች ርስትም የሚጸናው በአባታቸው በኩል ስለሆነ ምን እንኳን በእናቷ የሌዊ ወገን ብትሆነም ከላይ ዮሴፍ ልጅ የምናሴ ልጅ ታጋብተው ርስቱ በአባታቸው እንደጠና የሌዊ ወገን የሆነችው የድንግል ማርያም እናት ሐና ከይሁዳ ነገድ ከሆነው ኢያቄም ብትጋባም የድንግል ማርያም ርስት የሚጸናው በአባቷ በኩል ስለሆነ ከይሁዳ ነገድ ነች ርስቷ ስለዚህ ክህነት ደግሞ ከሌዌ ነገድ ነው ጳውሎስ እንደሚል ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ነገድ ቢሆንም ዕብ 7:12፤ክህነቱ፡ሲለወጥ፥ሕጉ፡ደግሞ፡ሊለወጥ፡የግድ፡ነውና። ክህነቱ ከይሁዳ ነግድ በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ ነገረን እራሳቸውን only Jesus ወይም የሐዋሪያት ተከታይ ነን ብለው የሚጠሩት ሊያፍሩ ይገባል ነገድ በሥጋ ካልሆነ በሌላ ሊቆጠር አይችልምና በሥጋ ካልሆነ በምንም ታምር ከይሁዳ ነገድ ገብቶ እንደማይቆጠር የታወቀ ነው
በየሐንስ ራዕይም እንድህ በማለት ይናገራል ራዕ 5:5፤ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ ፤እንሆ፥ #ከይሁዳ#ነገድ፡የኾነው፡አንበሳ፡ርሱም፡ #የዳዊት፡ሥር፡መጽሐፉን፡ይዘረጋ፡ዘንድ፡ሰባቱንም፡ማኅተም፡ይፈታ፡ዘንድ፡ድል፡ነሥቷል፡አለኝ። በማለት መጽሐፍ ቅዱስ በሰፊው የዳዊት ዘር እንደሆነ ከይሁዳ ነገድ ገብቶ እንደተቆጠረ ይነግረናል መናፍቃን እፈሩ
▶️ ሐዋ 2:29 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ #ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። 30 ነቢይ ስለ ሆነ፥ #ከወገቡም_ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ 31 ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ።
®ጴጥሮስ እንግድህ ኢየሱስን የወገቡም ፍሬ ይለዋል በክፍል አንድ በመዝሙር 131 ላይ የሆድ ፍሬ እንደተባለ አይተናል ያንነ ጴጥሮስ የወገብ ፍሬ ብሎት እናይ አለን በመጽሐፍ ቅዱስ የወገብ ፍሬም የሆድ ፍሬም አንድ ናቸው ሁለቱም ለሥጋ ዘር ነው የዋሉት የሆድ ፍሬ ለምን እንደዋለ አይተናል አሁን ደግሞ የወገብ ፍሬ የሚለውን እንይ መሳ 8:30፤ለጌዴዎንም፡ብዙ፡ሚስቶች፡ነበሩትና፡ከወገቡ፡የወጡ፡ሰባ፡ልጆች፡ነበሩት።በማለት ይናገራል እንድሀም
2ኛ ዜና 32:21፤እግዚአብሔርም፡ጽኑዓን፡ኀያላኑንና፡መሳፍንቱን፡አለቃዎቹንም፡ከአሶር፡ንጉሥ፡ሰፈር፡እንዲያጠፋ፡መልአኩን፡ሰደደ።የአሶርም፡ንጉሥ፡ዐፍሮ፡ወደ፡አገሩ፡ተመለሰ።ወደአምላኩም፡ቤት፡በገባ፡ጊዜ፡ከወገቡ፡የወጡት፡ ልጆቹ፡በዚያ፡በሰይፍ፡ገደሉት።እንድሁም 1ኛ ነገ 8:18፤እግዚአብሔርም፡አባቴን፡ዳዊትን፦ለስሜ፡ቤት፡ትሠራ፡ዘንድ፡በልብኽ፡ዐስበኻልና፥ይህን፡በልብኽ፡
ማሰብኽ፡መልካም፡አደረግኽ።
19፤ነገር፡ግን፥ከወገብኽ፡የሚወጣው፡ልጅኽ፡ርሱ፡ለስሜ፡ቤት፡ይሠራል፡እንጂ፡ቤት፡የምትሠራልኝ፡
አንተ፡አይደለኽም፡አለው።በማለት ይናገራል ምንም እንኳን ፍጻሜው ለክርስቶስ ቢሆንም ጅማሬው ለሰለሞን ነው ሰለሞን ለዳዊት የወገቡ ፍሬ ነውና
እንድሁም ዕብ 7:5፤ከሌዊ፡ልጆችም፡ክህነትን፡የሚቀበሉት፡ከሕዝቡ፡ማለት፡ከወንድሞቻቸው ፥እነርሱ፡ምንም፡ከአብርሃም፡ወገብ፡ ቢወጡ፥ከነርሱ፡ዓሥራትን፡በሕግ፡እንዲያስወጡ፡ትእዛዝ፡አላቸው፤ በማለት የሌዊ ልጆች ከአብርሃም ወገብ የውጡ ተብለዋል የወገብ ፍሬ የሚለው የሥጋ ዘርን እንደው በዚህ ታወቀ መጽሐፍ ቅዱስም በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለመወለዱ እንድህ በማልት ይናገራል " ይህም ወንጌል #በሥጋ #ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 1:3-4) በምን ነው አለ ከዳዊት ዘር የተወለደው በሥጋ ለዚያም እኮ ነው ዳዊት ከይሁዳ ነገድ ነውና ኢየሱስ ክርስቶስም ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የተገለጠ ነው የተባለው እርሱ እራሱ ጌታም "እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ "በማለት የሚናገረው እርሱ እራሱ ጌታ እራሱን የሰው ልጅ በማለት ብዙ ግዜ ጠርቷል
▶️" እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም #ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።"
(ወደ ዕብራውያን 2:14-15)
® ጳውሎስ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ ማለት ለምን አስፈለገው ከየት ነው ሥጋና ደም የምንካፈለው በሥጋና በድም የምንካፈለው ምንድነው ብለን መጠየቅ ይኖርብናል በሥጋና በደም የምንካፈለው ምንድነው ስንል ሞት ነው እንዴት ካላች ዘፍ 2:17፤ነገር፡ግን፥መልካምንና፡ክፉን፡ከሚያስታውቀው፡ዛፍ፡አትብላ፤ከርሱ፡በበላኽ፡ቀን፡ሞትን፡ት ሞታለኽና። ብሎ ለአዳም አዞት ነበር ስለዚህ እኛ የምንካፈለው ከየት ነው ከሥጋ ነው እግዚአብሔር አድስ ሥጋ አይፈጥርልንም ይሄንም ሔዋንን መመልከት እንችላለን ዘፍ 2:21-23፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡በአዳም፡ከባድ፡እንቅልፍን፡ጣለበት፥አንቀላፋም፤ከጐኑም፡አንዲት፡ ዐጥንትን፡ወስዶ፡ስፍራውን፡በሥጋ፡ዘጋው። ፤እግዚአብሔር፡አምላክም፡ከአዳም፡የወሰዳትን፡ዐጥንት፡ሴት፡አድርጎ፡ሠራት፤ወደ፡አዳምም፡አ መጣት።፤አዳምም፡አለ፦ይህች፡ዐጥንት፡ከዐጥንቴ፡ናት፥ሥጋም፡ከሥጋዬ፡ናት፤ርሷ፡ከወንድ፡ተገኝታለች ና፡ሴት፡ትባል። እንግድህ ለሔዋን አድስ ሥጋ እንዳላስፈለጋት አድስ አጥንት አድስ እስትንፋስ እፍ እንዳላለባት በዚህ ታወቀ ስለዚህ እኛም እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ባለው ቃል መሠረት ይሄን ሥጋ ስለሆን የምንካፈለው ይሄ ሥጋ ደግሞ ሞት የተፈረደበት ነው ስለዚህ ስለዚህ፥ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥በሚስቱም፡ይጣበቃል፤ኹለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡ይኾናሉ እንዳለች ኦሪት ልጆቹን ከመውለድ በቀር የባልና የሚስት ሥጋ አንድ መኾን ምንድን ነው። የወንድ ባ
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
ህርይ ከእርሷ የመዋለጃ ዘር ጋራ ተቀላቅሎ በሴቲቱ ማሕፀን ውስጥ በሚፀነስ የዘር ጠብታ ከጭኑ ይፈስሳል ። በእግዚአብሔርም ፍቃድ ሕፃን ይሆናል። በመሠራት አይደለም በሕይወት እስትንፋስም እፍታ አይደለም በአዳም ፊት ላይ እፍ የተባለ የሕይወት እስትንፋስ ሰውን በልቦና ከእንስሳት የሰው ልጅ ወደመኾን የሚያመጣው ሰው የመኾን መንፈስ ነው ። እርሱም በተጠመቀውም ባልተጠመቀውም ዘንድ ይገኛል ። ከሰው ልጅ ባህርይ ጋር ተዋህዷልና። በኖኅም ጊዜ እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙላት አለ። ስለዚህም ቃየል ሲወለድ በእጅ መሠራት የሕይወት እስትንፋስን መቀበል ተቋርጧል የአባቱና የእናቱ የሕይወት እድትንፋስ በቅቶታልና። ስለዚህም የጥበበኞች ጥበበኛ እግዚአብሔር አንዱ ከአንዱ የተለየ እንዳይኾን የሔዋንን ባሕርይ ከአዳም ባሕርይ ፈጠረ። ኹለቱም አንድ ሥጋ ይኾናሉ የተባለውም በልጆቻቸው ተፈጸመ። ከእንግድህ ልጆቻቸው በሥጋቸው የአባታቸው በነፍሳቸው የእናታቸው ልጆች አይባሉም። ዳግመኛም በሥጋቸው የእናታቸው በነፍሳቸው የአባታቸው አይባሉም ። የኹላቸው ሥጋና ደም ዐጥንትና ጅማቶች ነፍስና የሕይወት እስትንፋስ ተዋህዶ ወንድም ቢኾን ሴትም ብትኾን እግዚአብሔር በአደለው ገንዘብ አንድ ሕፃን ይኾናልና።በማለት ሊቁ ቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ ያስረዳናል ስለዚህ በዚህ መሠረት እኛም ከእናት እና ከአባታችን ሞት የትፈረደበትን ሥጋ ስለምንካፈል ጌታ ኢየሱስም ይሄን ሥጋ ተካፍሎ ሞት በተፈረደበት ሥጋ ሞትን በሞት እንዲሽር የእኛን ሥጋ ተካፈለ ባይካፈል ኑሮ በሞት ላይ ስልጣን ያለው ዲያብሎስ ምን ብሎ ይከስ ነበር ይሄን ሥጋ ሞት ፈርደኸበት የለ ሀሰተኛ ነህ ቃልህን ታጥፋለህ በማለት ይከሰው ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር ቃሉን አያጥፍም ቃሌ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፉ ይቀላል እግዚአብሔር ሰው አይደለም ሀሰትን የሚናገር እንዳለ ጌታ ኢየሱስ ይሄን ሥጋችን ተካፍሎ በዚሁ ሥጋ በመሞት በሞት ላይ ሥልጣን ያለው ዲያቢሎስ ውጥ ሊያስቀር ሲል በመለኮታዊ ኃይሉ ሲያቃጥለው ተፋው ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም ዲያብሎስም የሚከስብት ምክንያት አጣ ሞት ፈርደህበታል ይሄን ሥጋ እንዳይል ይዞ ማስቀረት አቃተህ እንጅ ትቸልህ አልነበር ይለዋል። ጌታ ከድንግል ማርያም ሰው በኾነ ግዜ ከአዳም መፈጠር ጀምሮ ከአባቶች ባሕርይ ከመጣ በእናቱም ላይ ካለው በቀር ሌላ የሕይወት እስትንፋስ ለራሱ አልተዋሐደም። ምድራዊ አባት ስለሌለውም የሰውነት ባሕርይ አልጎደለውም ። ብቻውን ከሴት በሥጋ በነፍስ በዕጥንትና በደም በጠጉርና በጅማቶች በሕይወት እስትንፋስም ፍጹም ያለመጎደልና ያለጭማሪ ፍጹም ሰው ኾነ። እንጂ ። በአርአያና በመልክ በብርሃንና በጸዳል በክብርና በሥልጣን በመቻልና በማድረግ ከአባቱ ያላነሰ ከወላጁም ያልበለጠ እንደኾነ እንዲሁ በመብላትና በመጠጣት በመራብና በመጥገብ በደስታና በኅዘን በድካምና በመውዛት በመታከትና በሕመም በሰውነት ከኛ ያነሰም የበለጠም አይደለም ።ከብቻዋ ከኃጢአትም በቀር የሰው ልጆች ሕግጋት አልቀሩትም ስለዚህም ብርሃን ዓለም ጳውሎስ በሁሉ ነገር እኛን ሊመስል ተገባው አለ እንድሁም “ነገር ግን የባሪያን መልክ #ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥”— ፊልጵስዩስ 2፥7“የአብርሃምን ዘር #ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።”
— ዕብራውያን 2፥16 በማለት ይናገራል
ስለዚህም ከእርሱ ጋር አንድ አካል የሆንን የክርስቶስ ብልቶች ስለሆንን የክርስቶስ አካል ደግሞ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳ ስለሆነ ሞት ውጦ ሊያስቀረን አይችልም ወንድሞች ሆይ ጌታ ኢየሱስ ሰው መሆን ያስፈለው ሁሉም በሞት ባርነት ተይዞ ስለነበር እግዚአብሔር ደግሞ ቃሉን አያጥፍም እና ያ ሞት የትፈረደበት ሥጋ ሞትን ድል አድርጎ የሚነሳበትን መንገድ ፈለገ ሲፈልግም የራሱ ክንድ መድኃኒት አመጣለት እንደተባለ ለዚያ ሥጋ መለኮት እንድዋሀደው እራሱ ቃል ሥጋን ተዋህዶ ያ ሥጋ ሞትን ድል አድርጎ በመነሣት ለእኛ ሕይወት ሰጠን ከእርሱ ጋር አንድ አካል በማድረግ እኛም የተጠመቅን ሥጋወ ደሙን የወሰድን በእርሱ በሥጋው በኩል ከእርሱ ጋር አንድ አካል ስለሆንን መግባት ሆነልን።
*⃣ክፍል ሦስት ይቀጥላል

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
➡️ ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን ⁉️⬅️
*⃣ክፍል ሦስት
በክፍል ሁለት ሥጋን መንሣቱ ግደታ እንደው ሔዋን ከአዳም ለመገኘት ሴት እንዳላስፈለገ ሁሉ የኢየሱስም ከድንግል ማርያም ለመገኘት ወንድ እንዳላስፈለገ አይተናል የሔዋን ከአዳም መገኘት ለአዳም አጥንት እንዳልጎደለው ሕመምም እንዳልተሰማ እንዴት እንደሆነም መመርመር እንደማይቻል ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስም ከድንግል ሥጋና ነፍን ነስቶ እንዴት ሰው እንደሆነ መመርመር አይቻለንም ይሄ ድንቅ ሥራ ነውና እያዩ ከመደነቅ እየሰሙ ከመገረም ውጭ ምንም ማለት አይቻልም መጽሐፍ እንደሚል ዕባ 1:5፤እናንተ፡የምትንቁ፡ሆይ፥አንድ፡ቢተርክላችኹ፡ስንኳ፡የማታምኑትን፡ሥራ፡በዘመናችኹ፡እሠራለኹና፡እዩ፥ተመልከቱ፥ተደነቁ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉ ነገር ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው እንደተባለ የሔዋንን መርገም ያርቅላት ዘንድ በማሕፀን አደረ እንደ ሕጻናትም የእናቱን ጡት ለመጥባት አፉን ከፈተ በማዘያም ታዘለ በሁሉ ነገር እኛን መሰለን ከኃጢያት በቀር።

▶️ማቴ 22:41-46፤ፈሪሳውያንም፡ተሰብስበው፡ሳሉ፥ኢየሱስ፦ስለ፡ክርስቶስ፡ምን፡ይመስላችዃል ፧የማንስ፡ልጅ፡ነው፧ብሎ፡ጠየቃቸው፦ የዳዊት፡ልጅ፡ነው፡አሉት።ርሱም፦እንኪያስ፡ዳዊት፦ጌታ፡ጌታዬን፦ጠላቶችኽን፡የእግርኽ፡መረገጫ እስካደርግልኽ ፡ድረስ፡በቀኜ፡ተቀመጥ፡አለው፡ሲል፡እንዴት፡በመንፈስ፡ጌታ፡ብሎ፡ይጠራዋል፧፤ዳዊትስ፡ጌታ፡ብሎ፡ከጠራው፥እንዴት፡ልጁች ይኾናል አላቸው።አንድም፡ቃል፡ስንኳ፡ይመልስለት፡ዘንድ፡የተቻለው፡የለም፥
®ስለዚህ የጌታን ቃል ምን እንላለን ድንግል ማርያምን ከዳዊት ወገን እንደተወለደች አውቀናታልና እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ነው ብሎ ተናግሮ የለምን ዳግመኛም የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጥ ለዚያ ሰው ወዮለት አለ እንደገናም የሰው ልጅስ እንደተጻፈ ይሔዳል አለ ኹለተኛም ስለዕረገቱ የሰውን ልጅ ቀድሞ ወደነበረበት ሲያርግ ታዩታላችሁ አለ ዳግመኛም ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም ። ከሰማይ ላልወረደ ለሥጋ የመለኮትን መውረድ ሲቆጥር እይ ። የመለኮት መውረድ ለሰውነት እንደተቆጠረ እንዲሁ መለኮት በሥጋ መከራዎችን የማይነካ ሲኾን የትስብዕት የሕማማቱ ቁጥር ለመለኮት ተቆጠረለት ። ትስብእት ግን በሰማይ አልተቀመጠም ነበር። ከመለኮት ጋር ያዛምዳት ዘንድ ይኸን ተናገረ እንጂ።(ቅዱስ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

በዚህም ቃል እራሱ ወደ ሥጋነት የተለወጠ ሳይሆን ቃል ከድንግል ማርያም ሥጋን ነስቶ እንደተዋሐደ ታወቀ።

ለፈሪሳውያን ዳዊት እራሱ ጌታዬ አለው እንግዲህ እንዴት ልጁ ይሆናል ያላቸው ግን መድኃኒታችን በመለኮት መዋሐድ ላማረ አምልኮ በአንድ አካል ኅብር መልክዕ እንጂ በሁለት ጠባይ እንዳያስቡት አንድ ትኾን ዘንድ ትስብእትን ከፍ ሲያደርጋት ነው እንጂ ፈሪሳውያንስ ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ይሉታል። ያለመለኮት መዋሐድ የተበተነ ሰውነት ያስተምራሉ የእግዚአብሔር ልጅ ከዳዊት ሴት ልጅ ሰው ኾኖ ተወልዶ የዳዊት ልጅ እንደሚባል አያምኑም ።ስለዚህ የዮሴፍ ልጅ አስመስለውታልና። ከወንድ ዘር እንደተወለደ እንዳያስቡት በቃሉ ጎራዴነት የአሳባቸውን ሥር ቆረጠ። እኛ እናቱን እና አባቱን የምናውቃቸውን እንግዲህ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል ብለዋልና። በዚህም ቄ ኹለተኛ ዳዊት ራሱ ጌታዬ አለው እንግድህ እንዴት ልጁ ይሆናል ባለ ጊዜ የልባቸውን ሸለፍት ገረዘ ከዳዊት ሴት ልጅ የነሣውን ሥጋ ግን በአንድ አካል ካለ መለኮት ጋራ አዋሀዳት እንዳትለይ እግዚአብሔርን ወደመኾን ከፍ አደረጋት ። ሰውነቱን ላየ የአባቱን መለኮት እንዳየ ቆጥሮለታልና። በዚህም ቃል ጎራዴነት ከነቢያት አንዱ ነው ያለውን የንስጥሮስን ምላስ ቆረጠ።በዚህም ቃል ስለትነት ከተዋሐደ በኃላ ሰውነቱ ከመለኮት ያንሳል ያለ የልዮንን ምላስ ቆረጠ። በዚህም ቃል ሰይፍነት መለኮትና ሰውነት በሁለት መንገድ ሥርዓት ናቸው ለመለኮት የሚገባውን መለኮት ሠራ ለሥጋም የሚገባው ሥጋን አደረገ ያሉ የኬልቄዶንን ማኅበርተኞች ምላሳቸውን ቆረጠ። በዚህ ቃል የመድኃኒታችን የመለኮትና የሰውነት መልክ ኹለት ነው ያለ የፍልብያኖስን ማላስ ቆረጠ።(ሊቁ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

በዚህም ቃል ቃል ከሥጋ ጋር ተዋህዶ የመለኮትን ቅድምና ቆጥሮ ለሥጋ የሰው ልጅ ቀድሞም እንደነበር ተናገረ የእግዚአብሔር ልጅም ቀድሞ እንደነበረ ቃል ሥጋን እንደተዋሀደ ታወቀ

▶️ ዮሐ 4:9-10፤ስለዚህ፥ሳምራዊቲቱ፦አንተ፡የይሁዳ፡ሰው፡ስትኾን፡ሳምራዊት፡ሴት፡ከምኾን፡ከእኔ፡መጠጥ፡እንዴት፡ትለምናለኽ፧አለችው፤አይሁድ፡ከሳምራውያን፡ጋራ፡አይተባበሩም፡ነበርና።፤ኢየሱስ፡መልሶ ፦ የእግዚአብሔርን፡ስጦታና፦ውሃ፡አጠጪኝ፡የሚልሽ፡ማን፡መኾኑንስ፡ብታውቂ፥አንቺ፡ትለምኚው፡ነበርሽ፡የሕይወትም፡ውሃ፡ይሰጥሽ፡ነበር፡አላት።

®የሰማያዊ መለኮት ንግግር ከምድራዊ ሰውነት አንደበት ወጣ በዚህም የማይታይ የአምላክ ባሕርይ ኃይል ዘወትር ከምትታይ የሰው ልጅ ባሕርይ ሰውነት እንደማይለይ ዐወቅን

▶️ሮሜ 9:4-5፤እነርሱ፡እስራኤላውያን፡ናቸውና፥ልጅነትና፡ክብር፡ኪዳንም፡የሕግም፡መሰጠት፡የመቅደስም፡ሥርዐት፡የተስፋውም ፡ቃላት፡ለእነርሱ፡ናቸውና፤አባቶችም፡ለእነርሱ፡ናቸውና #ከነርሱምም፡ክርስቶስ፡ #በሥጋ፡መጣ፥ርሱም፡ከዅሉ፡በላይ፡ኾኖ፡ለዘለዓለም፡የተባረከ፡አምላክ፡ነው፤አሜን።

®እንግድህ ክርስቶስ በሥጋ ካልሆነ በምንድነው ከነርሱ ጋር የተቆጠረው ከአባቶቻቸው በሥጋ እንደመጣ ተናገረ ለአባቾቻው ከነሱ እንደሚወለድ የነገራቸው የተስፋ ቃል እንደተፈጸመ ጳውሎስ ነገራቸው ከነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ በማለት ሥጋው ከሰው የተገኘ እንደው ተናገረ
▶️" ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን? አሉ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 7:42)

®በማለት እንደተናገሩ አታስተውሉምን እናንተ መናፍቃን ከዳዊት ዘር ሲሉት ተመልከቱ
ጳውሎስም ስለዚህ ሲናገር እንድህ በማለት ይናገራል
“በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤”— 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥8
ስለዚህ እናንተ የሰይጣን እስትንፋሶች እፈሩ እና ዝም በሉ

▶️1 ቆሮ 15:39፤ሥጋ፡ዅሉ፡አንድ፡አይደለም፥የሰው፡ሥጋ፡ግን፡አንድ፡ነው፥

®እናንተ ሰዎች ጳውሎስ ምን እንደሚል እየሰማችሁት ነው ሥጋ ኹሉ አንድ አይደለም የሰው ሥጋ ግን አንድ ነው እያላችሁ ነው ኢየሱስ ደግሞ እራሱን የሰው ልጅ ብሎ እንደጠራ እና ሰው እንደሆነ ብዙ መረጃ ሰጠናችሁ ታድያ ኢየሱስ ሰው አይደለም ልትሉት እንዴት ደፈራችሁ ስለዚህ እሱም ሰው መሆኑን ካመናችሁ የሰው ሥጋ አንድ ነው ስለዙህ ከእኛ ሥጋ ጋር ሥጋ አንድ እንደሆነ እምኑ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ ነው ስላችሁ ደግሞ ዕሩቅ ብዕሲ እንዳታደርጉት መለኮት የተዋሀደው ሥጋ እንጅ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል የመለኮት ሙላት በእርሱ በሰውነቱ ተገልጦ ይኖራልና።

▶️ ከእሴይ ሥር በትር ትወጣለች ከግንድም አበባ ይወጣል የሚል እንደተፃፈ ያሰበውን በማድረግ የሚከለክለው የለም ከኢያቄም አብራክ ተካፍላ በሐና ማህፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል ማርያም የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከስሩ መውጣት ምንድን ነው? የእመቤታችን ማርያም አባቷ ኢያቄም ከዕሴይ ዘር ነውና ዳግመኛም ከኢያቄም ሴት ልጅ የመለኮት ሰው መሆን በቀር የአበባ ከግንድ መውጣት ምንድን ነው?

በሰማያት ሥጋ ካለ ከእርሷ ሰው ሆኖ ይወለድ ዘንድስለምን በድንግል ማኅፀን አደረ፣ ከሥጋው ጋር በድንግል ማኅፀን አደረ ካላችሁ፣ የሥጋ በሥጋ ውስጥ ማደር ጥቅሙ ምንድን ነው? ቀድሞውንም ሥጋ ካለው የቀደመ ሥጋው በበቃው፤ ከድንግል ሥጋ መወለድ
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
ን ባልፈለገ
ነበር” ይላል፡፡ “እኛ ግን ‹የክርስቶስ ሥጋና ነፍሱ ከአዳም
ባሕርይ ብቻዋን ንጽሕት ድንግል (ከሆነች)፣ ማርያም
ከተባለች የገሊላ ሴት ያለ ወንድ ዘር የነሣው ነው›
እንላለን። (ሊቁ ቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📋 ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን ⁉️
*⃣ክፍል አራት
ክፍል 1,2,3 ያላነበባችሁ ቅድሚያ እሱን አንብቡ ከሁን በኃላ እነሱ ከሰማይ ነው ለማለት የሚያነሷቸውን ጥያቄ መመለስ እንጀምራለን

▶️ 1ቆሮ 15:47-48፤የፊተኛው፡ሰው፡ከመሬት፡መሬታዊ፡ነው፤ኹለተኛው፡ሰው፡ከሰማይ፡ነው።
፤መሬታዊው፡እንደ፡ኾነ፡መሬታውያን፡የኾኑት፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ናቸው፥ሰማያዊው፡እንደ፡ኾነ፡ሰማያውያን፡የኾኑት፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ናቸው።ለምን ኹለተኛው ሰው ከሰማይ ነው ተባለ?

🗒ክርስቶስ ከሰማይ ነው የሚባለው በእውነት አካሉ ስለተሠራበት ጉዳይ ሳይሆን ስለተሠራበት በጎነት ነው እዚያው ላይ መሬታዊ እንደሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንድሁ ናቸው ይላል ሰማያዊው እንደሆነ ሰማያውያን የኾኑት እንድሁ ናቸው ይላል እና እንደ እግዚአብሔር አምላክነቱም ቢሆን እንደአስፈላጊነቱ የአዳም አካል እንደነበረው የክርስቶስ ሰውነት ከአዳም የተገኘ ነው።
ክርስቶስ ሰማያዊ መባሉ እርሱ የሰማያዊያን ሕይወት ስለመራ እና ሁልግዜም ያለኃጢያት ነበር አዳም ለኃጢያት ተገዥ ስለሆነ ምድራዊ ተብሎ ይጠራል ። ክርስቶስ ከተፈጥሮ ተፈጥሮአዊ መንገድ በላይ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ሰማያዊ ኃይል ከድንግል ተፀንሶና ተወልዶ ሰማያዊ ተብሎ ተጠርቷል።
ክርስቶስ በመለኮታዊ እና ሰማያዊ ባሕርይው ምክንያት ሰማያዊ ተብሎ ተጠርቷል በተመሳሳይ መንገድ እርሱ የሰው ልጅ ተብሎ ተጠርቷል ማለትም ከሰማይ የወረደ ሰው።
ክርስቶስ ሰማያዊ ተብሎ የተጠራበት እርሱ ክቡር እና የማይጠፋ ነው ። ይህ ሰማያዊ ክብር ክርስቶስ ከተፀነሰበት ጊዜ አንስቶ በሰውነቱ ተዋህዶ ይኖራል ።አዳም የኃጢያት ሞት መሞትና የሚበሰብስ ስለሆነ ምድራዊ ተብሏል።
የመጀመሪያው ሰው የዚች ምድር ገዥ ኹኖ የተሾመ ነው ኹለተኛው ሰው ደግሞ የዚች ምድር ብቻ ገዥ አይደለም ከሰማይ በታች ከሰማይ በላይም ላሉት ለመላክት ለቅዱሳን እንድሁም በሰማያት ሁሉ ላሉት ፍጥረታት እንጂ ስለዚህ እሱ የምድርም የሰማይም ጌታ ስለሆነ ሰማያዊ ተባለ
ሁለተኛው ሰው ከሰማያት ከፍ ያለ ነው የመጀመርያው ሰው ኃጢያት በመሥራት ምድራዊ እንድንሆን ያደረገን ነው ሁለተኛው ከራሱ ጋር በማስታረቅ መንፈሳዊ እንድንሆን እና በሰማያዊ ሥፍራ እንድንቀመጥ ያደረገን ነው
ሁለተኛው ሰው እርሱም ክርስቶስ ከሰማይ ስለሆነ ሕይወትን ሰጭ መንፈስ ሆነ ምክንያቱም ከዚህ ባሕርይ ጋር የተዋሐደው መለኮታዊ ባሕርይ ስለሆነ እርሱ ከሰማይ ነው ስለዚህ እርሱ ሰማያዊ ተባለ።ማለትም ከሰማይ፡የሚመጣው፡ከዅሉ፡በላይ፡ነው።ዮሐ 3:31። ቢለዋ ከብረት ነው እንደሚባለው የመጀመሪያው ሰው ከምድር ነው ይላል ምክንያቱም ቢለዋ ከብረት ነው ቢለዋ የሆነው እናም አዳም የተፈጠረበት የመጀመሪያው ክፍል ምድር ስለሆነ ከምድር ነው ይባላል ። በዚህ መሠረት ክርስቶስ ሰው ተብሎ የተጠራው ከሰማይ ነው ሰውነቱን ከምድር ስለወሰደው ማለትም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም አካል ስለወሰደ ነገር ግን የሰውን ተፈጥሮ የተዋሐደው መለኮት ከክርስቶስ ሰውነት በፊት የነበረው ከሰማይ ነው ስለሆነም ልዪነቱ ግልጽ ነው ሁለተኛው ሰው እና የመጀመሪያው ሰው።
የመጀመሪያው ሰው ከመሬት እና ሟች ነው
1ቆሮ 15:22፤ዅሉ፡በአዳም፡እንደሚሞቱ፡እንዲሁ፡ዅሉ፡በክርስቶስ፡ደግሞ፡ሕያዋን፡ይኾናሉና።
ሁለተኛው ሰው ከሰማይ እና መንፈሳዊ እና የማይሞት ነው ስለሆነም ሁላችን የማንሞት እና መንፈሣዊ እንሆናለን
ሮሜ 6:5፤ሞቱንም፡በሚመስል፡ሞት፡ከርሱ፡ጋራ፡ከተባበርን፡ትንሣኤውን፡በሚመስል፡ትንሣኤ፡ደግሞ፡ከርሱ፡ጋራ፡እንተባበራለን፤
ሮሜ 8:29፤ልጁ፡በብዙ፡ወንድሞች፡መካከል፡በኵር፡ይኾን፡ዘንድ፥አስቀድሞ፡ያወቃቸው፡የልጁን፡መልክ፡እንዲመስሉ፡አስቀድሞ፡ደግሞ፡ወስኗልና፤

ሁለተኛው ሰው የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተግልጦ የሚኖር ነው።
ቆላ 2:9፤በርሱ፡የመለኮት፡ሙላት፡ዅሉ፡በሰውነት፡ተገልጦ፡ይኖራልና።እንድል
ይሄ የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተገልጦ መኖሩ
የሚጠፋ ስጋን ለበሰ ያንንም የሚጠፋ ሥጋ የማይጠፋ አደረገው ። የሚሞት ሥጋን ለበሰ ያንንም የሚሞት ሥጋ ከማይለወጥ
አኗኗር ሥጋ የተካከለ እንዲኾን የማይሞት አደረገው። ምድራዊ ሥጋን ለበሰ ያንንም ምድራዊ ሥጋ የእርሱ ከኾነ ልዕልና ጋራ የተካከለ እንዲሆን ሰማያዊ አደረገው ። ጒስቋላ ሥጋ የእርሱ ከኾነ ኃይል ጋራ የተካከለ ይኾን ዘንድ ለክብርና ለብርሃን አደለው። የሚታመም ሥጋን ለበሰ ያንንም የሚታመም ሥጋ ከማይታመም አኗኗር ጋራ የተካከለ እንድኾን የማይታመም አደረገው ። የተለየ እንዳይኾን በአንድነት አዋሀደው ።
አንተ ሞኝ የመለኮት ኃይልን አታቅም እንዴ እንኳን የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተገልጦ የሚኖርበት የሙሴ በትር እንኳን መለኮታዊ ኃይል ስላላት ባሕር አልከፈለችም እንዴ የኤልያስ ጨርቅስ ..ብዙ መጥቀስ ይቻላል ታድያ የኢየሱስ ሥጋ መለኮት የተዋሀደውን ሰማያዊ አይሆንም ብለህ ትከራከራለህ በውነት አፍህን ብዘጋው ምላስህን ብትቆርጠው ይሻልኃል።

ክርስቶስ ከሰማይ ነው መባሉ ግን አካሉ ስለተሠራበት ጉዳይ ሳይሆን ስለተሠራበት በጎነት ነው ከላይ እንደተባለው ከሰማይ መቶ የመለኮት ሙላት በክርስቶስ ሰውነት መኖሩ ሥጋውን ሰማያዊ አደረገው እሱ ሰማያዊ ሁኖ እኛ ሰማያዊ እንድንሆን አደረገን የአዳም ግን ከምድር የተገኘ ኃጢያት ምድራዊ እንድንሆን አደረገን በሱ ምክንያት።
ይቀጥላል....
ሼር ማድረግ አይርሱ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📋 ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን ⁉️
*⃣ክፍል አምስት
በባለፈው ክፍል ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ከሰምይ እንደተባለ ለምን ሰማያዊ እንደተባለ አይተናል እሱ ሰማያዊ ሁኖ እኛንም በሰማያዊ ሥፍራ እንዳስቀመጠን " በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:6-7) እንድል መጽሐፉ ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማያዊ ሥፍራ አስቀምጦናል ከዚህ ሥፍራ መወረድ መቀመጥም የእኛ ምርጫ ነው ብዚህ ሥፍራ ያልተቀመጡትንም እግዚአብሔር ይጣራል እሽ ብሎ ጥሪውን የተቀበለ በሰማያዊ ሥፍራ ከሰረጉ ይታደማል ስለዚህ ከእርሱ ጋር አንድ አካል የሆነ ሁሎ ሰማያዊ ነው። ዛሬ ደግሞ እንድ የሚያነሱትን ጥያቄ እናይ አለን

📃" የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።"
(ወደ ዕብራውያን 2:16) የሚለውን ስለ ሥጋ መያዝ አይናገርም ይላሉ
®ኧረ በድንብ ነው የሚናገረው እንደውም ይሄ ጥቅስ ብዙ ነገሮችን ያስረዳል ይሄ ጥቅስ የአብርሃም ዘር በማለቱ ከሕዝብ ወገን እንደው ያስረዳል ከአብርሃም ዘር ማለቱ የሰው ልጅ መባሉ የባሕርይ እንደው ያስረዳል ነፍስ እንደነሣ ያስረዳል ሥጋን ብቻ ነስቶ የተዋሐደ እንዳይመስላቸው ያስረዳል የእኛን ባሕርይ እንደተዋሐደ ከእኛ ልዩ የሆነ ባሕርየ መላእክትን እንዳልተዋሐደ የአብርሃም ዘርን እንጅ የያዘው የመላእክትን አይደለም በማለት አስረዳ።
የአብርሃም ዘር በማለቱ በፍቅር ገንዘብ እንዳደረገን አስረዳ በመዋሐድ አካላዊ ገንዘብ እንዳደረገን አስረዳ ወዳጄ ሆይ የሐዋሪያትን የጥበብን ብዛት አስተውል የክብራቸውን ብዛት የነገዳቸውን ደግነት ያስረዳ ዘንድ ዘርዐ አብርሃም አለ እንጅ በሁሉ ማለቱ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተፀንሶ ስለተወለደ በየጥቂቱ ስለአደገ መከራ ስለተቀበለ ስለሞቱ.. ነው ጌታ እኛን መምሰል እንደወደደ ጳውሎስ እንዳስረዳ እወቅ (ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ)
ከዘፍጥረት ጀምረን ብናይ የሰው ዘር ሰው እንጅ ሌላ አይደለም ለምሳሌ ብናይ
" አዳም ደግሞ ሚስቱን አወቀ፤ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም። ቃየን በገደለው በአቤል ፋንታ እግዚአብሔር ሌላ #ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:25) እንግድህ ሔዋን ሌላ ዘር ተክቶልኛል ያለችው ሰውን እንጅ ሌላ አይደለም እራሱ የአብርሃም ዘር ምን ማለት እንደው ለምን አናይም በመጽሐፍ ቅዱስ
" እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና። ይህችን ምድር #ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 12:7) እዚህ ጋ እንግድህ ለዘርህ የተባለው አብርሃም ሰዎች እንደው ግልጽ ነው
የተወሰኑትን ሁሉንም እንያቸው እስኪ
" የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 13:15)
እንድሁም " አብራምም። ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል አለ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 15:3) እንግድህ አብርሃም እራሱ ሲናገር ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም ማለቱ ልጅ አልሰጠኸኝም ማለቱ እንደው ግልጽ ነው

" በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና #ከአንተ በኋላ #ለዘርህ እሰጣለሁ፤ አምላክም እሆናቸዋለሁ። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 17:8)
" እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 17:9)
" በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 17:10) የአብርሃም ዘሮች እንግድህ ሰዎች ናቸው ሌላ ምንም አይደል
" ነዪ አባታቻንንም የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፥ ከአባታችንም #ዘር እናስቀር።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 19:32) ከአባታችን ዘር እናስቀር ማለታቸው ምን እንደው ግልጽ ነው መቼም
" እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይስሐቅ #ዘር ይጠራልሃልና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 21:12) በማለት የገባው ቃል ኪዳን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ ባለፈው አይተናል ይሄ ቃል እውን እንደሆነ
" የማንም ሰው #ዘር ከእርሱ ቢወጣ፥ ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።"
(ኦሪት ዘሌዋውያን 15:16) ሰው ዘር የተባሉት ሰዎች አይደሉም የሚል መቼም አይኖርም
" ቤትህም እግዚአብሔር ከዚህች ቈንጆ ከሚሰጥህ #ዘር ትዕማር ለይሁዳ እንደ ወለደችው እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን አሉት። "
(መጽሐፈ ሩት 4:12) እዚህም ዘር የተባለው ግልጽ ነው ማብራራት የሚያስፈልግ አይመስለኝም
" ዔሊም ሕልቃናንና ሚስቱን። ለእግዚአብሔር ስለ ተሳለችው ስጦታ ፋንታ ከዚህች ሴት እግዚአብሔር #ዘር ይስጥህ ብሎ ባረካቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ።"
(መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 2:20)ማየት ነው እንህድህ

"5-6 ባሪያዎቹ #የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ። "
(መዝሙረ ዳዊት 105:5-6) መጽሐፍ ቅዱስ እንግድህ የአብርሃም ዘር ያለው እዚህ ጋ ሰዎችን ነው የያዕቆብ ልጆች መቼም ሰው አይደሉም የሚል አይኖርም ።

" ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ #የአብርሃም ዘር ሆይ፥"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 41:8) የአብርሃም ዘር ሆይ የተባለው ያዕቆብ እንግድህ እንዴት ነው ሰው አይደለም ያዕቆብ የአብርሃም ዘር የሆነውስ በሥጋ አይደለምን

" #የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 7:15) ኤፍሬም ዘር የተባሉት ሰዎች እንደሆኑ የሰው ዘር ሰው እንደው እወቅ ወዳጄ።
" መምህር ሆይ፥ ሙሴ። የአንድ ሰው ወንድም ሚስቱን ትቶ ልጅ ሳያስቀር ቢሞት፥ ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ #ዘር ይተካ ብሎ ጻፈልን።"
(የማርቆስ ወንጌል 12:19)
" ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፤ ፊተኛውም ሚስት አግብቶ #ዘር ሳያስቀር ሞተ፤"
(የማርቆስ ወንጌል 12:20)
" ሁለተኛውም አገባት፥ #ዘርም ሳይተው ሞተ፤ ሦስተኛውም እንዲሁ፤"
(የማርቆስ ወንጌል 12:21)
" ሰባቱም አገቡአት፥ #ዘርም አላስቀሩም። ከሁሉም በኋላ ሴቲቱ ደግሞ ሞተች።"
(የማርቆስ ወንጌል 12:22) በነዚህ ጥቅስ እንግድህ ዘር ተብሎ የተጠራው ሁሉ የሥጋ ዘር እንደው ግልጽ ነው።

ለምን ጌታ ኢየሱስ እራሱ የአብርሃም ዘር ማለት ምን ማለት እንደው አይነግረንም
" እነርሱም መልሰው። #የአብርሃም ዘር ነን ለአንድም ስንኳ ከቶ ባሪያዎች አልሆንም፤ አንተ። አርነት ትወጣላችሁ እንዴት ትላለህ? አሉት።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:33)

" #የአብርሃም ዘር መሆናችሁንስ አውቃለሁ ነገር ግን ቃሌ በእናንተ አይኖርምና ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:37) እንግድህ ተወዳጆች ጌታ ኢየሱስ ከላይ ምን እንዳሉት እና እሱ ምን እንዳለ አያችሁ እንግድህ ጌታ ኢየሱስ የአብርሃም ዘር መሆናችሁን አቃለው ያለው ሰዎችን አይደለምን የአብርሃም ዘር የሆኑትስ በሥጋ አይደለምን? ወዳጄ ሆይ የአብርሃም ዘር የሚባሉት የሥጋ ዘር ነው ጌታ ኢየሱስም የአብርሃም ዘር ትብሏል ስለዚህ እሱማ በሥጋ የአብርሃም ዘር መሆኑን እወቅና።
ከሐዋሪያው ጳውሎስ ጋር ሁነህ እንድህ
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
በል
" ከዚህም #ሰው #ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።"
(የሐዋርያት ሥራ 13:23) ወዳጄ ከላይ የሰው ዘር ማለት ምን ማለት እንደው አየን አይደል ጳውሎስ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዳዊት ዘር እንደመጣ እየነገርኽ ነው ለምን አትቀበለውም
ሌላም ጳውሎስ እራሱን የአብርሃም ዘር እንደው በትናገረው ልጨርስ
" እንግዲህ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ። አይደለም እኔ ደግሞ እስራኤላዊና #ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 11:1) እንግድህ የአብርሃም ዘር ማለት ምን እንደው ብዙ ማስረጃ አቀረብንልህ ስለዚህ እመን እና ተቀበል ቃሉን ።

ይቀጥላል

ለመቀላቀል
@felgehaggnew

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
www.tg-me.com/felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📃ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን⁉️
*⃣ክፍል ስድስት

Only Jesus የሚባሉት ሰዎች ለሚያነሱት ጥያቄ ካቆምንበት እንቀጥላለን

" ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ "
"ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
"
(መጽሐፈ ኢዮብ 25:6)

ለእነዚህ ሰዎች መጀመሪያ መጠየቅ ያለብን የሰው ልጅ ትል ስለተባለ ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ ሊነሳ አይችልም ነው የሚሉት ። እና እነሱ እንድህ ካሉ ኢየሱስ የሰው ልጅ አልተባለም ወይ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል
" ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 4:4) ኢየሱስ ክርስቶስ ከሴት የተወለደ የሰው ልጅ ተብሏል ስለዚህ በእነሱ እረዳድ ከሄድን መጽሐፍ ቅዱስ ከሴት የተወለደ የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ አይደለም ሊሉን ነው ማለት ነው?: 🤣🤣🤣🤣

ብዙ ምንሳት እችል ነበር ግን ምን ማለት እንዴው እንይ ጥቅሱ እየተናገረ ያለው ሙሉ ምዕራፉን ብናዬው ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የማይባል እንደው መናገሩ ነው ከላይ ጀምሮ ስናነብ ጨረቃ እና ከዋክብት ጋር ያነጻጽራል ጨረቀና ከዋክብት ኃጢያት የሚሠሩ ሁነው አይደለም ነገር ግን ከእግዚአብሔር ንጽሕና ጋር ስታይ እዚህ ግባ እንደማይባል መናገሩ ነው።
እንደገናም ሰው ትል መባሉ ትል ደካማ አቅመ ቢስ ነች የሰው ልጅም እንድሁ ድሃ ነው ደካማ ነው አቅመ ቢስ ነው ይራባል.. እያለ ይቅጥላል በዚህ ምክንያት ሰው ትል ተብሏል እዚህ ትቅስ ላይ።
ሌላው የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ጸጋ ካረዳው በራሱ ደካማ ነው ስለዚህ የሰው ልጅ ትል ተብሏል ። የሰው ልጅ ጽድቅና ቅድስና ከእግዚአብሔር ጋር ሲወዳደር ምንም አይደለም ከዚህ አንጻር ትል ተብሏል።
ሲጀምር ትል የሚለው የሰው መግለጫ አይደለም ሁልግዜ ለምሳሌ ዳዊት እንድህ ይላል
" እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፤ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።"
(መዝሙረ ዳዊት 22:6) ዳዊት እንግድህ ሰው አይደለሁም ትል ነኝ ካለ ትል የሰው መግለጫ ሳይሆን የደካማነት መግለጫ ነው ማለት ነው

የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ደግሞ መለኮት የተዋሐደው ስለሆነ የሚበሰብሰው የማይበሰብስ ሆነ የሚሞተው የማይሞት ሆነ ምድራዊ ሰማያዊ ሆነ ደካማው ብርቱ ሆነ.. ብለን እንናገርለት አለን

" ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 6:51)

ሌላው የሚያነሱት ጥያቄ ከሰማይ የወረደ ለምን ተባለ ሥጋው ከሰማይ ካልወረደ ነው።
ለእነዚህ ሰዎች እኔም ጥያቄን በማንሳት እቀጥላለሁ
1⃣ " ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:13) ይላል ጌታ ኢየሱስ ይሄን የተናገረው ገና በምድር ሳለ ነው እንዴት እሱ በምድር ሳለ በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው አለ? ይሄን ይመልሱልን ምክንያቱም በእነሱ አስተሳሰብ የሰው ልጅ ሥጋ ነው ብለው ያምናሉ ስለዚህ ሥጋ ደግሞ በሰማይ አልነበረም እንዴት በሰማይ ተባለ ይመልሱልን እንደገናም የሰው ልጅ ከሰማይ ይወርዳል ወይ እንዴት ከሰማይ የወረደ የሰው ልጅ አለ?
2⃣ " እንግዲህ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደ ነበረበት ሲወጣ ብታዩ እንዴት ይሆናል?"
(የዮሐንስ ወንጌል 6:62) እዚህ ጋ እንግድህ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ አስቀድሞ ወደነበረበት ሲወጣ ይላቸዋል ስለዚህ የሰው ልጅ አስቀድሞ በሰማይ ነበር ወይ እንዴት አስቀድሞ ወደነበረበት አለ ?
እነዚህን መልሱልኝ
®እኔ መልሴን ላስቀምጥ ከሰማይ የወረደ መባሉ የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሁኖ ነው ። መለኮቱ እንጂ ሥጋው ከሰማይ አልወረደም ። መለኮቱ ነው ስልህ ደግሞ ለመለኮት ወረደ ወጣ የሚባልለት አይደለም በሥጋ መለኮት መገለጡ ወረደ ተብሎ ይነገርለታል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል የእርሱ የመለኮት ሙላት በሰውነቱ ተገልጦ ይኖራል እንደሚል ለምሳሌ በመጽሐፍ ቅዱስ እንድህ የሚል ቃል አለ " በሦስተኛው ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ይወርዳልና ለሦስተኛው ቀን ይዘጋጁ።"
(ኦሪት ዘጸአት 19:11) እዚህ ጋ እንግድህ እግዚአብሔር ይወርዳል ይላል ለእግዚአብሔር በሁሉ ቦታ ሙሉ ሲሆን መውጣት መውረድ አይነገርለትም ነገር ግን መገለጡ መውረድ ተብሎ ይነገራል ስለዚህ የኢየሱስ ሥጋ የመለኮት ሙላት ተገልጦበት የሚኖር ስለሆነ ከሰማይ የወረደ ይባልለታል። የመለኮት መውረድ ለሥጋ ተቆጠረ።
*⃣ይቀጥላል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር

@felgehaggnew
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
የእውነት ሚዛን(ቴቄል)
📃ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣምን⁉️ *⃣ክፍል ስድስት Only Jesus የሚባሉት ሰዎች ለሚያነሱት ጥያቄ ካቆምንበት እንቀጥላለን " ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ " "ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ! " (መጽሐፈ ኢዮብ 25:6) ለእነዚህ ሰዎች መጀመሪያ መጠየቅ ያለብን የሰው ልጅ ትል ስለተባለ ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ ሊነሳ አይችልም ነው የሚሉት ። እና እነሱ እንድህ ካሉ ኢየሱስ የሰው…
✍️ ኢየሰስ ከድንግል ማርያም ሥጋን አልነሳምን

ክፍል ሰባት
Only jesus የሚባሉት ከድንግል ማርያም ሥጋን አልነሳም ለሚሉት ዛሬን የሚያነሷቸውን ጥቅሶች እናያቸው አለን

" በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:2)

®ይህ ምዕራፍ ስለ ስለኢየሱስ ክርስቶስ መከራዎች የሚሞትበት መጨረሻ እና ከዚያ አስደናቂ ክንውን ለሰው ልጆች የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች ይተነብያል ። እንድሁም ሰው የተሰቃዬውን ኢየሱስን እንዴት እንዴተመለከተው ይገልጻል ፣መሲሑን እንዳልተቀበሉት ይገልጣል።
ገና ከቁጥር አንድ ሲጀምር የሰማንውን ነገር ማን አምኗል ብሎ ይጀምራል። መጽሐፍ እንደሚል
" የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1:11)
ዮሐንስ እንዳለ ኢሳያስም በትንቢቱ እንደተናገረ የመሲሑን መምጣት አላመኑም ነበር አልተቀበሉትም ነበር ኢሳያስም ያሰምንውን ማን አምኗል አለ ጌታ ኢየሱስም እንድህ አለ
" ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።"
(የማቴዎስ ወንጌል 23:37) ብሎ ተናገረ።
ከዚያም ኢሳያስ ይቀጥል እና የእግዚአብሔር ክንድ ለማን ተገልጧል ይለናል። እንግድህ ክንድ ለማን ተግልጧል ሲል ክንድ ከሰው ሳይለይ ከመሬት እቃ እንደሚያነሳ ሁሉ ጌታ ኢየሱስም ሰዎችን ከወደቁበት ለማንሳት ከአባቱ ሳይለይ መምጣቱን መናገር ነው። እና ኢሳያስ ለማን ተገልጧል ብሎ ሲናገር ለሰው ልጆችን ለማዳን መምጣቱን የሰው ልጆች ግን ይሄን አለማመናቸውን መናገር ነው። ይቀጥል እና ኢሳያስ እንድህ ይላል በፊቱ እንደቡቃያ ከደረቅ መሬት እንደሥርም አድጓል ይላል ። ከደረቅ መሬት መባሉም ደረቅ መሬት ዘር ቢዘሩበት በቃያ እንደማይስገኘው ሁሉ ሰዎቹም የጌታ መወለድ ቢያድተምሯቸው አይሰሙም ነበር አልተቀበሉትም እንዳለ መጽሐፍ ከላይ እንዳየንው ደረቅ መሬት የተባሉት ሰዎች ናቸው። አድጓል መባሉም በነሱ ዘንድ ትምህርቱ መስፋፋቱን መናገር ነው ።ይቀጥል መልክና ውበት የለውም ባዬንው ግዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም ይላል ይሄን ማለቱም ኢሳያስ ሰዎችን አደ ኢየሱስ ለመሳብ ስንሞክር በሰዎች ዘንድ ደስ የሚያሰኝ የሚማርክ ነገር አላገኘንም ሲል ነው ።እንጅ ምዕራፉ ሰዎች እንዳልተቀበሉት እና እንዴት እንደሚያገላቱት እያወራ ያለአውዱ ከድንግል ሥጋ አለመውሰዱን የሚናገር ነው ማለት የማይሆን ተረት ተረት ነው።ኢሳያስ ይቀጥል እና እንድህ ይለናል " የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 53:3)
ብሎ መከራን እንደተቀበለ ብዙ ስቃይ እንዳደረሱበት ይናገራል። ባጠቃላይ እሱን እንደናቁት እንዳላከበሩት ሲናገር ከደረቅ መሬት ሲል ተናገረ።

ሌላው only jesus የሚባሉት ከሰው ሥጋን አልነሳም ለማለት የሚያነሱት ጥቅስ ይሄ ነው
" #በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።"" ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ #ነበረ።"" ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ #አልሆነም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1:1-3)
" #ቃልም #ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ #አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።"
(የዮሐንስ ወንጌል 1:14)

ሌላው እነሱ የሚያነሱት ዮሐንስ ከላይ በመጀመርያ ቃል ነበር ብሎ ቁጥር 14 ያም ቃል ሥጋ ሆነ ስለሚል ሥጋ የሆነው ያ በመጀመሪያ የነበረው ቃል ነው ቃሉ ነው ሥጋ የሆነው ነው እንጅ ሥጋን አልነሳም ነው የሚሉት ።
ግን በመጀመሪያ ቃል ነበር ማለት ምን ማለት ነው ለሚለው ከታች ማብራሪያ አስቀምጥላችሁ አለው
ትንሽ ብቻ እዚህ ጋ ላስቀምጥ እንግድህ ዮሐንስ የቃል ቅድምና መናገሩ ነው አንድን ህፃን ተወለደ ለማለት መጀመሪያ ተፀነሰ ማለት እንደሚገባን ጌታ ቃልም ሰው ከመሆኑ በፊት በቅድምና የነበረ መሆኑን መናገሩ ነው ። ከዚያ ቁጥር 14 ላይ ቃልም ሥጋ ሆነ ብሎ በቅድምና የነበረው ቃል ሰው እንደሆነ ይነግረናል ቃልም ሥጋ ሆነ ማለት ቃልም ሰው ሆነ ማለት ነው ለዚህም ማብራሪያ ከታች አስቀምጥላችሁ አለው ትንሽ ነገር ብቻ ነው እዚህ ጋ የማስቀምጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ስናይ እንድህ የሚል ቃል አለ
" ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል።"
(መዝሙረ ዳዊት 65:2) እንግድህ መዝሙረኛው ዳዊት ሥጋ ሁሉ ሲል ሰው ሁሉ ማለት እንጅ ሥጋ ብቻውን ጸሎት የሚያቀርብ ሁኖ አይደለም ነፍስ የተዋሐደችው ሥጋን ማለቱ እንጅ ዮሐንስም ቃልም ሥጋ ሆነ ሲል ቃልም ሰው ሆነ ማልቱ ነው ። ሌላው ቃልም ሥጋ ሆነ ማለት ቃል ከሥጋ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ እንድህ የሚል ቃል አለ " ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 2:24) እዚህ ጋ እንግድህ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ሲል አዳም አዳምነቱን ትቶ ሔዋንም ሔዋንነቷን ትታ ሌላ ሥጋ ይሆናሉ ማለት አይደለም አዳምም አዳምነቱ እንዳለ ሔዋንም ሔዋንነቷ እንዳለ አንድ ይሆናሉ ማለት ነው እንጅ ቃልም ሥጋ ሆነ ሲል ቃልም ሳይለውጥ ቃልነቱን ሳይተው ከሥጋ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው እንድሁም ከእኛ ጋር አንድ ሆነ ማለት ነው እንጅ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል
" እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 1:23) ይላል እናም ቃልም ሥጋ ሆነ ሲል ቃል ሥጋን ተዋህዶ ከእኛ ጋር እንድ ሆነ ማለት ነው።
ሌላው አሁንም በመጽሐፍ ቅዱስ እንድህ የሚል ቃል አለ " ላባም። በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 29:14) ሲላው እናይ አለን ያዕቆብን ሥጋዬም ነህ ሲል ከአንድ ሥጋ እንደተካፈሉ መናገሩ ነው እናም ቃልም ሥጋ ሆነ ሲል ሥጋን ገንዘቡ ማድረጉን ሥጋን መንሳቱን መናገር ነው።" ኑ፥ ለእስማኤላውያን እንሽጠው፥ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አንጣል፥ ወንድማችን ሥጋችንም ነውና። ወንድሞቹም የእርሱን ነገር ሰሙት።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 37:27) እንደሚል የእኛን ሥጋ እንደነሳ ለመናገር ነው ሥጋ ሆነ ያለው ጸጋን እና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ እንድል።
@felgehaggnew
@felgehaggnew
በFacebook ማንበብ ለምትፈልጉ
👇
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2859730944287555&id=100007520311558
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላድቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
ይቆየን ይቀጥላል
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሥጋን አልነሳምን

✔️ክፍል ስምንት

ያው እንደተለመደው only Jesus ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሥጋን አልነሣም ለማለት ከሚያነሱት አንዱን እናይ አለን

" እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥"
(ወደ ዕብራውያን 10:19-20)

Only jesus ይሄን ጥቅስ ለምን እንደሚያነሱት እና እንዴት እንዳገናኙት አላቅም ኢየሱስ ከድንግል ሥጋ አልነሣም ለማለት እንዴት እንዳበቃቸው ባላቅም ጥቅሱ እንድህ ይላል በአድስ እና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት እንደምንገባ ይናገራል ይም የሚሆነው በኢየሱስ ደም እንዴው ይሄም አድስ እና ሕያው መንገድ እንዴው ወደ ቅድስት ለመግባት ይነግረናል አወ የአሁኑ አድስ እና ሕያው መንገድ ነው አዎ የክርስቶስ ደም ከእርሱ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የታረቅንበት አድስ እና ሕያው መንገድ ነው አዎ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም የላም የበግ ደም አይደለም ከእራሱ ጋር የታረቅንበት የራሱ ደም እንጅ ይሄ ደም አንድ ግዜ ቀርቦ ለዘላለም በቂ የሆነ መስዋዕት ነው እኛም የሔን ሥጋና ደም በመዉሰድ ሕያው እንሆናለም ሕይወትንም ይሰጠናል የብሉይ ኪዳን ሥርዓት መስዋዕቱ የላምና በግ ነበር ይሄ መስዋዕትም በየዓመቱ ቢያቀርቡትም እነርሱን ለዘላለም ከፈጣሪ ጋር ሊያስታርቃቸው እና ሕያው ሊያደርጋቸው አልቻለም የአድስ ኪዳን መስዋዕት ግን የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው ይሄን ለእኛ ሕይዎትን የሚሥጥ ሕያው እና ሰማያዊ የሚያደርገን ነው።" በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 3:12) እንድል በእርሱ አምነን ሥጋውና ደሙን በመውሰድ ወደ ቅድስት እንገባ አለን " አቤቱ፥ አንተ ታስገባቸዋለህ፥ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ፥ አቤቱ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፥ አቤቱ፥ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።"
(ኦሪት ዘጸአት 15:17)
" ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 26:28) ብሎ በሰጠን መሠረት ክርስቶስ በደሙ ለእኛ አዲስና ሕያው መንገድ ከፍቶልናል
" ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጥተዋል፤ ንጉሣቸውም በፊታቸው አልፎአል፥ እግዚአብሔርም በራሳቸው ላይ ነው።
"
(ትንቢተ ሚክያስ 2:13) እንድል እንድሁም
" ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፥ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 14:3)

" በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፥ ለንጹሐን ግን ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 35:8) ወደ ቅድስት ወደተባለች ወደ መንግስተ ሰማይ የምንገባበት መንገድ ይህ ነው። አዲስ ነው ምክንያቱም ክርስቶስ ከመምጣቱ በፊት ይሄን ያገኘው የለም
" ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:13)
ስለዚህ ወደ መንግስተ ሰማይ ለመግባት የቤተክርስቲያን አካል ሁኖ ድል ሊነሣ ይገባል
" መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።"
(የዮሐንስ ራእይ 2:7)
እርሱም ይመጣል እመጣለሁ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጥንተህሽያዝ ይላል
" ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።"
(የዮሐንስ ራእይ 3:12) መኖር ሁልጊዜ ይቅጥላል ክርስቲያን ሕያው ነው የምትቋረጥ ሕይወት የለችውም ምክንያቱም ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ነው በጥምቀት ሥጋውን ደሙን በመውሰድ ከክርስቶስ ጋር አንድ አካል ሁኗል የክርስቶስ አካል ደግሞ አይሞትም ሞትን ድል አድርጎ የተነሣ እንጅ ክርስቲያንም ሞት አያስቀረውም ።
" የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 45:15)

" እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፥ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 45:17)
ስለዚህ እንድህ ይላል ጌታ ኢየሱስ
" ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 14:1)
ወንድሞች ሆይ በቅዱስ ቁርባን በኩል ማለትም በተሰጠን ሥጋው እና ደሙ በኩል ወደ ቅድስት መግባት አለን። የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት መስዋዕት መንግስተ ሰማይ ሊያስገባ አይችልም ነበር ያ ጊዜያዊ ነበት የአሁኑ ግን ቋሚ ያ አቅመ ቢስ ነበር የአሁኑ ግን ፍጹም ነው ያ ምሳሌ ነበር የአሁኑ ግን አማናዊ እውነተኛ መስዋዕት ነው የአሁኑ በሥጋዊ የሕግ ትእዛዝ ሳይሆን በሕያው ሕግ ነው የማያልቅ ሕይወት የሚሰጥ ኃይል አለው። " በማያልፍም ሕይወት ኃይል እንጂ በሥጋ ትእዛዝ ሕግ ሳይሆን ሌላ ካህን በመልከ ጼዴቅ ምሳሌ ቢነሳ፥ ይህ እጅግ አብልጦ የሚገለጥ ነው።"
(ወደ ዕብራውያን 7:15-16)
" አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።
"
(ወደ ዕብራውያን 8:13) ይህ ግን አድስ ነው የብሉይ ሕግ ምንም ፍጹም አላደረገምና ዘላለማዊ የኃጢያት ሥርየት ማሠጠት አልተቻለምና
" ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።"
(ወደ ዕብራውያን 7:18-19)
" ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ። መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤"
(ወደ ዕብራውያን 10:5)
" በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።"
(ወደ ዕብራውያን 10:6)
ይህ በእጅ የተሠራ አይደለም
" ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።"
(ወደ ዕብራውያን 9:9-10)
" የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።"
(ወደ ዕብራውያን 9:12)
" የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥"
(ወደ ዕብራውያን 9:13)
" ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?"
(ወደ ዕብራውያን 9:14)
ስለዚህ የክርስቶስ ደም አድስና ሕያው መንገድ ነው

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@felgehaggnew
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📕ቁርባን በቅዱሳት መጻሕፍት

🗓 ክፍል አንድ

"ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፡- እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋም አንሥቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ፡- ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ይህ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። ' ( ማቴ. 26:26-28 )

💦ብሉይ ኪዳን

እግዚአብሔር የቃል ኪዳን ልጆቹን ያሳድጋል
ኢየሱስ የቅዱስ ቁርባንን ዋና ዋና የክርስቲያን ሃይማኖት ሥነ ስርዓት አስተዋወቀ። በብሉይ ኪዳን ዘመን አልነበረም። ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችን እንድንቀበለው ቀስ በቀስ አዘጋጀን። እነዚህ የብሉይ ኪዳን ዘገባዎች የቅዱስ ቁርባን ቅድመ-ምሳሌዎችን ይገልጻሉ።ስለዚህ ከብሉይ ኪዳን ምሳሌዎች ተነስተን ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሄድ አለን

💦አቤል
የክርስቶስ ሥጋ እና ደሙ የቅዱስ ቁርባን የመጀመሪያ ጥላ የአዳም እና የሔዋን ታናሽ ልጅ አቤል ነበር። ቃየን መልካሙን እረኛ አቤልን ገደለው። ጌታ ቃየንን፣ ዘፍ 4፡10 “የወንድምህ የደም ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” ብሎታል። የዕብራውያን መጽሐፍ፣ ዕብ 12፡24 ያስታውሰናል “…[የክርስቶስ]  ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር መርጨት ደም ደርሳችኃል”።

💦መልከ ጼዴቅ
መልከ ጼዴቅ ክርስቶስን አስቀድሞ አቅርቧል(በዚያን ጊዜ በዓለም ሁሉ ባሉ ክርስቲያኖች ለእግዚአሔር የሚቀርበው መስዋዕት አስቀድሞ ተገለጠ)ከክስተቱ ከረጅም ጊዜ በኋላ ይህ መስዋዕት ገና በሥጋ ሊመጣ ባለው በክርስቶስ እንደሚፈጸም በነቢዩ ተናግሯል። አብራም ኮሎዶጎመርን ድል አድርጎ ሲመለስ፣ ዘፍ 14፡18 “የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅ እንጀራና የወይን ጠጅ አወጣ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበረ…” በማለት አብራም በዚያን ጊዜ የልዑል እግዚአብሔር ካህን በሆነው በመልከ ጼዴቅ በግልጥ ተባርኮ ነበር። . የዕብራውያን መጽሐፍ ይነግረናል ዕብ 7፡2 "[መልከ ጼዴቅ] በመጀመሪያ ስሙ የጽድቅ ንጉሥ ነው ከዚያም በኋላ የሳሌም ንጉሥ ነው እርሱም የሰላም ንጉሥ ነው። አባትና እናት የትውልድም ቍጥር የሉትም፥ ለሕይወትም መጀመሪያና መጨረሻ የለውም፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።
ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ይልቅ የልዑል እግዚአብሔር ካህን ማን ነው?ለእግዚአብሔር አብ መስዋዕት አቀረበ መልከ ጼዴቅም ያቀረበውን ያንኑ እንጀራንና ወይንን እርሱም ሥጋውንና ደሙን አቀረበ?

💦ሙሴ
ሙሴ የመጀመሪያው የእስራኤል ካህን በሲና ተራራ ሥር ለተሰበሰቡት ስድስት መቶ ሺህ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ኦሪትን አንብብ።የታረደውን የበሬ ደም በሕዝቡ ላይ ረጨ።፡ ዘጸ 24፡8 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን ደም እነሆ አለ። ኢየሱስ በመጨረሻው እራት ላይ፣ ማቴ 26፡28 “ይህ የቃል ኪዳኑ ደሜ ነው” ብሏል።
ዘፀአት 34:29 ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ከተራራው ሲወርድ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ... ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ነበርና የፊቱ ቁርበት አበራ... በፊቱም መጋረጃ አደረገ።
ኢየሱስ በእንጀራና በወይን መልክ ተሸፍኖ ወደ እኛ ይመጣል።በኃጢአት ከጨለመችው የራሳችን ነፍሳችን ጋር ሲነጻጸር እጅግ የላቀውን የሙሉ ክብሩን ድንቅ ብርሃን መቋቋም አንችልም።።

💦መከሩ
በጥንቷ እስራኤል የፀደይ መከር እህል ወይም ስንዴ ያቀፈ ነበር። ዳቦ ለረጅም ጊዜ የፀደይ መከር ምልክት ነው. የበልግ መከር በአብዛኛው ወይን እና ወይራ ነበር። የወይን ወይን እና የወይራ ዘይት የበልግ መከር ምልክቶች ነበሩ። ዳቦ እና ወይን. ዘሌ 23፡12-13 " ነውር የሌለበትን የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ከእርሱም ጋር የእህል ቍርባን ከመስፈሪያው ሁለት እጅ ሁለት በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ይሁን። ከእርሱ ጋር ያለው የመጠጥ ቍርባን የወይን ጠጅ ይሁን። ካህናት በዘይት ይቀባሉ። ኦሪት ኅብስትንና ወይንን፣ ካህኑንም ከበጉ መሥዋዕት ጋር አንድ ያደርጋል።

💦የድንኳን መስዋዕት
💧የመገኘት እንጀራ
የመገኘት ኅብስት፣ በጥንታዊው ድንኳን እና በኋላ በቤተ መቅደሱ፣ 1 ነገ 7፡48 ኢየሱስን በቅዱስ ቁርባን ተመስሏል።
በማደሪያው ድንኳን ውስጥ እግዚአብሔር ሙሴን ዘጸ 25፡8 "በመካከላቸው አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ" ብሎ አዘዘው። በመቅደሱ፣ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ነገረው፣ ዘጸ 25፡22 “በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ ከስርየት መክደኛውም በላይ በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ አገኛለሁ። ከአንተ ጋር... እግዚአብሔር አክሎ፣ ዘጸ 25፡30 “የመሥዋዕቱን እንጀራ ሁልጊዜ በፊቴ በገበታው ላይ አድርግ። ኢየሱስ ማቴ 28፡20 "እኔ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሎናል ።
ካህኑ አቢሜሌክ ይህን የተቀደሰ እንጀራ ለዳዊት ሰጠው። 1ኛ ሳሙ 21፡6 ካህኑም የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው፤ በዚያም ከበፊቱ እንጀራ በቀር እንጀራ አልነበረምና። ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሁሉ እንደሆነ አስተምሮናል። ማቴዎስ 12:1 ፡— በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት በእርሻ አለፈ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተራቡ፥ እሸትም ይቀጥፉ ይበሉም ጀመር።… ዳዊትም በተራበ ጊዜ ከእርሱም ጋር የነበሩት አደረጉ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ የመገኘትንም እንጀራ እንደ በላ... እላችኋለሁ፥ ከመቅደስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
ኢየሱስ ከመቅደስ የሚበልጠውን አሳይቶናል። ሉቃስ 22፡19 “እንጀራም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና፡— ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፡ አላቸው።
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
አንድ ሙስሊም በቻናሉ ላይ ቅዱስ ዮስጥኖስ ሰማዕት(St.Justin Martyr) የተናገረውን በመውሰድ እንድህ ይላል

ቅዱስ ሰማዕት ጀስቲን ጥንታዊ ክርስቲያን "Apologist" ሲሆን በአንደኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ሰው ነው፤ ይህ ሰው ለክርስትና ህይወቱን አሳልፎ እስከመስጠት ደርሷል። እና ይህ ሰው የተናገረውን እውነታ ላሳያችሁ ወደድኩ ክርስትና ሀይማኖት ስለ ኢየሱስ አስተምህሮ አዲስ ነገር ይዞ ሳይሆን የመጣው ከጣዖታውያኑ የፀሃይ አምላክ ሳተርን ወይም ከጁፒተር ልጅጋ ተመሳሳይ አስተምህሮ እንደሆነ በአንደበቱ መስክሯል።
justin martyr
when we say that jesus christ was produced without sexual union,was crucified and died, and rose again,and ascended to heaven, we propound nothing new or different from what you believe regarding those whom you call the sons of jupiter
ትርጉም፦
ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ወሲባዊ ግንኙነት ተፈጠረ፣ተሰቀለ፣ሞተ፣ተነስቶ ወደ ሰማይ ስንል የጁፒተር ልጆች ከሚያምኑበት አዲስ ወይም የተለየ ነገር ሳይሆን ያመጣነው ተመሳሳይ አስተምህሮ ነው።
ክርስትና ምንጩ የጣዖታውያን አስተምህሮት ነው ስንል በማስረጃ ነው! በማለት ይናገራል
መልስ፦

ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ለምን ይሄን አለ ስንል እርሱ በነበረበት ዘመን እነዚህ ጣዎትን አምላኪዎች ክርስቲያኖችን ብቻ ያሳድዱና ይገሉ ነበር ስለዚህም ለእነዚህ ጣዎት አምላኪዎች የጻፈው first apology በሚባለው መጽሐፍ

እንድህ በማለት ይጽፍላቸዋል

If, therefore, on some points we teach the same things as the poets and philosophers whom you honour,
and on other points are fuller and more divine in our teaching, and if we alone afford proof of what we assert,why are we unjustly hated more than all others?

ትርጉም፦
ስለዚህ በአንዳንድ ነጥቦች ላይ እንደምታከብሯቸው ገጣሚዎች እና ፈላስፎች ተመሳሳይ ነገሮችን የምናስተምር ከሆነ ፣
እና በሌሎች ነጥቦች ላይ በትምህርታችን የበለጠ እና መለኮታዊ ናቸው ፣ እና እኛ ብቻ የምናረጋግጠውን ማረጋገጫ ከያዝን ፣ ከሌላው ሁሉ በበለጠ ለምን በግፍ እንጠላለን?

በማለት እነሱ የሚወዷቸውን ገጣሚዎች እና ፈላስፎች በማንሳት እንድህ ይላቸዋል
ለምሳሌ ያህል ቅዱሱ ካነሳው

For while we say that all things have been produced and arranged into aworld by God, We shall seem to utter the doctrine of plato;

ትርጉም፦እኛ ነገሮች ሁሉ በእግዚአብሔር ተፈጥረው እና ተዘጋጅተዋል ስንል የፕላቶ አስተምህሮ የምንናገር ይመስለናል።

While we affirm that the souls of the wicked , being endowed with sensation even after death , are punished, and that those of the good being delivered from punishment spend a blessed existence, we shall seem to say the same things as the poets and philosophers;

ትርጉም፦
እኛ የኃጥአን ነፍሳት ከሞት በኃላም ቢሆን ቅጣት እንደሚያገኛቸው እንድሁም መልካሞች ከቅጣት እንደሚድኑ የተባረከን ኑሮ ያሳልፋሉ ስንል እኛ እንደገጣሚዎች እና ፈላስፎች ተመሳሳይ ነገሮችን የምንናገር ይመስላል
While we maintain that men ought not to worship the works of their hands, we say the very things which have been said by the comic poet Menander

ትርጉም፦
እኛ ሰዎች የእጃቸውን ሥራ ማምለክ የለባቸውም ብለን ብናስብም ፣ በአስቂኝ ገጣሚው ሜንደር የተናገሩትን እንናገራለን

Other similar writers, for they have declared that the workman is greater than the work

ትርጉም፦ሌሎች ተመሳሳይ ጸሐፊዎች ፣ ሠራተኛው ከሥራው እንደሚበልጥ አውጀዋልና
ተወዳጆች ይሄ ሙሲልም ወንድማችን የቅዱሱን ሃሳብ ቆርጦ በመውሰድ ምን ለማለት እንፈለገ ሳይረዳ እሱ በጻፈው መሠረት ይሄ ቅዱስ የተናገረውን ውስደን እነሱም ከሞት በኃላ ነፍስ ትቀጣለች ብለው ያምናሉ ስለዚህ እስልምናም የፈላስፎች ትምህርት እንጅ ከሰማይ የወረደ የአላህ ቃል አይደለም ወይም የአምላካቸው ቃል አይደለም እንበላቸው ምክንያቱም ቅዱሱ ፕላቶ የተናገረውን በመጥቀስ ሁሉንም ፍጥረት አምላክ እንደፈጠራቸው እና እንዳዘጋጃቸው ስንናገር የፕላቶን አስተምህሮ የምንናገር ይመስላል ስላለ እነሱም ሁሉን የፈጠረው አላህ ነው ብለው ስለሚናገሩ የነሱ ትምህርት የፕላቶ ነው እንበላ 😁
ኧረ እንደውም እነሱ ምን ብለው ያስተምራሉ

ሰው ሲሞት ነፍስም አብራ ትሞታለች ብለው ያምናሉ ልክ እንደነሱ የይሖዋ ምሥክሮች እና ሰባተኛ ቀን አድቨንቲስት የሚባሉትም ሰው ሲሞት ነፍስም አብራ ትሞታለች ምንም አይነት ስሜት የለም ብለው ይናገራሉ ስለዚህ የነሱ አስተምህሮ የሰባተኛ ቀን አድቨንቲስቶች ነዋ ወይም የይሖዋ ምስክሮች ስለዚህ እነሱን ሰባተኛ አድቨንቲስት እምነት ተከታዮች እንበላቸው?
ምክንያቱም እነሱ የሚወዷቸው እነ ፕላቶ በአንዳንድ ነገር የሚመሳሰል ትምህርት ስለነበራቸው እነሱን እየወደዱ ለምን ክርስቲያኖችን በጣም እንደሚጠሉ ይጠይቃቸዋል ለምሳሌ ፕላቶ ምን ብሎ ያምን ነበር ከላይ ቅዱስ ከጠቀሰው ውጭ
ፕላቶ እንድህ ይልነበር “[አንድ ሰው ሲሞት] የማትሞት ነፍስ ብለን የምንጠራት የእያንዳንዳችን እውነተኛ ማንነት፣ አማልክት ወደሚገኙበት በመሄድ . . . በዚያ ለፍርድ ትቆማለች፤ ይህ ደግሞ ጥሩ ሰዎች በመተማመን፣ ክፉ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ፍርሃት የሚጠብቁት ነገር ነው።”— ፕላቶ፣ ሎውስ (12ኛ ጥራዝ)

እንድሁም ሶቅራጥስና እና ፕላቶ የግሪክ ፈላስፎች አንድ የሚያደርጋቸው ሐሳብ አስተምረዋል፦ ነፍስ “ከመንከራተት፣ ከከንቱነት፣ ከፍርሃትና መረን ከለቀቀ ምኞቷ እንዲሁም የሰውን ልጅ ከሚያምሱት ሌሎች ሥቃዮች ነፃ” የምትሆነው የአቅም ገደብ ካለበት የሰው አካል ተላቅቃ “ከአማልክት ጋር ለሁልጊዜ” መኖር ስትችል ብቻ ነው። —ፕላቶስ ፋይዶ፣ 81፣ ኤ ተወዳጆች ቅዱስ እንዳነሳው እንግድ በአንዳንድ ነገሮች ብሎ ነው እና በአንዳንድ ነገር የሚመሣሰልን ምንጩ ይሄ ነው ብሎ የሚናገሩ ከሆነ ጣዎት አምላኪዎች የሚናገሩት በእስልምና ሃይማኖት ስንት ነገር አለ እና ጣዎት አምላኪዎች መሆናቸውን ለምን አያምኑልንም 🤔

እናም ቅዱስ እንደዝህ አይነቶችን ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን አነሳ እንጅ አንድ ነን አላለም እናም ይሄን መሠረት አድርጎ ይናገራል
ስለዚህ ቅዱስ እንደዚህ እያለ እነሱ የሚወዷቸውም ተመሳሳይ እየተናገሩ ለምን ክርስቲያኖች እንደሚጠሉአቸውና እንደሚገሏቸው እየጠየቀ ከሄደ በኃላ ወደ እነሱ አምልኮ በመምጣት እንድህ ይላቸዋል
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
And when we say also that the Word, who is the first-birth of God, was produced without sexual union, and that He, Jesus Christ, our Teacher, was crucified and died, and rose again, and ascended into heaven, we propound nothing different from what you believe regarding those whom you esteem sons of Jupiter.
ትርጉም፦
ደግሞም የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ልጅ የሆነው ቃል ያለ ወሲብ ተወለደ ስንል እርሱ ደግሞ መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሞተ ተነስቶ ወደ ሰማይ አረገ ስንል የጁፒተር ልጆች የምትቆጥሯቸውን በተመለከተ ከምታምኑበት የተለየ ነገር የለም ፡፡

ይላቸዋል ምክንያቱን ሲናገር ሊቁ ይቀጥል እና
For you know how many sons your esteemed writers ascribed to Jupiter: Mercury, the interpreting word and teacher of all; Æsculapius, who, though he was a great physician, was struck by a thunderbolt, and so ascended to heaven; and Bacchus too, after he had been torn limb from limb; and Hercules, when he had committed himself to the flames to escape his toils; and the sons of Leda, and Dioscuri; and Perseus, son of Danae; and Bellerophon, who, though sprung from mortals, rose to heaven on the horse Pegasus

ትርጉም፦
የተከበሩ ጸሐፊዎችዎ ለጁፒተር ምን ያህል ልጆች እንደሰጡ ያውቃሉና
የሁሉም አስተርጓሚ ቃል እና አስተማሪ ሜርኩሪ
ኤስኩላፒየስ ፣ እርሱ ታላቅ ሐኪም ቢሆንም ፣
በነጎድጓድ ተመታእናም ወደ ሰማይ አረገ
እና ባኮስ እንድሁ የእጅና እግርን ከአጥንቱ ከተቀደደ በኃላ እና ሄርኩለስ ከድካሙ ለማምለጥ ራሱን በእሳት ነበልባል ሲሰጥ የሊዳ ልጆች እና ዲዮስኩሪ ፐርሴስ የዳኔ ልጅ እና ቤለሮፎን ከሰው ልጆች ቢወጣም በፈረሰ በፔጋሰስ ወደ ሰማይ ወጣ ...


እያለ የሚሉትን ይነግራቸው እና እኛ ታድያ ተነስቶ ዓርጓል ስንል ለምን ትቃወማላችሁ ይላቸዋል
ተወዳጆች በሊቁ አነጋገር እስኪ ለራሱ እንጠይቀው እነሱ የጂፒተር ልጆች እንዳረጉ ይናገራሉ እንደሞቱ ግን አይነገሩም እንሱ ታድያ ኢየሱስ ሳይሰቀል ነው የተወሰደው ሲሉ ከጣዎት አምላኪዎች አምጥጠውት ይሆን ?


ሲጀመር ቅዱስ እነሱ ለጂፒተር ብዙ ልጆች አሉት እንደሚሉት እየተናገር እሱ ግን የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ብሎ እየተናገረ ከጣዎት አምልኮ ነው የመጣው ክርስትና ይባላልን ሊቁ እየተናገረ ያለው እነሱ የጁፒተር ልጆች ወደ ሰማይ ዓርገዋል ብለው ሰለሚናገሩ እኛ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቶ አርጓል ብንል ምንድነው ጥፋቱ እያለ ይዘቱን እየተናገረ እንጅ ከእናንተ ነው የወሰድንው እያለ አይደለም የቅዱሱን ሙሉ ጽሑፍ ሳያነቡ እንድህ ብሎ መናገር ድፍን ጥላቻ እንጅ ምን ይባላል
ቅዱስ የነሱን ጣዎት አምልኮ እየተቃወመ ከነሱ እንደመጣ ተናግሯል ብሎ መናገር ድንቁርና እንጅ ምን ይባላል
ሊቁ የነሱን ትምህርት ሲቃወም

we not only deny that they who did such things as these are gods, but assert that they are wicked and impious demons, whose actions will not bear comparison with those even of men desirous of virtue. Chapter 6
ትርጉም፦
እንደነዚህ ያሉትን ያደረጉ አማልክት መሆናቸውን መካድ ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን እነሱ ክፉ እና ርኩስ አጋንንት መሆናቸውን እናረጋግጣለን ፣ ድርጊታቸውም በጎነትን ከሚሹ ሰዎችም እንኳ ጋር አይወዳደርም ፡፡ ምዕራፍ 6
And neither do we honour with many sacrifices and garlands of flowers such deities as men have formed and set in shrines and called gods; since we see that these are soulless and dead, and have not the form of God (for we do not consider that God has such a form as some say that they imitate to His honour), but have the names and forms of those wicked demons which have appeared. chapter 9
እኛ ደግሞ ሰዎች መስርተው አማልክት ተብለው በተጠሩ እና በመሰሉአቸው አማልክት በብዙ መስዋእቶች እና በአበቦች የአበባ ጉንጉን አናከብርም። እነዚህ ነፍሶች የሞቱ እና የእግዚአብሔር መልክ እንደሌላቸው ስለምንመለከት (እኛ አንዳንዶች ለክብሩ ይመስላሉ እንደሚሉት አይነት እግዚአብሔር አለው ብለን አንቆጥርም) ፣ ነገር ግን የእነዚህ ክፉ አጋንንት ስሞች እና ቅርጾች አሉት ፡፡ ተገለጡ ፡፡ ምዕራፍ 9

በማለት ቅዱሱ ይናገራል እንድሁም እነሱ አምላክ ለሚሏቸው ተበቂ እንደሚያስቀምጡ ከነገራቸው በኃላ እኛ ግን ለአምላክ ጠባቂ አያስፈልገውም እሱ እኛን ይጠብቀናል እንጅ እንድሁም ሥራው ከሠሪው እንደሚያንስ እናተ የሠራችኃቸው የእጅ ሥራዎቻችሁ ከእናንተ ያነሱ ስለሆኑ አምላክ አይደሉም ይላቸዋል ታድያ እንድህ ባለበት የቅዱሱን ሃሳብ አንስቶ ክርስትና ከጣዎት ነው የመጣው ስንል በማስረጃ ነው ማለት አያሳፍርም
እስኪ እንጠይቃቸው ከነሱ ቁራን አንድ አንስተን


وَإِذْ فَرَقْنَا بِكُمُ الْبَحْرَ فَأَنجَيْنَاكُمْ وَأَغْرَقْنَا آلَ فِرْعَوْنَ وَأَنتُمْ تَنظُرُونَ

በናንተም ምክንያት ባሕሩን በከፈልን ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ ወዲያውም አዳንናችሁ፡፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች እናንተ የምትመለከቱ ኾናችሁ አሰጠምናቸው፡፡ሱራ 2፣50 ይላል ቁራን ታድያ ይሄ በመጽሐፍ ቅዱስ አለ እና ሞሐመድ ይሄን ከክርስትና እንደወሰደው ለምን አይነግሩንም ሊቁስ ያነሳው ይዘቱን እንጅ እንዳለ ሃሳቡን አይደለም ምክንያቱም በዚያ ጽሑፍ እነሱ የሚሉት ውሸት እንደሆነ ነግሮናል እና እነሱ ግን ሃሳቡን እንዳለ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወስደዋልና
@felgehaggnew
@felgehaggnew
@felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባትኖር ኑሮ በዓለም ላይ ጴንጤ የሚባል አይኖርም ነበር ብሎ የተናገረውን የአንድ ፕሮቴስታንት ንግግር እንዴ ጥሩ ነገር የምትቀባበሉ ኦርቶዶክሳዊያን ታሳፍራላቹ ንግግሩ ትክክል የሚመስል ግን ደግሞ መርዛማ የሆነ ንግግር ነው ። ምክንያቱም የጴንጤ አስተምህሮ ስሕተት ነው የስሕተት ትምህርት አስተማሪ ደግሞ ዲያብሎስ ነው የሕሰት አባት ዲያብሎስ አስተማራቸው እንጂ ኦርቶዶክስ የስሕተት ትምህርት አስተማሪ አይደለችም "እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።" እንዲል ቃሉ
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📜 መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የሚለው የ ፕሮቴስታንቶች አስተምህሮ በተግባር ሲፈተን ለፕሮቴስታንቶች "ሁሉም በቂ" ነው?
ፕሮቴስታንቶች “መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ አምናለሁ” ብለው ደጋግመው ይናገራሉ፣ ነገር ግን አንድ ሰው ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃቀማቸውን ሲመረምር ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ለምሳሌ ፕሮቴስታንቶች ስለ ዶክትሪን እና በአጠቃላይ ስለ ክርስትና ሕይወት ብዙ መጽሃፎችን ለምን ይጽፋሉ፣ በእርግጥ አስፈላጊው መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ? አንድ ሰው እንዲረዳው መጽሐፍ ቅዱስ ብቻውን በቂ ከሆነ፣ ታዲያ ፕሮቴስታንቶች ለምን መጽሐፍ ቅዱስን በቀላሉ አይሰጡም ሌላ ነገር ለምን ?
እና "ሁሉም በቂ" ከሆነ, ለምን ወጥነት ያለው ውጤት አያመጣም, ማለትም ለምን ፕሮቴስታንቶች ሁሉም ተመሳሳይ አያምኑም?
የሚያስፈልገው መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ ከሆነ የብዙ ፕሮቴስታንቶች ጥናት መጽሐፍ ቅዱስ ዓላማ ምንድን ነው?
በራሪ ወረቀቶችና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያከፋፍሉት ለምንድን ነው?
ሌላው ቀርቶ የሚያስተምሩት ወይም የሚሰብኩት ለምንድን ነው? ለምን መጽሐፍ ቅዱስን ለሰዎች ማንበብ ብቻ አይደለም መስበክ ለምን አስፈለገ ለምን መጸሐፍ ቅዱስን ብቻ አያነቡላቸውም የራሳቸውን ማብራሪያ መጨመር ለምን ?

መልሱ ብዙውን ጊዜ ባይቀበሉትም ፕሮቴስታንቶች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻውን መረዳት እንደማይቻል በደመ ነፍስ ያውቃሉ።
እና በእውነቱ እያንዳንዱ የፕሮቴስታንት ኑፋቄ የራሱ የሆነ ወግ አለው ማለትም ለእያዳንዱ ኑፋቀአቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኙት ሳይሆን ከስዎች ያገኙት ወይም ደግሞ እራሳቸው የፈጠሩት ነው። @felgehaggnew
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
📜 "በክርስቶስ ያለው እኔ ባይነት የመለኮት ነው" ወይም "ሥጋው እኔነት የለውም፤ ግን የመለኮትን እኔነት የራሱ አድርጎ እኔ ባይ ተባለ እንጅ የሥጋ እኔነት ገንዘቡ አልሆነም ከተባለ " የአብርዮስ ምንፍቅና ነው የሚሆነው አብርዮስ ክርስቶስ ነፍስና ልብ የለውም መለኮቱም በነፍስና በልብ ፈንታ ሆነው ይል ነበርና ። ክርስቶስ የሰውነቱ እኔ ባይነት ከሌለ ምክንያታዊ ነፍስንም አልነሳም ማለት ነው ስለዚህ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መባሉ ቀርቶ ፍጹም በድን ፍጹም አምላክ ነው ሊባል ነው የሚገባው ማለት ነው ምክንያቱም እኔ ባይነት የሌለው ሰው የለምና እኔ ባይነት የሌለው ሥጋ ደግሞ በድን ነው። እኔ ባይነት የሌለው ፍጹም ሰውም የለም ። በቤተ ክርስቲያን አባቶች ታሪክም እንድህ ብሎ ያስተማረ አንድስ እንኳን የለም አለ የሚል ካለ ግን አምጥታችሁ አሳዩን
Forwarded from ጥያቄኽ ምንድነው ሳትሄድ ፈልገው (መሸ በከንቱ)
Semagn Derese
IT & Application Development Professional | Programming Instructor
🚀 Seeking Opportunities to Train and Inspire Future Developers 🚀
Are you ready to take your programming skills to the next level? Look no further! I offer comprehensive programming courses designed to equip you with the knowledge and expertise needed to thrive in the IT industry.
Why Choose My Programming Courses?
🔹 Expert-Led Training: Learn from an experienced professional with a proven track record in IT and application development. Benefit from real-world insights and practical knowledge.
🔹 Comprehensive Curriculum: Master a wide range of programming languages and frameworks, including Python, Java, JavaScript, C#, and more. From fundamentals to advanced concepts, I've got you covered.
🔹 Hands-On Approach: Apply your skills to real-world projects and sharpen your problem-solving abilities. Build a professional portfolio that showcases your talent and sets you apart from the competition.
🔹 Flexible Learning Options: I understand the importance of flexibility in your busy schedule. Choose from in-person or online classes, allowing you to learn at your own pace and convenience.
🔹 Supportive Learning Community: Join a vibrant community of like-minded individuals passionate about programming. Engage in discussions, collaborate on projects, and expand your professional network.
Are you ready to embark on an exciting journey of learning and growth? Let's connect and discuss how my programming courses can help you achieve your career goals. Together, we'll unlock your full potential and open doors to exciting opportunities in the world of IT.
📩 Message me or visit my LinkedIn profile[https://www.linkedin.com/in/semagn-derese-34a88b140/] to learn more about the courses and how to enroll. Let's shape the future of technology together!
✝️ ለኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ ጉዞ ጥሪ ወደ ሳማ ሰንበት  ✝️

እኩለ ፆም ወይም ደብረ ዘይት በዓል የጌታ ምፃት የሚታሰብበት በዓል ነው በምፃቱ ወቅት የአባቴ ብሩካን ወደ እኔ ኑ  እንዲለን መልካም ስራ በመስራት ገዳማትን እንጎብኝ እንባረክ የፊታችን እሁድ መጋቢት 29 ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሳማ ሰንበት ተዘጋጅቷል በዚህ ጉዞ አገልጋይ ዘማሪያን እና መምህራን ይገኙበታል ኑ ከእኛ ጋር ይጓዙ

👉 ህሙማንን እንጠይቃለን
👉 ፀበል እንጠመቃለን
👉 ሌሎች ገዳማትንም እንሳለማለን
    😳   የደርሶ መልስ ክፍያ ምግብን ጨምሮ 600 ብር ብቻ


🚍🚙 መነሻ ከፒያሳ ከእስጢፋኖስ  ከቃሊቲ የሚቀርቦት ቦታ መሆን ይችላሉ

📌 ማሳሰብያ :-  መሄድ ለማይችሉ በተለይ ለህሙማን ፀበል እና እምነት ይዘን እንመጣለን ይደውሉ ! 

  📞 +251907609696 , +251967791717      

   ዘማሪ ዲ/ን አሸናፊ ብለው  ይደውሉልን
2024/05/08 07:17:39
Back to Top
HTML Embed Code: