በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ ይቆማል " -
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የተማሪዎች ምደባ እንደሚያቆም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ አስታወቁ።
ይህ ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስቴር ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቁልፍ ተግባራት የፊርማ ስነስርዓት ባከናወነበት ወቅት ነው።
በዚሁ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ጠንካራ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንደገለፁት፤ በሚቀጥሉት ዓመታት የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ምደባ እንደሚያቆምና የማለፊያ ነጥብ የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች በሚፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎችና የትምህርት መስኮች እንዲያመለክቱ ይደረጋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደከዚህ ቀደሙ በትምህርት ሚኒስቴር ምደባ ሳይሆን በተማሪዎቹ ምርጫ ይሆናል " ብለዋል።
" ተማሪዎች የሚማሩበትን ዩኒቨርሲቲ ሲመርጡም ምክንያታዊ በመሆን በዬትኛው ዩኒቨርሲቲ የተሻለ የትምህርት መስክ፣ እውቀትና የስራ እድል ላገኝ እችላለሁ በማለት ይመርጣሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
@DBU11
@DBU111

👏27
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዩኒቨርሲቲው የሚደረግለት የገንዘብ ድጎማ በቂና ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ በሚፈለገው ልክ ልክ አለመሆኑን ተገለፀ ።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከሰብል ልማት 1 ሺህ 400 ኩንታል ምርት ለማምረት እየሰራ ስለመሆኑ የኢንተርፕራይዙ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው መልካሙ ተናግረዋል ።
በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ ኢንተርፕራይዙ የተለየ ትርፍ አትርፎ ለራሱ የሚጠቀም አድርጎ የማሰብ አዝማሚያዎች እንዳሉ የጠቆሙት የኢንተርፕራይዙ ም/ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አለምነው መልካሙ የመገዘዝ ንግድና ማማከር ስራዎች ከ2025 በኋላ ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን በሚሰራው ስራ 10 ፐርሰንት የዩኒቨርሲቲውን ገቢ ለመደገፍ የተቋቋመና የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራተኞች ከልማት ድርጅቱ በቀጥታም ይሁን በሌላ እየተጠቀሙ መሆኑን ካለመረዳት የመነጨ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
መረጃውን ከዩኒቨርሲቲው ገፅ ተመልክተናል ።

🤔2
በኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች የጥራት ጉድለት እንደታየባቸዉ ጥናቶች ማመልከታቸውንና
የዩንቨርስቲዎች የህግ ትምህርት አሰጣጥ የትምህርት ክፍሉን እስከማዘጋት ሊያደርስ የሚችል የጥራት እንከን እንደታየበት ተገለፀ።
የፌደራል ህግ እና ፍትህ ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ህብረት ጋር በጋራ በመሆን በሀገሪቱ የሚታዩ የህግ ትምህርት ቤቶች ተግዳሮቶች ዙሪያ ያተኮረ ጥናት አስጠንቷል።
ጥናቱን ካጠኑት ባለሙያዎች ዉስጥ የሆኑት አቶ ተገኘ ዘርጋዉ፤ በሀገሪቱ ያለዉ የህግ ትምህርት አደጋ ላይ መዉደቁን ጥናቱ ማሳየቱን ገልጸዋል።
የተወሰኑ ለዉጦች ቢኖሩም የህግ ትምህርት ቤቶቹ የጥራት ጉድለት የሚታይባቸው እንደሆኑም ተናግረዋል።
አቶ ተገኘ ዘርጋዉ ፤ የባለሙያዎች በህግ ትምህርት ቤቶች የመስራት ተነሳሽነት ማጣት እና የመምህራን ጥራት እንደምክንያት የሚጠቀሱ መሆናቸዉን አንስተዋል።
ነገር ግን ከነዚህ ምክንያቶች በተለየ አብዛኞቹ ዩንቨርስቲ ህግን እንደ አንድ የልህቀት ማዕከል ወይም (focus area ) አድረገው እንደማይመለከቱት ገልፀዋል።
ከዚህ አንፃር ከሁለት ዩንቨርሲቲዎች ዉጪ በሀገሪቱ የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች የህግ ትምህርትን በልህቀት ማዕከል ወይም( focus of area ) አድርገዉ እንዳልመረጡ ነዉ አቶ ተገኘ ያስረዱት።
በሀገሪቱ የተሻለ የፍትህ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ለህግ ትምህርቱ ጥራት ማሻሻል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጿል።
የመረጃ ምንጫችን Ethio Fm ነው።
@dbu1
@dbu11

😢2
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ 3ኛ አመት የቋንቋ ተማሪ እና አምባሻው ቲቪ በተሰኘ የ ቲክቶክ ፕላትፎርም ላይ አዝናኝ ይዘቶችን በማቅረብ የሚታወቀው ነገሰ ይቻለዋል ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ህክምና እንደሚያስፈልገው መገለፁን ተከትሎ እና ተማሪ ነገሰ የህክምና ወጭውን መሸፈን ባለመቻሉ ዛሬ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር፣የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ፓሊስ ጽህፈት ቤት፣የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የበጎ አድራጎት ክበብ እና የዩኒቨርሲቲያችን ልበ ቀና ተማሪዎች በጋራ በመሆን ለተማሪ ነገሰ ይቻለዋል የህክምና ወጭ ገንዘብ አሰባስበዋል።
ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች እና ሰራተኞች መግቢያና መውጫ በር ላይ እንደዚሁም ከ እረፍት ቀናት ተማሪዎች መማሪያ ክፍል በመዞር መሰብሰብ ተችሏል።በዋነኛነት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ወደ ደብረ ብርሀን ከተማ በመሄድ ከለጋሱ የደብረ ብርሀን ከተማ ማህበረሰብ የድጋፍ ገንዘብ ተሰብስቧል።
በአጠቃላይ በዛሬው እለት 18,269. ብር የተሰበሰበ ሲሆን የህክምና ምርመራ ውጤቱ እየታየ ተጨማራ ገንዘብ የማሰባሰብ እንቅስቃሴው ተጠናክሮ ይቀጥላል።
በዛሬው እለት የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም የደብረ ብርሀን ህዝብ ላሳያችሁን መልካም ትብብር በወንድማችን ስም እናመሰግናለን ፈጣሪ ልፋታችሁን ቆጥሮ ለወንድማችን ምህረትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።በበጎ አድራጎት ስራው ላይ ለተሳተፋችሁ ተማሪዎች በገንዘብ ማሰባሰብ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፉ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፤
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ፓሊስ ፅህፈት ቤት እና
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ በጎ አድራጎት ማህበር ምስጋናቸውን አድርሰዋል።
በባንክ አካውንት መላክ የምትፈልጉ ከታች ባለው የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር መላክ የምትችሉ መሆኑን ለdaily news መልዕክታቸውን ልከዋል።
account 1000719984448
ነገሰ ይቻለዋል ማሞ
@dbu11
@dbu111

👍23😢4
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ3 ቢሊዮን ብር የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ.ር)እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው 230 መምህርንን ተጠቃሚ የሚያደርግ አፓርታማ በ3 ቢሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ግንባታው የመዝናኛና የገበያ ማዕከላትን ጨምሮ ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የግንባታውን ሂደት በማፋጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
የደብረ ብርሃ ከንቲባ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በትልቅ ለውጥ ውስጥ ያለና ለከተማው ጥሩ ዕድል ያመጣ ነው ብለዋል፡፡
የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ የተጀመረው ግንባታ ትልቅ መሆኑን ገልጸው መምህራን ወደ ውጪ ሳያስቡ ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩና ትውልድ የመቅረጽ ኃላፊነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡