Telegram Web Link
ለማጥቃት የሄደው አራዊት ሰራዊት ቀልጦ ቀረ!

አራዊት ሰራዊቱና አባሪ ኃይሎቹ ከአዊ ዞን አዘናና ግምጃቤት በመነሳት በሁለት አቅጣጫ ወደ ችባ ችባሳ የጥቃት እቅድ ነድፈው ጉዞ ይጀምራሉ። የአማራ ፋኖ በጎጃም ደግሞ የጅምሩ ጀምሮ የአራዊት ሰራዊቱ የእቅድ መረጃ አለውና የጓጉሳ ብርጌድና የቡሬ ዳሞት ብርጌድ ዘመነ ካሴ ሻለቃ ለግዳጅ ዝግጁ ሆኑ።

አራዊት ሰራዊቱ በሁለት አቅጣጫ ችባ ችባሳ ሲደርስ ግን በሻለቃ አዳነ አንዷለም የሚመራው የጓጉሳ ብርጌድና እና በሃምሳ አለቃ ጌታቸው ታረቀኝ የሚመራው የዘመነ ካሴ የሻለቃ በቅፅበት ከበባ ውስጥ አስገብተው ይወቁት ጀመር። ውጊያ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 7:00 ለተከታታይ 5 ሰዓታት ተደረገ።

ፋሽስታዊው አገዛዝ "ጥምር ጦር" እያለ የሚጠራው ኃይል በርካታ አባሎቹን ለምድር ገበረ፤ ጥቂት የማይባሉትን ደግሞ ለሆስፒታል አልጋ አስረከበ። "የመከላከያ" ፓትሮል መኪናው ሳይቀር ከበርካታ የነፍስወከፍ መሳሪያዎች ጋር በፋኖዎቻችን ገቢ ሆነ። ፋኖዎቻችን ለጥንቃቄ በሚል የመኪና ጉዞ ያቆሙ በመሆኑ፣ ፓትሮሏ መጨረሻ መንቦግቦግ እንደነበርም ለማወቅ ችለናል። በሶምሶማ ከመጣው የአገዛዙ ኃይል ውስጥ በህይወት የተረፈውም፣ ሽምጥ እየጋለበ ወደመጣበት መፈረጠጡ ታውቋል።

ይህንን ወደል ጣፋጭ የድል ዜና ከሰማን በኋላ ውጊያውን የመሩትን የፋኖ አመራሮቻችንን "እህሳ?" አልናቸው። <<ወቅቱ አጭዶ የመከመር ደንበኛ ጊዜ በመሆኑ ሲሮጥ የመጣውን አጥብቀን ለማጫን ዝግጅታችንን በሚገባ አጠናቀናል>> የሚል ነበር መልሳቸው!
@BW
መረጃ ጎጃም
ሰከላ!
አዲስ ቅዳም
ዱርቤቴ
አማሪት
ዳንግላ
ምርኮኛ
ሙትና ቁስለኛ ሚኒሻ አድማ ብተና እና መከላከያ  ሲኖረን የወገን ጦር ድል በድል ሆኗል።
ባንዳው ተቀንድሿል..‼️

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የኤፍራታና  ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበረው #ባንዳ አልብስ አደፍራሽ በትላንትናው ዕለት ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በቤቱ እያለ ባልታወቁ ኃይሎች ወደማይመለስበት ተሸኝቷል።

ይቀጥላል‼️

#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
#ድል_ለክንደነበልባሉ_ፋኖ💪

25/09/16 ዓ.ም
የኦሮሙማው ቡድን ግፍ !
--------

ከደቡብ ክልል ከወላይታና ከአዋሳ በግድ ታፍሰዉ ወደ ብር ሸለቆ የግዳጅ ዉትድርና ገብተዉ በሌሊትና በቀን አምልጠዉ። ለአባይ ብርጌድ ለብር ሸለቆ ቀጠና አካባቢ ፋኖዎች እጅ የሰጡ ህፃናት ናቸዉ።

.
#በምንም ታምር
የዚህ ዘመን አማራ መፈጸም የሌለበት

1ኛ ለዚህ ስረዓት ለመገዛት መሞከር
2ኛ ትጥቅ መፍታት
3ኛ የህልውና ትግሉን አለመደገፍ
4ኛ ድርድር በሚል ትግሉን ማደናቀፍ
5ኛ በህልውና ትግሉ መሰላቸት

እነዚህን ከፈጸመ ጠላት እንደሚለው አማራ ታሪክ ሆኖ በታሪክ ውስጥ ነበር የሚል ስም ብቻ ይኖረዋል።
“አማራ ለሀገሩ ዋጋ ያልከፈለበት ጊዜ የለም”ደራሲ አሰግድ መኮንን

ደራሲ አሰግድ መኮንን ዘጠኝ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል፡፡ ኮብላይ፣ ጥብቅ ምስጢር፣ አዳኝ እና ገዳይ፣ ነፀብራቅ፣ ከኢትዩጲያ ወንዞች ማዶ …በሚሉት ድርሰቶቹ ይታወቃል፡፡

ከ1983 ጀምሮ የነበረውን የፖለቲካ ጉዞም በቅርብ እንደ ጋዜጠኛ እየተከታተለ ከትቧል፡፡ ከጋዜጠኛ እና ደራሲ አሰግድ መኮንን ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

የት ተወልደህ አደግህ ከሚለው ልጀምር?
ሰሜን ሸዋ፣ ኤፍራታ እያሪኮ ከምትባል ቦታ ተወለድሁ፡፡ ያደግሁት ደግሞ እዛው ሸዋ ራምሴ ከሚባል ቦታ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ሰሜን ሸዋ ላይ ብዙ ስያሜዎች የእስራኤልን (የእብራውያንን) ይመስላል፡፡ በዚህ ዙሪያ ላይ "ከኢትዮጵያ መንዞች ማዶ" በሚል መጽሐፍ ላይ ለምን የሸዋ ስያሜ ከእብራውያን ጋር እንደተያያዘ ተንትኛለሁ፡፡ ኤፊሶን፣ ኬብሮን፣ ጌልጌል፣ ናዝሬት፣ አንፆኪያ፣ ገሊላ፣ የሚሉ ስያሜዎች አሉ፡፡

ኢትዮጵያ እና እስራኤል በብዙ ነገር የተጣመሩ ናቸው፡፡ እስራኤል የመጀመሪያዋ የኦሪት ህግ አማኝ ሀገር ናት፡፡ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በኦሪት ዘፀዓት እንደተፃፈው ዮቶር የሚባል አባት አለ፡፡ እነ ሪቻርድ ፓንክረስት እንዳጠኑት ዮቶር መነሻው ጐንደር ነው፡፡ ዮቶር የአማሮች አባት ይባላል፡፡ ዮቶር የሙሴ አማት ነው፡፡ የዮቶር ልጅ ሲፓራ የሙሴ ሚስት ናት፡፡ ስለዚህ ኦሪት በእስራኤላዊው ሙሴ እና በኢትዮጵያዊቷ ሲፓራ በአቻነት ተጀምሯል ማለት ነው፡፡

በግብፅ በሲና በረሀ ሙሴ እስራኤልን ሲመራ የአስተዳድር እርከን አስር አለቃ፣ አምሳ አለቃ… የሚል ያስተማረው አማቱ ካህኑ ዮቶር ነው፡፡ የሰው ልጆችን የሚስተዳደሩበትን የስልጣን እርከን ዮቶር ሠራ፡፡ ሙሴ እና ሲጳራ ኦሪት ህግን ተቀብለዋል፡፡ ስለዚህ ሸዋም የኢትዮጵያ መሀል እንደመሆኑ መጠን ከሙሴ ሀገር ከሆነችው ከእስራኤል ስያሜን ተጋርቷል፡፡

ራስህን አስተዋውቅ ብለህ ብዙ መንፈሳዊ ነገር ተነተህልኝ፡፡ ሐይማኖታዊ ትምህርት ተምረሀል?
አዎ! ዳዊት ደግሚያለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አነባለሁ፡፡ ሐይማኖታዊ ትምህርት ተከታትያለሁ፡፡ አጠናለሁም፡፡…

በድርሠት ከአንባቢያን ጋር የተገናኘኸው በ1991 ነው?
አይደለም፡፡ በ1985 ዓ.ም ጀምሬ በየጋዜጦች እጽፍ ነበር፡፡ የመጀመሪያ መጽሐፌን በ1991 ነው ያሳታምሁት፡፡ ኮብላይ ይሰኛል፡፡ ከኮብላይ በፊት ግን ጥብቅ ምስጢር የሚለውን መጽሐፌን ነበር ለማሳተም የሞከርሁት፡፡ ለማሳተም ወደ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት ሄድሁ፡፡ ስሄድ የድርጅቱ ኃላፊ ሥነ ጽሑፍ በእጀ እንዳልነካ አድርጐ ሰደበኝ፡፡ ምክንያቱን ሳጠና ሜጋ የህወኃት ስለነበር፣ ህወኃትን የሚተች መጽሐፍ በመጻፌ የመጣ ጣጣ ነው፡፡

ጥብቅ ምስጢር ኢትዮጵያ አንድነት የሚያተኩር ልብወለድ ነው፤ ነገር ግን በሌሎች መጻሕፍት ዳግም ተመልሰህ ስለ አማራ መደራጀት ጽፈሀል…

አስተዳድግ ወሳኝ ነው፡፡ በደርግ ጊዜ ስማር ለኢትዮጵያነት ቅርብ እንድሆን አድርጐኛል፡፡ ደርግ ፊውዳል አና አቆርቋዥ ብሎ መጀመሪያ የመታው አማራውን ቢሆንም፣ እየገደለም ስለ ኢትዮጵያዊነት ይሰብክ ነበር፡፡

በ1967 ዓ.ም 60 ባለስልጣናት ሲረሸኑ ብዙዎች የመንዝ እና የጐጃም አማራዎች ነበሩ፡፡ መንዝን እና ይፋትን ደርግ ከ1967 እስከ 1971 በአውሮፕላን ደብድቦታል፡፡ መንዝ ግሸንን ሁሉ ደብድቦታል፡፡ ይሄን የሚያደርገው በአውሮፕላን ነው፡፡ አውሮፕላኑ ዝናብ አይደለም የሚጥለው፡፡ ጥይት ነው፡፡

አማራ ለሀገሩ ዋጋ ያልከፈለበት ጊዜ የለም፡፡ ህወኃትም፣ ጣሊያንም ሸዋን እና በአጠቃላይ አማራውን በተለየ መንገድ በድለውታል፡፡ ምክንያቱም ሸዋ ማዕከላዊ ቦታ በመሆኑ፣ ሸዋን በማድከም ኢትዮጵያን መግዛት ይቻላል የሚል እሳቤ ነበራቸው፡፡ የሸዋ አማራ ከሌላው አማራ የተለየ ገዥ መደብ ሆኖ ሳይሆን ግፍ የበዛበት፣ ለባህር በሩ እና ለማዕከላዊው ቦታ ቅርብ በመሆኑ ነው፡፡ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባም ሸዋ ላይ ናት፡፡ ሸዋን መያዝ ሙሉ ኢትዮጵያን እንደመያዝ ይቆጠራል፡፡

በሸዋ ከጣሊያን እስከ ህወኃት በተሰራው ግፍ ምክንያት መሪ አላገኘም፡፡ ሸዋ እንደ ብአዴን እንኳን ሸዋውን የሚወክል ሰው የለውም፡፡ ብዙዎቹ ሞራላቸው የተመታ፣ ሲታዘዙ የሚሮጡ ናቸው፡፡ ህወኃት ወደ መቀሌ ቢሸሽም ሸዋ ላይ ግን አለ፡፡ ሸዋን የሚመሩት በብዛት ዛሬም ህወኃቶች ናቸው፡፡ ህወኃቶች መጀመሪያ ሸዋን ለማድከም ተሯሩጠው ነበር፤ አሁን ደግሞ ጐንደርን ለማሸበር እየተሯሯጡ ነው፡፡ ይሄን ሁሉ ሳይ እና ሳጠና ስለአማራ መጻፍ ለጭንቅላቴ ግዴታ ሆነብኝ፤ እና ስለአማራነት መፃፍ ጀመርሁ፡፡

ከጣሊያን እስከ ሌሎች የሀገራችን ብሔርተኞች ለምን በአማራው ላይ ጠላት ሆነው ተነሱ?
ለዚህ ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች ይነሳሉ፡፡ አንደኛው የአድዋ ጦርነት ነው፡፡ የአድዋ ድል የሁሉም ነው፡፡ መሪው ግን አማራው ብለው ስለሚስቡ አማራን ቅኝ ገዥዎች ይጠላሉ፡፡ የምኒልክ የሀገር ግንባታ ታሪክን ሌሎች ብሔርተኞችም በመልካም አልተመለከቱትም፡፡ አማራውን ለመውቀስ አፄ ምኒልክን ማጠልሸት ዋና ተግባር ነው፡፡

በምኒልክ የተመራው የአድዋ ጦርነት ለጥቁር የሰው ዘሮች በሙሉ ድል ነው፡፡ ድሉ የተመራው በሽዋው አማራ በምኒልክ በመሆኑ ቅኝ ገዥዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራን መምታት እንደ ስተራቴጂ ተጠቀሙበት፡፡ ሌላው ከኢትዮጵያዊነት ጋር በተለየ ሁኔታ ጥብቅ ትስስር ያለው አማራው ነው ብለው ስለሚያስቡ ኢትዮጵያን ለማድከም አማራን መምታት አንዱ የማሸነፊያ ስልታቸው አደረጉት፡፡

ጣሊያን በ1928 ወደ ኢትዮጰያ ሲመጣ ሰሜን ጫፍ ተቀምጦ አማራ የህዝቦች ሁሉ እና የዴሞክራሲ ጠላት አድርጐ ይሰብክ ነበር፡፡

አማራ ለእስልምና ሐይማኖት ፀር እንደሆነ እየሰበከ ወሎን ለመቆጣጠር ፈልጐ ነበር፡፡ ነገር ገነ አማራ ከአክሱም ጀምሮ እስልምናን ፈጥኖ የተቀበለ ህዝብ ነው፡፡ ጣሊያን እስልምናን ወዶ ሳይሆን ለመለያየት ተጠቅሞበታል፡፡ አማራ በረጅም ጊዜ ሥርዓቱ እስልምናን፣ ክርስትናን፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን በብዝኃነት አቻችሎ የኖረ ህዝብ ነው፡፡ ግን ጣሊያን ይሄን ሀቅ ክዶ አማራን በፀረ ህዝብነት ፈርጆ ሰብኳል፡፡

ካንተ ቀድሞ ግን ስለአማራ የፃፈ አለ?
በመጽሔት እና በጋዜጣ ካልሆነ በስተቀር በመጽሐፍ የለም፡፡ በ1990ዎቹ ጀምሬ እጽፋለሁ፡፡ ፕሮፈሰር አስራት እስር ቤት ሲገቡ ጀምሬ ነው መጻፍ የጀመርሁት፡፡ ሁሉ ነገር ለነበረው፤ ሁሉን ነገር ላጣው አማራ አለመፃፍ አይቻልም፡፡ ሁሉም በጠላትነት የተነሳበት ህዝብ ነው፡፡ ለአማራ አማራው እንኳ ሲሞት አልደረሰለትም፡፡ አማራው ራሱ አሳዳጅ እና ተሳዳጅ ሆኖ ነው የኖረው፡፡ ነፍጠኛ ነው፣ ግደሉት ብለው ያወጁት እኮ አማራን ወክያለሁ ብሎ የክልሉን የማስተዳደር ኃላፊነት ይዞ የነበረው የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ናቸው፡፡ ትምክህተኛ የሚሉት የቀድሞ የብአዴን መሪዎች ናቸው፡፡

አማራ በሌላ ወገን በጉዲፈቻ ሲተዳደር የነበረ ህዝብ ነው፡፡ አማራ ብራና ዳምጦ፣ ለሀገር ብሎም ለዓለም ስልጣኔን አሳይቷል፡፡ ግን ህዝቦች ሁሉ ጠላት ሆነው ተነስተውበት እንዲሳደድ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ካልተፃፈ ሌላ ስለምንም አይፃፍም፡፡

ፕሮፌሰር አስራትን ታውቃቸው ነበር?
ከውስጥ ምንጮቻችን የደረሰን የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ!

የተለያዮ አመራሮቻችንን በስም መጥራት "ድብቅ ድርድር ጀምረዋል" የምትል የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እንዲሰራጭና እንዲሰራበት ለብልፅግናው መንጋ ስምሪት መሰጠቱን ባህርዳር ዊክሊክስ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል። ዓላማው የአመራሮቻችንን ተዓማኒነት ማሳጣትና ክፍፍል መፍጠር ነው።
የመረጃን ሃይል ያየንበት ደንበኛ ድል አስመዝግበናል። አስገራሚ እቅድ፣ አስገራሚ የኦፕሬሽን አፈጻጸም! መጀመሪያ በደፈጣ፣ ቀጥለው በቆረጣ ነድፈው ነድለው ጥለውታል።

እንመለስበታለን!
በቁጥጥር ስር የዋሉት ባንዳዎች
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ስም ዝርዝራቸው ይፋ ሆነ፦ ሰኞ ዕለት በፋኖ ቁጥጥር ስር የዋሉት የአምሐራ ሳይንት ወረዳ ባንዳዎች ቁጥር 12 ደርሷል፤

ከአርሶ አደሩ ግብር እየሰበሰቡ ለጥምር ጦር ቀለብ ሲሰፍሩ እና በግና ፍየል እየገዙ ህዝብን ለሚጨፈጭፍ አረመኔ ስጋ የሚቀልቡት የአምሐራ ሳይንት የንግድ እና ገቢዎች ፅ/ቤቶች ባለሙያዎች በብዛት የተካተቱበት የመንግስት አሽቃቦጮች ቡድን ግብር ሰብስቦ በመኪና ሲመለስ በፋኖ እጅ መግባቱ ይታወሳል። የእነዚህ ኮልኮሌዎች ስም እና ሀላፊነት እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1·ወንድምሰው እንየው- የፍርድ ቤት የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢ

2. መስፍን ደረሰ አየለ- የግብርና ትምህርት ኮሙኒኬሽን ባለሙያ

3. እንዳለ አማረ ታደለ- የኮምፒውተር ባለሙያ

4. አለምነው ገሰሰ አበባው- ክትትል ባለሙያ

5. ጀንበሩ ብርሀኑ ጋሻው- የታክስ ሂሳብ ሰራተኛ

6. አሻግሬ አድማሱ አወቀ- የኢንስፔክሽን ባለሙያ

7. ገሰሰ ገበያው ታደሰ- የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ

8. መለሰ ወዳጄ እሸቱ- የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያ

9· አንተነህ ታረቀ ታደሰ- የክትትል ባለሙያ

10· ጀንበሩ ተስፋው መንግስቱ- የንግድ ገበያ ልማት ባለሙያ

11· ታከለ ታደሰ ተገኘ- የሰው ሀብት ባለሙያ

12· ቃኘው አፍሬ ሊበን- ሾፌር

አሁን ላይ በፋኖ ቁጥጥር ስር ነው ያሉት፤ ነገር ግን በሸጋው ሎጋው የሚመራ የማፊያ ቡድን 200 ሺህ ብር በእያንዳንዳቸው ከተከፈለኝ እንድለቀቁ አደርጋለሁኝ ብሎ ውዥንብር በመፍጠሩ የተነሳ የመንግስት ሰራተኞች ለስራ ባልደረቦቻችን ማስለቀቂያ የሚሆን ገንዘብ እናዋጣ እያሉ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል።

የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ እስክንድር ነጋ ክፍለ ጦር በበኩሉ የተያዙት አመራሮችን በድርድር ለመልቀቅ የሚሞክር ኃይልን እንደማይታገስ እገምታለሁ። የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ የሆነው ፊታውራሪ ሀብታሙ ደምሴ (አባ ጨፍልቅ) በእንዲህ አይነት ጉዳይ ቀልድ እንደማያውቅ እስካሁን ከነበሩት ውሳኔዎቹ ተነስቼ መናገር እችላለሁ።

የተያዙ ባንዳዎች የፓለቲካ እና ወታደራዊ ስልጠና ወስደው ፋኖ ሆነው ማየት እንፈልጋለን። በድርድር ከተለቀቁ ትግሉም ትግል አይሆንም፤ ለፋኖ መልካም ስም እና ዝናም ጥሩ አይደለም። ህዝቡም በፋኖ ላይ እምነት ሊኖረው የሚችለው እነዚህ ባንዳዎች ሳይለቀቁ ሲቀሩ ነው። ያዝ ለቀቅ ከተለመደ ህዝብም በፋኖ ላይ እምነት አይኖረውም5
ከአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም የተሰጠ      አስቸኳይ መግለጫ

ሕገ መንገስቱ ሕገ አራዊት ካልሆነ ሕግ ይከበር !
አንድ የሆነን ማሕበረሰብ ወይም አካል አንድ ሁኑ ማለት ይከብዳል፡፡ ምንአልባትም የተሻለ ሊሆን የሚችለው የበለጠ አንድ ሁኑ ማለት ሳይሻል አይቀርም፡፡ በመሰረቱ፣አንድ እንሁን ያልነው አንድ የመሆን ተፈጥሯዊ ማንነታችን ስለሚፈቅድ ነው፡፡

መገለጫችን ስለሆነና ስለምንችል እንዲሁም አንድ መሆን ማለት የግዴታ አንድ አይነት ማለትም አይደለም፡፡  ‹‹ አንድ እንሁን ›› ያልነው አንድ አለመሆናችን ያስከተለውን፤ያስከፈለንን እና የሚስከፍለንን ከባድ ዋጋ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው ፡፡ የአማራ ፋኖ ፣ የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም እንዲሁም መላው የአማራ ሕዝብ ፈጽሞ ከማይደራደርባቸው ቁልፍ አበይት ጉዳዮች አንዱ አምሓራዊ አንድነቱ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ትናንቱ እኛ አምሓራዊያን ከኢትዮጵያዊነት ሊያወርዱን አማሓራዊነታችን በታትነው እንደ አናሳ ብሔረሰብ ሊሳንስኑን ለሚመጡ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጠላቶች ረመጥ እሳት ነን፡፡  የነጻነት ታጋይን ልታስር ትችላለህ እንጅ ነጻነትን አታስርም ፤ ታጋይን ልትገድል ትችላለህ እንጅ ዓላማን የሰነቀ ትግል ሕያው ሆኖ ስለሚቀጥል ትግል አይሞትም፡፡

ዛሬ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከፊት በማስቀደሙና ዲሞክራሲያዊ የአምሓራዊ ብሔርተኝነቱን በማስቀደሙ ብቻ ለዘርፈ ብዙ ስቃይና መከራ ተዳርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ሊያበቃ ይገባል እያልን አሁናዊ የሀገሪቱን ሁኔታ በጥልቅ በመረዳት የሚከተለውን መግለጫ አውጥተናል፡፡ ሰጠናል፡፡

ከምክክር ኮሚሽን አንጻር የምናነሳቸው ጥያቄዎች፤-

1ኛ. የአምሓራ ሕዝብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በሆነበት ሰዐት እና የአምሓራ ሕዝብ በጦርነት ላይ በሚገኝበትና አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት በአልተደረገበት ሁኔታ
2ኛ. በሕዝብ ጥያቄ የተያዙ ምሁራንና አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሚሣተፉ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞችና ወጣቶች በታሰሩበት ሑኔታ እንዲሁም  በሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት ያሉ ምሁር አምሓራዊያን በማንነታቸው ምክንያት እየተገፉና እየተሳደዱ በሚገኙበት ሁኔታ

3ኛ. በሃገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ሚና በሚጫወቱ የእምነት ተቋማት ላይ ለአብነትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ አምሓራ ሕዝብ ስቃይና መከራ ስደት እየተቀበለችበት ባለችበት ሰዐት እና በሃገራዊ አጀንዳ ተሳታፊ እንዳትሆን በተደረጉበት ወቅት

4ኛ. አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች ዝግ በተደረጉበት ሁኔታ ከዚህ በተጨማሪም  መዋቅራዊ ተሳትፎ የሚደረግበት ምንም አይነት አደረጃጀት እና ተዋረድ በሌለበት ሁኔታ

5ኛ. ነጻ እና ገለልተኛ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችን በአገለለ ሁኔታ እና አዲስ አበባ ጨምሮ ሁሉም ክልሎች የሚኖሩ የአምሓራ ተወላጆችን አካታች እና አሳታፊ ባላደረገ መልኩ የተካሄደው የምክክር ሒደት

6ኛ. ሁሉም የተቃዋሚ ፖርቲዎች በአልተሳተፉበትና ከምክክሩ በተገለሉበት ሁኔታ

7ኛ. የአማሓራ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ ክተት አዋጅ በታወጀበት ሰዐት የትኛዋ ኢትዮጵያ ናት ስትመክር የነበረችው እያልን ጥያቄችን እያቀረብን ከሐገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር የነበረን ሒደት እና ስለ ኮሚሽኑ አሰራርና ግልጸኝነት በቀጣይ ራሱን በቻለ መግለጫ ለመላው የአማራ ህዝብና ለኢትዮጵያዊያን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

            ስለሆነም 


አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ከመጠናቀቁ አንጻር ያለን አቋም ፤-
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ተጠናቋል፡፡

  በዚህ መሠረትም

1ኛ. በአዋጁ አተገባበር ዐውድ ውስጥ የቆዩ በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ የታፈኑ እና ለስቃይ የተዳረጉ የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ

2ኛ. በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎችና በመላው አምሓራዊያን ላይ የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከአሁን በኃላ በሕገ መንግስቱ መሠረት ተቀባይነት ስለሌለው ለሕገ መንግስቱ ስርዓት መከበር ‹‹ ሕግ እያስከበር ›› ነው የሚሉ አካላት የሚፈጽሙት የኮማንድ ፖስት ተግባር ሁሉ ሕገ - አራዊት መሆኑን እንድታውቁት

3ኛ. በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ፈርሶ የክልሉ ሕዝብ በነጻነት ከሰዐት እላፊ ገደብ ወጥቶ ሠላማዊ ኑሮውን የሚመራበት ምቹ ሁኔታዎች ለመፍጠር ሁሉም አካል የጋራ ተሳትፎና ርብርብ እንዲያደርግ

4ኛ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ምክንያት በጦርነቱ የተጎዱ አምሓራዊያን ለማቋቋምና ለማገዝ ሁሉም በየአካባቢው የድርሻውን እንዲወጣ እንዲሁም አርምሞ ላይ የነበራችሁ በአምሓራዊያን ስም የተደራጃችሁ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የተቋቋማችሁበትን ዓላማ ትልቁ ፍጡር ሰው ከሌለ እናተም የላችሁምና ሰውን ለማዳን በምናደርገው ርብርብ ከጎናችን እንድትቆሙ እየጠይቅን

5ኛ. ‹‹ አንድ ሁኑ ! ›› ወዳዳችሁም ጠላችሁም አምሓራዊያን አንድ ሁነናል ፡፡ ቃሉም በተግባር ተፈጽሟል ፡፡ ወንድም እህቶቻችን ፤ አባት እናቶቻችን የሆናችሁ አምሓራዊ በሁለት ጎራ ተከፍላችሁ የቤተሰብ ጦርነት የከፈታችሁ ወገኖች የጠላት መሳቂና መሳለቂያ ሳንሆን አንድ እንሁን፡፡ ጊዜው የአንድነት ሀይሎች የአሸናፊነት ዘመን እያልን

ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ፤-  በተሳሳተ የ50 ዓመት የፖለቲካ ታሪክና ትርክ በመርዝ በተለወሰ ሴራ ከወንድም የትግራይ ሕዝብ ጋር ተዋጋን፡፡ የትግራይ ሕዝብና አምሓራዊያን ምን አተረፍን ? 1 ሚሊየን በላይ አምራች ክብር የሆነውን ሰው አጣን ፤ በመቶሽዎች አካላቸው ጉደለ ፤ በትሪሊየን የሚቆጠር ሀብት ወደመ ሕዝብ ተጎዳ የፖለቲካ ቁማርተኞች ግን እስከ ከራባታቸው በሐሴትና በደስታ አሉ፡፡

ስለዚህ የእኛን ደስታ የነጠቁ ቁማርተኞች ወደ ጎን በመተው ሕዝብ ለሕዝብ ወዳጅነታችን እናጠናክር ዘንድ በጋራ እንድንሰራ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የተከበርከው የኦሮሚያ ሕዝብ ፤- በኦሮማራ ሴራ ሳይገባን በቅንነት የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው ብለን ጎንደር ላይ መስዋዕትነት ከፍለናል ፡፡ እናተም ጣና ኬኛ ብላችሁ በአምሓራዊያን መዲና ባህርዳር የጣና እንቦጭን አረም አርማችዋል ፡፡

የሚያምርብን ይህ ነው፡፡ እኛ አልተጣላንም ፡፡ አንጣላም ፡፡ የጋራ እንቦጭ አረም ለማረም ግን ዛሬም የኦሮሞና አምሓራዊነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናችን በተግባር እንድናሳይ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለተከበራችሁ ወንድም የሌሎች ክልል ህዝቦች፤- አምሓራ ከማስተዋል፣ ጥበብን ከእውቀት፣ፈሪያ እግዚአብሔርን ፣ከሀገር ፍቅር ጋር አስተባብሮ የረቀቀ ሕዝባዊነት መገለጫ ነው፡፡ አምሓራነት ከመለያየት አንድነትን፤ከባርነት ነጻነትን ፤ ከውርደት ሞትን ፤ከመግፋት መገፋትን የሚል የአስተዋይ ሕዝብ ስነልቦናዊ ውቅር አናጭ ማንነት በመሆኑ በልዩነት ውበትን በመፍጠር ለዘመናት ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተጋብቶ፣ተዋልዶና ተዋዶ ኑራል ፡፡

ዛሬም ለወደፊቱም ይኖራል፡፡ በመሆኑም አብሮነታችን የጋራ መገለጫችን ነውና አብሮነታችን በጽኑ መሰረት ላይ እንድናስቀጥል በአምሓራዊያን ስም እንጠይቃለን፡፡

ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም ! ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም                            ባህርዳር
ቅጠረኛው እና ተላላኪው ብአዴን በፋኖ ስም ያለ ቤት እና ንብረት መወረስ አለበት የሚል ትዕዛዝ ማውረዱ ተሰምቷል። ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታዎች የፋኖዎችን ቤት ማቃጠል፣ ንብረታቸውን ጭኖ መውሰድ እና ቤተሰቦቻቸውን የማሰር እና የማንገላታት ሥራ ሲፈጽም እንደነበር ይታወቃል።

ከሰሞኑ፤ አደረኩ ባለው ግምገማ 'ለፋኖ መሪ ለሆኑት፣ በስማቸው ደብዳቤ ተጽፎ እንዲደርሳቸው በማድረግ በይቅርታ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው እንዲገቡ ጥረት እናድርግ' ይህን ካልተቀበሉ ግን፣ በሥማቸው ያለውን ቤት እና ንብረት መውረስ አለብን የሚል ውሳኔ ላይ ደርሷል። እነሱን የሚረዳ የቅርብ ዘመድ ካለም፣ የዘመድ አዝማዳቸው ሃብትና ንብረትም መወረስ አለበት ማለቱ ታውቋል።

በዚህ መነሻ፣ ደብረ ማርቆስን ጨምሮ በተያዩ ከተሞች ነጋዴዎችን 'የፋኖ መረጃ፣ ሎጅስቲክ እና ደጋፊ ናችሁ' በሚል ነዴዎችን በጅምላ ማስር፣ ማዋክብ፣ ማስፈራራት እና ቤትቻውን ማሸግ እየሰራ ይገኛል።

ስለሆነም፤ ሕዝባችን ይህን የአገዛዙን ዘራፊነት ተገንዝቦ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርግ እናሳስባለን
እምሽክ !

በደቡብ ጎንደር ዞን #ላይ_ጋይንት ከ107 በላይ የጁላ ሰራዊት እና 9 ባንዳ ሚሊሻዎች እምሽክ ተደርገዋል። በዚህ ውጊያ ከ60 በላይ የጁላ ሰራዊት ደግሞ ቁስለኛ ተደርጓል።

ይህን ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ያስተናገደው አገዛዙ ኮለኔል ታደሰን ገድያለው ብሎ ቢያስወራም ኮለኔሉ ግን አሁንም ስራ ላይ ናቸው። ከወገን መጠነኛ ቁስለት ከማጋጠም ውጭ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ያገኘንው መረጃ ያመላክታል
መረጃ -ጎንደር
፨፨፨፨፨፨፨፨

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜዳድ እና በጌምድር ክፍለጦሮች በቋራ እልህ አስጨራሽ ውጊያ እያደረጉ ነው።

ክፈፍለጦሩቹ በጠላት ሐይል ላይ የበላይነትን ሲቀዳጁ ጠላት በበኩሉ ከቀጠናው ለማፈግፈግ ተገዷል። በአሁኑ ሰዓት ከገጠር አካባቢወች በተጨማሪ ሽንፋ ከተማም በፋኖዎቹ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

የአድማ ብተናና የፖሊስ ሐይል እጅ እንስጥ እያለ እየተማፀነ ሲሆን መከላከያ ሐይል ተራራ ላይ ተከቧል ሲል የዕዙ ቃል አቀባይ ተናግሯል።

በተያያዘ መረጃ መንግስት ተብየው ቡድን የህዝብ ማመላለሻ አውሮፕላን ተጠቅሞ አየር ወለድ ለማውረድ ያደረገውን ሙከራ እንዳከሸፉበት  ቃል አቀባዩ ተናግሯል። በዛሬው ዕለት ሚካኤል ደብር አፄ መስክ የተባለ ሰፊ ሜዳ ላይ አየር ወለድ ለማውረድ የሞከረ ሲሆን በሙከራ ላይ እንዳሉ በተከፈተበት ተኩስ ሳይሳካለት ቀርቷል ብሏል።

የሲብል  መንገደኞች አውሮፕላን በተደጋጋሚ እየፈፀመው ባለው የጦር ወንጀል የሚጠየቅበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ብሏል ቃል አቀባዩ ኮማንዶ ያለው አዱኛ።

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ 
ዋና አዛዥ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ 

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
የጠላትን ቅስም ከሁለት "ቋቋቋ" ያደረገው ድል!

ከሰሞኑን ከዘገብናቸው ፊልም የሚመስሉ የነበልባሎቻችን ድል ውስጥ ወደ በረኸት ለመግባት በ17 መኪኖች ተግተልትሎ የመጣውን አራዊት ሰራዊት አብዛኛው ኃይሉን መንገድ ላይ ያስቀረንበት ነው።

ይህንን ተከትሎም ሁለት አስገራሚ ነገሮች መፈጠራቸውን ሰምተናል፦

1. የበረኸት ፋኖ እንደማይቀመስ ያወቀው አራዊት ሰራዊት እንደምንም የተረፈውን ኃይሉን ከበረኸት እስከ ምንጃር ሸንኮራ ድረስ 72 ኪሎሜትሮችን ደፈጣ ፍራቻ በእግር እየተጓዘ ተመልሷል። ከሞጆ በመኪና ተግተልትሎ መጣ… በደፈጣ ተራገፈ… ቀሪው በእግሩ እየተንፏቀቀ ወደ ሞጆ ተመለሰ።

2. ከቀን ግንቦት 23 እስከ ግንቦት 28 ድረስ ደግሞ የተጎዱ ወታደራዊ አመራሮች እና ወታደሮች በሄሊኮፕተር ሲያወጣ እንደነበር ባህርዳር ዊክሊክስ ለማወቅ ችለናል። 

ይህ ለጠላት ቅስም ሰባሪ የሆነን ታሪካዊ ድል የተመዘገበበትን አውደውጊያና ኦፕሬሽን የመራው በትግል ስሙ ሻለቃ አዝንበው የሚባል ወጣት፣ ቆፍጣና ነበልባል የከሰም ክፍለጦር ዋና አዛዥ ነው።
#ማስጠንቀቂያ

በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ የግዮን ሸመቾች ህ/ስ/ማ/ኋ/የተወሠነ የግል ማህበር ተቋም ውስጥ ንፁሐንን የሚያሳፍኑና በስርቆት ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከአፀያፊ እኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ተጠቆመ

1,መስፍን ፈጠነ=ሊቀመንበር
2,አምሳለ አረፍዓይኔ= ፀሀፊ
3,አለሙ ገላየ=ስራ አስኪያጅ
በጋራ በመተባበር ተቋሙን የመዘበሩ ሲሆን ንፁሃንን ለፋሽስቱ ስርዓት ሰለባ እንዲሆኑ ማድረጋቸው ተረጋግጧል
ሰሞነኛ የብልፅግና ጀነራሎችና ካድሬዎች ስብከት " እናንተ ፋኖን እንደምንም አምጡልን፣ እናንተ ያመጣችኃቸውን አይደለም መግደል ቀርቶ በጥፊ አንነካቸውም፣ እናንተ አምጧቸው እንጅ እኛ ወልቃይት ጠገዴን ጠለምትን ራያን እንጠብቃለን" ሁኗል። በጥፊ እንደተመታህ ሲገባህ ጥፊ ትዝ ይልሃል😁

ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ አላማጣ የብልፅግና ስልጣን ማስጠበቂያ የህዝባችን ደግሞ የሰቀቀን አጀንዳ መሆን አይችልም። እድሜ ልክ ጦርነት የሚፈልግ ካለ ይሞክረው። ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ አላማጣ ብልፅግና እንዳቀደው የሚድንበት ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ መቀበሪያው የፖለቲካ ፣ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ማዕከል ነው። አማራ ወይ ፍንክች።

በነገራችን ላይ ብልፅግና ከተወገደ ህውሃት አንድ ቀን አያድርም። እርስ በርስ ነው የሚጠባበቁት። ብልፅግና ካለ የህውሃት ሰርቫይቫል ይቀጥላል።

ድል ለፋኖ
ሰራዊቱ ፎጣ ሊለብስ ነው - ማረጋገጫ አግኝተናል!

ምንጮቻችንን ጠቅሰን በትናንትናው ዕለት ላወጣነው የቅድመ ጥንቃቄ መረጃ ማረጋገጫ አግኝተናል። ከታች በቁጥር ሁለት ላይ እንደሚታየው፣ "አርሶአደር መስሎ ስምሪት የሚወስድ አራዊት ሰራዊት ተመልምሎ መሰማራቱን" ገልፀን ነበር።

ዛሬ ያገኘነው መረጃ የትናንትናውን የሚያጠናክር ሆኖ አግኝተነዋል -- "በሺዎች የሚቆጠር ፎጣ ተገዝቶ ወደ ጎጃም ቀጠና ለስርጭት መዘጋጀቱ" ታውቋል።

ይህ ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎቻችን እንዲደርስ በማዛመት አግዙን።
2024/06/17 08:39:48
Back to Top
HTML Embed Code: