Telegram Web Link
💫ሰሙነ-ህማማት

ክፍል ሶስት
#ለማን_ብሎ? #ምን_በወጣው
💫ሰሙነ-ህማማት

ክፍል ሶስት

#ለማን_ብሎ? #ምን_በወጣው

@BiniyamDesalegn
💫ሰሙነ-ህማማት

ክፍል አራት
#ይግረፉት_ደግ_አረጉ!
💫ሰሙነ-ህማማት

ክፍል አራት

#ይግረፉት_ደግ_አረጉ!

@BiniyamDesalegn
Forwarded from ይቅርታዬ 🔥🔥 (𝐒𝑨M𝐈 𝑨Z𝐔𝐒𝑨)
ምነው ምን ነካዎት!

አንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን የሚማሩ ተማርዎች ለፈተና ተቀምጠው መፈተን ጀመሩ፥ በዝህ ጊዜ ከመካከላቸው አንድ በዕድሜያቸው ተለቅ ያሉ ተማሪ ፈተናው ከበዳቸውና🤔 መልሱን ለማግኘት የተማሩበትን ደብተር እያገላበጡ ሥሰሩ አስተማሪው በማየት ገረመውና ጠጋ ብሎ "ምነው ምን ነካዎት? ይኸኮ ፈተና ነው ከደብተር እያዩ መሥራት አይችሉም!"😡 ብሎ ስነግረው ምን ብል ጥሩ ነው? "ትቀልዳለክንደ!😒 ለራሴ መሰለህ የምሰራው፤ ለጌታ ቤት እኮ ነው!" ብለው አረፉ😂

ለጌታ ስንሠራ እውነትን እና ጽድቅን ተጫምተን ይሁን እንጂ፤ ግብዝነት በሞላበት በከንቱ ውዳሴ እንዳይሆን ጌታ ይርዳን።🙏
❗️ሼር እንዳትረሱ

⁰▬▭▬ @yikrtayee ▬▭▬⁰
⁰▬▭▬ @yikrtayee ▬▭▬⁰
SAMI_AZUSA
Forwarded from ሚኪያስ ፈይሣ
ባለጊዜ መቶ ጊዜያችን ሰረቀው
ባለወንጌል መቶ ወንጌሉን ሰረቀው
ባለጉልበት መቶ ቀልባችን ሰረቀው
ባለስልጣን መቶ ተስፋችን ሰረቀው
እኛ ግን ዘላለም
የጌታን መምጣት ነው የምንጠብቀው
በቆምንበት ስፍራ
ጠላት ጦር ቢከብም
ማምለጫ ቀዳዳው ከመርፌ ቢጠብም
አከተመ እያለ ገዳይ ሰው ቢያናፋም
የዘንድሮው እልቂት ከአምናው ቢከፋም
እንጥፍጣፊ እምነት ከጓዳ ቢቀረን
እርሱን መጠበቅ ነው ወንጌል ያስተማረን
ቅስማችን ቢሰበር ወኔያችን ቢደቅም
ከእርሱ መምጣት በቀር ምንም አንጠብቅም
ከሁካታው ይልቅ
ከጫጫታው ይልቅ የርሱ ቃል ይበልጣል
እንጠብቀዋለን እየሱስ ይመጣል
ቢሰድቡንም እንኳን
ቢገፉንም እንኳን ማራናታ ለአለም
እርሱ ካልመጣማ የሚያድነን የለም

@mikiyas_feyisa
ወረት አያውቀው ጌታዬ - ቢኒያም ደሳለ...
ቢኒያም ደሳለኝ - Biniyam Desalegn
📀 ባማ ትኩስ ዜማ 📀

የCOVER ዝማሬ - ቢኒያም ደሳለኝ

   ወረት አያውቀው

@Bama_Tube
@Bama_Tube
ነካ አድርገው ይቀላቀሉን።
Forwarded from ሚኪያስ ፈይሣ
"ቀንበር ሸክሙ ፍስስ ይላል
ጭንቅ ነፍሱ ይረጋጋል
ኢየሱስን የቀመሰ
ለዓለም ጣዕም መች ይጓጓል"
ነበር ቃሉ የሰማሁት
ሰርክ ፀሎት ተቀምጬ
በወንጌልህ የምስራች
በስብከትህ ተመስጬ
ታድያ ሁሌ ሳላቋርጥ
ከደጅህ ስር እያነጋው
ለምን እኔ ጣዕም የለሽ
ባንተ ፍቅር የማልረጋው?

ትቼህ ሄጄ ስንት ጊዜ
ሳዝን ካንተ እንዳልመጣው
ለምንድን ነው ስትምረኝ
ዳግም መሄድ የምቃጣው?

ስስ ቃልህን እየሰማው
ሜሮን ነክቶኝ በካህን ጣት
ክርስቶስ ነው ህይወት ብዬ
ፍቅርህ ነፍሴን እየዋጣት
መስቀልህን አንጠልጥዬ
ባንገቴ ላይ በጥቁር ክር
ለምን አንተን በቃል ብቻ
በልቤ ግን ማልመሰክር?
በምህረትህ ፊትህ ቆሜ
ከእኔ በላይ ነፍሴ ወዳህ
ለምንድን ነው ሲቀልልኝ
እንደ ባዳ የምከዳህ?

ስንሰቀሰቅ ከመቅደስህ
ሃጥያቴን እንዳለፍከኝ
እያሰብኩኝ ስንት ጊዜ
አይዞህ ብለህ እንደማርከኝ
ሰላምህን አጣጥሜ
ቃልህ ስቦኝ በእንጥልጥል
ለምን ይሆን በንጋታው
አንተን መውደድ የማልቀጥል?

@mikiyas_feyisa
ቢኒያም ደሳለኝ | Biniyam Desalegn pinned «"ቀንበር ሸክሙ ፍስስ ይላል ጭንቅ ነፍሱ ይረጋጋል ኢየሱስን የቀመሰ ለዓለም ጣዕም መች ይጓጓል" ነበር ቃሉ የሰማሁት ሰርክ ፀሎት ተቀምጬ በወንጌልህ የምስራች በስብከትህ ተመስጬ ታድያ ሁሌ ሳላቋርጥ ከደጅህ ስር እያነጋው ለምን እኔ ጣዕም የለሽ ባንተ ፍቅር የማልረጋው? ትቼህ ሄጄ ስንት ጊዜ ሳዝን ካንተ እንዳልመጣው ለምንድን ነው ስትምረኝ ዳግም መሄድ የምቃጣው? ስስ ቃልህን እየሰማው ሜሮን ነክቶኝ…»
2024/05/19 08:05:59
Back to Top
HTML Embed Code: