Telegram Web Link
ሙሓደራ 31 ማንንነው ጓደኛ ምታደርገው በኡስታዝ አቡ ሙስሊም المحاضرة 31 من تصاحب؟ الأستاذ…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ ሀፊዘሁሏህ
🔹 ማንንነው ጓደኛ ምታደርገው?

🔹 من تصاحب؟

ጠቃሚ ምክሮች አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች

•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•
           
🎙Uŝtaź Ꭺbû Ꮇũslim Oûmēr
ᎪL Ꭺŕusii {حفظه الله}

@ArkemMy
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

''ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሰላት የሰገደበት መስገጃዉ ላይ እስካለ እና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢኮች በርሱ ለይ ሰለዋት ያወርዱለታል። ''አሏህ ሆይ ወንጀሉን ማረዉ: አሏሀሰ ሆይ እዘንለት።'' ይላሉ።''

@ArkemMy
#ረሱል ﷺ መንገድ ዳር አፈር እየጫሩ ቁጭ ብለው አሸዋ ጫር ጫር እያደረጉ በሀሳብ ተጉዘው ተከዙ ምነው ያረሱለላህ ﷺ ሲሏቸው?
በጣፋጭ አንደበት እንዲህ ሲሉ መለሱ
"ኢሽተቅቱ ኢላ ኢኽዋኒ"
እኔ ወንድሞቼ ናፈቁኝ ከኔ ቡሃላ የሚመጡ አማኞች ናቸው እኔን ሳያዩ ያመኑብኝ .. ወንድሞቼ ናፈቁኝ

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱላለህﷺ❤️
ፊዳከ ሩሂ ወደሚ ያሀቢበላህﷺ❤️
ማመስገን አታቁም!

የጎደለህን አትቁጠር የተሰጠህን አስብ፤ ብዙ ያልጠበካቸው መልካም ነገሮች በህይወትህ ብዙ ጊዜ ደጋግመው ተከስተዋል፤ የዛሬው ቀን አንዱ ስጦታ ነው።

ትናንት ሲስቁ ውለው ዛሬ ጠዋት ግን ከእንቅልፋቸው ያልነቁ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ይሄንን ፅሁፍ ለማንበብ ቢያንስ መተንፈስ አለብህ፤ በህይወት እስካለህ ደግሞ የማይስተካከል ነገር የለም። ወዳጄ መስጠት ለማይሰለቸው ፈጣሪህ ማመስገን አትሰልች!

https://www.tg-me.com/ArkemMy
ትልቁን ምክንያትክን አዘጋጅ

ገና በጠዋት ከእንቅልፍክ ከመነሳትክ ድክም ብሎክ ተኝቼ አይደለም እንዴ ያደርኩት የሚያስብል አጋጣሚ ኖሮክ ያውቃል? እናቶቻችን አባቶቻችንና አያቶቻችን ከኛ ምንም ያክል በእድሜ ከፍ ቢሉም ግን ባላቸው ጉልበትና ብርታት ሁላችንም በጣም እንገረማለን ከየት አመጡት? ሁሉም ቢጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ የሚሆነው ትልቅ ምክንያት ስላለኝ ነው የሚል ነው!

አንተ አዎ አንተ ልጃቸው ነህ ትልቁ ምክንያታቸው ላንተ ሲሉ ግዴታ መበርታት አለባቸው ስለዚህ አንተም ምክንያት ይኑርክ ትልቅ ምክንያት አዘጋጅ ያኔ በፍፁም መድከም አይፈቀድልክም

መልካም ዕለተ ሰንበት ተመኘን🙏
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️

https://www.tg-me.com/ArkemMy
ከትውስታ
እንዲህ ነበርን

ሰው ሰው እሚመስለው፣ በስብእናው ቢሆን፡፡


ውስጡ በታጨቀው፣ ለብሶ ሰውነቱን
ቀንድ፣ ጭራ ኑሮት ፣ ግማሹ ያዳም ዘር
ሰው መሆኑ ቀርቶ፣ አውሬ ይሆን ነበር
(መዚዳ ተማም)

ሌሎች ግጥሞች እንዲደርሶ👇
@ArkemMy
እንደዚህ ተፈላስፌ Join አስብያቹ ተመልሳቹ ትወጣላቹ ኧረ አስብልኝ 🙏 በልመና ሳይሆን በፍቅር አብራቹን ቆዩ
#እባክሽ
:
:
ትናንት ባማን ደና በሚያስቀና ለዛ፣
ሆነን አቻ ላቻ ያበጀነው ታዛ፣
ቀን በገፋ ቁጥር የኋላ የኋላ፣
ዘመም እዳይልብን በዳዋ እንዳይበላ፣
ዘላለም እንዲከርም የልባችን ምግብ ሆኖ በአንድ ትሪ፣
ባክሽ የኔ ፍቅር ሰው መምሰሉን ትተሽ ሰው መሆን ጀምሪ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@ArkemMy
@ArkemMy
@ArkemMy
@ArkemMy
ነጭ ጀለቢያ የለበሱት ማን እንደሆኑ ታውቃለህ
ሲታዩ ተራ ሰው ይመስላሉ ኣ ግን አይደሉም ቢፈልጉ ንጉስ መሆን የሚችሉ ነበሩ
ግን ......
እኚህን አዛውንት የሳውዲ አረቢያ የመጀመሪያው ንጉስ ልጅ የንጉስ ሳልማን
ወንድም ልዑል ማምዱህ ቢን አብዱል አዚዝ አል ስዑድ ናቸው።
ህይወታቸውን በሙሉ ለቅዱስ ቁርኣን አገልግሎት የሰጡ በህይወት ዘመናቸው
ወደ 70,000 ለሚጠጉ ተማሪዎች ቅዱስ ቁርኣንን ያስተማሩ።
የታቡክ ግዛት ገዥ ሆነው ተሹመው ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ስልጣን
አልፈልግም በማለት ስልጣናቸውን የለቀቁ።
# አጂብ የዱንያን ንግስና ያልፈለጉ ለአኼራ የሰነቁ # ድንቅ ሰው ረጅም እድሜ
ከአፊያ ጋ ይስጥዎ
@ArkemMy
@ArkemMy
@ArkemMy
ሴት ልጅ ከቤቷ ውጭ ለበእድ ወንዶች
ተኳኩላና ተበጃጅታ ከወጣች ከእሷ ዘንድ መልካም ነገር የለም
እንዲሁም ተኳኩላ ስትወጣ እያዩ ዝም የሚሉ ወንዶች እነሱ ዘንድ መልካም ነገር የለም ምክንያቱም እነሱ ደዩስ (ቅናት አልባ) ወንዶች ናቸውና ቅናት አልባ ወንድ ደግሞ ጀነትን አይገባም

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
@ArkemMy

@ArkemMy
ሙታኗ ላይ ዝሙት ፈፀምኩ
"""""""""""""""""""""""""""""""""
ማንኛውም ሙስሊም ታሪኩን ያንብበው አስገራሚና አስደናቂ እንዲሁም አስተማሪ ታሪክ ነው

ዑመር (ረ.ዐ) ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እያለቀስ ገባ፤ ይህን የተመለከቱት መልዕክተኛውም፦ ምን ያስለቀስሀል ኡመር" አሉት።
አንቱ የአላህ መልዕክተኛ…! በር ላይ አንድ ወጣት ሲያለቅስ ተመልክቼ አንጀቴን አላወስው" አላቸው።

"አንተ ልጅ ሆይ… ለምን ታለቅሳለህ ?" በማለት መልዕክተኛው ወጣቱን ጠየቁት።
የሀፍረት ስሜት እየተስማው፦"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ…ብዙ ወንጀሎች ያስለቅሱኛል የተቆጣብኝ ጌታዬንም ፈርቻለሁ አላቸው ።
ነቢዩ (ሰ.ዓ.ወ) "በአላህ ላይ ሌላን አካል አጋርተህ አምልከሀልን?" አሉት።
አይ…አላቸው።
"ነፍስን ያለ አግባብ ገለሀልን?" አሉት።
"አይ…" አላቸው።
እንግዲያውስ ወንጀልህ የሰባት ስማያት፣ የሰባት ምድርን፣ የተራራዎችን እና የኮረብታዎችን ያህል እንኳ ቢሆን አላህ ይቅር ይልሀል" አሉት።

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ… ወንጀሌ ከስባት ስማያት፣ ከስባት ምድር፣ ከተራራዎች እና ከኮረብታዎች ይበልጣል እኮ" አላቸው።
"ወንጀልህ ይበልጣል ወይስ ኩርሲይ?" ብለው ጠየቁት።
"ወንጀሌ ይበልጣል" አላቸው።
"ወንጀልህ ይበልጣል ወይስ አርሽ?" ደግመው ጠየቁት።
"ወንጀሌ ይበልጣል" በማለት ደግሞ መለስላቸው።

"ጌታህ መሀርታው ይበልጣል ወይስ ወንጀልህ?" ብለው ጠየቁት።
"አላህ ይበልጣል፣ ይልቃልም" ብሎ መለስላቸው።
"ታዲያ ትልቁንም ወንጀል እኮ ትልቁ አላህ እንጂ ማንም አይምርህም" አሉት

መልዕክተኛው።
"አንተ ልጅ እስቲ ወንጀልህን ንገረኝማ…አሉት
እሱም፦"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ…!ወንጀሌም በእርሶ ፊት መናገር ያሳፍረኛል" ብሎ መለስላቸው።
"እስቲ ወንጀልህን ንገረኝ" ጥያቄውን ደገሙለት።
"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ…! እኔ ቀብር ዘራፊ ነበርኩ
ላለፉት ሰባት አመታት መቃብሮችን ስዘርፍ አሳልፊያለሁ።
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት የመዲና እንስት ሞታ ቀብሯን በቀን ልዘርፍ ቆፍሬ ከፈኑን ከላይዋለይ ገለብኩት፤ ከፈኗን ይዤ ትቻት መሄድ ጀመርኩ ነገር ግን ብዙም ሳልርቅ ሽይጧን ወደ ቀብሩ እንድመለስ ጎተጎተኝ…! ተመለስኩኝ እና ዘሞትኳት

ከዚያም ተነስቼ መሄድ ጀመርኩ፤ ብዙም ሳርቅ ሙታኗ ብድግ ብላ፦"ዋ ጥፋትህ… አንተ ወጣት…!! ያ ዙፋኑን ለፍርድ አስቀምጦ ከበደለኞች ሀቃቸውን ይዞ ለተበዳዮች የሚያደርስውን ጌታ አታፍርምን
በሙታን አውድማ ብቻዬን ትተህኝ ትሄዳለህን…?
አላህ ፊትም ለሂሳብ ስቆም ከነጀናባዬ አቆምከኝ…! ትርክቱን ሳይጨርስ……

መልዕክተኛው አፋቸውን ይዘው፦"አንተ ፋሲቅ ዞር በልልኝ፤ አንተ ለእሳትም ምንኛ ተገቢ ነህ…!
ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ ከመልዕክተኛው ዘንድ ወጣ። ለአርባ ቀናት ያህልም አላህን ሲማፀን ከረመ።
አርባኛ ቀኑ ሲሞላ እጁን ወደ ላይ አንስቶ፦"አንተ የሙሀመድ፣ አንተ የአደም፣ እና፣ የሀዋ ጌታ ሆይ… ፀፀቴን ተቀብለህ ምረህኝ እንደሆን ለሙሀመድና ለባልደረቦቹ አሳውቅልኝ።

ያ-ሳይሆን ቀርቶ ፀፀቴን ያልተቀበልከኝም እንደሆነ፤ ከስማይ እሳት አውርደህ አሁኑ አቃጥለኝ'ና ከጀሀነሚቱ እሳት ገላግለኝ" በማለት አላህን ተማፀነ።
ፈጣኑ መልዕክተኛ , የረሱል (ሰ.ዓ.ወ) ባልደረባ ጅብሪል (ዐ.ስ) ሰማያትን አቋርጦ ወደ ነብዩ ( ሰ.ዓ.ወ) ዘንድ የጌታውን ትዕዛዝ ይዞ ብቅ
አለና፦

ሙሀመድ ሆይ…! ጌታህ ስላም ይልሀል" አላቸው።
ነቢዩም (ሰ.ዓ.ወ ) ፦"እሱ ስላም ነው፤ ስላምም ከሱ ነው፤ ወደሱም ተመላሽ ነው" ብለው በንግግር ተጠበቡ።

"አላህም ብሎሀል (ፍጥረትን አንተ ነህ እንዴ የፈጠርከው)" አላቸው ጅብሪል።
"እንዴታ…! እኔን እና ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረው ጌታ ነው የፈጠራቸው)" በማለት መለሱ።
"ጌታህም ይልሀል (አንተ ነህ እንዴ መሀርታን የምትለግስው)" ዳግም ጅብሪል ጥያቄያዊ መልዕክቱን አስተላለፈላቸው።
"እንዴታ…! አላህ እኮ ነው እኔንም ፍጥረታትንም ይቅር የሚለው መሀርታ የሚለግስው" በማለት መለሱ።
አላህም ይልሀል (ባርያዬን ይቅር በለው፤ እኔም ይቅር ብየዋለሁ)" በማለት ጅብሪል የጌታውን መልዕክት አስተላለፈ።

ይሄን ጊዜ መልዕክተኛው ያን ወጣት በማስጠራት አላህ ይቅር እንዳለው አበስሩት።

በማያልቀው የአላህ አጅር ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ላይክ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመዶ ያካፍሉ

♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
@ArkemMy

@ArkemMy
<<በቀናት የኢላሂን ቃል ማነብነብ ጀመርኩ… ስለ ሞት፣ ጀሂም እና ስለ አስፈሪዉ የቂያም ቀን እያነበብኩ ልቤ መደንገጥ፣ አይኖቼ ማንባት አለመቻላቸውን ሳስተውለው…>>
.
.
<ልስቅ አልፈልግም!>
የ5 ሰከንዶች ፈገግታ ፎቶ ላይ የሚያንፀባርቅ ከሆነ ሁሌም ፈገግ ብትል ህይወትህ ምን ያህል ቆንጆ እንደሆነ ሁልጊዜ አስብ፡፡ ፈገግ በል🙏
ፈገግታ ሱና ነው
💔 የሰው ማጣት ፍራቻ ሳይሆን
ሁሉንም ለማስደሰት ብለህ እራስን
የማጣት ፍራቻ ይኑርህ ።
💔
••ৡ✵ @Dah_lake_32 🚶🏽
አሰላሙ አለይኩም ያጀምአ
ለምሽቱ ድምቀት አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ!?😘

አምስት እህትማማቾች ቤት ውስጥ ብቻቸውን ቁጭ ብለው ድብርት ሲያጨናንቃቸው እራሳቸውን ከድብርት ለማላቀቅ ሲሉ ....
አንደኛዋ ልብስ ማጠብ ጀመረች
ሁለተኛዋ ምግብ ማብሰል ጀመረች
ሶስተኛዋ ዳማ መጫወት ጀመረች
አራተኛዋ ደሞ ቤት መጥረግ ጀመረች

ጥያቄውም:- አምስተኛዋ ልጅ ምን እየሰራች ነው
#Share@ArkemMy
መልሳችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ👇👇
ሁሉም ሙስሊም የሚመለከት ጉዳይ!

ጀናባን የሚመለከቱ ህግና ደንቦች!

የቃላት መፍቻ

1) መኒይ (የዘር ፈሳሽ)
- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311]
ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ ቡኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር) ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡ [ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

2) መዚይ
- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡

3) ወዲይ
- ከሽንት ቡኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው። (ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም)

4) ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ
- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች ቡኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡

ገላን መታጠብ ግዴታ የሚሆነው መቼ ነው?
1) በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ቢፈስም ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው!
2) ግንኙነት ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
3) በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
4) በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡
ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ” ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
5) በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ አለበት!
6) በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግን ሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡
7) በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን መለየት ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደ መሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡
8) በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን መለየት ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደ የትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን 11/161]

የጀናባ አስተጣጠብ ሁለት አይነት ነው!
1) የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረስ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ ቡኋላ ውዱእም ባያደርጉ መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡
2) ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

ማሳሰቢያ!
ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ኡሙ ሰለማህ ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም]
ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡
ለማጣቀሻነት የተጠቀምኩት
1)ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን
2) ፈትሑልዐላም ፊ ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና ሌሎችም ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡

#ሙሀመድ አህመድ

ለበለጠ ኢስላማዊ ዳዕዋ በዚህ ይከታተሉን!

share @ArkemMy
አልሀምዱ ሊላህ

አሏሁ አክበር

በሲዳማ ክልል በራሳቸው ተነሳሽነት
1000 ሰወች ወደ ኢስላም እንደተመሙ ተነግሯል።

ይህ ትልቅ የአሏህ ተአምርና እድለኝነት ነው።

https://www.tg-me.com/ArkemMy
♡ በእያንዳንዷ ሰከንድ
መመለስ የማንችለው እስትንፋስ
ከአፋችን ትወጣለች
▼ በዚህች ውድ እስትንፋስህ ሰው አምተህ
ዑለማእን ሰድበህ እራስህን ኪሳራ ውስጥ
አትጣል ... ባይሆን
▼ ለወዲያኛው ሀገርህ { አኺራ }
የሚጠቀምህን ነገር ተናገርበት ።
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

@ArkemMy

@ArkemMy
@ArkemMy

@ArkemMy

@
2025/10/16 23:09:00
Back to Top
HTML Embed Code: