Telegram Web Link
...
"ማነሽ? ተናገሪ!"
"ፍቅር!"
"የት አገኘሽው?"
"እግሬ ሥር?"
"ምን እያ'ረገ?"
"ሲቆፍር።"
"ትለቂያለሽ?"
"አለቅ'ም!"
"ትለቂያለሽ?"
"አለቅ'ም!"
"አትለቂም?!"
"እለቃለሁ!"
(ይኸኔ እስቃለሁ)
አንቺን ሲጠይቁሽ እኔ እመልሳለሁ።

"ምሱን ተናግረሽ አሁን ልቀቂ!"
"በመጀመሪያ አረቂ"
"ከዚያስ?"
"ጠላ፣ ጠጅ - - እንጀራ ጋር"
"ከዚያስ"
"እኔና እሱን መዳር!"

ቂቂቂቂ!

ለቅምሻ የተሰፈረ ነው። ሙሉውን አንብቡት። ብትጠሉት? ጆሮ ልይዝ። ብትወዱት? ድገሙት ልል። ለምንም ለማንም ግን ሰኞ እንድንገናኝ ይሁን። ጊዮን ግሮቭ ጋርደን
ምሽት 11:30
@Bookfor
#ከስላንች እስከ #ወሬ ነጋሪ

ያላለቀ የጥበብ ጉዞ ተገታ !
ታሪኩ ብርሀኑ (ባባ)
#ነፍስህ በሰላም ትርፍ

@Bookfor
በ አጸደ ስጋ
(በእውቀቱ ስዩም)
ሰው ሟች መሆኑን መርሳት የሚፈልግ ፍጡር ነው፤ ስልጣኔ ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን ሞትን ያስረሳል፤ በአውሮፓ በአሜሪካ በጃፓን ኮረና እስኪመጣ ድረስ ሞትን የሚያሳስብ ነገር አልነበረም፤ የመቃብር አጸዶች እንኳ እጀግ ውበ ከመሆናቸው የተነሳ የፍርሀት እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት አይቀሰቅሱም፤ ስልጡን ማህበረሰብ ሞትን ማስቀረት ባይችል እንኳ ማዘግይት ችሏል፤
በአገራችን የተለየ ነው፤ ሞት የማይንጸባረቅበት የኑሮ ዘርፍ የለም፤ ስንምል “ አባቴ ይሙት ፤ እናቴ ትሙት “ እንላለን፤ ስናጋብዝ “ በሞቴ ! አፈር ስሆን “ ብለን እንለማመጣለን፤ ራሳችንን ስንወቅስ “ ሞት ይርሳኝ “ እንላለን፤ ስንጸልይ ፤ “ አሟሟቴን አሳምርልኝ” እንላለን፤ አኗኗሬን አሳምርልኝ ሲባል ሰምቼ አላውቀም፤ ከልደታችን እና ከሰርጋችን ቀብራችን ይደምቃል፤ አንድ ሰው በሕይወት ያለን ሰው ካሞገሰ ወይም ካመሰገነ ድሮ “ እበላ ባይ “ ይባል ነበር፤ ዘንድሮ “ አሽቃባጭ “ የሚል ስም ይቀዳጃል፤ የሞተውን ማወደስ ግን የዜግነት ግዴታ መስሏል፤ በሕይወት መወደስ ፐርሰናሊቲ ከልት “ አሰኝቶ ያስወነጅላል፤ በሕይወት ዘመኑ ሀውልት የተሰራለት፤ መንገድ የተሰየመለት ትልቅ ሰው አይታችሁ ታውቃላችሁ? መንገደኞቻችን ረጃጅም መካነ መቃብሮች ሆነዋል፤
የፖለቲካ አስተዳደሮቻችን ለህይወት ያበረከቱት ነገር ጥቂት ነው፤ ባንጻሩ የሞት ፋብሪካ መሆናቸውን ታዝበናል፤ የመስዋአት አምልኮ ተነስራፍቷል፤ የአገረሰቡም ሆነ የብሄረሰቡ መዝሙር “ ስለ ደም ማፍሰስ እንጂ ስለ ደም መለገስ “ አይደለም፤ የሚሞት እና የሚገድል እንጂ፥ የሚኖርና የሚያኖር እንደ ጀግና አይታይም፤
በሀኪም ስተት ከሞተው ይልቅ በአስተዳደር ስህተት የሚያልቀው ይበልጣል፤ ያም ሆኖ ፥ ቆም ብሎ የመጣንበት መንገድ አያዋጣም ለማረም የሞከረ የለም፤

ባጭሩ፥ የሞት አገር ነው በውቄ! በዚህ ሁኔታ ውስጥ፥ ሕይወትህን መንዘንጋት ቀላል ነው፤ ጌታ ኢየሱስ ፥ ነቢዩ መሀመድ ሀዋርያው ጳውሎስ እንደነገሩን ከዚህ የተሻለ አለም አለ፤ ጌታ ኤፌቅሮስ እንደ ነገረን ደግሞ ይህ አለም የመጀመርያውም የመጨረሻውም እድላችን ሊሆን ይችላል ፤ እና በተቻለህ መጠን፤ ለመኖር ተፍጨርጨር፤ ለበጎ ምግባርህ ምድራዊውም ሆነ ሰማያዊ ሽልማት ሳትጠብቅ በጎ ሁን! ከቅኔ ከተረት፥ ከሙዚቃ፤ ከእውቀት ከሚገኘው ፍስሀ ተሳተፍ! ቢሰምርልህ ተቃቀፍ! እንደ ራስ አዳል እና እንደ አቤቶ ምኒልክ አብረህ ብላ! አብረህ አጭስ፥ እንደ ጌቶች ረዳና እንደ ብሬ ጁላ ፤ ከህይወት ጸጋዎች አብረህ ባትሳተፍ ከሞት እዳዎች አብረህ መሳተፍህ አይቀርም፤ ሻምበል ፍቅረስላስላሴ ወግደረስና ገለሳ ዲልቦ በህይወት ዘመናቸው የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ያላቸው “ተጻራሪዎች “ ነበሩ፤ አሁን ስላሴ ቤተክርስትያን ጎን ለጎን ተኝተዋል ፤ እንደዚያ ነው!

@Bookfor
@Bookfor
(ምናብ)

መስሎ እንደሚጓዝ ወንዝ
ፈልቆ ከአንድ ቦታ
በነገሰ ድባብ
በሃሳብ ከፍታ

መወለድ አይደለም
መፀነስ ያልቻሉ

ረቂቅ ሀሳቦች
ከብሩኽ አዕምሮ
ከንፁህ ልቦና ሁሌም ያደባሉ ።

ብ.አ.ከ.

@Bookfor
@Bookfor
+ ያላለቀው ሰፌድ +

ዓሥር ብር ኖት ላይ የነበረችው የዚህች ሴት ነገር አንጀት ይበላል:: ሰፌድዋን ሠርታ ሳትጨርስ ጊዜዋን ጨረሰች:: ቀና ብዬ ወሬ ልይ ሳትል አቅርቅራ ሥራዋ ላይ እንዳተኮረች ኖረች:: ትዳር ልያዝ ሳትል የየሰዉን ኪስ ለመሙላት እንዳቀረቀረች ኖረች::

መልእክቱ ይኼ መሰለኝ :-

ወዳጄ ነገሮች መቼ እንደሚለወጡ አታውቅም:: እጅህ ላይ ያለውን ሥራ ሁሉ በቶሎ ጨርስ:: ማንም ሊሠራባት የማይችላት ሌሊት ሳትመጣ በፊት ሥራህን አከናውን::

ብዙዎቻችን ከአጭሩ ዘመናችን ብዙ እናባክናለን:: ምንም ያላደረግንባቸው ባዶ ጊዜያትና ያልተኖሩ ብዙ ቀናት አሉ:: ከገንዘብ በላይ የማይተካው ብክነት የጊዜ ብክነት ነው:: ሰዎች ጊዜያቸውን ተጠቅመው የሠሩትን ክፋት ማውራት ትተን ጊዜያችንን መጠቀም ይኖርብናል::

በጊዜህ በአግባቡ ተጠቀም:: የማትጨርሰው ለዓመታት የማያልቅ ሰፌድ አትጀምር:: ለነገሮች ቅደም ተከተል ሥጣቸው:: አንዱን ሳትጨርስ ሌላ አትጀምር:: ቁምነገሩ በነገሮች መወጣጠርና ቢዚ መሆን አይደለም:: ጉንዳኖችም ቢዚ ናቸው:: ቁምነገሩ ጊዜ የምታጠፋው ምን ላይ ነው የሚለው ላይ ነው:: እነርሱ ቢያንስ ለገብረ ጉንዳን ይተርፋሉ:: ያንተ ቢዚነት ለማን ይተርፋል?

ስልክህ ውስጥ ባለ ጌም ላይ ያሉ ግንቦችን ለማፍረስ አለዚያም ለመገንባት ጊዜ የምታጠፋ ከሆነ ድንገት ብትሞት እንኳን በጣም ታሳዝናለህ:: ምድር ካንተ ብዙ ትጠብቃለች:: ሰዎች ገንዘብ እንዲያገኙ አንተ ገንዘብ የማታገኝበት ነገር ላይ ትሰቃያለህ::

የምትሰፋውን ሰፌድ አሁኑኑ ወስን:: ነገ ዓለም ሳትቀይርህ በፊት ሥራህን ወስን:: ጊዜህን ተጠቀምበት:: ባላስፈላጊ ነገር ላይ ጊዜ አትውሰድ:: መጽሐፍ ቅዱስ "ለሚጠፋ መብል አትሥሩ ለዘላለም ሕይወት ሥሩ" ይልሃል::
ከቻልክ ትውልድ የሚጠቅም ለአንተም ለነፍስህ የሚበጅ ነገር ሥራ:: ብቻ እየሰፋኸው ያለኸውን ሰፌድ ቆም አድርገህ ምን እያደረግኩ ነው? ብለህ ራስህን መጠየቂያህ ጊዜ አሁን ነው:: አለዚያ ግን ድንገት ሕልውናህ አብቅቶ ሰዎች ባዩህ ቁጥር እንደዚህች ሴትዮ "ውይይይይ ይቺ ሴትዮ አሥር ብር ላይ የነበረችው እኮ ናት" እያሉ ከንፈር ይመጡብሃል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 11 2013 ዓ ም

@Bookfor
.....
" ያልነገሩኝማ ብዙ ታሪክ አለ። በዚህ ብቻ አያልቅም!.... ባይሆንማ መልካቸው የዚህን ያህል ከግድግዳው ጋር ባልተመሳሰለ ነበር! "
.....

@Bookfor
ያለንን ማወቅ ... ራስን መሆን ..... ለሁኔታዎች ሚዛናዊ ምላሽ መስጠት...

መቻል መታገስ ለኮሽታዎች ሁሉ አለመገረም....

በስሜት ብልህነት ከፍ እያሉ መምጣት .....

ልምድ ይባላል።

@Bookfor
@Bookfor
ታዋቂዋ የሙዚቃ ንግስት ድምፃዊ አስቴር አወቀ ከሰዋሰው መልቲሚዲያ ጋር መፈራረሟ ይፋ ተደርጓል።

ድምፃዊቷ ቀጣይ አልበሟን በዚሁ በሰዋሰው መተግበሪያ በጥምቀት ዋዜማ ለአድማጭ የምታቀርብ ይሆናል።

@Bookfor
ለመላው የክርስትና እምነት የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አንቺ ቤተልሔም፥የይሁዳ ምድር፥ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፥ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና፥በይሁዳ ቤተልሔም የአለም መድሀኒት ፣ የፍጥረታት ጌታ ፣ የሀያላን ሀያል ፣ የጌቶች ጌታ ፣ የንጉሶች ንጉስ የስጋም የነፍስም ፈጣሪ እርሱ መድሐኒት እየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዷል።
የገና በዓል አምላክ በፈጠራት ምድር አንድያ ልጁን ለአዳም መድሀኒት እንዲሆን ስጋ ለብሶ የተወለደበት እንደመሆኑ በልባችን ፍቅር  ፣ ሰላም  ፣ ቅንነት ፣ ምክንያታዊነት እና በጎነትን በልባችን ፀንሰን እንድንወልድ እድል የተሰጠን ነው።
በዓሉን ስናከብር በቅንነት ስራ ፣ በበጎ ተግባር መሆን ይገባዋል። የፍቅርና የይቅርታ አምላክ የተወለደበት ቀን ነውና ሁላችንም ልባችንን በፍቅር ህይወታችንን በይቅርታ እንመራ ዘንድ አደራ እያልን ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ በመላት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

@Bookfor
@Bookfor
ማፍቀር መቻል ለአንድ ሰው የመኖር ፣ ተስፋ የማድረግ እና አምነትንና ብርታትን የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡ ማፍቅር ለዚህች ቁራጭ ሕይወት ትርጉም ይሰጣል ብዬ አስባለሁ ፡፡ አንድ ጊዜ ከታላላቆቹ የኢትዮጵያ ልብ ወለድ ጸሐፊዎች መካከል በአሉ ግርማ በአንድ ወቅት አንዲ ብሎ ነበር “እኔ ደደብ ነኝ ፤ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ፣ በአለም ላይ ሲኖሩ በሁሉም ነገር ላይ እምነት ከማጣት የበለጠ ሀገርን የሚያፈርስ ነገር የለም” ብሎ ነበር፡፡ እና ለእኔ ማፍቀር መቻል ማለት አንድ ሰው በህይወቱ ትርጉም እና እምነትና ተስፋ እንዲኖረው ሊያደርግ የሚችለው ብቸኛውና ዘላለማዊ ነገር ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ለነገሩስ ፊዮዶር ዶስቶቭስኪን "እውነተኛ ገሃነብ ምንድ ነው?" ቢሉት "ማፍቀር አለመቻል ነው "ብሎ መልሶ ነበር፡፡"
@Bookfor
@Bookfor
" በድሮ ጊዜ ---- ድሮ ሩቅ የሚመስላቸው የዋሃን ናቸው ፣ ትውልድ በተስፋ መቁረጥ ሲመክን የጊዜም ስፍር ይዛነቃልና ÷ ለመኮኑ የዋህነት ምንድነው ? ደርባባ አስተዋይነት የሌለው ÷ ግልብ ፈጣንነት አይደለም ወይ ? ... " የቸኮለ አፍስሶ ለቀመ " ፣ " የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል " ፤ " የእነ ቶሎቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ " ፤ " ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል " ... የፈጠኑ የት ይደርሳሉ ?

የማያልቅ ዘላለማዊ ህዋ ውስጥ በሚያበቃ ታሪክና በሚያከትም ኑባሬ የተወሰንን ፍጡራን ነን :: ፈጣሪም ይሰስታል --- ካልጎደለበት ሺህ አመት ፣ ካላጣው አፈርና ሰማይ በስድሳ ሶስት ዓመት የሚፈራርስ ገላና የሚሸመግል መንፈስ እንደአሻቦ ሰፍሮ ያከፋፍለናል :: ከየት ፈጥነን የት ደርሰናል ?

አድበን ፣ ስሜታችንና መርማሪ ጠያቂ ያልተቀጣ አሳባችንን በአንዳንች ልጓም ገትተን በብዙኃኑ መንገድ " ብቸኛው ተኩላ ይሞታል " ይላሉና አዋቂዎች ከአዳም ጀምረን ብንቆጥር የምንደርሰው አሸብር ዘንድ ነው :: ተመሳሳይነታቸው እስኪያስደንግ ድረስ ነው :: አዳም በሔዋን ሳተ ፤ አሸብር በሔለን ወይ በአንቺናሉ አይተነው ዳምጤ ሳተ :: ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥፍ :: ለመሆኑ አሸብር ማነው ? አናውቅም :: ሕይወቱም እንደህልውናው የሚመረመር ያልሆነ ልሙጥ ተረክ ይሆናል :: ታሪክ ግን መርጦ ያነሳል መርጦ ይጥላል :: ታሪክ ጉልበት የሌለው የሚመስላቸው አሉ :: እኔ ግን እላቹሃለሁ ታሪክን በዕውቀት ለሚጠቀመው የእግዜር እጅ ነው ... በድሮ ጊዜ .... "

ስለትናንሽ አለላዎች
ዮናስ . አ
ሁለተኛ ዕትም
@Bookfor
@Bookfor
◉◉◉

...ምናልባት፥ቀና ስንል...
...ሊያየን ካቀረቀዉ ጋር እንተያይ ይሆናል...!!

◉◉◉


@Bookfor
አንድ ቀን፤ ሁሉም ነገር ተጠቅልሎ የእውነት እና የህሊና ጥያቄ ብቻ ይሆናል፡፡ ትርጉም ያለው ነገር እንፈልጋለን፡፡ ምን አይነት ሰው ልሁን? እንዴት ያለ ኑሮ ልክ ያደርገኛል ማለታችን የነፍሳችን ዓላማ ነው፡፡ ምዕመኑ አምልኮውን፣ መሪዎችም አገዛዛቸውን ይጠይቃሉ፡፡ መምህራን ከሚናገሩት፣ ነጋዴዎችም ከትርፋቸው ወዲያ ስላለው ነገር ማሰባቸው አይቀርም፡፡ ሁላችንም የገዛ ራሳችንን ጽድቅ ለመፈጸም የማንሻገረው ወንዝ አጠገብ እንቆማለን፡፡ ዳሩ ግን ብልጠት የመሰለን ስግብግብነት ከላያችን እስኪራገፍ ድረስ ብዙ ነፍስ [ነፍሶች] ሸቀጥ ሆነው ያልፋሉ፡፡ ደግሞ ከበሰለው ኋላ፣ ካለፈው ያልተማረ፣ ጥሬ ትውልድ ከማሕፀን በር ላይ ይገኛል፡፡
@Bookfor
@Bookfor
በጋራ ካኖርናቸው ታሪኮቻችን ግንባር ቀደም የዓድዋ ድል ነው፡፡
ዓድዋ ዛሬ ላይ አላሻግር፣ ነገን አላሳይ ያለንን የልዩነት አጥር ለመጣስ የምንማርበት የአንድነት፣
የልዩነት እና የመቻቻል ጥበብ ማስተማሪያ ፊደል ነው።
እስቲ የጥቁር ድል የሆነውን አደዋ የሰጡን የኢትዮጵያ ጀግኖች እናውሳ።
ንጉሱ ተጠርተው ማን ይምጣ ቢሏቸው
ከዚህ ሁሉ ጀግና መሾም አቃታቸው
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor
#አደዋ
ጣሊያን ሰሓቲ ላይ እግሩን ቢዘረጋ
በብረት ምጣዱ በሰሓቲ ኣደጋ
አንገርግቦ ቆላው አሉላ አባነጋ
አውሮፓውያን "The Garibaldi of Abyssinia" በማለት ከታላቁ የጦር አበጋዝ ጋር ያወዳድሩታል።
አሉላ አባነጋ ለሀገሩ ያለውን ታማኝነት በተግባር ኖሮ በአንደበቱም ሲመሰክር እንዲህ ነበር ያለው "ጣሊያን ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው እኔ የሮማ ገዢ ሆኜ ስሾም ብቻ ነው"።
ጀግኖቻችንን እናክብር!
ሳይለያዩ ያኖቆዩልንን ሀገር ተለያይተን ልንኖርበት አንችልም!
#አደዋ

@Bookfor
@Bookfor
አሻግሮ ገዳይ ዲብ አንተርሶ
የዳኘው አሸብር ባልቻ አባነፍሶ
ብልህነት ፣ ታማኝነት ፣ ሀገር ፍቅርና ጀግንነት ባንድ ላይ ቢሰደሩ ባልቻ ሳፎን ይመስላሉ ይላሉ ታሪክ ነጋሪዎች። አደዋ ላይ ታሪክን በደማቁ ከከተቡ ጀብደኞች አንዱ ናቸው። በግዜ ሒደት በስርዓት መለወጥ ያልተቀየረው ሀገር ፍቅር በ80 አመታቸው ዳግም የጣልያንን ጦር አሳፍረዋል። በወቅቱም ለምን ይዘምታሉ በስተርጅና ሲሏቸው "ሸምግያለሁ መሞት እንደሆነ አይቀር በሰማይ ላይ ጌታዬ ሚኒሊክ በኢትዮጲያ ዙፍኔ ላይ ማነው ያለው ቢሉኝ ምን እመልሳለሁ" ብለው መልሰዋል።
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor
ተኩሶ የሚጥል ጠላት ማርከሻ
የዩሐንስ ልጅ እራስ መንገሻ
ራስ መንገሻ ዩሐንስ የአፄ ዮሐንስ ልጅ ሲሆኑ በአደዋ ጦርነት ታላቅ ጀብዱ የፈፀሙ የጦር መሪ ናቸው።
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor
ንጉስ ተክለሃይማኖት ወዴት ይሆን ድርሻ
ጀግናው ሰው ናጣቸው በጦር በጎራዴ መክቶ በጋሻ
ንጉስ ተክለሀይማኖት ዘ ጎጃም በአደዋ ድል በሀገር ፍቅር ፣ በወኔ ፣ በጦር ጥበብ ፊት ከነበሩ ጀግኖች መካከል ይጠራሉ።
#ክብር_ለጀግኖቻችን
#አደዋ
@Bookfor
@Bookfor
ንጉስ ሚካኤል መክተው በጋሻ
ለጠላት አታጣም ጥጋብ ማስታገሻ!
ንጉስ ሚካኤል የአጤ ሚኒሊክን የክተት አዋጅ ተቀብለው የወሎን ጦር ይዘው ወደ አደዋ ዘምተው ታላቅ ጀብድ የፈፀዉ የጦር መሪ ናቸው።
#አደዋ
#ክብር_ለጀግኖቻችን

@Bookfor
@Bookfor
2024/06/01 18:03:39
Back to Top
HTML Embed Code: