Telegram Web Link
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ነባር መደበኛ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ይገኛል፡፡

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ዘመኑ ነባር መደበኛ ተማሪዎችን መስከረም 08- 09/ 2018 ዓ.ም ለመቀበል ዝግጅት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በወጣዉ መርሐግብር መሠረት ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ ነው፡፡


ዩኒቨርሲቲዉም ለተማሪዎቹ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያለ የትምህርት ዘመኑ የሰላም እና የስኬት እንዲሆንላቸዉ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!

@DBU11
@DBU11
👏10
ቅሬታ

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የእረፍት ቀናት ተማሪዎች

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የእረፍት ቀናት ተማሪዎች የዚህን ዓመት  የሴሚስተር ክፍያ ምክንያቱን ባልተገለፀልን እና የተማሪዎቹን የመክፈል አቅም ያላገናዘበ ጭማሬ ተደርጎብናል።

ጭማሬው ግልጽነት የጎደለውና ፍትሃዊ ያልሆነ ጭማሬ ስለሆነ  እኛ ተማሪዎችም የመክፈሉ አቅም ስለሌለን  የሚመለከተው አካል ይሄን ነገር ተመልክቶ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን?

@DBU11
@DBU111
👍46🤬2
መልካም የትምህርት ዘመን

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከትላንት 8/01/2018 ጀምሮ ነባር ተማሪዎቹን እየተቀበለ ይገኛል።

በጉዞ ላይ የምትገኙ መልካም መንገድ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

@DBU11
@DBU111
👍5👏3
ዲፓርትመንት ላልመረጣችሁ 2ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ

@DBU11
@DBU111
ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ገቢዎች ሚንስቴር ።

በ2018 የትምህርት ዘመን ወደ መንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) በሁሉም ቅርንጫፎች እየሰጠ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የታክስ ከፋዮች ምዝገባ እና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ፋና፤ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራትን በተመለከተ  ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ክፍያ የመክፈል በሕግ የተቀመጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ይህንን የወጪ መጋራት ክፍያን ለመሰብሰብ እንዲያመች በአዋጁ መሠረት ለገቢዎች ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት፤ በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች ተግባራዊ  እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን የፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋማት ወይም ቀጣሪዎችና ባለድርሻ አካላት የወጪ መጋራትን ከመሰብሰብ አንፃር የተሰራው ሥራ ክፍተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ያለውን አሰራር ለማሻሻል ያለመ መሆኑን  ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች የወጪ መጋራት ክፍያቸውን በግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በቀላሉ መፈፈም እንዲችሉ ለማድረግም ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ፤ በሁሉም የገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች በመገኘት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ባሉባቸው ዩኒቨርስቲዎች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲያገኙ የሚደረግበትን አሰራር ለማመቻቸት እየተሰራ ነው ተብሏል ።

አሐዱ ሬዲዮ

@DBU11
@DBU11
👍6🤬1
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ ስምምነት ፈራረመ

በመስከረም 8/2018 ዓ.ም፣ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት በተሳታፊ አካላት መካከል ተፈራረመ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ በመነሻ ንግግሩ የቃልኪዳን ቤተሰብ ምስረታ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተ መሆኑን አስታውቆ አሁን ላለው ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ መፍትሄ ሰጭ መሆኑን ገልፀዋል።

የተማሪዎች ከቤተሰብ ርቀት የሚያስከትለውን የመነጠል ስሜት ለመቀነስ፣ በአካባቢው ባህልና ወግ ስምምነት በማድረግ ተማሪዎች እንደ ሁለተኛ ቤታቸው ደብረብርሃንን እንዲያውቁ የሚያበረታታ እና የተማሪ ህይወትን የሚያስተካክል አጋጣሚ ነው ተብሏል።

በፕሮግራሙ የሃይማኖት አባቶች፣ የከተማው ም/ል ከንቲባ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ዳይሬክተሮችና ዲኖች ተሳትፎ ያደረጉበት ነው።

በመጨረሻ፣ የፕሮግራሙ መዝገበ ፊርማ በፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማረ መለሰ እና የከተማው ም/ል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ተካሂዷ ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

@DBU11
@DBU111
🤔4👌3
2025/10/25 03:55:00
Back to Top
HTML Embed Code: