Telegram Web Link
ማስታወቂያ
notice

ተማሪ ብርቱካን ኤርሚያስ ት/ት ክፍል IS
ተማሪ ሀና ተስፋዬ ት/ት ክፍል  Agro Economics
የሆናችሁ ተማሪዎች የ Non-Cafe መረጃችሁ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሄዳችሁ
እንድታስተካክሉ እናሳውቃለን።

@DBU11
@DBU111
👍2
እንኳን ደህና መጣችሁ 👏👏 የ2018 አዲስ ተማሪዎች

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ርቀት ከክልሉ መዲና ባህርዳር 690 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች  ፡፡

ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሀን መንገድ  ከ2:00ሰአት እስከ 2:30 ሰአት ጉዞ ነው ፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን ለመጓዝ በዋነኝነት የላምበረት መነሀሪያን እንደ አማራጭ የቃሊቲ መነሃሪያን መጠቀም ትችላላችሁ ፡፡

ከአዲስ አበባ አስከ ደብረ ብርሀን ሲጓዙ  እነዚህ ከተሞች ይቃኛሉ ፡፡ ለገጣፎ፡ ለገዳዲ፡ ሰንዳፋ ፡ በኬ፡አሌልቱ ፡ፍቼ ገነት ፡ ሀሙስ ገበያ፡ ሸኖ፡ ሰምቦ ፡ጨኪ ፡ ጫጫን  በመጨረሻም ደብረ ብርሀን ፡፡

እንኳን ደህና መጣችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
የደብረ ብርሀን ከተማ በ1446 ዓ.ም በአፄ ዘረያቆብ ተመሰረተች ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ዋና መናገሻም ሆና አገልግላለች ፡፡ ከተማዋ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚ እየተናቃቃች ያለች የኢንደስትሪ ከተማ ናት ፡፡ 

ከተማዋ ከባህር ጠለል በላይ 2750 እስከ 2850 ድረስ ከፍታ ያለው ነው በመሆኑም የአየር ሁኔታው ብርዳማ እንዲሆን ያደርገዋል ፡፡ የከተማው አመታዊ የሙቀት መጠን 10°ዲግሪ ሴልሲየስ ነው ፡፡

በ2000ዓ.ም  ግንቦት ወር የሙቀት መጠኑ ከዜሮ በታች 6.6 ማለትም -6.6 ደርሶ ነበር በወቅቱ የነበረው ከፍተኛ ብርዳማ አየር ከተማዋ በታወሰች ቁጥር ብርዳማዋ ከተማ እየተባለች እንድትነሳ አድርጓል ፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሙቀት መጡኑ ቀዝቃዛ ቢሆንም እንደቀድሞ ብርዳማ የሚባል አይደለም ፡፡( ቢሆንም ወፈር ያለ ልብስ ብትይዙ ይመረጣል)

ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ
👇👇👇👇👇👇👇

የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተው 1999 ዓ.ም ነው ፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው አገልግሎት ሲጀምር በ725 ተማሪወች  ነበር ።


ዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ  የሚገኘው ጠባሴ የሚባል አከባቢ ሲሆን ወደ ከተማ ለመሄድ  ታክሲ መጠቀም የግድ ነው ።


የህክምና ትምህርት  ግቢ(ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ)  በከተማው መሀል ላይ 04 ቀበሌ (ማዕከል) ይገኛል ፡፡


መንዝ መሀል ሜዳ ካምፖስ አዱስ የተገነባው ግቢ ሲሆን : ከደብረ ብርሀን በ150Km ርቀት ላይ ይገኛል ።

ለአዲስ ተማሪወች
👇👇👇👇👇👇

ለአዲስ ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትመጡ
ከመግቢያው እስከ ዶርም የሚያደረሱ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎች አሉ ፡፡ በግቢ ውስጥ 2ካፌ ፡  3 የተማሪወች ላውንጅ  5 ላይብረሪዎች ፡2 የተማሪ ሱቆች እንዲሁም 1 ጁስ ቤት  ይገኛሉ ፡፡

ለአዲስ ተማሪወች  መማር አማራጭ የሌለው ነገር ነው ፡፡ 👉ክላስ መከታተል ፡👉ማንበብ 👉ውጤት መስራት  እነዚህ የሁል ጊዜ ተግባሮች መሆናቸውን አትርሱ ፡፡

❗️❗️የዘመኑ አፃያፊ በሽታ ዘረኝነት፡ ጎጠኝነት ፡ መንደርተኛነት በዩኒቨርሲቲው ቦታ ስለሌላቸው እዛው ተፈውሳችሁ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን ፡❗️፡ ዩኒቨርሲቲው ከሁሉም የሀገሪቷ ክፍል የሚመጡ የኢትዮጵያ ልጆች መነሀሪያ ስለሆነ በመከባበር ፡ በመተሳሰብ መኖር ግዴታ ነው፡፡

ጥሩ ግዜ እንደምታሳልፉ ተስፋ እናደርጋለን ፡፡

ነፃ ሀሳብ እና አስተያየት በDbu Daily news discussion ግሩፕ  ላይ መስጠት ይቻላል ፡፡


@ wende abebe መ'ኪያ

@DBU11
@DBU111
👏40😢2👍1🤔1👌1
ምርቃትን በተመለከተ ላቀረባችሁልን ጥያቄ እስካሁን ባለን መረጃ በዚህኛው ዓመት ምርቃት የሚካሔደው ሁለት ጊዜ ሲሆን
• ጥር ወር ላይ በቀን 23 የጤና ሳይንስ ተማሪዎች እና ኢንጅነሪንግ ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን
• የመደበኛ የምርቃት ፕሮግራም ሰኔ 23 ላይ እንደሚሆን ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

@DBU11
@DBU111
82,838 ተማሪዎች ለሪሚዲያል እንዲያልፉ ተደርጓል

ትምህርት ሚኒስቴር ብሔራዊ ፈተና ያላለፉ ከ82 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ማካካሻ (ሪሚዲያል) ትምህርት እንዲወስዱ ፈቀደ::

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ ለሪፖርተር እንዳሉት፣ በ2018 የትምህርት ዘመን 82,838 ተፈታኞች የማካካሻ ትምህርት ለመውሰድ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገቡ ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒቴር በ2018 የትምህርት ዘመን በሪሜዲያል መርሐ ግብር ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባውን ነጥብ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ሚኒስቴሩ በግልም ሆነ በመንግሥት ተቋማት የሪሜዲያል ፕሮግራም መከታተል የሚችሉት፣ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 33 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች መሆናቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አጋርቷል።
👍3😢1
የደብረብርሐን ዩንቨርስቲ የቦርድ አባላት።

ፎቶ :- ከዩንቨርስቲው ቦርድ አባል አንዱ የሆነው ተወዳጁ አርቲስት እና ጠበቃ አበበ ባልቻ።

@dbu11
@dbu111
👍21🤔13👏2😢1
🤬3
#AD

ኤርፖድ፣ሄድሴት እና ኤርፎን እየተበላሸ ከተቸገሩ ለእኛ ይደውሉልን...

አስተማማኝነት እና ዋስትና ያለው የጥገና አገልግሎትን በግቢ ውስጥም ከግቢ ውጭም ያሉበት ድረስ ተገኝተን በተመጣጣኝ ዋጋ ልናገለግሎ ሁሌም ዝግጁ ነን።

እርሶ ብቻ ስልኮን አውጥተው በ 0936370157 ወይም 0714935861 ላይ ይደውሉ።

EB የኤርፖድ፣የኤርፎን እና የሄድሴት ጥገና አገልግሎት
https://www.tg-me.com/ne_jamais_abandonner

@DBU11
@DBU111
👍4👏1
በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " -
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።

ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡

" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።

" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርጣሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

@DBU11
@DBU111
👏27
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው  መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዩኒቨርሲቲው የሚደረግለት የገንዘብ ድጎማ በቂና ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ በሚፈለገው ልክ  ልክ አለመሆኑን  ተገለፀ ።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከሰብል ልማት 1 ሺህ 400 ኩንታል ምርት ለማምረት እየሰራ ስለመሆኑ የኢንተርፕራይዙ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው መልካሙ ተናግረዋል ።

በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ ኢንተርፕራይዙ የተለየ ትርፍ አትርፎ ለራሱ የሚጠቀም አድርጎ የማሰብ አዝማሚያዎች እንዳሉ የጠቆሙት የኢንተርፕራይዙ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው መልካሙ  የመገዘዝ ንግድና ማማከር ስራዎች ከ2025 በኋላ ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን በሚሰራው ስራ 10 ፐርሰንት የዩኒቨርሲቲውን ገቢ ለመደገፍ የተቋቋመና የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች ከልማት ድርጅቱ በቀጥታም ይሁን በሌላ እየተጠቀሙ መሆኑን ካለመረዳት የመነጨ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

መረጃውን ከዩኒቨርሲቲው ገፅ ተመልክተናል ።

@DBU11
@DBU111
🤔2
በኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች የጥራት ጉድለት እንደታየባቸዉ ጥናቶች ማመልከታቸውንና
የዩንቨርስቲዎች የህግ ትምህርት አሰጣጥ የትምህርት ክፍሉን እስከማዘጋት ሊያደርስ የሚችል የጥራት እንከን እንደታየበት ተገለፀ።

የፌደራል ህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ህብረት ጋር በጋራ በመሆን በሀገሪቱ የሚታዩ የህግ ትምህርት ቤቶች ተግዳሮቶች ዙሪያ ያተኮረ ጥናት አስጠንቷል።

ጥናቱን ካጠኑት ባለሙያዎች ዉስጥ የሆኑት አቶ ተገኘ ዘርጋዉ፤ በሀገሪቱ ያለዉ የህግ ትምህርት አደጋ ላይ መዉደቁን ጥናቱ ማሳየቱን ገልጸዋል።

የተወሰኑ ለዉጦች ቢኖሩም የህግ ትምህርት ቤቶቹ የጥራት ጉድለት የሚታይባቸው እንደሆኑም ተናግረዋል።

አቶ ተገኘ ዘርጋዉ ፤ የባለሙያዎች በህግ ትምህርት ቤቶች የመስራት ተነሳሽነት ማጣት እና የመምህራን ጥራት እንደምክንያት የሚጠቀሱ መሆናቸዉን አንስተዋል።

ነገር ግን ከነዚህ ምክንያቶች በተለየ አብዛኞቹ ዩንቨርስቲ ህግን እንደ አንድ የልህቀት ማዕከል ወይም (focus area ) አድረገው እንደማይመለከቱት ገልፀዋል።

ከዚህ አንፃር ከሁለት ዩንቨርሲቲዎች ዉጪ በሀገሪቱ የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች የህግ ትምህርትን በልህቀት ማዕከል ወይም( focus of area ) አድርገዉ  እንዳልመረጡ ነዉ አቶ ተገኘ ያስረዱት።

በሀገሪቱ የተሻለ የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ለህግ ትምህርቱ ጥራት ማሻሻል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጿል።

የመረጃ ምንጫችን Ethio Fm ነው።

@dbu1
@dbu11
😢2
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ 3ኛ አመት የቋንቋ ተማሪ እና አምባሻው ቲቪ በተሰኘ የ ቲክቶክ ፕላትፎርም ላይ አዝናኝ ይዘቶችን በማቅረብ የሚታወቀው ነገሰ ይቻለዋል ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ህክምና እንደሚያስፈልገው መገለፁን ተከትሎ እና ተማሪ ነገሰ የህክምና ወጭውን መሸፈን ባለመቻሉ ዛሬ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር፣የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ፓሊስ ጽህፈት ቤት፣የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት ክበብ እና የዩኒቨርሲቲያችን ልበ ቀና ተማሪዎች በጋራ በመሆን ለተማሪ ነገሰ ይቻለዋል የህክምና ወጭ ገንዘብ አሰባስበዋል።

‎ከዩኒቨርሲቲው  ተማሪዎች እና ሰራተኞች መግቢያና መውጫ በር ላይ እንደዚሁም ከ እረፍት ቀናት ተማሪዎች መማሪያ ክፍል በመዞር መሰብሰብ ተችሏል።በዋነኛነት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ወደ ደብረ ብርሀን ከተማ በመሄድ ከለጋሱ የደብረ ብርሀን ከተማ ማህበረሰብ የድጋፍ ገንዘብ ተሰብስቧል።

‎በአጠቃላይ በዛሬው እለት 18,269.  ብር የተሰበሰበ ሲሆን የህክምና ምርመራ ውጤቱ እየታየ ተጨማራ ገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ ይቀጥላል።

‎በዛሬው እለት የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም የደብረ ብርሀን ህዝብ ላሳያችሁን መልካም ትብብር በወንድማችን ስም እናመሰግናለን ፈጣሪ ልፋታችሁን ቆጥሮ ለወንድማችን ምህረትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።በበጎ አድራጎት ስራው ላይ ለተሳተፋችሁ ተማሪዎች በገንዘብ ማሰባሰብ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፉ ‌‎የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፤
‎የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ፓሊስ ፅህፈት ቤት እና
‎የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ በጎ አድራጎት ማህበር ምስጋናቸውን አድርሰዋል።

‎በባንክ አካውንት መላክ የምትፈልጉ ከታች ባለው የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር መላክ የምትችሉ መሆኑን ለdaily news መልዕክታቸውን ልከዋል።

‎account 1000719984448
‎ነገሰ ይቻለዋል ማሞ



@dbu11
@dbu111
👍23😢4
2025/10/21 13:14:35
Back to Top
HTML Embed Code: