Telegram Web Link
ብዕሬን ሞጫጨርኩ ማስታወሻዬ ላይ
ባገኘው ብዬ ጥበብ ውስጥ ቢታይ
ሸፍኖትስ ቢሆን የወረቀት ክምር
ገፆቼን ከፈትኩ ባገኘው ከስር
በወይኒ ውስጥ ሆኖ ይሰማል ጩኸቶ
መንገድ የሚያስጀምር መውጫ በማጣቴ
አልጠብቅም ለሊቱ እስኪለቅ
እንደ አርዮብ ልውጣ እና ልድመቅ
Tomorrow I will be having my first interview with Dawit aka D on the breakfast show at afro fm after 8 am. Tune in to our conversation regarding my music and the journey.
Chelina seems to love the music! 🙏 What about you? Your feed back is everything to me.
👍1
How is the EP?
Anonymous Poll
84%
Great
9%
Good
7%
Needs Improvement
Dawit Cherent pinned «https://www.youtube.com/playlist?list=PLsGRENXlTBMuxzesZX6hJq_u5wQgV2_7L»
ማለዳ ይነሳል ዛሬን ለማሸነፍ
ከቤቱም ሲወጣ እንዲ ብሎ ነበር
ፈጣሪዬ ሆይ በቀኝህ አውለኝ
ህይወት እንዳትከዳኝ አቤቱ አስበኝ
ቀስ በቀስ ይራመዳል እንቁላል እግር ያወጣል
የሚኖር ባይመስልም አንድ ቀን ይሄዳል
ቢገርምም ነገሩ ይሆናል ግድ የለም
ከቅፊት ሲወጣ ያስተውላል አለም
አይ አለማስተዋል ስር እየሰደዱ
ቅርንጫፉ እንዳይኖር ይቆረጣል ግንዱ
ቀንበጡ እረግፎ ጉቶ እየመሰለ
ግን እሚያስገርመው ስር ውስጥም ዘር አለ
እስከምድር ጫፍ ተጏዝኩ ስፈልግ
ተስፋን አንግቤ በፅናት
አገኘው ይሆን ወይ የልቤን ጥማት
አውቀውስ ይሆን ወይ ሳገኘው ያን ለት
ምን አለ ቢተዉኝ እንዳፈርስ አጥሩን
እስከ መቼ ፈርተው ይዘጋሉ ቅጥሩን
2025/10/22 20:36:33
Back to Top
HTML Embed Code: