Telegram Web Link
💫🌟የማለዳ ቃል💫🌟

“ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።”
  — ፊልጵስዩስ 4፥4

#ኢየሱስ_ይመጣል
@Biniyam_Desalegn
አንተ ቸር አልምደኸኝ🥺🥺🥺
💫🌟የማለዳ ቃል💫🌟
.
.
ለካ ምድርም ባዶ ነበረች።
.
.

#ኢየሱስ_ይመጣል
@Biniyam_Desalegn
💫🌟የማለዳ ቃል💫🌟
.
.
በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ነበር።
.
.

#ኢየሱስ_ይመጣል
@BiniyamDesalegn
Audio
🥺🥺🥺🥺🥺 ስሙት በጌታ
“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 1፥3

ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፤ በዚህ አመት ቅድስተ ማሪያም ዩኒቨርሰቲን የምትቀላቀሉ ክርስቲያን ተማሪዎች ከላይ ባለው ስልክ ይደውሉልን
ተባረኩ🥰
ቀን: ማክሰኞ
ቦታ፡ ልደታ ሙሉ ወንጌል
ሰአት፡ 6:10- 7:30
👉ኸረ እንዲህ አይኖርም!

    አንድ ወዳጄ በቅርቡ አግብታለች እንኳን ደስ አለሽ አትሏትም እንዴ? እናም ይህቺን ወዳጄን ዛሬ አግኝቻት አብረን አሳለፍን በሁዋላም በፊት እንደ ለመድኩት ካላመሸን እራት ካልበላን ብዬ አስጨነኳት።
       እሷም በመገረም " እንደ ድሮው እኮ አልኖርም" አለቺኝ! እሷ እንደ ሀሳብ መዝጊያ ብታወራውም በህሊናዬ ውስጥ ግን የጥያቄ መጀመሪያ ሆኖ አረፈው ። ሆኖም ጊዜው በጭንቅላቴ ውስጥ የተፈጠረውን ጥያቄ መመለሻ  እንዳልሆነ ስለገባኝ ሀሳቤን ሰብስቤ ጫወታችንን ቀጠልን --------
   ሆኖም ያወራናቸው ወሬዎች መሃል ሁሉ ውዴ እኮ እንደዚህ አርጎ እንደዛ ተፈጥሮ ብቻ ምን አለፋቹ ወሬው ሁሉ መሃል ውዷ አለ ጎደኛዬ ፍቅር ውስጥ ናት እንደ ድሮው በፍጹም አይደለችም ጥያቄዬ በረታብኝ ። በመጨረሻም ባለቤቷ እደሚጠብቃት አስረዳችኝና ተለያየን
  ✍️በመንገዴ ላይ እያለው እንዲህ አሰብኩ አይ ፍቅር...
ፍቅር ወስጥ ኃላፊነት አለ ሰው ለሚያፈቅረው ነገር ምንም ያደርጋል አኗኗር ይቀይራል!


    ✍️ ለነፍሴ እንዲህ ስል ነገርኳት ጌታሽን አፍቅሪው ለአፍቃሪሸ መልስ ስጪው በመስቀል ለዋለልሸ ባይመጥነውም የፍቅር መልስ ስጪው ፍቅር ውስጥ ኃላፊነት ስላለ እንዲህ አትኖሪም!!! እንዳበደ ሰው ኢየሱስ ኢየሱስ ትያለሽ 🙆‍♀️ኢየሱስ ሲባል normal አትሆኚም ለፍቅሩ ትጠነቀቂለታለሽ ስለሱ አብዝተሽ ታወሪያለሽ ብታፈቅሪው እንዲህ አትኖሪም ነበር 😭አልኳት......እንድንወደው እንዴት እንደወደደን ያብራልን 🙌 በፍቅሩ እንድናብድ ይርዳን አሜንንን
   👉  የመልክቴ  ዋና ሀሳብ
  "ሰማይን ያፈቀረ ሰው ያስታውቃል አምኖ አይደለም ክዶ እንደ ፔጥሮስ ከእርሱ ወገን ነህ ይባላል "
" ሰማይን ያፈቀረ ያስታውቃል " እንደ ጳውሎስ ምን ላድርግልህ ሲል ይገኛል

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤”
  — ዮሐንስ 14፥15-16

  ተባረኩ ሰላማችሁ ይብዛ
✍️ መሰረት
ቢኒያም ደሳለኝ | Biniyam Desalegn pinned «👉ኸረ እንዲህ አይኖርም!     አንድ ወዳጄ በቅርቡ አግብታለች እንኳን ደስ አለሽ አትሏትም እንዴ? እናም ይህቺን ወዳጄን ዛሬ አግኝቻት አብረን አሳለፍን በሁዋላም በፊት እንደ ለመድኩት ካላመሸን እራት ካልበላን ብዬ አስጨነኳት።        እሷም በመገረም " እንደ ድሮው እኮ አልኖርም" አለቺኝ! እሷ እንደ ሀሳብ መዝጊያ ብታወራውም በህሊናዬ ውስጥ ግን የጥያቄ መጀመሪያ ሆኖ አረፈው ። ሆኖም ጊዜው በጭንቅላቴ…»
ኢየሱስ ደግ ነህ - Biniyam Desalegn
ተወዳጁ የደስታዬ እልልታ
ከአባትነትህ መርጦ ድሎት፤
ደክርቶ ሲመለስ ከሸፈተበት፤
እየሮጠክ ሄደህ አንገቱን ሳምከው፤
ስታየው ራርተህ አንጀትህ ተላውሶ፤
ምህረትን ሰጠኸው፤
እንደወደድከኝ ቀርቶ አንተን ላፍቅር፤
እንዲያው ተችሎ ቦታ እንቀያየር፤
አትጠራጠር ሀሳብ ሳልቀይር፤
እንኳን ልምርህ ገድዬህ ነበር።

ኢየሱስ ደግ ነህ - ቢንያም ደሳለኝ
Albastros.com
@Yedestaye_Elilta
2024/05/27 13:02:00
Back to Top
HTML Embed Code: