Telegram Web Link
ታላቅ የኪነጥበብ ድግስ

ሆሄ ተስፋ ኪነጥበብ ቡድን በበዓልና በፈተና ምክንያት ሲያሸጋግር የቆየውን የኪነጥበብ ዝግጅቹን ለታዳሚዎች ለማቅረብ ዝግጅቴን ጨርሻለው ይላል።

በዝግጅቱ እንደተለመደው ፦
ግጥም
ሙዚቃ     
መነባነብ

ሙዚቃዊ ግጥሞች እንዲሁም
የመፅሃፍ ጥቆማ ና የተለያዩ አዝናኝ ፕሮግራሞችን አዘገጅቶ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርስቲው PR ተገኙልኝ ብሏል።
                           ሆሄ ተስፋ

@dbudaily
@dbu11
@dbu_entertainment
ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን

ለሴሚስተሩ የመጀመሪያ የሆነውን የኪነጥበብ ፕሮግራም ቅዳሜ 10/9/2016 በደመቀ ሁኔታ አመሻሹን አቅርበዋል።

ግጥም፣ተውኔት፣ሙዚቃ እና የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶችን በወር 2 ጊዜ በቋሚነት የሚቀርብ ሲሆን በዘንድሮ ሴሚስተር በትምህርት ፕሮግራም መጣበብ እና በበዓል መደራረብ ምክኒያት ሊዘገይ ችሏል።

ከወትሮውም አቀራረብ ለየት ባለ መልኩ በኪነጥበቡ የሙዚቃ መሳሪያ ባለሞያዎች የተሰራ አዲስ የመሳሪያ ሙዚቃ(Instrumental Music) በዝግጅቱ ላይ ቀርቧል።

@dbu11
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሆሄ ተስፋ ኪነት
...ቅምሻ ሙዚቃ

ዮናስ ተገኝ
ባዬ አዘዘ
ይስሙ ትርፌ

@DBU11
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን አሳወቀ።

በ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 እስከ 21/2016 መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

የአገልግሎት ክፍያ  500.00 ብር በ ' ቴሌ ብር ' ብቻ የሚፈጸም መሆኑ አስገንዝቧል።

#ለመጀመሪያ_ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማቸው በኩል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አሳውቋል።

@DBU11
#Notice

ለሴት ተማሪዎች
ሐሙስ በቀን 15-09-2016ዓ.ም የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሮክትሬት በብሎክ 07 ከቀኑ 9:00ሰዓት ጀምሮ ሴት ተማሪዎችን ለማቀራረብ የሚያግዝ ውይይት አዘጋጅቷል። በዝግጅቱ አዝናኝና አስተማሪ ፊልሞች እንዲሁም የካርድ ሽልማቶችን አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።


ቦታ፦ ብሎክ 07
ሰዓት፦ ከቀኑ 9:00
የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሮክትሬት


@dbu11
@dbu_entertainment
ሆሄ ተስፋ- አዲስ አበባ

መሰረቱን ደብረብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያደረገው ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን 4ኛ የሆነውን የኪነጥበብ መድረክ እሁድ ግንቦት 18 አዲስ አበባ መገናኛ ዋአች ህንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ጣዕም ባህላዊ የምግብ አዳራሽ ያቀርባል።

መገኘት የሚችሉ ቤተሰቦቹንና የኪነጥበብ አድናቂዎችን በዕለቱ እንዲገኙለት ግብዣውን አስተላልፏል።

ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን
@DBU11
ጂሲ ካፕ

የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ ተጠናቋል።

በመጀመሪያ የጨዋታ ቀን በተደረገው የቅዳሜ ጨዋታ ላይ COTM VS Software Engineering ጨዋታ COTM በ1-0 ውጤት COTM ወደ ቀጣይ ዙር ተሸጋግሯል።

Law VS Electrical Engineering በተደረገው ጨዋታ ደግሞ በ3-0 ውጤት Law ወደ ቀጣይ ዙር ሊያልፍ ችሏል።

በቀጣይ በተደረገው የእሁድ ጨዋታ
Chemical Engineering VS Industrial የነበረ ሲሆን
በ2-2 አቻ ውጤት የተለያዩ ሲሆን በፔናሊቲ ጎል 4-2 በመሆን Industrial Engineering ወደቀጣይ ዙር ተሸጋግሯል።

ከCivil Engineering ጋር ለሚደረገው ጨዋታ ምርጥ ተሸናፊ መለያ ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ከሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ጋር ማክሰኞ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን በ1-1 አቻ ውጤት የተለያዩ ሲሆን ኬሚካል ኢንጅነሪንግ በፔናሊቲ ጎል 3-2 ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ከሲቪል ጋር ለመጫወት ውድድሩን አልፏል።

ዛሬ ረቡዕ በተደረገው ጨዋታ
ኬሚካል ኢንጅነሪንግ ከሲቪል ኢንጅነሪንግ ጋር በ8-1 ጎል ሲቪል ኢንጅነሪንግ ወደቀጣዩ የግማሽ ማጣሪያ ጨዋታ ሊያልፍ ችሏል።
2024/05/23 00:29:34
Back to Top
HTML Embed Code: