Telegram Web Link
ሳይኮሎጂ እንዲ ይላል💁
ዝምተኛ ሰዎች 😊

ከሚወዱት ሰው ጋር

ወረኞች ናቸው👍💞



❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ወንድ ልጅ የ እዉነት ሲወድሽ

ስለ ወደፊት እቅዱን ያወርሻል

በየቀኑ ይደዉላል
መልእክት ይልካል

ያቆላምጥሻል

ትኩረት ይሰጥሻል

ደክሞት አንቺን
ለማዉራት ይቆያል

መልእክት በ ፍጥነት ይመልሳል

ይተማመንብሻል

ይንከባከብሻል
ይከላከልልሻል
❤️❤️❤️❤️❤️
ወንዶች ተሚጠላቸው
የሴት አይነቶች

1፡ ለ ወንድ ልጅ ጥላቻ ያላቸው

2፡ ጥቅም ፈላጊ

3፡ ቺት ምታደርግ ወንድ አተራማሽ

4፡ የ ክለብ ና ፓርቲ ሱስ ያለባቸው

ወጪ የምታበዛ ሴት

5፡ ከሁሉም ጋር የምትሽኮረመም

የሰዎችን ትኩረት የምትፈልግ
💔💔💔💔እጣፋንታዬ 💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 1 💔💔💔💔

ልእልና እባላለው ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ነው ...የሀብታም ቤተሰብ ልጅ ባሎንም እስከተወሰነ የዕድሜ ግዜዬ በእናትና በአባት እጅ ሞልቀቅ ብዬ ባድግም ከ6 አመቴ ቡሃላ ግን አብሮኝ አልዘለቀም አባቴ በ H.I.V በሽታ ሞተ በርግጥ ይህ ቫይረስ እንደነበረበትና በዚ እንደሞተ ያወኩት ካደኩ ቡሃላ ነበር ... የሆነው ሆኖ ከአባቴ መሞት ቡሃላ የኑሮ ጫናው እናቴ ላይ ወደቀ በዛ ላይ እናቴም ልክ እንዳባቴ በሽታው በደሟ ነበርና መዳኒት (ማራዘሚያ ) ትወስዳለች።
ብዙም ሳንቸገር 10 አመቴ ሞላ በመጠኑም ቢሆን ነብስ አወኩ አባዬ ሲሞት ቤት ስለነበረን ለሆዳችንና ለትምህርት ቤት ወጪ ካልሆነ ለቤት ኪራይ አናስብም ነበር ግን ምን ዋጋ አለው አባዬ እኛ ሳናውቅ የነበረበት እዳ ነበር በዛ ላይ ደግሞ ከእማዬ በድብቅ ልጅ ወልዶ ኖሮ በፍርድ ቤት ቤታችን ተሸጠና የድርሻችን ተሰጥቶን ኑሮን መግፋት ጀመርን...
እናቴ በጣም ቆንጆ ወጣትነት ያላለፋት ሴት ብቶንም ኑሮና በሽታ እየተዳመሩ አጎሳቆልዋት እኔም ይህን ሁኔታዋን ሳይ ያመኛል ኑሮ ክብድ አለን ትምህርት ቤቴን ቀይሬ የመንግስት ገባሁ የ5ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ግን ሁሌም የማስበው እናቴንና ኑሮዋን ነበር ከመማር ይልቅ ብር ማግኘት የምችልበትን ነገር ነበር የማሰላስለው...
ሁሌም ክፍል ተቀምጬ ከድሜዬ በላይ ስላሉ ሰዎች ስራ አስባለው አላጠናም የምማረውም አልገባሽ አለኝ እናቴ የምቶስደው መዳኒት የግድ የተመጣጠነ ምግብ ይፈልጋል ግን የለም ብር ከየትም ለፍታ ስታመጣ ከምግባችን ይልቅ ቤት ኪራይና የኔ የትምህርት መሳርያ ቦታ ይሰጠዋል ግን እኔ ትምህርቱን ብተወው እንዴት በተደሰትኩ...
ግዜዎች ሄዱ አምስተኛ ክፍል ተንጠልጥዬ ባልፍም 6 ላይ ግን ለመድገም ተገደድኩ ያኔ ከትምህርት ሰአት ቡሃላ ስራ መስራት እንዳለብኝ ወስኜ ነበርና ጎረቤታችንን እንደሷ ፅዳት ስራ እንድፈልግልኝ ነገርኳት ... እሷም አገኘችልኝ ...
ለግዜው ክረምት ላይ ነን ያም ማለት ትምህርት የለም እናቴንም ለቀጣይ ትምህርት ግዜ ላንዳንድ ነገር መግዣ ትንሽ ልስራ ብዬ ነው ያሳመንኳት ... ስራው የአንድ ወንደላጤ ቤት ጠዋት ሄጄ ማፅዳትና እቃውን ማጠብ ነው ሰውየው ህፃንነቴን አይቶ ቢያዝንልኝም በወር 150 ሊከፍለኝ ተስማማን።
አንድ ክፍል ቤት ስለነበር ምንም ሳይከብደኝ ሁለት ወር ሰራው የትምህርት መከፈቻውና 12ኛ አመቴ የሚሆንበት መስከረም ደረሰ ግን መጥፎ አጋጣሚ ጠዋት ተነስቼ የምሰራበት ሰውዬ ቤት ስገባ እርቃኑን ተኝቷል። አገር ሰላም ብዬ ሰላምታ ጠየኩትና ስራ ለመጀመር ጉድ ጉድ ስል ሳልስበው በሩን ዘግቶ ተጠጋኝ ሰውነቴን ወረረኝ መጮህ ፈልጌ ግን ሲከብደኝ ይታወቀኛል....

#ይቀጥላል
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 2 💔💔💔💔

ሰውየው ሊደፍረኝ ነው እኔ በድንጋጤ ተርበተበትኩ ምን እንዳልኩ ባላውቅም ልመና የሚመስሉኝን ቃላቶች በጠቅላላ መቀባጠሬን ቀጠልኩ ግን አላዘነልኝም የህፃን ገላ ለወሲብ እንዴት ይጋብዛል? አላውቅም ብቻ ከመጀመሪያው ጠነከረብኝና ብጮህ ቀርቶ ድምፄን ከፍ አድርጌ ባወራ እናቴንም እኔንም እንደሚገለን ነገረኝ እኔስ ብሞትም ግድ የለ ግን የእናቴን ስም ሲጠራ ድንዝዝ አልኩ በዝምታም ተመለከትኩት ...
አሁን ከመጀመሪያው ቀዝቀዝ አለና የሚለኝን እንዳዳምጥ አዘዘኝ እኔም በፍርሃት የማላቀው ሙቀትና ላብ ውስጥ ተዘፍቄ መስማቴን ቀጠልኩ "እኔ አንቺን መጉዳት አልፈልግም ነገር ግን የማዝሽን ታረጊልኛለሽ ደሞ ህፃን አይደለሽም ካንቺ በታች ያሉ ባለትዳር ሴቶች መኖራቸውን ላንቺ አልነግርም ..." አለኝ ህልም ይሆን ብዬ አይኔን ጨፍኜ መልሼ ገለጥኩት ግን አሁንም ይሄ ጨካኝ ሰው ከፊቴ ነው "እምቢ ብትይ በግድ እደፍርሻለውኮ ግን ተስማምተሽ ሳልጎዳሽ የምልሽን አርጊ ከዛ ከምሰጥሽ (ከምከፍልሽ) ተጨማሪ 300 ብር እሰጥሻለው !" አለኝ ሳላስበው 300 ብር ማለት ባንድ ላይ በወር 450 ? አልኩት በኩራት ወደሱ እያስጠጋኝ "አዎ እናትሽ ገንዘብ እንደሚቸግራት ሰምቻለው "አለኝ ...
የገንዘብ ችግሬ ከሰአታት በፊት ከከተተኝ ፍርሃት እንዳገግም አረገኝ ገና እንኳ ለአቅመ ሄዋን አልደረስኩም 12 አመቴ ነው እሱን ለወሲብ የሚገፋፋ ምንም የለኝም ጡቶቼ እንኳ የህፃን ልጅ ከንፈር ነው የሚያክሉት ... እንባዬ ሳላስበው ልብሴን ማራስ ጀመረ ምንም ቃል ሳልናገር በሁኔታዬ መስማማቴን አመነ ... ሰውነቴን በእጁ ይነካካኝ ጀመር አባ ጨጓሬ የሄደብኝ ይመስል ዝግንንንን አለኝ ቀፈፈኝ በእጄ ገፋውትና እጁን ከላዬ ላይ አነሳሁት ሳላስበው ብድግ ብዬ ከየት የመጣ ድፍረት ይሁን ሳላውቀው ... እኔኮ ህፃን ነኝ ብትችል እንደ ልጅህ ልታየኝ ይገባል የገንዘብ ችግር እንጂ ያለ እድሜዬ የሰው ቤት የሚያፀዳኝ እንደጓደኞቼ የመጫወቻዬ ግዜ ነበር ...ብዬ እልህና ንዴት የተደባለቀበት ለቅሶዬን ለቀኩት ... "አንቺን ብሎ ህፃን" አለና በጥፊ መታኝ ጎትቶ ልብሴን አወለቀው እርቃኔን አስቁሞኝ "ቅድም እንዳልኩሽ ይሄን ሚስጥር ለራስሽም ደግመሽ እንዳትነግሪው !!" አለና የልጅነት ህልሜንና ገላዬን ተጫወተበት...
ይህም ሆኖ ባስጠነቀቀኝ መሰረት ለማንም ትንፍሽ ሳልል ኑሮን ቀጠልኩ እሱጋም ስራ አላቆምኩም ስድስተኛ ክፍልን ተመዝግቤ እማራለው ባይባልም ትምህርት ቤት ግን እመላለሳለው ደስታ ከኔ ራቀ ስቄ ቀርቶ ፈገግ ብዬ
የማውቅበትን ቀን አላስታውስም እናቴም ከወር ውስጥ 3 ቀን እንኳ ጤነኛ ሁና አታውቅም። ስለሷ አስባለው ስለኔም እጨነቃለው ትምህርት ስለማይገባኝ አስተማሪዎች ሁሌ ይቆጡኛል ይሰድቡኛል ደስ ሲላቸው ደሞ ይመክሩኛል ... ግን ለእናቴ ስል እማራለው ባይሆን አልማርም ነበር ... ሰውየው ሁሌም ቤቱ ካለ ይደፍረኛል እኔም ለምጄዋለው ገንዘብ የተወሰነ ሲሰጠኝ ለእናቴ መዳኒትና የተወሰነ አስቤዛ እገዛለው ...
ግዜ ግዜን ወልዶ ከመኖር እና ከሞቱት መሀል ሁኜ የስምንተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ደረሰ ግን አንድ ክፉ አጋጣሚ እኔና እናቴ በተኛንበት ሰውየው ሲደፍረኝ የምለምነውንና የምለፈልፈውን በእንቅልፍ ልቤ ስለፈልፍ ሰምታ በጣም ደንግጣ ቀሰቀሰችኝና ጠየቀችኝ ጥያቄዋ አጋጣሚ ስለነበርና ተኝቼም ስለነበር መዋሸት አልቻልኩም ስታለቅስ አለቅሳለው በዚም እናቴ ገብቷት ራሷን ሳተች ምንም ምን ሳትለኝ ጎረቤት እንኳ ደርሶ ህክምና ሳቴድ ደም ግፊቷ እናቴን ላትመለስ ሸኛት
ካለእናት አንድ ደቂቃ መኖር ይከብዳል ጤነኛ ነኝ ብዬ ለመናገር እንኳ እቸገራለው ማንም የለኝም ለቅሶ እንኳ አልተመቀጥንም ምክንያቱም ማንም አልነበረኝም በሀዘን ተቆራምቼ ዛሬ ከነገ ጎዳና የምወድቅበትን ቀን ስጠብቅ የኔን ህልም አጨልሞ እናቴን ለመሞቷ ምክንያት የሆነው ሰው ቤቴ መጣ ክው ብዬ ቆምኩ ... አንቺ እርኩስ የድሃ ልጅ H.I.V እንዳለብሽ ለምን ደበቅሽኝ ብሎ ገፍትሮ ዘረረኝ ያኔ ነበር እኔም አለብኝ እንዴ ብዬ ያሰብኩት...
Any comments inbox @Juliiian
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 3 💔💔💔💔

ሰውየው ሲገፈትረኝ ወለል ላይ በማረፌ ብዙም አልተጎዳው ግን ድንጋጤውና እሱ የተናገረኝ ነገር ይበልጥ ጭንቅላቴን በጠበጠው አስራ አራት
/14/ አመት ሞልቶኛል 8ኛ ክፍልንም ልፈተን ነው ግን እንዴት እስከዛሬ እናቴ ማራዘምያ እየወሰደች አባቴም በ H.I.V ሞቶ እኔ በደሜ እንዳለ ማሰብ አቃተኝ ? አላውቅም! ሰውየው እሳት በለበሰ ፊቱ እየገለማመጠኝና ከተዘረርኩበት አንቆ እያነሳኝ "እገልሻለው" ብሎ በቦክስ መታኝ ከምቱ ይልቅ እስከዛሬ ልቤን በሀዘን የሞላው አስገድዶ ልጅነቴን እንዳላረከሰው ሁሉና ህፃንነቴ ወላጅ አልባነቴ ሳይታየው ማንም ጠያቂ የለኝም ብሎ ጥፋተኛዋ እኔን አርጎ እንደዛ አጥብቀው ሊይዙት የሚያሳሳ የልጅነት ፊቴን ያለምንም እርህራሄ መታቱ የልብ ቁስል ሆኖኝ ቀርቷል... ሰውየው ከወጣ ከሰአታት ቡሃላ እርቃኔን ልብሴ በደም ተጨማልቆና አፍንጫዬ ላይ የነስር ደም ደርቆ የእናቴ እሬሳ የወጣበት አልጋ ላይ እ በጀርባዬ ተንጋልዬ እራሴን አገኘውት ...
ለመነሳት ስሞክር እግሮቼ መሀል ህመም ተሰማኝ ግራ ገባኝ ይህ ለኔ አዲስ ነው እንደምንም ተንፏቅቄ ተነሳው የምንኖርበት ደሳሳ ጎጆ አከራይም ሆነ ከኛ ሌላ ተከራይ ባለመኖሩ የሚያየኝም የሚሰማኝ የለም ... እየተጎተትኩ ስነሳ አንድ ወረቀት ላይ አይኔ አረፈ አነሳውት የሰፈረው ፅሁፍ ቀልቤን ሳበኝና እንደምንም አልጋው ላይ ተመልሼ ማንበብ ጀመርኩ...
"ስሚ አንቺ ድሃ የሙት ልጅ " ይላል ሲጀምር ያአውሬ እንደፃፈው አወኩ እንባዬ የደረቀ ደሜን እያራሰው ማንበቤን ቀጠልኩ... "እስከዛሬ አንቺን ላለመጉዳት በስትክክል እንኳ ሴክስ አላረኩሽም ነበር ልጅ ነሽ ትጎጃለሽ ብዬ ግን ምን ዋጋ አለው ከምናምንቲያም ወላጆችሽ በሽታን አምጥተሽ አሸከምሽኝ ሀሀሀ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ገነጣጥዬሽ ሄድኩ ብትሞች ሀጥያት ትሆኝብኛለሽ እንጂ ጨርሼሽ እሄድ ነበር! ምንም ቢፈጠርና ደግመሽ ብትፈልጊኝ ውርድ ከራሴ አላቅሽም አታቂኝም! " ይህን አንብቤ ሳላስበው ጭንቅላቴን ይዤ ጮሄ አለቀስኩ ግን ሰሚ አልባው ኡኡታዬ ከጣሪይዬም አላለፈ ... ሰውየውን ያገኘው ይመስል ወረቀቱን በጥርሴ ቦጫጭቄ በተንኩት ...
ከቀናት ቡሃላ ማገገም ጀመርኩ እናቴ እያለች የነበሩትን ጥቂት እህሎች ጨርሼ ስኳርና ሙቅ ውሃ ብቻ ተግቼ ማደር ከጀመርኩ 3 ቀን ሞላኝ... ፈተናም አምልጦኛል ... ታድያ እኔንም እንደሌላው የሰው ፍጡር አምላክ ያውቀኛል? በፍፁም አያውቀኝም! ወይ እረስቶኝ ይሆናል ህይወት ምርር ማለቷን ቀጠለች ያለእድሜዬ ፈተናዬ ልክ አጣ ይቤት ክራይ ለመክፈል የነበሩትን እቃዎች በርካሽ ሸጥኳቸው ...
ከቤት ወጥቼ ጎዳና ላይ መዋል ጀመርኩ ለመጀመርያ ግዜ የጎዳና ልጆች ቢሆኑም ጓደኛ ኖረኝ በብዛት እንደኔ ችግረኛ ስለሆኑ አስጠግተው ምግብ ያበሉኛል ... ይህ በዚ እንዳለ የቤት ክራይ ግዜው አልፎ ተባረርኩና እኔም እንደነሱ ማደርያዬም ጎዳና ሆነ የውስጤን ቁስል ማንም አያውቅም ግን ያዝኑልኛል ትላልቆቹ ወንዶች ደግሞ ሲሰክሩ ያስቸግሩኛል ጥሎብኝ በዛ ሁሉ ጉስቁልናዬ መሀል ውበቴ ይታያል ለነገሩ በእናቴ ወጥቼ ነው ... የጎዳናው ህይወት ብርድና ፀሃዩ ካሎነ በሌላ በኩል ተመስገን ያስብላል ቢያንስ እርስ በርስ ፍቅር አለን ...
ከ8 ወር በላይ ግን እዛ መቆየት አልቻልኩም ህልሜን ያጨለመውን ሰው መበቀል እንዳለብኝ ወሰንኩ ያለችኝን ቡትቶ እጥብ አርጌ ፊቴን ታጥቤ ደላላጋ ሄድኩ ስራም እንዲያስገባኝ ጠየኩት ሁሌም ተራ ሴት እንደሆንኩ አስባለው አንድ ቀን እንደምሞት እርግጠኛ ነኝ ተስፋም ሆነ አላማ የሚባል ነገር የለኝም ውስጤ ለተሰበረው ልቤ መጠገኛ በቀል ብቻ ነው ያለው ስለዚ ደላላው የትም ስሪ ቢለኝ እሰራለው ብቻ ከጎዳና ልነሳ ... ደላላውም 3 ቀን በተያዥ ሰበብ ካመላለሰኝ ቡሃላ ያቅሜን ስራ እንዳገኘልኝ ነገረኝ...
ዘመድ ቀርቶ የማውቀው ሰው የለም ከጎዳና ልጆቹ ውጭ ይሄን ሳስበው ለኔ ፈጣሪ የሚባል ነገር የለም ብዬ ደመደምኩ ...
ስራ ከገባው 2 ቀን ሆነኝ የገባሁት ጭፈራ ቤት ነበር ስራዬም አልጋ ማንጠፍና ለቤቱ ሴተኛ አዳሪዎች ቀን ቀን ቡና ማፍላት ነው ... ትንሽነቴን ያዩ የዛ ሁላ ግፍ ባለቤት አልመስልም ደጋግመው ሴቶቹ "እንቺ ትንሿ የመጀመርያውን ስትበይ ታስቅሚናለሻ " ይሉኛል ሳይገባኝ ፈገግ ያልኩ ሳምንት አለፈኝ ...
💔💔💔💔 እጣ ፋንታዬ 💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 4 💔💔💔💔

የገባሁበት ጭፈራ ቤት ማታ ማታ እጅግ ይቀወጣል እኔም እንቅልፍ የሚባል ባይኔ ሳይዞር ነው የሚነጋው የምተኛው ለብቻዬ ባንድ ክፍል ውስጥ ነበር ግን ጫጫታው አያስተኛም ልክ ጫጫታው በርዶ እንቅልፍ ሸለብ ሲያረገኝ አንድ የስራ ድርሻው ምን እንደሆነ የማላቀው መልከ መልካም ወጣት ይመጣና "ትንሿ ተነሽ ነጋ ወደ ስራሽ" ይለኛል ... ተነስቼ አልጋዎቹን አንሶላ እየቀየርኩ ካነጣጠፍኩ ቡሃላ የቤቱ ቆነጃጂት ሴቶች በየተራ እየተነሱ እዛች ቡና አፍልቼ ሲቅሙና ሺሻ ሲስቡ የምንውልባት ክፍል ውስጥ ይሰበሰባሉ ... ተቀምጬ ቡና ሳፈላ እነሱ የዛሬ ስራ ሪፖርት እያሉ ከብዙ ገጠመኝ ጋር እርስ በርስ ያወራሉ ይስቃሉ .... ከሁሉም ግን ሁሌም ቀልቤን የሚስበኝ በየቀኑ አገኘን የሚሉት ገንዘብ ነው አባዬ እንኳ በህይወት እያለ በወር የማያገኘውን "ዛሬ እንደዚ ያህል ብር ሰራው " ሲሉ በውስጤ ታድለው ... እኔም እንደነሱ መች ይሆን ደና ስራ የማገኘው እላለው ...
ይገርማል ስራቸው ምን እንደሆነ እንኳ አላውቅም የማቀው ዘናጭ እንደሆኑና ሁሌም ደስተኛ እንደሆኑ ነው በዛ ላይ በየቀኑ ቢያንስ 500 ብር ያገኛሉ ... ይሄን ስራቸውን ለማወቅ ታድያ ጉጉት አልኩኝ ከመሀላቸው በእድሜ ተለቅ የምትለው አስቴር ናት ውይ ስታዝንልኝ ስታየኝ እንኳ ትለያለች በስስት ነው የምታየኝ እኔ 15 አመት ሞልቶኛል ግን ሰውነቴ በጉዳት ምክንያት ስለከሳው 12 ና 13 ነው የምመስለው ... አንድ ቀን ታድያ አስቴር ልብሷን እንዳስተጣጥፋት አዘዘችኝና የሷ አልጋ ጫፍ ተቀምጠን ማጠፍ ጀመርን ከዛ እዚ ለምን እንደመጣው ጠየቀችኝ እኔም ወላጅ እንደሌለኝና መኖርያ ስላጣው ስራ እንደተቀጠርኩ ነገርኳት ... ብዙ ታሪኬን ባልነግራትም አለቀሰች ግራ ገባኝና አብሬአት አለቀስኩ እስዋም አቅፋኝ አይዞሽ እሺ ታድያ ወይዘሮ አሰገደች ገና አላገኙሽም አለችኝ ግራ ተጋብቼ ማናቸው አልኳት የጭፈራ ቤቱ (የቡና ቤቱ) ባለቤት መሆናቸውን ነገረችኝ አሁንም ግራ ስለገባኝ እና እኔን ለምን ያገኙኛል ብዬ ምላሽዋን ሳልሰማ ያ ከእንቅልፌ የሚቀሰቅሰኝ የቤቱ ልጅ "ትንሿ ልእልና " ብሎ ሲጠራኝ ሰማውት አስቴርም ነይ እንባሽን ጠራርጊና ሂጅ ብላ ሶፍት ሰጠችኝና እየጠረኩ በፍጥነት ወጥቼ ልጁጋ ደረስኩ...
ነይ ተከተይኝ አለኝ እርጋታው ደስ ሲል ከኋላው እየተከተልኩት የት ልኔድ ነው አልኩት ስራ ልጀምሪ ይሆናላ ምን አቃለው አለኝ ድንገት ልቤ ስንጥቅ አለ እንዴ ምን አስደነገጠኝ ? ድንጋጤዬ ለራሴም እየገረመኝ ስራ ከጀመርኩ ሳምንት ሞላኝ አይደል አልኩት ... ዞር ብሎ አየኝ አስተያየቱ ደረቴን ሰንጥቆ ልቤ ውስጥ ሲገባ ታወቀኝ ቆም አለና ምስኪን አታውቂም ማለት ነው አለ እውነት ለመናገር ከተናገረው ይልቅ የልጁን አይኖች ነበር ያስተዋልኩት ...እሱም ምላሽ አልጠበቀም አንድ ትልቅ ሳሎን የሚመስል ክፍል ውስጥ ይዞኝ ገባ ከአንዲት ወፍራም ትልቅ ሴትዮ በቀር ማንም የለም ...
አድርሶኝ ተመልሶ እስኪወጣ በአይኔ ተከተልኩት ምን እየተሰማኝ ነው? በልጁ ለምን ይሄን ያክል ተመሰጥኩ? ለጊዜው መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች ስለ ፍቅር እንኳ ሲባል እንጂ በፊልምም አላውቀም .. .ልጁ መውጣቱን ያስተዋለችው ሴትዮ "አቤልን ታቂዋለሽ" አለችኝ ማነው እሱ በሚመስል አስተያየት ተመለከትኳት "ይሄ እኔጋ ያመጣሽን ነዋ አፈጠጥሽበትኮ "አለችኝ (ውይ ስታስፈራ ) እኔም እንደመደንገጥና መቅለስለስ እያልኩ ኧረ አላቀውም አልኳት "ለመሆኑ እድሜሽ ስንት ነው ወንድ ደርሶብሽ ያውቃል ? " ብላ ጠየቀችኝ 15 አመቴ ነው አልኩና ዝም አልኩ "ድንግልናሽን ሸኝተሻል ወይ ?የዛሬ ልጆች መቼም አትታመኑም" አለች ያለፈ ስቃዬን ያክፉ ሰውዬ በአይምሮዬ መጣ እንደማንገሽገሽ አረገኝ ... ግን ለምን ጠየቀችኝ ተናደድኩ በውስጤ ምን አገባት አልኩ "መልሽልኛ" ብሎ ስትጮህ የደነገጥኩት ድንጋጤ ዛሬ ድረስ ትዝ ሲለኝ ላብ ያጠምቀኛል ...ኧረ በፍፁም እኔኮ ህፃን ነኝ አልኳት በምን ታቃለች ? ተደፍሬ ነበር ብዬማ ለማንም አላወራም ...በደስታ ካካካካ ብላ ሳቀችና ጎሽ ታድያ ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ጠንካራ ደፋር ሴት ሁኚ እሺ አለች ... የእውነት ሳይገባኝ ወደ አስቴር እራሷ ይዛኝ ሄደችና "ጥሩ ጥሩ ልብስ ግዙላት ሁለት ቀን በደምብ ተንከባክበሽ ደምበኞቼን እንዳታስቀይምብኝ አሰልጥኛት "...ብላ ካዘዘች ቡሃላ ተመልሳ ሄደች... አስቴር እንዳልገባኝ ስላወቀች እውየልሽ ትንሿ ከዛሬ ጀምሮ ስራሽ እንደኛ ነው አለችኝ ደስ አለኝና እንደናተ በዚ እድሜዬ እችላለው ? ብዙ ብር ላገኝ? ብዬ ጠየኳት ግራ ገብቷት እኛኮ ገላችንን ነው የምንሸጠው አለችኝ ሰማይ ወርዶ የተጫነኝ ያህል ተሰማኝ ...
ያለፈ ታሪኬን እያሰብኩ ተስፋ ቢስ ሴት መሆኔ እና ከዚ የተሻለ ምንም እጣ እንደሌለኝ አስቤ ያን አውሬ አግኝቼ ተጫውቼበት ወይ ገድዬው እስከምሞት ይህን የህይወት እጣ አሜን ብዬ መቀበልን ወሰንኩ አስቴር ልብሶች ገዛችልኝ ... ውብ ሆንኩ እራሴን በመስታወት አይቼ ለራሴ አድናቆትን ቸርኩት ... ከሁለት ቀን ቡሃላ የተባለው ሰአትና ቀን ደረሰና ምሽት ላይ ያ ልቤ የደነገጠለት ወጣት ወደኔ መጣ በጣም እንዳማረብኝ ከልጁ ቃላት በተጨማሪ ድንጋጤው ነገረኝ እንዳማረብኝ ነገረኝና ወደሴትየዋ (ወይዘሮ አሰገደች )ጋር ይዞኝ ሄደ ለዚ ልጅ ለየት ያለ ስሜት ተሰምቶኛል ግን ምን እንደው አላቅም ...
ሴትየዋም ከአንድ ጎልማሳ ባለሀብት ጋር አገናኝታኝ ብዙ ገንዘብ ተቀብላ በል ነገ ይዘሃት ና አለችው ገንዘቡን እያሳየችኝም ይሄ ያንቺም ነው ብቻ አስደስተሽው ነው ብላኝ ካካካ ብላ ያ የሚቀፍ ሳቋን ለቀቀችው ... እሱም ይዞኝ በመኪናው አንድ እጅግ በጣም ያማረ ግቢ ደረስን ፍርሃት ወረረኝ ልቤን ልተፋት ደረስኩ ሰውነቴ ውሃ ሆነ ድንዝዝ አልኩ... ከሰአታት ቡሃላ ሌባ እያለ ይቀጠቅጠኝ ጀመር ብለምነውም አልሰማኝ አለ ድንግል ነች ብላ ገንዘብና ግዜዬን በላቹ... የሱን ዱላ የምችልበት አቅም አጣው ብጮህ ባለቅስ ብለምነው ትርጉም አልባ ሆንኩ...
በቅጡ እንኳ ሳይነጋ እንደቆሻሻ እየተጠየፈ ወደ ጭፈራ ቤቱ መለሰኝ ... እዚም ሌላ ስቃይ የጭፈራ ቤቱን ክብርና ስም አጠፋሽ ተብዬ ከተገረፍኩ ቡሃላ ጨለማ ክፍል ውስጥ ያለ ምግብና ውሃ ተዘጋብኝ...

ቶሎ ቶሎ አንብቡትና ቀጣዩን ክፍል ልልቀቅላችው
ምን ያህል ሰው አነበበው☝️☝️☝️☝️
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 5 💔💔💔💔

ምድር ላይ እንደኔ በበደልና በግፍ እድሜውን የሚጨርስ ፈፅሞ አይኖርም በቃ የኔ ይለያል ...ወንዶች ሁሌም ከስሜታቸው መወጫነት በዘለለ ቅንጣት ለሴት ልጅ ርህራሄ እንደሌላቸው አይቻለው አባቴም ይሄኔ ቫይረሱን እሱ ይሆናል አምጥቶ ለእናቴም መዘዝ የሆናት ...እዛች ጨለማ ክፍል ውስጥ ሆኜ የማላስበው የለም በዚ መሀል ያሳለፍኩትን መከራ አንድ በአንድ ማሰብ ጀመርኩ ድንገት ትዝ ሲለኝ HIV እንዳለብኝ አስታወስኩ ይሄኔ ዱላና ርሃብ ያደከመው ሰውነቴ ዳግመኛ በፍርሃት ይውረገረግ ጀመር.... ማልቀስ ቢገል ኖሮ ወይ እንባችን በመውረዱ ሟሙተን የምናልቅ ቢሆን እዚች ክፍል ውስጥ እሬሳዬም አይገኝም ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ማልቀስ ሌላ ለቅሶን እንጂ ምንም አልፈጠረልኝም ... አሁን በሽታው እንዳለብኝ ሲሰሙ ያ ሀብታም ሰውዬ ከዚች አስፈሪ እርጉም እኔን በመሳሰሉ እንቡጦች ከርሷን ከምትሞላው የሴት አረመኔ ጋር ሁነው ሲሰቅሉኝ ታየኝ ገና በሀሳብ ብቻ ታይቶኝ 'ዋይይይይይይይ' ብዬ ቀወጥኩት...
ድንገት በሩ ተከፈተና አንድ ሰው ክፍል ውስጥ ገባ ሸሽቼ ጥግ ያዝኩና ማንነቱን ማስተዋል ጀመርኩ ዝም እንድል እስጠነቀቀኝና በቀስታ ወደኔ ተጠጋ "የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ..." አይደል ከዚ ቡሃላ ከሞት ያነሰ ከስቃይ የከፋ ምን ይደርስብኛል እንደገና እልህና የማላቀው የድፍረት ስሜት ተሰማኝ ማነህ አልኩት ... አስቴር ናት እዚ እንዳለሽ የነገረችኝ ብሎ የስልኩን መብራት አበራው ያ ልጅ ነው አቤል ቆንጂዬው እሱ መሆኑ የሆነ ስሜት ሰጠኝ በጆቹ ዳበሰኝ ቀና ብዬ ሳየው ከአይኖቹ እንባ ይፈሳል ኦ ፈጣሪ ለመጀመርያ ግዜ ወንድ ልጅ ሊያውም ለኔ ሀዘን ተሰምቶት አየው ገረመኝ በጥሞና አስተዋልኩት ከንፈሮቼ ደርቀዋል ልጁን እንቅ እቅፍ አርጌ አንገቱ ስር ገብቼ ባለቅስና ቢወጣልኝ ብዬ ተመኘው እሱ ግን እንባውን እየጠረገ ተመልሶ በፍጥነት ወጣ ... ተናደድኩ የተናደድኩት ለምን ሄደ ብዬ ሳይሆን ለምን የማላቀው ስሜት ለወንድ ተሰማኝ ብዬ ነበር ...
አቤል ወቶ አፍታም ሳትቆይ አስቴር ምግብና ውሃ ይዛልኝ መጣች አልቅሳ እንደነበር ታስታውቃለች ምግቡን ተስገብግቤ ስበላ ውሃውንም ስጠጣ እራሴን አላስተዋልኩትም እንጂ ለተመልካች አስገርም እንደነበር አልጠራጠርም ... ልክ ስጨርስ ማንም መቶ ቢጠይቅሽ ከአቤል ውጪ መብላትሽን እንዳትናገሪ ብላኝ ወጣች ... ሁለቱ በድብቅ እንዳበሉኝ ተረዳው ... ይህ በዚ መልኩ ቀጠለና ልክ በ3ኛው ቀን አስቴር እንደተለመደው ምግብ ይዛልኝ መታ ከበላው ቡሃላ ለምን ድንግል ነኝ ብዬ እንደዋሸው ጠየቀችኝ እኔም ስቅስቅ ብዬ እያለቀስኩ ሁሉንም ታሪኬን አጫወትኳት ...
አይ አስቴር ያኔ ያዘነችው ማዘን ቃል አይገልፀውም አፅናናችኝና እቅፍ አርጋ ከዚ ቡሃላ ስፈልግ እንደ እህት ስፈልግ እንደ እናት እንዳያት ነገረችኝ ከዚም ክፍል ሴትየዋ እንደምታስወጣኝ ከዛም ግን እዛው ቤት ሴተኛ አዳሪ ሆኜ እንደምቀጥል ነገረችኝ ...
ልክ በሳምንቴ ከቤቱ ልጆች ጋር ተቀላቀልኩ እራሴን መጠበቅ ና መዘነጥ የስራ ድርሻዬ ሲሆን ለ5 ወር የምሰራውን ለሴትየዋ ማስረከብ እንዳለብኝ ተነግሮኝ ተስማማው ባልስማማስ? የታባቴ እደርሳለው ... አሁን ውስጤ የሚጠይቀኝን ጥያቄ ለምትቀርበኝ አስቴር ልጠይቃት ወሰንኩ...ለአስቱም HIV እንዳለብኝ ስነግራት ደንግጣ ተመርምረሻል ስትል ጠየቀችኝ አልተመረመርኩም ግን እናትና አባቴ በሱ እንደሞቱ ስነግራት መመርመር እንዳለብኝ ነግራ በነጋታው ማንም ሳይሰማ ጤና ጣብያ ሄድን ... ከምርመራ ቡሃላ ግን የሰማውትን ማመን አቃተኝ ነፃ ነኝ አላመንኩም በህይወቴ ለመጀመርያ ግዜ የደስታ እንባ ከእይኔ ወረደ አስቴር ነፃ ያረገችኝ ይመስል አስሬ እያመሰገንኩ ሳምኳት ...
ወደጭፈራ ቤቱ ስንመለስ አቤልን ሲመለከተን አየውት አቤል ማለት አስቱ እንደነገረችኝ ከሆነ የባለቤቷ (የ አሰገደች ) ዘመድ ነው እዛ ቤትም ሰራተኛ መቆጣጠር ነው ስራው ... ወደኛ መቶ ሰላም ካለን ቡሃላ ተመልሶ ሄደ አቤልን ሳየው እደነግጣለው የማላውቀው ስሜት ይሰማኛል ይህም ሌላ ፈተና ሆነብኝ... በተለይ አስቴር ይሄ ልጅ ሳይወድሽ አይቀርም ካለችኝ ወዲ ከሀሳቤ ውስጥ አሎጣ ብሎኛል ግን ደሞ ማንነቴን ዞር ብዬ ሳስብ እንኳን በአቤል ልፈቀር እኔም ፍቅር የሚባል ነገር ላስብ ቀርቶ መኖር መቻሌ ራሱ ጥያቄ ምልክት ነው!!!
አሁን የቢዝነስ ስራ(ሴተኛ አዳሪነት) ን ጠለቅ ብዬ ከገባሁበት 4ኛ ወሬን አጋምሻለው ትንሽነቴና ቆንጆነቴ ብዙ ወንዶች እንዲመኙኝ አርጎኛል ሱስ ውስጥም መግባቴ ግድ ነበርና ማጨስም ሆነ መቃም የግሌ ሆነዋል ብቻ ባጠቃላይ ብዙ ገጠመኝና ፈተናዎችን ባሳልፍም ሲመሽ ሲነጋ ግን የሚፈታተነኝ የአቤል ነገር ሆነ አሁን በግልፅ አረጋግጫለው አቤል ያፈቅረኛል!! ከነማንነቴ ከነምንነቴ አምኖ ተቀብሎ ለኔ ክንፍ ብሏል ... እኔም ምንም እንኳ ልቤ በሀዘን እንክትክት ቢልና ያለፈውም ሆነ ያለሁትበ ማንነት አስቀያሚ ቢሆንም ለማፍቀር ግን እድል አላጣውም በቃ አፈቀርኩት ... ማፍቀር ሀጥያት ቢሆን ይህ ለኔ ሀጥያት ይሆን ነበር ማፍቀሬ ከኔ አልፎ አስቴርን አስጨነቃት ግን እራሴን እንድጠብቅና ፈጣሪ የሰጠኝን ፀጋ ባግባቡ እንድጠቀምበት መከረችኝ...
ከአቤል ጋር በድብቅ ፍቅር ጀመርን ያቺ አረመኔ ሴትዮ ብሰማ እንደምትገለኝ ሁሉም አስጠንቅቀውኛል እሱንም ቢሆን ከንደኔ አይነቷ ሴት ፍቅር ጀመረ ቢሏት ያለምንም ማስጠንቀቅያ ታባረዋለች ከዚ ቤት ከወጣ ደሞ ምንም ዘመድ እንደሌለው ነግሮኛል ... ከአቤል ጋር እቅድ አቀድን ለመጀመርያ ግዜ አላማ ኖረኝ ትንሽ ብር አጠራቅመን ከዚ ቤትና ህይወት ነፃ ወተን አብረን ልንኖር በእንባዎቻችን ቃል ተገባባን...
ግን ምን ዋጋ አለው ድሮም ፈጣሪ እኔን መች ያውቀኝና በፍቅርና ደስታ 5 ወር ከቆየን ቡሃላ ማርገዜን አወኩ ማን እንደነገራት ሳናውቅ ከአቤል ጋር ልንጠፋ ከተነጋገርንበት ቀን ቀድማ ሰምታ ኖሮ እንዴት ከሴተኛ አዳሪነት ሳትላቀቂ ፍቅር ያምርሻል ብላ 100 ብርና ጥቂት ልብሴን ሰታ አቤልን ዳግም የማላገኝበት ቦታ ወስዳ ጣለችኝ ድጋሚ ሌላ ጨለማ ህይወት ...
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 6 💔💔💔💔

እድሜዬ 17 ሊሞላ ቀናት ቀርተውኛል ያለፈው ህይወቴ መራራነት የወደፊቱን እንዳልናፍቅ አርጎኛል የሁለት ወር ፅንስ በሆዴ ይዤ የምገባበት ግራ ገብቶኛል፤ እዛው ሴተኛ አዳሪ ሆኜ መኖር ትልቅ እድል እንደነበር ሳስብ ያኔ አቤልን ያየሁበትን ቀን ምናለ አይኔን ባጠፋው ብዬ አለቀስኩ... ግን የሚገርመው ተስፋ አለኝ እዛ ግቢ ሲያጣኝ ይፈልገኝ ይሆናል ብዬ አስባለው ከዛም ሳላስበው ስቅስቅ እያልኩ እያለቀስኩ ፈጣሪን ምርር አረገዋለው... ለምን እንደረሳኝ ለምን ያለእድሜዬና ያለጥፋቴ እንደሚፈትነኝ መልስ ላላገኝ ድምፄን ከፍ አድርጌ እጠይቃለው...
በቤተክርስቲያን ደጅ ማደር ከጀመርኩ 3 ቀን ሞላኝ በቃ አይርበኝም ሳለምን ይሰጡኛል አንድ ሰው ምግብ የሚሰጠኝ ግን እዛ ተቀምጬ ስውል ሲያዩኝ የኔ ቢጤ መስያቸው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ አማራጭ ስላልነበረኝ እንጂ እንደ የሰው ፊት የሚከብድ የሰው እጅ እንደማየት ቅስም የሚሰብር ምንም የለም! ለነገሩ ምን ቅስም አለኝ ገና በልጅነቴ ነጥቀውኝ... የማላውቀው የበቀል ስሜት ደሜን እያንተከተከው ከተቀመጥኩበት የቤተክርስቲያን ደጅ ተነስቼ ተሳለምኩና ወደ ቀድሞ ሰፈሬ ልጅነቴን ፤ ህልሜን ውደነጠቀኝ ሰው ጉዞ ጀመርኩ ትዝ ይለኛል ጀሞ እሚባል ቦታ ወስዳ እንደጣለችኝ ...ታክሲ ውስጥ ስገባ በእጄ የያዝኩት የልብስ ፌስታልና 100 ብር ነበር ለሚያየኝ ሰው ከሰው ቤት የወጣው እመስላለው ...
የድሮ ሰፈሬ ልክ ስደርስ ትንሽ ነገር ተቀያይሯል ግን ትዝታው እንዳለ ነው እኛ የነበርንበት ቤት ፈርሶ ትልቅ ቤት ተሰርቶበታል ወላጆቼን በተለይ እማን እያሰብኩ የማያባራው እንባዬ ይዘንባል ማንም ቢያየኝ አያውቀኝም... አንድ ጥግ ይዤ አሁን ምን እንደማረግ እያሰብኩ ብዙ ከተቀመጥኩ ቡሃላ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ... ያኔ ልጅ እያለው ያን ሰው አግኝታ ስራ ያስቀጠረችኝን ልጅ ማግኘት... እንዳሰብኩትም ካንድ ቀን ሙሉ ፍለጋ ቡሃላ ቤት ቀይራ ሌላ ሰፈር ተከራይታ አገኘዋት እድለኛ ነበርኩና አላወቀችኝም ... የእናቴን ስም ነገርኳት እንድታውቀኝ ግን አልፈለኩም ነበር ከዛም የእናቴን ታሪክ እንባ እየተናነቃት ነገረችኝና ልጇ(እኔ) የት እንደገባሁ እንኳ እንደማታውቅ ነገረችኝ እኔም ዘመዳቸው ነኝ በማለት ስለሰውየው ዘዴ እየፈጠርኩ አወጣጣኋት ...እሷም አንዲት ሴት ደፍሮ እስር ቤት እንደገባ ነገረችኝ የውስጥ ንዴቴ ይባስ ጨመረ አልምረውም!! ስል ፎከርኩ ልጅቷም ግራ ገብቷት "እ" አለችኝ ምን እንዳልኩ ለማጣራት ለካ ድምፄን ከፍ አርጌው ነበር ... አይ ምንም ብያት የታሰረበትን ቦታ ካጣራው ቡሃላ ተሰናብቻት ቤት እንዳለው ሰው ወደ ቤቴ ልሂድ ብዬ ወጣው...
አሁን ሴትነቴ ማለትም ለአካለ መጠን መድረሴ ጎልቶ ይታያል ወንድ አይን ውስጥ በቀላሉ እገባለው በዛ ላይ እርጉዝ መሆኔን ከኔ ውጪ ማንም አያውቅም ታድያ ተመልሼ እዛው ቤተክርስትያን ልሄድ አልኩና መልሼ ደግሞ ሀሳቤን በመቀየር የዛሬ 2 አመት ባለውለታዎቼ የጎዳና ልጆች ጋር ሄጄ ለማደር ወሰንኩ... ስደርስ አላወቁኝም ነበር ከዛ ግን ስነግራቸውና ትዝ ስላቸው ልክ እንደ እህታቸው በደስታ ተቀበሉኝ ስታገኚ ተውሽን ያለማለታቸው ለራሴ እራሱ ተሰማኝ... በነጋታው በነሱ ምክር ተነስቼ ካገኘው ሰው ቤት ካለዛም እንደለመድኩት ቡና ቤት ስራ ለመቀጠር ወስኜ ደላላጋ ሄድኩ...
ልክ ስደርስ ያልጠበኩት አቤል እዛ ሰራተኛ ይዞ ሊሄድ ፊት ለፊት ተገናኘን ልቤ ስንጥቅ ሲል ታወቀኝ ግራ በተጋባ ስሜቴ በደመነብስ ፍቅር ብዬ ስቀርበው እንዳትጠጊኝ ክብሬን የሚያዋርድ (አፀያፊ ቃል) ሰደበኝ ፍቅር ልእልናኮ ነኝ አልኩት እንባዬ ያለገደብ እየወረደ ..."ሂጅ ከዚ ፍቅር ስሰጥሽ በክህደት አቁስለሽኝ ከነ እርካሽ ማንነትሽ ልቤን ባስረክብሽ በምላሽሽ ማንነትሽን እርካሽነትሽን ማሳየትሽ አልበቃ ብሎ ከማንም የደቀልሽውን ዲቃላ ልጅህ ነው ልትይ ስትይ መንጥራ አባረረችሽ አይደል ? አንቺ ደረጃ ቢስ" አለ ይህን ሁላ ሲለኝ ከሰው ፊት ከመዋረዴ ይልቅ ማን እንዲ ብሎ ነግሮት ባንዴ እንደጠላኝ አሰብኩ ከዛች ሴትዮ በቀር ማን ይህን ያረጋል? እሷን ደሞ አቤሌ በፍፁም አያምናትም! ይህን በውስጤ እያልኩ እያለቀስኩ እባክህ አንዴ ስማኝ ብዬ ስቀርበው በጥፊ መቶኝ ምራቁን ተፍቶብኝ ሄደ ...ሰማይ ምድሩ ዞረብኝና ወደኩ
ከሰአታት ቡሃላ እንደመባነን ስል ልብሴ በውሃ እርሶ የጎዳና ጓደኞቼ የሚያድሩባት ላስኪት ቤት ውስጥ በጀርባዬ ተኝቼ ነበር ... እንደነቃው ሲያዩም ምግብ ለማምጣት ሁሉም በየፊናቸው ሄዱ ለመጀመርያ ግዜ ጨለማና ብቸኝነት ፍርሃት ለቀቀብኝ ቀን ስላጋጠመኝ እያሰብኩ እያለቀስኩና በፍርሃት እየተንቀጠቀጥኩ አንድ በጣም የሰከረ ሰው ካጠገቤ ደርሶ የሚለው በቅጡ ባይሰማም " እዴዴዴ ዛሬ በነፃነት... አገኘው ..." እያለ ቀበቶውን እየፈታ ተጠጋኝ ...ደንዝዣለው..
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔💔 ክፍል 7 💔💔💔💔

ሰካራሙ ሰውዬ ሊደፍረኝ እንደሆነ ባውቅም ለመሸሽ እንኳ ጥረት አላረኩም በቃ የኔ እጣ ይህ ነው ቃየልን ያዩት ሁሉ ይፈነክቱት እንደነበር ሁሉ እኔንም ያዩኝ ሁሉ ሰውነቴን ይጠቀሙበትና ጥለውኝ ይሄዳሉ!! እሱስ ወንድሙን አቤልን በቅናት መንፈስ ተነሳስቶ ገሎት ስለነበር ነው እኔ ግን ያለ ሀጥያቴ አርክሰው አርክሰው ሰው መሆኔን እንድጠላ አረጉኝ ወደዚች ምድር ከመጣው ጀምሮ ህይወቴ በማልቀስና በስቃይ የተሞላች ናት ... ሰውየው እየተወላገደ ሱሪውን አውልቆ ጨርሶ ከተቀመጥኩበት ፈንግሎ በጀርባዬ አስተኛኝ የኔ እምባ ከመውረድና ሰውነቴ ከመንቀጥቀጡ ውጪ ምንም አይነት ድምፅ አላወጣሁም መጮህ እራሱ የጠፋብኝ ይመስለኛል ምክንያቱም ያኔ ልጅ እያለው ጀምሮ ስጮህ የደረሰልኝ አይዞሽ ያለኝ የለም ስለዚ ከንቱ ጩኸት ለትንሿ ልእልናም አልበጀ ዝም ድንዝዝ ብዬ የሚያረገውን መመልከት ብቻ...
በጀርባዬ አስተኝቶ ልብሴን ለማውለቅ ሲታገል ከጓደኞቼ አንዱ የሆነው አቡቸር ምግብ ይዞልኝ ድንገት ሲበር ደረሰ በሰውነትም ሆነ በእድሜ ከሁላችንም የሚበልጠው አቡቸር ይህን በመጠጥ የወላለቀ ሰውዬ ከመቅስበት ከላዬ ላይ አንስቶ ካጠገቡ ያለው አጥር ጋር አጋጨው መልሶ መሬት አስተኝቶ ደጋግሞ ሲመታው በደም ተነከረ የጨረቃዋ ብርሃን ወለል ብሏል ተከታትለው ሁሉም ልጆች ከሄዱበት መጡ ...ምን እንደተፈጠረም ጠየቁን አቡቸርም ሊደፍረኝ ሲል ደርሶበት እንደሆነ ሲነግራቸው በንዴት እንደእባብ ይቀጠቅጡት ጀመር... ካሰቃዩት ቡሃላም ልብሱን አሶልቀውና ኪሱ ውስጥ የነበረውን የኪስ ቦርሳ አውጥተው አባረሩት... እንባዬ ደረቀ ከልብ የመነጨ ደስታ ተሰማኝ ለካ ከጎኔ ተቆርቋሪ አለኝ ...ሁፍፍፍ እውነት ለመናገር እንደዚ ቀን ኮርቼ አላውቅም የተናቀ ሰው ልብ ለካ ንፁ ነው እነሱን እንደሰው እንኳ የሚቆጥራቸው የለም ግን ልዩ ናቸው ተስፋ የቆረጠው እኔነቴ ላይ ተስፋ ዘሩበት በጥዋት ተነስተው ውሃ አምጥተውልኝ ተጣጥቤ ቆንጆ ልብሴን ለበስኩ ጠንካራ ሴት መሆን እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩትና ፊት ለፊቴ ያለችው የኪዳነምህረትን ቤተክርስትያን ተሳልሜ ...ታክሲ ውስጥ ገባው...።
ታክሲ ውስጥ አንድ ሀሳብ መጣልኝ ሀኪም ቤት ገብቼ ልጄን ማሶረድ እንዳለብኝ ወሰንኩ ወደዚች ምድር ተጨማሪ ነብስ አምጥቼ ከማሰቃይ ምንም ትልቅ ሀጥያት ቢሆንም አሶጣዋለው ብዬ ወሰንኩ ...በውሳኔዬም ፀንቼ ከታክሲ ወረድኩና አንድ ሀኪም ቤት ገባው ከዛም ግን 3 ወር አልፎታልና አትችይም ብሎ ከለከሉኝ አልቅሼ ለመንኳቸው ግን አልሰሙኝም ካለዛ እራሴን አጠፋለው ስለው ዶክተሩ በዚ እድሜዬ እንዲ ያስመረረኝ ነገር ባይገባውም 1000 ብር ካለኝ በግል እንደሚረዳኝ ነገረኝ እኔ 100 ብርም አይሞላምና የነበረኝ ተነስቼ ወጣሁ...
ብሞትም ልሙት ብዬ በራሴ ፈርጄ በአፍ ሲወራ እንደሰማውት ብዙ የአሞክሲሊን ኪኒን በኮካ አድርጌ ለመውሰድ ወስኜ ከገዛው ቡሃላ ይዤው ቤተክርስትያን ደጅ ሄጄ ተቀመጥኩ ...ከዛም ወሰድኩት ... ከሰአታት ቡሃላ አይኔን ስገልጥ እራሴን ሀኪም ቤት አገኘውት ብዙ ደም ይፈሰኝ ነበር ...ልክ ስነቃ አንድ ትልቅ ሴትዮ " ልጄ እንኳን ተረፍሽ ልክ ግን አልሰራሽም እዛ እራስሽን ስተሽ ወድቀሽ ነው ያገኘንሽ ብትሞችስ?"አሉኝ ዞር ብዬ አየዋቸውና እዚ እርሶ ኖት ያመጡኝ አልኳቸው በአዎንታ እራሳቸውን አነቃነቁና ቤተሰቦችሽ እንዳይጨነቁ እንደውልላቸው አሉኝ ... እንባዬ ከንግግሬ ቀደመ እሳቸውም የእናትነት አንጀታቸው እየተላወሰ "አይዞሽ ልጄ ዛሬን አድረሽ ትወጫለሽ የህክምናውንም ወጭ እኔ እችልልሻለው አታልቅሽ እኔ ከእግዜር አገኘዋለው "አሉኝ ... ይህችን አጋጣሚ እኚን ሴት ጥሎልኝ ተረፍኩ ተመስገን ፈጣሪ ደጁ ላይ ሀጥያት ብሰራም ይቅር ባይ ነውና አተረፈኝ ሴትየዋንም ከልቤ አመስግኜ ስለያቸው 300 ብር ሰጡኝ በልቤ ስንት አይነት ሰው አለ ? ለካ እንዲ ሲያጋጥም ደጋግ ሰዎችም አሉ? ፈዝዤ ካይኔ እስኪርቁ ተመለከትኳቸው...
ካገኘዋት 300 ብር ላይ 200 ለነአቡቸር ሰጥቻቸው ደላላጋ ስራ ልቀጠር ሄድኩ ... ባንድ ጭፈራ ቤት አስተናጋጅነት ገባው ጭፈራ ቤት የመረጥኩት ማደርያ ስላልነበረኝ እዛው ለማደር እንጂ ሴተኛ አዳሪ ፈፅሞ የመሆን እቅድ የለኝም !
ልክ በ 2 ሳምንቴ እዛ ጭፈራ ቤት አንድ ሰው ቢራ አዞኝ ልክ ስወስድለት በድንጋጤ ቀጥ አልኩ ሰውየውም ግራ ተጋብቶ በጎንና በጎን ዞሮ ምን እንዳየው ካጤነ ቡሃላ "ችግር አለ ቆንጆ?" ብሎ ጠየቀኝ ወደኋላ ተመልሼ ልጅነቴ ላይ ያን ጨካኝ ሰውዬ ፊቴ ላይ ሳልኩት አዎ እራሱ ነው " እናቱ" ሲል እንደምንም እራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ አይ ምንም ችግር የለም ብዬ በፈገግታ የቢራ ጠርሙሱን ከፍቼለት ተመለስኩ ትዝታ አሰመጠኝ በቢራ ጠርሙስ አናቱን ብለው ደስ ባለኝ በቀሌን መበቀያዬ ቀን ዛሬ ነው ግን ሴት ደፍሮ ታስሮ አልነበር ? እንዴት አሁን መጣ? ውስጤ የፈጠረው ጥያቄ ነበር ከዛም አይ ሀገሬና ህጎችሽ ብዬ የንዴት ፈገግታ ፈገግ አልኩ...
ሰውየው ደጋግሞ ከጠጣ ቡሃላ ሴት እንደሚፈልግ ነገረኝ የቤቱ ሴተኛ አዳሪ ባልሆንም ለእቅዴ መሳካት አብሬው ላድር ተስማማውና አንድ ጥግ ብቻውን ያለ መኝታ ክፍል ውስጥ ይዤው ገባው ... እንዴት ዘመኗን ያበላሸውን ልጅነቷን የነጠቃትን ሴት ይረሳል ? ብቻ ምን ባደርገው ነብሱ ሳይወጣ በስቃይ እድሜውን እንደሚጨርስ እያሰብኩ የክፍሉን በር ቆለፍኩት...
ነገ መጨረሻውና ይበልጥ በኛ እድሜ ላለን መልክት ያዘለው ክፍል....

የእውነት ይህን ታሪክ ስፅፈው እራሱ እምባ ይተናነቀኛል😓😓😞 በጣም አስተማሪ ነው ያልጀመራቹም የጀመራቹትም እንድታነቡት ስል አጠር አርጌ ለማቅረብ እሞክራለው!
💔💔💔💔እጣ ፋንታዬ💔💔💔💔
💔💔💔የመጨረሻ ክፍል 💔💔💔
#አስተማሪ #እንዲሁም #አሳዛኝ

በሩን ዘግቼ ዞር ስል አጅሬ ልብሱን ያወላልቅ ጀምሯል አናቱን ብሎ መገላገል ነበር እያልኩ በልቤ እንዴ አትቸኩል እንጂ ትንሽ እየጠጣን እንጫወት አልኩት ተስማማና "እሺ እዘዢ የኔ ልእልት" አለኝ ባነጋገሩ በጣም ብገረምም ስካር ስላጠናበዘው ፈገግ ብዬ አለፍኩት ... ቢራውን ላመጣ ስሄድ አንድ ሀሳብ መጣልኝ በፍጥነትም ክፍሌ ገብቼ የእንቅልፍ ኪኒን ይዤ ተመለስኩ.... እየተሳሳቅን መጠጣት ጀመርን ከዛ ሳልጠይቀው መለፍለፍ ጀመረ ...
"ይገርምሻል ቆንጆ ከ7 አመት በፊት አንዲት ሴት የወሲብ አጋሬ ነበረች በርግጥ ትንሽ ልጅ ናት ግን እንዴት ትመቸኝ እንደነበር ... ከዛንልሽ እናትና አባቷ በ HIV መሞታቸውን ስሰማ ኤች.አይ.ቪ አስያዘችኝ ብዬ በንዴት የሰራሁባት ግፍ እንዴት እንደሚፀፅተኝ..." እያለ በቁጭት ሲያወራ ቱ ጨካኝ አረመኔ ነህ ... አልኩት ድምፄን ከፍ አድርጌና ልክ ያየሁት አስመስዬ በምሬት ስሰድበው ደንግጦ "እ ታቂያታለሽ እንዴ? " አለኝ ስካሩ እንደበረታበት አይንና ድምፁ ሳይቀር ያስታውቃል እንደገና መለስ ብዬ አይ ሴት ልጅ ስለምታሳዝነኝ ነው አልኩት በውስጤ ያቺ ሴት ልትበቀልህ ትንሽ ደቂቃዎች እንደቀሯት ማ በነገረህ እያልኩ ... ልጅቷን ታድያ ይቅርታ ጠየካት ስል ጠየኩት " ኧረ ሞታ ይሆናል ... " አለና በዛው ቀጥሎ " ባክሽ አሁን እስዋን ተያትና ነይ አውልቂ ሳትሰሪ ብር ልትቀበይኝ አማረሽ እንዴ አለኝ" ...
ሳያየኝ የእንቀልፍ መዳኒቱን ጨምሬ አጠጣሁትና ... ወድያው ያቺ ትንሿ ልእልና እንደዛ በግፍ ህይወቷን ያበላሸሃት ገና ምንም በማታውቅበት እድሜዋ በዚ አናትህ ላይ በወጣ ስሜትህ የተጫወትክባት ያለሃጥያቷ እናቷ እንድትሞት ሰበብ የሆንካት ትምርቷን አቁማ ጎዳና ላይ እንድትወድቅ ያደረካት... ብቻ ዘርዝሬም አልጨርሰው ግን ያቺ ህፃን እኔ ነኝ ዛሬ ልበቀልህ እድሉን ሳገኝ የተሰማኝ ደስታ ወደር የለውም ብዬ ...ከት ብዬ የንዴት ሳቅ እንባ እየተናነቀኝ መሳቅ ጀመርኩ ... በጣም ደንግጦ "ምንድነው ምን ልታረጊኝ ነው..." ብሎ ሳይጨርስ እንቅልፍ ይዞት ሄደ
አሁን የማረገው ግራ ገባኝ ግን በቃ ይህ ሴትን እንደልቡ እየተጫወተባት የሚማግጥበትን ብልቱን መቁረጥ አሰብኩ ግን ዝግንን አለኝ ...ምን ላርገው ግራ ገብቶኝ ብዙ ከተቀመጥኩ ቡሃላ ከአልጋው ጋር አስሬ አይኑ ውስጥ እየገለጥኩ ሚጥሚጣ ጨመርኩበት አፉን አፍኜ ጆሮ ውስጥ የጠርሙሱን ቢራ ጨመርኩበት ... ከዛም ቤቱን ለቅቄ ልብሴን እንኳ ሳልይዝ እሱ ኪስ ውስጥ ያገኘውትን በግምት 3000 ብር ይዤ ወጥቼ መሮጥ ጀመርኩ ... ምንም እንኳ እኩለ ለሊት ቢሆንም ሰው ግን ይጓዝ ነበር ለዚም አንድ ኮንትራት ታክሲ ፈልጌ እነአቡቸር ጋር ሄድኩ ...
ስደርስ ተሰብስበው አንዱ ባንዱ ላይ ካርቶናቸውን ለብሰው ተኝተዋል ከጎናቸው ሄጄ ቁጭ አልኩና ስለተፈጠረው ነገር ማሰብ ጀመርኩ ሰውየውን ያረኩት ነገር ምንም አላረካኝም ... በንዴት በገደልኩት ኖሮ አልኩ ሳይታወቀኝ ጮክ ብዬ ኖሮ አቡቼ ነቃ እንዴ ሚስ ልእልና ብሎ ጥምጥም አለብኝ እኔም በፍቅር ጥምጥም አልኩበት እንባዬ መጣ "ምን ሆነሽ ነው በዚ ለሊት?" አለኝ ለአቡቼ ከሰው ተጣልቼ እንደሆነ ነገርኩት እሱም ሄጄ ካልገደልኩት አለኝ ... እሱን አረጋግቼ ተቀመጥን...
እነአቡቼ ጋር ተቀምጬ ማሰብ ጀመርኩ ከዛም ቶሎ በያስኩት ብር ፓስፖርት አውጥቼ አረብ ሀገርም ቢሆን መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ ...መታወቅያ ከማውጣት ጀምሮ ብዙ ፈተና ቢገጥመኝም በመጨረሻ ግን ተሳክቶልኝ ቤሩት (ሊባኖን) ለመምጣት ቪዛ መጠበቅ ጀመርኩ ...
ታድያ አንድ ቀን እነአቡቸር ያቺን ላኪት ቤታቸውን ለማደስ ኮተት ሲያወጡ አንድ የኪስ ቦርሳ እጄ ላይ ገባ ተቀምጬ ስለነበር አቡቸሬ ዋሌትህ ውስጥ ስንት አለ እያልኩ ከፈትኩት እሱም ፈገግ ብሎ " አቡቸር ሲጀመር ብሩን ከባንክ ውጪ መች ያስቀምጥና " አለኝ ግን እኔ ስንቀዠቀዥ የከፈትኩት ቦርሳ ውስጥ የአባዬን ፎቶ በማግትቴ በጣም ደንግጬ ከተቀመጥኩትበ በመነሳት የማነው አልኩ ... እነሱም አንድ ቀን ሊደፍረኝ ሲል ያስጣሉኝ ሰው ልብስ ውስጥ የተገኘ እንደሆነ ነገሩኝ ... ገልብጬ አየሁት ..."አባዬ እወድሃለው" ይላል ኦ አምላኬ ያ ሊደፍረኝ የነበረ ሰው እናቴን ቤት አሽጦ የተካፈላት ወንድሜ ነበር !! .... ግን ምንም አድራሻ የለውም ቢኖረውም ግን ላገኘው አልፈልግም!...
ህይወት አድካሚ ናት ከዚ ሁሉ ውጣ ውረድ ቡሃላ ከነበረኝ ላይ እነአቡቸር ጨምረውልኝ ቪዛው መጣልኝና ከፍዬ ከሀገር ወጥቼ አረብ ሀገር ገባሁ አሁን እዚ ከመጣው 8 ወር ሆኖኛል ለነ አቡቸር ገንዘብ ልኬላቸው ከጎዳና እንዲነሱ ለማረግ ሀ ብያለው ያንዱ ታሪክ ለሌላው አስተማሪ ትረካ ነውና ታሪኬን አካፈልኳቹ !!

✧══════•❁አበቃው❁•══════✧
አስተማሪ እንዲሁም አሳዛኝ የመከራን ጥግ የሚያሳየን ታሪክ ነው የሆነ ነገር እንደሚያስተምራችው ተስፋ አደርጋለው ምን ያህል ሰው እንዳነበበው ማወቅ ፈልጋለው
ብዙ ግዜ እየጠፋው እንደሆነ አውቃላው የገባሁላችሁን ቃልም እያከበርኩ እንዳልሆነ አውቃለው ግን ምንም ማድረግ አልችልም ማለት እምችላው ይቅርታ ብቻ ነው! ይቅርታ ስለሁሉም ነገር። ሁሉም ነገር ከአቅም በላይ ሆኖ ለራሴ እምለው ግዜ እንኳን አጣው! ስለዚም ለተወሰነ ግዜ የጀመርኩላችው ታሪክ ይቋረጣል ፋታ ሳገኝ መፃፌን እቀጥላለው ለተወሰነ ግዜ ታገሱኝ። እስከዛው ሌሎች ታሪኮችን አድሚኖቹ ያቀርቡላቹሃል እናንተም አሪፍ የምትሉት የሚያስተምር ፅሁፍ ካላችው 👉 @Juliiian አሳዩት በጣም ተሰጥኦ ያላችው ጎበዝ ልጆች እንዳላችው አውቃለው አሪፍ ፅሁፎችን ለሚያዘጋጅ አድሚን እንሰጣለን።
ሰላም ውዶችየ😍
እንዴት ናችሁ?

ስለተፈጠረው የመቆራረጥ ችግር ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏
አሁንም የበዛው ትዕግስታችሁ አይለየኝ እያልሁ በቅርቡ አዳዲስ ሀሳቦችን ይዤ የምመለስ ይሆናል።
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel

For Photography lovers join us
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel

For Photography lovers join us
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa University 🏢

Order now 📸 @Juliiian
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel

For Photography lovers join us
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa University 🏢

Order now 📸 @Juliiian
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel

For Photography lovers join us
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa University 🏢

Order now 📸 @Juliiian
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel

For Photography lovers join us
👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa 🏢

Order now 📸 @Juliiian
https://www.tg-me.com/Julian_photography

New Photography channel
 
For Photography lovers  join us
           👇👇👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/Julian_photography

Hawassa University 🏢

Order now 📸 @Juliiian
2024/06/17 03:39:35
Back to Top
HTML Embed Code: