Telegram Web Link
✍️#ትዳሮት የትኛው ደረጃ ላይ ነው ያለው?

♥️♥️ውድ የዶክተር አለ ተከታታዮች ዛሬ ይዘን የቀረብነው ፁሁፍ ስለ ትዳር ደረጃዎች ስሆን ደስተኛ ያልሆነን ትዳር ማዳን ይችላሉ? ከትዳር አጋሮ ጋር ደስተኛ ባልሆነ ትዳር ውስጥ እንደተሰሩ ይገነዘባሉ ወይም ከዚያ በኋላ ፍቅር ሊኖር/ላይኖር ይችላል፡፡ አሁን ትዳራችሁን እዴት ማዳን እንደሚችሉ ማወቅ እና ወደ ቀድሞው ሁኔታ መመለስ ከፍለጉ በዚህ ደረጃ ላይ

1️⃣.የጫጉላ ሽርሽር ደረጃ/ Honeymoon stage
🔹 የጫጉላ ሽርሽር ደረጃ እስከ ሁለት አመታት ድረስ ሊቆይ ይችላል፤ በዚህ ጊዜ የፍቅር እና የደስታ ስሜት ከመጠን
በላይ ማሽቆልቆል ይጀምራል፡፡ ውጫዊ ክስተቶች የደስታ ስሜትን ለጊዜው ሊያሳድጉ ወይም ሊያወርዱ ይችላሉ።

🔹 ይህ መላመድ ቲዎሪ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በትዳር ውስጥም ሊተገበር ይችላል። በጫጉላ ሽርሽር ወቅት፣ ሁሉም ነገር ትኩስ፣ አዲስ እና አስደሳች ነው። የአጋርዎን ጉድለቶች ላያውቁ ይችላሉ ወይም ባለዎት ፍቅር ምክንያት ሊታገሷቸው ይችላሉ። ደስታን ለመጠበቅ በትዳር ውስጥ ጥረት ሳያደርጉ ደስታ መጥፋት ይጀምራል።

🔹 ፍቅር ለትዳር አስፈላጊ ተደርጎ ይወሰዳል። በፍቅር ጥንዶች ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የፍቅር ግንኙነቱን ለመቀጠል ፍቅርን ማቆየት ግንኙነቱን ማቆየት ማለት ነው፡፡

2️⃣. የኃይል ትግል ደረጃ/ Power struggle stage
🔹 የጫጉላ ሽርሽር ደረጃ ሲያልቅ፣ የስልጣን ሽኩቻ ደረጃ ይጀምራል።እንደ ባልና ሚስት ሕይወታችሁ በዚህ ደረጃ ከባድ ይሆናል። በጋብቻ ውስጥ ብቸኛነት ስሜት ይሰማዎታል፤ ይህም የእርስዎ ወይም የትዳር አጋሮ ህልሞች/እቅዶች እንደጠበቁት ሳይሆኑ ሲቀሩ ነው፡፡

🔹 የእርሶ ግምት ግንኙነት ምን ማለት እንደሆነ እና ከግንኙነቱ የሚጠብቃችው ነገሮች ማለትም(ሁል ጊዜ ደስታ እና ለዘላለምደስታ ፣ ያለ ምንም ጥረት) በመጨረሻ ከእውነታው የራቁ ሆኑን ይረዳሉ።በዚህ ደረጃ ስሜታዊ ርቀት ሊሰማዎት ይችላል፡፡ የትዳር አጋሮት ካገባችሁት ሰው የተለየ እንደሆነ ሊሰማዎት ይችላል፤ ሆኖም አሁንም ስለ እርስ በራሳችሁ እና ስለ እያንዳንዱ ስሜታዊ ፍላጎታቹ እየተማራችሁ ነው፡፡ በተጋባቹሁበት ጊዜ እርስ በርስ የሚትተዋወቁ ሊመስላቹ ይችላሉ ግን የዚህ ደረጃ የሚፈጠር የመማር ሂደት አካል ነው፡፡

🔹 የስልጣን ሽኩቻ ደረጃን ለመዳሰስ አስቸጋሪ እና ከወራት እስከ አመታት ሊቆይ ይችላል። በዚህ ደረጃ ላይ ያሉ ብዙ
ጥንዶች አዲስ ግንኙነት መፈለግ ይጀምራሉ ወይም ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ከጠበቁት ነገር ጋር ለማዛመድ አጋራቸውን ለመቀየር ይሞክራሉ። ይህ ያለማቋረጥ አለመግባባትን እና አጋራችሁ እንዳልተረዳችሁ፣ እራስሆን መሆን እንደማይችሉ ወይም በእንቁላል ቂርፋት ላይ እንደሚራመዱ እንዲሰማዎት ሊያደርግ ይችላል፡፡

3️⃣. የመረጋጋት ደረጃ/Stability stage
🔹 በዚህ ደረጃ አጋርዎን እንደ እንድ ልዩ ግለሰብ ያይታል/ይቀበሉታል፤ አጋርዎ እንዲለወጥ ከመመኘት ይልቅ አሁን
የአጋርዎን ማንነት ተቀብለዋል። ልዩነቶችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ አውቀዋል እና ሁለታችሁም ሀላፊነትን
ትከፋፈላላቹ/ትገነባላችሁ።

🔹 ይህ ደረጃ ሰላምን እና መረጋጋትን ያመጣል፤ ነገር ግን መደበኛ ሀላፋነትን ወይም ህግን ያስቀምጡ፤ይህ ለአንዳንዶች
አሰልቺ ሊሆን ይችላል፡፡ ጤናማ ትዳር እድገት፣ ትብብር እና ቀጣይነት ያለው ትምህርት ይጠይቃል።

4️⃣. የቁርጠኝነት ደረጃ/ Commitment Stage
🔹 በዚህ ደረጃ የማይጠሉ አጋሮች ወይም ደስተኛ ግንኙነት እንደሌለ ያስተውላሉ። በዚህ ደረጃ ያገቡት ግለሰብ ላይ ቆራጥ እምነት ይጥላሉ፡፡ ሁለታችሁም እንዴት መግባባት እንደምትችሉ ተማራላችሁ እናም ይህን ማድረግዎን ይቀጥላሉ፡፡በነፃነት መልካሙን እና መጥፎውን ነገሮች ለመነጋገር ያስችሎታል፡፡

🔹 የትዳር አጋሮን እንደሚወዱት ለመገንዘብ የቁርጠኝነት ደረጃ ላይ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዜ ላይወዷቸው
ይችላሉ፤ ሁላችንም ሰዎች ነን ፍፁም አይደለንም፤ ፍቅር ከፍፁምአዊነት በላይ ነው፡፡

5️⃣. በጋራ የመስራት ደረጃ/Co-creation stage
🔹 በዚህ ደረጃ እርስዎ እና አጋርዎ አጋርነታችሁን ከትዳራችሁ ባለፈ ሰዎችን ለመጥቀም ተጠቀሙበታላችሁ። ይህ በተለምዶ በጋራ የፈጠራ ፕሮጀክት ውስጥ መሳተፍን ያካትታል።

🔹 የአጋርነትዎን ጥንካሬ በመጠቀም ሁለታችሁም አንድ ላይ ዋጋ የሚሰጠ ስራ ይሰራሉ/ይፈጥራሉ፡፡ በሌሎች ሁኔታዎች ልጆች ለመውለድ ሊወስኑ የሚችሉት ወቅት ነው፤ ይህ ደግሞ ደስተኛ/ጤናማ ላልሆነ ትዳር ነገሮችን ያወሳስባል።በጋብቻዎ ውስጥ ከእነዚህ ደረጃዎች ውስጥ እራስዎን ብዙ ጊዜ ሊያገኙ ይችላሉ። ነገር ግን በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ ባለፍክ ቁጥር እርስዎ እና አጋርዎ ጥልቅ ግንኙነት እየገነብ መሆኑን አይርሱ፡፡
✍️ #ማድያት #ፊትዎት #ላይ #ወጥቶ #ተቸግረዋል?
ማድያት (Melasma) ለቆዳችን ቀለም የሚሰጡ ህዋሶች (Melanocytes) ከመጠን በላይ ሲመረቱ ከተለመደዉ የቆዳችን ቀለም ለየት ባለ መልኩ የቆዳ መጥቆር ሲኖር ይከሰታል፡፡ይህ ችግር በየትኛዉም የቆዳ ክፍል ላይ የሚወጣ ሲሆን በአብዛኛዉ ፊት ላይ ሲከሰት ይስተዋላል፡፡
👉👉 #ለማድያት #የሚያጋልጡ #ሁኔታዎች
🔹 ለከፍተኛ ፀሀይ/ጨረር መጋለጥ
🔹 የሆርሞን መለዋወጥ
🔹 እርግዝና
🔹 ጭንቀት እና ድባቴ
🔹 የፊት መታጠቢያ እና መዋቢያ ነገሮች
🔹 የወሊድ መከላከያ አማራጮች
🔹 የእንቅርት በሽታ (የታይሮይድ ሆርሞን መዛባት)
🔹 የሆርሞን ህክምና
🔹 የቫይታሚን ቢ12 እጥረት
👉👉 #ለማድያት #የሚደረግ #ህክምና
🔹 ማድያትን በቅድሚያ ለማድያት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ማከም ያስፈልጋል ከዛ በተጨማሪ በባለሙያ የሚታዘዙ የቆዳ ቀለም ሰጪ ህዋሶችን የሚቀንሱ እና የጸሐይ መከላከያ መድሐኒቶች ይታዘዛሉ፡፡
👉👉 #ማድያትን #በቤት #ዉስጥ #ለማከም #የሚረዱ #መንገዶች
🔹 አጃ- የተፈጨ የአጃ ዱቄት ከማር ጋር በመለወስ መቀባት እና ለግማሽ ሰአት አቆይቶ ለብ ባለ ውሃ መታጠብ
🔹 የአፕል አቼቶ-1 ማንኪያ የአፕል አቼቶ ከ1 ማንኪያ ውሀ ጋር በመደባለቅ መቀባት እና ከ3 እስከ 5 ደቂቃ በኋላ አቆይ
🔹 እርድ- 1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ እርድ ከ 2-3 የሻይ ማንኪያ ወተት ጋር በመቀላቀል ማዋሀድ መቀባት እና ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ መታጠብ
🔹 እሬት- 1 የእሬት ቅጠል ዉስጥ ያለዉን ፈሳሽ በመቀባት ለ 2 ደቂቃ ማሸት ከ 15-20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ
🔹 ፓፓያ - ግማሽ የሻይ ሲኒ የበሰለ ፓፓያ መፍጨት ከ 2 ማንኪያ ማር ጋር ቀላቅሎ መቀባት ለ 20 ደቂቃ አቆይቶ ለብ ባለ ውሀ መታጠብ
🔹 አንድ ቲማቲም በመፍጨት ከአንድ የሻይ ማንኪያ እርጎ እና አንድ የሻይ ማንኪያ የአጃ ዱቄት በመቀላቀል ፊትን በደንብ አዳርሶ በመቀባት ለ20 ደቂቃ ቆይቶ ሲደርቅ መታጠብ
✍️ 9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።
👉 በሚከተሉት የማህበረሰብ ትስስር ድህረ ገጾች ይከታተሉን:-
👉የዶክተር አለ የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/Doctoralle8809
👉 የዶክተር አለ የዩቱብ ቻነል Subscribe ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCg8YTjuR_i3pUeQ0Jexa5yQ
👉 የዶክተር አለ የዶክተር አለ 8809 የቲክቶክ ገፅ Follow ያድርጉ
tiktok.com/@doctoralle8809
👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102 OK
✍️ #ስለ #አንጀታችን #የማያውቋቸው #ስድስት #አስገራሚ #እውነታዎች #በሀኪም #መረጃ!
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

ሁሉንም የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ያለ ማንም ትዕዛዝ የሚፈጽመውና ለአጠቃላይ ጤናችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አንጀታችን በብዙዎች 'ሁለተኛው አንጎል' በመባል ይጠራል።

የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንጀታችን ምግብ ከመፍጨት የበለጠ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያከናውናል።

ዶክተሮች እንዲውም አንጀት የአእምሮ ህመምን ለማከምና የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት የሚያደርገውን አስተዋጽ በግልጽ ለመለየት ምርምር ጀምረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አውስትራሊያዊቷ ሜጋን ሮሲ በአንጀት ጤናና ህክምና ላይ በተለይ የሚሰሩ ዶክተር ናቸው። ስለምንበላቸው ምግቦችና በአንጀታችን ዙሪያ ማወቅ ስላሉብን ስድስት እውነታዎች ነግረውናል።

🔹 1. ራስ ገዝ የነርቭ ሥርዓት

ከሌሎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን በተለየ መልኩ አንጀታችን በራሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ከአንጎላችን እስኪመጣ አይጠብቅም።

አንጀታችንን የሚያዘው አንጎላችን ሳይሆን ''ኢንትሪክ የነርቭ ሥርዓት'' የሚባለው ሲሆን፤ ይህም በዋነኛነት የሚቆጣጠረው ከሥርዓተ-ልመት (የምግብ መፈጨትና መዋሃድ) ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ነው።

ምንም እነኳን አንጀታችን ነገሮችን በራሱ ቢያናከውንም፤ ከማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ጋር ግን መረጃዎችን ይለዋወጣል።

🔹 2. 70 በመቶ የሚሆኑት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሴሎች በአንጀታችን ውስጥ ይገኛሉ

እንደ ዶክተር ሮሲ ከሆነ ይህ እውነታ አንጀታችን ከበሽታ መከላከልና ከአጠቃላይ ጤንነታችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንዲሆን ያደርገዋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአንጀት ህምም ባጋጠመን ጊዜ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ ተጋላጭ እንሆናለን።

🔹 3. 50 በመቶ የሚሆነው የሰዎች አይነምድር ባክቴሪያ ነው

ግማሽ ያህሉ ከሰውነታችን የሚወደው አይነ ምድር ባክቴሪያ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ግን ጎጂ አይደሉም። ጎጂ ቢሆኑ እንኳን የአንጀታችን የመከላከል ብቃት ከፍተኛ ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም።

ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ሮሲ አንጀታችንን ሥራ ካበዛንበትና ካልተንከባከብነው ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሰው በቀን ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ ቢል መልካም ነው ባይ ናቸው።

🔹 4. የተለያዩ አይነት ምግቦች ስንመገብ አንጀታችን ደስ ይለዋል

አንጀታችን ውስጥ በትሪሊዮኖች የሚቆዎጠሩና ብዙ ጥቅም ያላቸው "ማይክሮብስ" የሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱ ደግሞ የተለያየ አይነት ምግቦች ወደ አንጀታችን ሲገባ የሥራ ፍጥነታቸው ይጨምራል።

እነዚህ ማይክሮብ የተባሉት ነገሮች የሥርዓተ ልመቱን ከማፋጠን አልፎ በምግቦች ውስጥ ያለውን ውሃ ለመምጠጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

''ማይክሮብስ'' በቤታችን እንደሚገኙ የቤት እንስሳት እንደማለት ናቸው። የእኛን እንክብካቤ ይፈልጋሉ በማለት ገልጸዋቸዋል ዶክተር ሮሲ።

🔹 5. የሆድ እቃችን ከጭንቀትና ስሜቶቻችን ጋር ግንኙነት አለው

ከሆድና አንጀታችን ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ህመም ሲሰማን መጀመሪያ ልናስበው የሚገባው ነገር በሰዓቱ ጭንቀት ውስጥ መሆን አለመሆናችንን ነው።

ለዚህም ነው በቅርቡ እየተሞከሩ ባሉ አዳዲስ የህክምና አይነቶች የአእምሮ በሽታና ቀላል ጭንቀቶችን ለማከም ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን ወደ አንጀት ማስገባት የተጀመረው።

የዘርፉ ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው ጥናት ጤናማ የሆነ አንጀት ያላቸው ሰዎች ጤናማ ካልሆነ አንጀት ካላቸው ጋር ሲወዳደሩ ለጭንቀትና ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ ነው።

🔹 6. የአንጀትዎትንና የሥርዓተ-ልመት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚከተሉትን ያድርጉ
የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ይመገቡ
ጭንቀት ይቀንሱ
የሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ
የአንጀት ህመም ካለብዎት የአልኮል መጠጦችን፣ ቡና እንዲሁም ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አያዘውትሩ
ረጅምና ያልተቆራረጠ እንቅልፍ ያግኙ

9102 ok ብለዉ በእጅ ስልክዎ በመላክ አጭር መልእክቶቻችንን በቀላሉ መከታተል ይችላሉ።

👉 የዶክተር አለ የአጭር መልእክት:-
👉👉👉 9102
#7_የዝንጅብል_ጥቅሞች

1. ዝንጅብል ፀረ-ብግነት ባህሪ ስላለው ህመምን እና እብጠትን ለመቀነስ ይረዳል።
2. ዝንጅብል በተለይም ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ ማቅለሽለሽ እና ማስታወክን ለመቀነስ ይረዳል።
3. ዝንጅብል በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመቀነስ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት መንስኤዎችን ለማሻሻል ይረዳል።
4. ዝንጅብል ኃይለኛ አንቲኦክሲዳንት እና ፀረ-ካንሰር ባህሪይ ሊኖረው ይችላል።
5. ዝንጅብል የወር አበባ ህመምን ለመቀነስ እና ሌሎች የወር አበባ ምልክቶችን ለማሻሻል ይረዳል።
6. ዝንጅብል ሥር የሰደደ የምግብ መፈጨት ችግርን እና የምግብ ፍላጎት ማጣትን ለማከም ይረዳል።
7. ዝንጅብል የኮሌስትሮል መጠንን ለመቀነስ እና ከኦክሳይድ ጭንቀት ለመከላከል

መልካም ቀን💚💛
✍️ #ህፃናት #የወይራ #ዘይት #መቼ #መጀመር #አለባቸው?

🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

🔹 ከ 6 ወር ጀምሮ ምግባቸው ላይ ጠብ እያደረግን መመገብ እንችላለን፡፡

#የትኛውን #መምረጥ #አለብን?

🔹 ተጨማሪ ምግብን በተመለከተ ኤክስትራ ቨርጅን የወይራ ዘይት የተሻለ እና ተስማሚ ነው።

🔹 የወይራ ዘይት ስብጥር ለሚያድግ አካል በጣም አስፈላጊ የሆኑት “ጠቃሚ” ኮሌስትሮል እና ያልተሟሉ የሰባ አሲዶች አሉት(fatty acid) ቅንብሩ በተጨማሪ በጡት ወተት ውስጥ ከሚገኙ ቅባቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ቅባቶችን ያጠቃልላል ፡፡

🔹 የወይራ ዘይት ከሌሎቹ የአትክልት ዘይቶች ሁሉ በተሻለ የህጻናት ሰውነት ላይ በዳይፐር አማካኝነት የሚፈጠርን ሽፍታ ለማጥፋት፣ እንዲሁም ህፃናት ላይ የሚወጣን ብጉር ለማጥፋት ይጠቅማል፡፡

#ስለልጅዎ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ በመደወል ያማክሩ!! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!
✍️ #ስለ #አንጀታችን #የማያውቋቸው #ስድስት #አስገራሚ #እውነታዎች #በሀኪም #መረጃ!
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

ሁሉንም የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ያለ ማንም ትዕዛዝ የሚፈጽመውና ለአጠቃላይ ጤናችን ከፍተኛ ሚና የሚጫወተው አንጀታችን በብዙዎች 'ሁለተኛው አንጎል' በመባል ይጠራል።

የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚሉት አንጀታችን ምግብ ከመፍጨት የበለጠ ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያከናውናል።

ዶክተሮች እንዲውም አንጀት የአእምሮ ህመምን ለማከምና የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም ለመገንባት የሚያደርገውን አስተዋጽ በግልጽ ለመለየት ምርምር ጀምረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ቢቢሲ ያነጋገራቸው አውስትራሊያዊቷ ሜጋን ሮሲ በአንጀት ጤናና ህክምና ላይ በተለይ የሚሰሩ ዶክተር ናቸው። ስለምንበላቸው ምግቦችና በአንጀታችን ዙሪያ ማወቅ ስላሉብን ስድስት እውነታዎች ነግረውናል።

🔹 1. ራስ ገዝ የነርቭ ሥርዓት

ከሌሎቹ የሰውነት ክፍሎቻችን በተለየ መልኩ አንጀታችን በራሱ ጊዜ የሚያደርጋቸው ነገሮች ብዙ ናቸው። ማንኛውንም አይነት ትእዛዝ ከአንጎላችን እስኪመጣ አይጠብቅም።

አንጀታችንን የሚያዘው አንጎላችን ሳይሆን ''ኢንትሪክ የነርቭ ሥርዓት'' የሚባለው ሲሆን፤ ይህም በዋነኛነት የሚቆጣጠረው ከሥርዓተ-ልመት (የምግብ መፈጨትና መዋሃድ) ጋር የተያያዙ ሂደቶችን ነው።

ምንም እነኳን አንጀታችን ነገሮችን በራሱ ቢያናከውንም፤ ከማዕከላዊው የነርቭ ሥርዓት ጋር ግን መረጃዎችን ይለዋወጣል።

🔹 2. 70 በመቶ የሚሆኑት የሰውነታችን በሽታ ተከላካይ ሴሎች በአንጀታችን ውስጥ ይገኛሉ

እንደ ዶክተር ሮሲ ከሆነ ይህ እውነታ አንጀታችን ከበሽታ መከላከልና ከአጠቃላይ ጤንነታችን ጋር በጥብቅ የተቆራኘ እንዲሆን ያደርገዋል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት የአንጀት ህምም ባጋጠመን ጊዜ እንደ ጉንፋን ላሉ በሽታዎች በቀላሉ ተጋላጭ እንሆናለን።

🔹 3. 50 በመቶ የሚሆነው የሰዎች አይነምድር ባክቴሪያ ነው

ግማሽ ያህሉ ከሰውነታችን የሚወደው አይነ ምድር ባክቴሪያ ቢሆንም፤ አብዛኞቹ ባክቴሪያዎች ግን ጎጂ አይደሉም። ጎጂ ቢሆኑ እንኳን የአንጀታችን የመከላከል ብቃት ከፍተኛ ስለሆነ ብዙም የሚያሳስብ አይደለም።

ነገር ግን ይላሉ ዶክተር ሮሲ አንጀታችንን ሥራ ካበዛንበትና ካልተንከባከብነው ውጤቱ አስከፊ ሊሆን ይችላል። ማንኛውም ሰው በቀን ቢያንስ ሦስት ጊዜ ወደ መጸዳጃ ቤት ጎራ ቢል መልካም ነው ባይ ናቸው።

🔹 4. የተለያዩ አይነት ምግቦች ስንመገብ አንጀታችን ደስ ይለዋል

አንጀታችን ውስጥ በትሪሊዮኖች የሚቆዎጠሩና ብዙ ጥቅም ያላቸው "ማይክሮብስ" የሚባሉ ጥቃቅን ነገሮች ያሉ ሲሆን እነሱ ደግሞ የተለያየ አይነት ምግቦች ወደ አንጀታችን ሲገባ የሥራ ፍጥነታቸው ይጨምራል።

እነዚህ ማይክሮብ የተባሉት ነገሮች የሥርዓተ ልመቱን ከማፋጠን አልፎ በምግቦች ውስጥ ያለውን ውሃ ለመምጠጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

''ማይክሮብስ'' በቤታችን እንደሚገኙ የቤት እንስሳት እንደማለት ናቸው። የእኛን እንክብካቤ ይፈልጋሉ በማለት ገልጸዋቸዋል ዶክተር ሮሲ።

🔹 5. የሆድ እቃችን ከጭንቀትና ስሜቶቻችን ጋር ግንኙነት አለው

ከሆድና አንጀታችን ጋር የተገናኘ ማንኛውም አይነት ህመም ሲሰማን መጀመሪያ ልናስበው የሚገባው ነገር በሰዓቱ ጭንቀት ውስጥ መሆን አለመሆናችንን ነው።

ለዚህም ነው በቅርቡ እየተሞከሩ ባሉ አዳዲስ የህክምና አይነቶች የአእምሮ በሽታና ቀላል ጭንቀቶችን ለማከም ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎችን ወደ አንጀት ማስገባት የተጀመረው።

የዘርፉ ባለሙያዎች እያደረጉት ባለው ጥናት ጤናማ የሆነ አንጀት ያላቸው ሰዎች ጤናማ ካልሆነ አንጀት ካላቸው ጋር ሲወዳደሩ ለጭንቀትና ሌሎች የአእምሮ በሽታዎች ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ ነው።

🔹 6. የአንጀትዎትንና የሥርዓተ-ልመት ሂደቶችን ለማስተካከል የሚከተሉትን ያድርጉ
የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ይመገቡ
ጭንቀት ይቀንሱ
የሰውነት እንቅስቃሴ ያድርጉ
የአንጀት ህመም ካለብዎት የአልኮል መጠጦችን፣ ቡና እንዲሁም ቅመም የበዛባቸው ምግቦች አያዘውትሩ
ረጅምና ያልተቆራረጠ እንቅልፍ ያግኙ
#በህፃናት #ላይ #የሚከሰት #የአፍ #ውስጥ #ፈንገስ #ምንድን #ነው?
👉👉 #የህፃናት የአፍ ውስጥ ፈንገስ የሚከሰተው ፈንገሱ በአፍ ውስጥ አድጎ በሚፈጥረው ኢንፌክሽን ምክንያት ነው፡፡ ይህ ኢንፌክሽን ብዙን ጊዜ ህፃናት ለከፋ ጉዳት የማይጥል ቢሆንም አልፎ አልፎ ግን ከባድ የጤና ችግር የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ በተለይ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተዳከመ ከሆነ ኢንፌክሽኑ ወደ ተለያየ የሰውነት ክፍላቸው በመዛመት ውስብስብ የጤና ችግር የማምጣት እምቅ አለው፡፡ በተመሳሳም ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ይተላለፋል፡፡
👉👉 #የአፍ #ውስጥ #ፈንገስ #መንስኤዎች#በልጆች #ላይ
ካንዲያሲስ ፈንገስ
አልቢካንስ ሲ በተባለ ፉንገስ አማከኝነት ሊከሰት ይችላሉ
እናቶች ብዙን ጊዜ ወተት እንዳይፈስ በማለት ጡታቸውን የሚሸፍኑባቸው ነገሮች አማካኝነት ባክቴሪያዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ
በእርግዝና ጊዜ እናት ማህፀን ኢንፌክሽን ተጋልጣ ሳትታከም ከቀረች በምቶልድበት ሰአት ከስዎ ወደ ልጁ በመተላለፍ ልጁ ላይ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል
እናት በምታጠባበት ወቅት ህመም እና ከጡቷ ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ ከወተት ወጪ እነዚህ ካሉ ኢንፊክስን ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል በሚያጠቡበት ወቅት ወደ ህፃኑ ስለሚተላለፍ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል ስለዚህ ህክምና ማድረግ ይኖረባቸዋል::
👉👉 #የአፍ #ውስጥ ፈንገስ #ምልክቶች
ነጭ ወይም ቢጫ ቀለም ያላቸው ያበጡ ነገሮች በትንሽ ቦታ ላይ ውስጠኛው ጉንጭ ክፍል፣ በምላስ፣በቶንሲሎች፣ በድድ ወይም በከንፈር ላይ ይወጣሉ፡፡
እብጠቱ በሚፋቅበት ጊዜ አነስተኛ ደም ይወጣዋል
በአፍ ውስጥ ቁስል ወይም የማቃጠል ስሜት ይፈጠራል
የጥጥ ስሜት አፍ ውስጥ መሰማት
በአፍ ጥግ ላይ መድረቅና የቆዳ መሰንጠቅ ሊያጋጥም ይችላል
ለመዋጥ መቸገር የአፍ መጥፎ ጠረን ሊፈጠር ይችላል
ምግብ የማጣጣም አቅም መቀነስ ወይም ጣእም ማጣት አንዳንዴም የምግብ መውረጃ ትቦ (ኦሶፋገስ) በዚህ ኢንፌክሽን ሊጠቃ ይችላል፡፡
👉👉 #በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ምንድን ነው
የህፃናቱን እድሜ ባማከለ መልኩ ለልጆች እርጎን መስጠት እንችላለን፡፡ እረጎ ላክቶስ በሲላይ የተባለ እጥረ ነገርን ስለያዘ ፈንፈፉን ለመቀነስ ይረዳናል
ለብ ባለ ውሃ ላይ ጨው በመጨመር አካባቢውን መጥረግ
👉👉 #ሕክምናው
የአፍ ውስጥ የህፃናት ፈንገስ ለማከም የጤና ባለሙያዎ የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ይኖራሉ ፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ፀረ- ተዋህሲያን መድኃኒቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቁና በትክክል ሊወሰዱ የሚገባቸው ናቸው ፡፡
✍️ እናቶቻችን #ከሚጠቀሙበት #ባህላዊ #መድኃኒቶች #በጥቂቱ
👉👉 #ፌጦ፦ ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል።
👉👉 #የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ፦ ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያስገኛል።
👉👉 #ነጭ ሽንኩርት፦ ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ ይናገራሉ።
👉👉 #ጤና አዳም፦ ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ ህመም ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒት ነው።
👉👉 #እንስላል፦ በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል።
👉👉 #ሽፈራው: - የዚህ ዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል ፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅቶ በውሃ መጠጣትም ይቻላል ፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል።
👉👉 #ዳማከሴ፦ ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ስቦ መውሰድ ፣ ለመተንፈሻ አካል ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው።
👉👉 #ሬት ልጣጩ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ ፈሳሽ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት ጥቅሙን ያገኙታል።
👉👉 #አርማ ጉሳ፦ አረንጓዴውን ቅጠል በማድረቅ ወቅጠው እንደ ሻይ ለረጅም ጊዜ በመጠጣት የስኳር ህመምተኞች በደማቸው ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ፈጥኖ የማውረድና የመቀነስ አቅም አለው። ቅጠሉን ደግሞ በአረንጓዴነቱ ወቅጠው ጨምቀው ቢጠጡት ከቁርጥማት የመፈወስ ኃይልና የምግብ ፍላጎት የመክፈት ኃይል አለው።
👉👉 #የእንጆሪ ቅጠል፡- በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል።
👉👉 #ጣዝማ ማር፦ ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም ማገገም ይቻላል። ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል።
👉👉 #ሎሚ፡- ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው።
👉👉 #እንቆቆና መስመስ፦ ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው።
👉👉 #የእንሰት ስር(አምቾ)፡- ከውስጥ አካሉ የሚገኘው ውሃ እና አሚቾው ተቀቅሎ ደጋግሞ መብላት እንዲመግል የተፈለገ የተጎዳ የሰውነት አካልም ሆነ በሰውነት የወጣ ማንኛውም እባጭ መግል ሆኖ እንዲፈነዳ/እንዲወጣ ያግዛል ፣ የተሰበረ አጥንት በወጌሻ ማጀል ሲያስፈልግ የተሰበረው ቦታ ለማለዘብ (ለማለስለስ) አምቾውን በእርጎ እያማጉ ደጋግሞ መብላት ነው ፣ በጠቦት ሾርባ ደጋግሞ መብላት በመኪናም ሆነ በጦር ሜዳ ስጋው የተቦጨቀ ወይም አጥንቱ ላይ አደገኛ ስብራት ያጋጠመው ቁስሉ እንዲሽር(እንዲጠገን) ያደርጋል።
👉👉 #ኮሶ፡- የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል።
👉 👉 #እነዚህ እፅዋቶች እንደየ አከባቢው አጠራር ስማቸው ሊለያይ እንደሚችል ግንዛቤ ይወሰድ።
2025/07/07 18:53:19
Back to Top
HTML Embed Code: