Telegram Web Link
◼️ ከትላንት ወዲያ ገና እድሜውን ሳያጣጣጥም በመኪና አደጋ ህይወቱ ስላለፈው የ20 ቁጥር ለባሹ ምትሃተኛ አንዳንድ የህይወት ታሪኩን ለመመልከት እንሞክር ፦

-> ሙሉ ስሙ ዲያጎ ጆሴ ቴክሴራ ዳሲልቫ ይባላል

-> እድሜው ገና 28 አመቱ ነበረ ( 1996-2025 )

-> የሶስት ልጆች አባት የነበረው ጆታ በ6ቀናት በፊት ነበረ በ3ልጆቹ እናት ጋር በጋብቻ የተሳሰረው

#PART1

--> ጆታ እግርኳስን ሀ ብሎ የጀመረው በሃገሩ ፖርቹጋል በሚገኘው ፓኮስ ዴ ፌሬራ በሚባል መካከለኛ ክለብ ውስጥ ነበረ ።

--> ጆታ የፕሮፌሽናል እግርኳስን የጀመረው በስፔኑ ሃያል ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ የአምስት አመት ኮንትራት በመፈረም ነበረ ።

--> ጆታ በአትሌቲኮ ቤት ይሄን ያህል የተሳካ የሚባል ጅማሮን ባለ ማረጉ ምክንያት በ 2016 መልሶ በፖርቹጋል ለሚገኘው ፖሮቶ በውሰት ተሰጠ ።

--> ጆታ በፖርቶ ቤት የአንድ አመት ቆይታን ካደረገ በኃላ ክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ለእንግሊዙ ክለብ ዎልቭስ በድጋሜ በውሰት አስተላለፈው ።

--> ዲያጎ የእንግሊዝ ምድርን በፍጥነት በመላመድ እና በወልቭስ ቤት ጥሩ የሚባል አቋምን በማሳየቱ በ 2018 ላይ ዎልቭሶች ጆታን በቋሚ ውል አስፈረሙት ።

--> በወልቭስ የሶስት አመት ቆይታ ካደረገ በኃላ በ2020 በ41€ M የእንግሊዙን ሃያል ክለብ ሊቨርፑልን ተቀላቀለ !

#ይቀጥላል...

RIP DIOGO 💔
ዴምቤሌ የጆታን የደስታ አገላለፅ ተጠቅሟል ❤️🙏

" SHARE " | @DREAM_SPORT
ኮናቴ በኢንስታግራም ገፁ 🙏

" SHARE " | @DREAM_SPORT
Thank You Dembelé 🙏❤️

" SHARE " | @DREAM_SPORT
◼️ " አሁን ላይ በአለም ላይ ደስተኛው ሰው እኔ ነኝ " ዲያጎ በተከታታይ ባገኛቸው ደስታ ምክንያት በኢንስታግራም ገፁ ያጋራው ፅሁፍ ነበረ !

-> ጆታ የ 20 ቁጥር ማሊያን ለብሶ ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር የ20ኛ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ካሳካ ገና የወራት እድሜ ብቻ ነበሩ የተቆጠሩት ።

-> በተመሳሳይ እንዲሁ ከሃገሩ ፖርቹጋል ጋር የዩኤፋ ኔሽን ሊግን ስፔንን በመርታት ካሳካ ገና 1ወሩ ነበረ ።

-> ከሁሉም በላይ አሳዛኙ ከተሞሸረ ገና በአምስት ቀኑ ማረፉ ነበረ ።

#PART 2

--> ዲያጎ ጆታ በፕሮፌሽናል የእግርኳስ ህይወቱ እስካሁን 448 ጨዋታዎች ያረገ ሲሆን በነዚም ጨዋታዎች 150 ጎሎችን እና 77 አሲስቶችን ማስመዝገብ ችሎ ነበረ ።

--> ጆታ የፕሮፌሽናል ኮንትራት ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረመበት አትሌቲኮ ማድሪድ አንድም ጨዋታም ሆነ ጎልም ማስቆጠር አልቻለም ነበረ ።

--> ጆታ በፖሮቶ ቤት በ27 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ የቻለው ጆታ 8 ግቦችን ከመረብ ማዋሃድ ችሎ ነበረ ።

--> ጆታ በወልቭስ ቤት በቆየባቸው ሁለት አመታት 111 ጨዋታዎች ያደረገ ሲሆን 33 ግቦችን ከመረብ ማዋሃድ ችሎ ነበረ ።

--> ጆታ በሊቨርፑል ቤት በ182 ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ሲሆን 85 ግቦችን ከመረብ ጋር ማዋሃድ ችሎ ነበረ ።

--> ጆታ ለሃገሩ ፖርቹጋል 23 ጨዋታ ያረገ ሲሆን 8ግቦችን እና 5 አሲስቶችን ማበርከት ችሎ ነበረ ።

#ይቀጥላል...

RIP DIOGO 💔
◼️ ዲያጎ ጆታ በመላው የእግርኳስ እንዲሁም በሁሉም የሊቨርፑል ደጋፊዎች ልብ ውስጥ ለዘላለም የማይረሳ ድንቅ ተጫዋች ነው !

-> አንዳንዶች የጆታን ሞት ከሃገራችን አባባሎች ጋር ያመሳስሉታል - "ሞቴን አሳምርልኝ "

-> አንዳንዶችም ደስታ ሲደራረብ ሃዘን ይዞ መምጣቱ የማይቀር ነው ሲሉ ይደመጣሉ !

-> አንዳንዶችም የሰው ልጅ ከተሞሸረ በኃላ ለ40 ቀን ያህል ከቤት መውጣት የለበትም ይላሉ ፤ ያም ሆነ ይህ ግን ፈጣሪ የፈቀደው ሆኗል !

#PART 3

--> ወንድሜ ዲያጎ በህይወት እስካለሁ ድረስ ልጆችህን እና መላው ቤተሰብክን እንደምንከባከብልክ ቃል እገባለው ። 🗣 ቡሩኖ ፈርናዴስ

--> ሰዎች ስለ ሞትክ ሊረሱክ ይችላሉ እኔ ግን መቼም አረሳክም ለኔ የህይወቴ ምርጡ አንተ ነበርክ ። 🗣 ሩበን ኔቬስ

--> በጣም የምትሳሳለትን ሰው እንዳጣኸው ለማመን ከአዕምሮህ እና ልብህ ጋር እየታገልክ የሚሰማህን ስሜት ለመግለፅ ቃላቶችን ማግኘት ይከብዳል ።🗣 ትሬንት አርሎንድ

--> ሀዘኔን ቃላቶች አይገልፁልኝም፣ ለቤተሰቡ እና ልጁ መፅናናትን እንዲያገኙ ፈጣሪን ተንበርክኬ እለምነዋለሁ ። 🗣ሮቤሮቶ ፈርሚኒሆ

--> የምሰቃይበት ጊዜ አሁን ነው፣ በ ዲዮጎ እና ወንድሙ ህልፈተ ህይወት ልቤ ተሰብሯል። 🗣 የርገን ክሎፕ

--> የተፈጠረው ነገር የማይታመን ነው... በቅርቡ በብሔራዊ ቡድን ውስጥ አብረን ነበርን፣ ብዙ ሳይቆይ አገባ። ለቤተሰብህ፣ ለሚስትህና ለልጆችህ የላቀ የሀዘን መግለጫዬን እልካለሁ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶችህ እና አድናቂዎችህ ለሁሉም መፅናናትን እመኝላቸኋለሁ። 🗣 ክርስቲያኖ ሮናልዶ

#ይቀጥላል...

RIP DIOGO 💔
◾️ ጆታ በእግርኳስ ህይወቱ ተከታታይ ጉዳቶችን ያስተናገደ ቢሆኖም እራሱን ግን ሁሌም ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ያረግ ነበረ !

-> ጆታ በሊቨርፑል ቤት ውስጥ ከየትኛውም ተጫዋች ከፀብ እና አተካራ የሌለበት እንደሆነ የቡድን አጋሮቹ ይናገራሉ !

-> ጆታ በአንድ ወቅት " የ2026 የአለም ዋንጫን ለክርስቲያኖ ሮናልድ ስንል እናሳካለን " ጆታ ይህን ንግግር በማህበራዊ ትስስር ገፁ ካጋራ ከ 2ወራት ከደማ በኃላ ነበረ የአሳዛኙ የሞቱ ዜና የተሰማው

#PART 4

--> እ.ኤ.አ ሰኔ 22 ቀን ጆታ ሰርጉን ከመደገሱ በፊት ነበረ የሳንባ ቀዶ ጥገና ያደረገው ፤ ዶክተሮቹም በዚህ ምክንያት የአውሮፕላን በራረ እንዳያደረግ ከለከሉት !

--> በዚህም ምክንያት ከሊቨርፑል ከተማ በጀልባ ወደ ሰሜናዊው የስፔን ክፍል ሳንታንዳር በመጓዝ በህይወቱ ትልቅ ቦታ የሚሰጣትን ፍቅረኛውን በሰርግ ያገባት !

--> ከ5 ቀናት በኃላም በክለቡ ሊቨርፑል የቅድመ ውድድር አመት ልምምድ ለመሳተፍ ከወንድሙ አንድሬ ዳ ሲልቫ ጋር በ መኪና ጉዞውን የጀመረው !

--> በሰዓቱ እነ ጆታ እያሽከረከራት የነበረችው የአለም ፈጣኗ ላንበርጊኒ ሁራካን መኪና ነበረ !

--> መኪናዋ ሌላ መኪናን ደርባ ለማለፍ በምትሞክርበት ጊዜ ጎማዋ በመሰንጠቁ መኪናዋ ፍጥነቷን መቆጣጠር ባለ መቻሏ ከመንገድ በመውጣት በእሳት ልትያያዝ መቻሏል የስፔን ፖሊስ አስታውቋል !

--> ይህ አሳዛኝ ክስተት ከሌሊቱ 6:40 CEST አካባቢ A-51 በሚባለው አውራ ጎዳና ላይ ነበረ የተከሰተው !

--> የስፔኑ የዜና ምንጭ ማርካ ነገሩን ቀድሞ ለአለም ያሳወቀ የመጀመሪያው ሚዲያ ሲሆን ከሰዓታት በኃላም የስፔን ድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የነገሩን እውነተኝነት አረጋግጠዋል !

RIP DIOGO 🕊

" SHARE " | @DREAM_SPORT
አሁኑኑ ይመዝገቡና የ 30 ብር ጉርሻ ያግኙ
Register Now and Get 30 ETB WELCOME BONUS
ቶማስ ሙለር ዛሬ ለሙኒክ የመጨረሻ ጨዋታው አድርጓል 💔

🏟️ 755 ጨዋታዎች
250 ግቦች
🎯 276 አሲስቶች
🏆 33 ዋና ዋንጫዎችች

13 - Bundesliga 🏆

6 - DFB-Pokal 🏆

8 - DFL-Supercup 🏆

2 - UEFA Champions League 🏆

2- UEFA Super Cup 🏆

2- FIFA Club World Cup 🏆

A true one-club 𝒍𝒆𝒈𝒆𝒏𝒅. Danke, Thomas! 🐐👏

" SHARE " | @DREAM_SPORT
የሪያል ማድሪድ አሰላለፍ !

5:00 | ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

" SHARE " | @DREAM_SPORT
︎|| ኔይማር ጁኒየር ለሙሲያላ የላከው መልዕክት

"በፍጥነት አገግመህ ወደ ሜዳ ተመልሰህ ማንፀባረቅን እንድትቀጥል እመኝልሀለው እግር ኳስ ያንተን ተሰጥኦ ትፈልጋለች ጠንከር በል 🙏::"

"SHARE" || @DREAM_SPORT
DREAM SPORT
የሪያል ማድሪድ አሰላለፍ ! 5:00 | ማድሪድ ከ ዶርትመንድ " SHARE " | @DREAM_SPORT
የዶርትመንድ አሰላለፍ !

5:00 | ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

" SHARE " | @DREAM_SPORT
ምናልባት ዛሬ ያያችሁት ምርጥ ነገረ ❤️

"SHARE" || @DREAM_SPORT
● ፔዤ ለመጀመርያ ጊዜ አምስት ተከታታይ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን ማሸነፍ ችለዋል!

◉ 1-0 vs. Arsenal (UCL)
◉ 2-1 vs. Arsenal (UCL)
◉ 5-0 vs. Inter (UCL)
◉ 4-0 vs. Inter Miami (CWC)
◉ 2-0 vs. Bayern (CWC)

14-1 on aggregate. 🔥

" SHARE " | @DREAM_SPORT
ዱዌ የዛሬው ጨዋታ የጨዋታው ኮከብ በመባል መመረጥ ችሏል !

" SHARE " | @DREAM_SPORT
ሮድሪጎ ለአራተኛ ተከታታይ ጨዋታ ቤንች ተደርጓል ።

ሮድሪጎን ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ ?

" SHARE " | @DREAM_SPORT
🚨OFFICIAL

በርሚንግሃም ሲቲ ኪዮጎ ፉሩሃሺ ከሬንስ በሶስት አመት ውል ማስፈረማቸውን ይፋ አርገዋል !

" SHARE " | @DREAM_SPORT
ጉስታቮ ኦሊቬራ በዲያጎ ጆታ ሞት ማዘኑን ዛሬ ካደረገው ውድድር በኃላ አሳይቷል !

በእውነት በሁሉም ቦታ ክፍተት ጥሎ ሄዷል 💔

" SHARE " | @DREAM_SPORT
በማህበራዊ ሚድያዎች የሙሲያላ እግር ነው ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ስህተት ነው ።

ይህ ምስል ከአመታት በፊት የኤቨርተኑ አማካይ አንድሬ ጎሜስ ከሶን ሂንግ ሚን ጋር ተጋጭቶ ከሙሲያላ ጋር ተመሳሳይ የቁርጭምጭሚት ጉዳት ካጋጠመው ቡሀላ ተነስቶ የተለቀቀው ምስል ነው ።

ሲጀመር ሙሲያላ ጉዳቱ ያጋጠመው ግራ እግሩ ላይ ነው የጎሜስ ደግሞ ቀኝ እግሩ ላይ ነው ።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ የምታዩትን ነገር ዝምብላችሁ አትመኑ አስተውሉ ።

" SHARE " | @DREAM_SPORT
2025/07/06 18:58:13
Back to Top
HTML Embed Code: