Telegram Web Link
ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?

³⁶ ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።

³⁷ በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።

³⁸ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥

³⁹ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።
ባለራዕይ ትክክለኛው ዓለሙ አሁን ያለበትና በስጋ ዓይን የሚታየው ዓለም ሳይሆን በልቡ የሚያየው ዓለም ነው።🔥

ራዕይ የማይታየውን የምታይበት የማይቻለውን የምትችልበት ከውስጠኛው ማንነትህ የሚጮህ ድምፅ ነው።🔥

የመኖር አቅምህ ጉልበት እንዲኖረውና ነገህ የናፍቆት እንዲሆን ከፈለክ ጥርት ያለ የሕይወት ራዕይ ይኑርህ🔥

#Evangelist_Bina
ራዕይ የተፈጠርክለት የሕይወትህ ዓላማ ነው።

ራዕይ የምትኖርበትን አላማ አጥርተህ የምታይበት የልቦና አይን ነው።

የተፈጠርክለትን እስካልኖርክ ድረስ በሕይወትህ በፍፁም ደስተኛ ልትሆን አትችልም።

በሕይወታችን እውነተኛ ደስታ የሚኖረን ከውጪ በምናገኘው ቁሳዊ ነገር ሳይሆን ውስጣችን ያለውን ራዕይ መኖር ስንጀምር ነው።

ሕይወት ጉልበት የሚኖራት ሕይወት ኃይል የሚኖራት ከራዕይ በሪዕይ ለራዕይ ሲኖር ነው።

ራዕይ የሕይወት ጉልበት የሕይወት ነዳጅ ነው።


#Evangelist_Bina
joy like a river
Peace like a fountain
#my_life_is_sweeter

Joy overflow 😍😍
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤
— ሐዋርያት 10፥38


ዛሬም እግዚአብሔር በኢየሱስ ይሰራል ኢየሱስ ትናንትናም ዛሬም እስከ ዘለዓለም ያው።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
በሕይወት ልምምድህ የምትፈልገውን ነገር ሳይሆን ራዕይህ የሚፈልገውን ነገር አድርግ።

ለራዕይህ እንዳትኖር (እንዳትገኝ) ከሚያደርጉህ ሰዎችም ሆኑ ልምምዶች በፍጥነት ሽሽ ራቅ። ምክኒያቱም እየገደሉህ ነው።

በምድር ላይ የምትኖርበት ብቸኛው ምክኒያት ራዕይህ ነው።

#Evangelist_Bina
"የጌታን #ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።"ሐዋ. ሥራ 2:21
#ኢየሱስ

ስሙ ከስሞች ሁሉ የተለየ የመለኮትን አቅም ና ስልጣን የተሸከመ እሱም መለኮት የሆነ ስም ነው። በጠራነው ቁጥር ተአምራት ፡ በጠራነው ቁጥር ድንቅ ፡በጠራነው ቁጥር መዳን ፡ በጠራነው ቁጥር ፈውስ ፡ በጠራነው ቁጥር ደስታ ና ሀሴት የሞላን እና የሚሞላን ስም……

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ
የምኖረውም የምሞተውም ለወንጌል ነው።🔥

ወንጌል ለማዳን የሆነ የእግዚአብሔር ኃይል ነው🔥
יְהֹוָה צִדְקֵנוּ
Yᵉhôvâh tsidqênûw #እግዚአብሔር_ጽድቃችን

በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም ስም፦ #እግዚአብሔር_ጽድቃችን ተብሎ ነው።
— ኤርምያስ 23፥6

በእርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም በሰላም ይኖራል፤ የሚጠራበትም ስም፣ ‘
#እግዚአብሔር_ጽድቃችን’ የሚል ነው።
— ኤርምያስ 23፥6 (አዲሱ መ.ት)

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤
#እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ #ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኖአል።
— 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30 (አዲሱ መ.ት)

እኛ በእርሱ ሆነን
#የእግዚአብሔር_ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።
— 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥21 (አዲሱ መ.ት)


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የሰይጣን የዘመናት ጠላትነት ኢየሱስ ከሚለው ስም ጋር ነው።

ይሄ ስም እንዲነገር እንዲሰበክ እንዲዘመር አይወድም ምክኒያቱም ይህ ስም በተሰበከበት በዛው ቅፅበት የሚገለጥ መለኮታዊ አሰራር አለ🔥🔥🔥🔥

ኢየሱስ የሚለው ስም የመለኮትን ዓለም የተሸከመ በኃይልና በስልጣን የተሞላ የተቀባ ስም ነው መንፈሳዊው ዓለም የሚገዛለት ብቸኛው ስም የኢየሱስ ስም ነው🔥🔥🔥

ይህንን ስም በእምነት መጥራት ስትጀምሩ መንፈስ ቅዱስ የስሙን ኃይል ስልጣንና ቅባት ማንቀሳቀስ ይጀምራል በ ዲያቢሎስም መንደር ከባድ ችግር ይፈጠራል🔥🔥🔥

ይሕንን ስም በእምነት ጥሩት መንፈስ ቅዱስ በኃይል የስሙን ስልጣን በሕይወታችሁ ይገልጠዋል🔥🔥🔥

ሐዋርያት 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ? ብለው ጠየቁአቸው።


¹⁰ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።


¹⁷ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ።

¹⁸ ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው።

¹⁹ ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው፦ እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤


የጨለማውን መንደር ኃይል የሚሰብር በስልጣን በኃይል በቅባት የተሞላ መሳሪያ የኢየሱስ ስም ተሰጥቶናል እንጠቀመዋለን🔥🔥🔥

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ባለፈ ኃጢአት ራሳችንን ማሰቃየት ለዲያቢሎስ አትሂድ አንተ አጠገቤ መሆንህ ያስደስተኛል እንደማለት ነው።

ባለፈ ኃጢአት ዘወትር እራሳችንን መውቀስ የእግዚአብሔርን የምህረትና የፍቅሩን ትልቅነት ማቅለል ነው።

ባለፈው ኃጢአት ራሰችንን ማስጨነቅ ጥፋታችንን ከእግዚአብሔር ምህረትና ፍቅር አግዝፎ እንደማየት ነው።

ማድረግ ያለብን ብቸኛው ነገር በንስሃ መመለስ ለእግዚአብሔር ድካማችንን መንገር ነው ቀጥሎ ያለው ስራ የአባታችን የእግዚአብሔር ነው። እሱ ኃጢአታችንን ደግሞ ላያስበው ምህረቱን በሕይወታችን ላይ ያፈሰዋል።

ኢሳይያስ 43
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ መተላለፍህን፦ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ
#ኃጢአትህንም #አላስብም

²⁶ አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።

“እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥
#ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ #አላስብምና።”
— ኤርምያስ 31፥34

ዓመፃቸውን እምራቸዋለሁና፥
#ኃጢአታቸውንም ደግሜ #አላስብም።”
— ዕብራውያን 8፥12

#ኃጢአታቸውንና_ዓመጻቸውንም ደግሜ #አላስብም ይላል።
— ዕብራውያን 10፥17

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እጅግ ልቀህ || ኢዮብ አሊ
ተወዳጁ የዜማ ስንቅ Tube
. እጅግ ልቀህ
ዘማሪ ኢዮብ አሊ

ሃሳባችሁ ላይ መንፈስ ቅዱስ ይላቅ ይድመቅ😭❤️


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
ከአብ ጋር ላለን የዘላለም ኪዳናዊ ሕብረት የማረጋገጫው ማሕተም የኢየሱስ ደም ነው።
ቲቶ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥

⁵ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤

⁶-⁷ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።
ተጠንቀቋቸው‼️

Negative መረዳትን ጨምረው ከሚረዳችሁ መንፈስ ቅዱስ የሚያርቋችሁን ሰዎች ተጠንቀቁ።

ዳግም የተወለደ አዲስ ፍጥረት የሆነ ክርስቲያን #ያለ መንፈስ ቅዱስ ተራ የዲያቢሎስ መጫወቻ ነው የሚሆነው።

እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። #ያለ_እኔ #ምንም #ልታደርጉ #አትችሉምና....
— ዮሐንስ 15፥5


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
የኢየሱስ ደም🔥
The Blood Of Jesus
🔥

እነርሱም #ከበጉ_ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።
— ራእይ 12፥11

መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥
#ታርደሃልና#በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።
— ራእይ 5፥9-10

ለወደደን ከኃጢአታችንም
#በደሙ ላጠበን፥
— ራእይ 1፥4-5


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
2ኛ ጢሞቴዎስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥

¹⁰-¹¹ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።
አዕምሮ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቅ ሀብት ሲሆን ካልታደሰ ደግሞ ከሰይጣን የበለጠ የሰው ቀንደኛ ጠላት ነው።

በእግዚአብሔር ተዓምራት ከግብፅ ልትወጣ ትችላለህ ከግብፅ አስተሳሰብ ግን በእግዚአብሔር ቃል እንጂ በተዐምራት አትወጣም።

እግዚአብሔር ከዓለም ወደ መንግሥቱ የጠራን ነጠላ ሊያስጥለን ሳይሆን አሮጌውን አስተሳሰብ ሊያስጥለን ነውና ነጠላ የጣልክ ክፉ አሳብ ያልጣልክ አትሁን።

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
እግዚአብሔር አውቀነውና በመንፈስ ቅዱስ ተረድተነው እንድናመልከው የሚፈልግ አምላክ ነው።

እናንተስ #ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና #ለምናውቀው እንሰግዳለን።
— ዮሐንስ 4፥22


እግዚአብሔርን አውቀንና በመንፈስ ቅዱስ ተረድተን ስናመልከው አምልኮዎአችን ኃይል ይኖረዋል መለኮታዊውንም ዓለም በኃይል መለማመድ እንጀምራለን።

በመንፈስ ቅዱስ መገለጥና ዕውቀት የሆነ አምልኮ የእግዚአብሔርን መገኘት ይስባል🔥

ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን፥ ከሚቃጠልም መሥዋዕት
#ይልቅ እግዚአብሔርን #ማወቅ እወድዳለሁና።
— ሆሴዕ 6፥6

@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
📌መንፈሳዊ እድገት
📌መንፈሳዊ ፍሬ

የመንፈሳዊው ሕይወት እድገት መገለጫው መንፈሳዊ ፍሬን ማፍራት ነው።


@Binarevivalist
@Binarevivalist
@Binarevivalist
2024/06/02 02:32:38
Back to Top
HTML Embed Code: