Telegram Web Link
ዲፓርትመንት ላልመረጣችሁ 2ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ

@DBU11
@DBU111
ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ገቢዎች ሚንስቴር ።

በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ መንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በሁሉም ቅርንጫፎች እየሰጠ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዮች ምዝገባ እና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ፋና፤ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራትን በተመለከተ  ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ክፍያ የመክፈል በሕግ የተቀመጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ይህንን የወጪ መጋራት ክፍያን ለመሰብሰብ እንዲያመች በአዋጁ መሠረት ለገቢዎች ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት፤ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች ተግባራዊ  እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋማት ወይም ቀጣሪዎችና ባለድርሻ አካላት የወጪ መጋራትን ከመሰብሰብ አንፃር የተሰራው ሥራ ክፍተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ያለውን አሰራር ለማሻሻል ያለመ መሆኑን  ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያቸውን በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በቀላሉ መፈፈም እንዲችሉ ለማድረግም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ፤ በሁሉም የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች በመገኘት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ተብሏል ።

አሐዱ ሬዲዮ

@DBU11
@DBU11
👍6🤬1
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ ስምምነት ፈራረመ

በመስከረም 8/2018 ዓ.ም፣ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት በተሳታፊ አካላት መካከል ተፈራረመ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ በመነሻ ንግግሩ የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተ መሆኑን አስታውቆ አሁን ላለው ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ መፍትሄ ሰጭ መሆኑን ገልፀዋል።

የተማሪዎች ከቤተሰብ ርቀት የሚያስከትለውን የመነጠል ስሜት ለመቀነስ፣ በአካባቢው ባህልና ወግ ስምምነት በማድረግ ተማሪዎች እንደ ሁለተኛ ቤታቸው ደብረብርሃንን እንዲያውቁ የሚያበረታታ እና የተማሪ ህይወትን የሚያስተካክል አጋጣሚ ነው ተብሏል።

በፕሮግራሙ የሃይማኖት አባቶች፣ የከተማው ም/ል ከንቲባ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ዳይሬክተሮችና ዲኖች ተሳትፎ ያደረጉበት ነው።

በመጨረሻ፣ የፕሮግራሙ መዝገበ ፊርማ በፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ እና የከተማው ም/ል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ተካሂዷ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

@DBU11
@DBU111
🤔4👌3
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ መሐል ሜዳ ካምፓስ የ2018 ዓመት መደበኛ ተማሪዎች ለመቀበል ሙሉ ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ::

የደብረ ብርሐን ዩንቨርስቲ የመሐል ሜዳ ካምፓስ የ 2018 ዓመት የመደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቱን መጨረሱን የካምፓሱ ማኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ሰለሞን ገሰሰ ለዲጂታል ሚዲያችን ገልፀዋል::

በካምፓሱ ቅጥር ግቢ ተገኝተን እንደዘገብነው በ 2017 የትምህርት ዘመን : የሪሜዲያል ተማሪዎችን በመቀበል የትምህርት ዘመኑን የጀመረው ካምፓሱ ፣ ከመጀመሪያው የተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደት በርካታ ልምዶችን መውሰዱን ማኔጂንግ ዳሬክተሩ ገልፀዋል::

በ 2018 የተማሪዎች ቅበላን ለማድረግ በየትምህርት ዘርፋ እና በሌሎች የትብብር ኮሚቴዎችን በማቋቋም ሰፊ ስራ መሰራቱን አሳውቀው ፤ በተለይም ቅጥር ግቢውን ለተማሪዎች ሳቢ እና ማራኪ ለማድረግ በክረምቱ በርካታ ሀገር በቀል ችግኞችን በመትከልና በግቢው ባሉ የዶርሚታሪ እና የመማሪያ ክፍሎችን በማስተካከል ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል::

በተለይም የግቢው የውበት ስራ እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ ለግቢው የውስጥ ገቢ የሚያስገኙ ለግንባታ የማይውሉ መሬቶችን ለአካባቢው ማህበረሰብ በኪራይ ጨረታ በመስጠት የካምፓሱ የማህበራዊ ዘርፍ ግዴታዎችን ለመወጣት ጥረት ተደርጓል ብለዋል::

ማኔጂንግ ዳሬክተሩም በገለፃቸው እንደተናገሩት በ 2018 የአዲስና የነባር ተማሪዎችን ለመቀበል የነበሩትን ችግሮች ከዋናው የደብረ ብርሐን ዩኒቨርስቲ ግቢ አስተዳደር አካላት ጋር በመነጋገር የቤተ - መፅሐፍት ፣ የመመገቢያ ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ፣ የመፀዳጃ ቤትና ሌሎች ተያያዥ የተማሪዎች መሰረታዊ አስፈላጊ ሁኔታዎችን ፈትተን ተማሪዎቻችንን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል::

@DBU11
@DBU111
🤔3😢3🤬1
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል የአለም የህሙማን ደህንነት ቀን ተከበረ

-“የታካሚዎች ደህንነት ከውልደት” በሚል መሪ ቃል መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም የአለም የህሙማን ደህንነት ቀን በዩኒቨርሲቲው አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ሀኪም ግዛው ሆስፒታል ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ።

- በበዓሉ ላይ የከተማው ም/ከንቲባ እና የሆስፒታሉ ቦርድ አባል አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በንግግራቸው የታካሚዎች ደህንነት ሊያደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን (የመድሃኒት ስህተት፣ ኢንፌክሽን፣ መውደቅ፣ የተሳሳተ መለያ መጠቀም፣ ያልተጠበቀ ደም መውሰድ ወዘተ) በማስወገድ የታካሚዎችን ደህንነት ማረጋገጥ እንዳለበት ጠቅሰዋል።

- ዶ/ር ዘመድ ገለታ ይህ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የጉዳት አሰራሮችን ማስወገድ ላይ የተሰማራ መሆኑን ገልጸዋል።

- ዶ/ር ቴዎድሮስ ክፍለዮሐንስ ደግሞ የታካሚ ደህንነት ሁሌም ቅድሚያ መሆኑን እና ታካሚዎች በትክክለኛ ሰዓት በትክክለኛ መመሪያ መታከም አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

- በመድረኩ ላይ የተሰጠ ምስክርነት ውስጥ አቶ ሳሙኤል ጌታቸው ከ2 ዓመት በፊት በ1 ኪ.ግ ክብደት የተወለደችው ልጃቸው በሆስፒታሉ የተሻለ ክብካቤ ተቀብላ አሁን በጤና መሆኗን አስረው ምስጋና አቀረቡ።

- በመጨረሻ የታካሚ ደህንነት መሠረት፣ የIPC ተግባር በአዲስ የተወለዱ ሕፃናት ሞት ላይ ያለው ተፅዕኖ እና የአዲስ የተወለዱ ህፃናት እንክብካቤ ላይ የተዘጋጀ ውይይት ተካሂዷል።

- ከበዓሉ በተጨማሪ ሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ ትግበራዎችንና የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን እየተካሄዱ መሆናቸውን አሳውቋል።

@DBU11
@DBU111
🤔1
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
@DBU11
@DBU11
2025/10/22 15:13:46
Back to Top
HTML Embed Code: