Forwarded from Habtom Woldeab
💵ጢጦስና ቴክላ👑
የማይጨርሱ ከሆነ አይጀምሩ ከጨረሱ ያጋሩ!

በተለያዩ ምክንያቶች መጽሐፍት ከማንበብ ርቄ ነበርና ከረዥም ጊዜ በኋላ ሰሞኑን በድንገት የገዛሁትን አዜብ በርሄ ያዘጋጀችውን ‹‹ዝክረ ቅዱሳት አንስት ዘተዋህዶ›› የተሰኘውን ቅጽ 1 መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር፡፡ ይሄንን መጽሐፍ ገና የመጀመሪያ ምዕራፎች ላይ ብሆንም ከመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች የቅድስት ቴክላን ታርክ ሳነብ ታርኳ በጣም መሰጠኝና ካነበብኩ በኋላ በአእምሮዬ ሳመላልስ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ‹‹ፍያታዊ ዘየማን/ጢጦስ›› ፡፡ ምን ያገናኛቸዋል ትሉኝ ይሆናል እርግጥ አይገናኙም ግን ለምን ትዝ እንዳለኝ ልንገራችሁ፡፡ የሁለቱንም ሰዎች የነበሩበትን ሕይወት ስንመለከት በጭራሽ የማይገናኝ ጫፍና ጫፍ ያለ ሲሆን አንድ የሚያደርጋቸው ጥሪያቸውን የተጠቀሙበት አጋጣሚ ነው፡፡ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ የመጨረሻው የውርደት/የድቀት ኑሮ የሚባለው ሽፍትና/ውንብድና ሲሆን የመጨረሻ ከፍ ያለ/የተከበረ ኑሮ የሚባለው ደግሞ ባለጠግነት ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን ኑሮ ደግሞ የምንመለከተው በነዚህ ሁለቱ ሰዎች ነው፡፡ ጢጦስ ሀገርን ያሰለቸ፣ ይሄ ቀረው የማይባልለት ሽፍታ፣ ሰዎን ሁሉ ያስቸገረ የመጨረሻ ወንበዴ ሲሆን ቴክላ ደግሞ ከባዕለፀጋ ቤተሰብ የተገኘች ይሄን አጣሁ የማትል፣ በድሎት ያደገች፣ በተመረጠ ት/ቤት የተማረች፣ ምንም የማይወጣላት መልከ መልካም የነበረች ናት፡፡ በዕድሜም ካየን ጢጦስ በዘመነ ሥጋዌ/ክርስቶስ/ የነበረ ሲሆን ቴክላ ደግሞ በዘመነ ሐዋሪያት የነበረች ናት፡፡ እናም እነዚህን ሁለቱን ያገናኘሁበትን ምክንያት ስነግራችሁ ጢጦስ ለሦስት ሰዓት ያህል ከክርስቶስ ጋራ ቆይቶ ለድኅነት ያበቃውን ሃይማኖት ያገኘ ሲሆን ቴክላ ደግሞ ሐዋሪያው ቅዱስ ጰውሎስ ሲያስተምር በመስኮት ተምራ ከአንስት ሰማዕታት ሊቀ ሰማዕታት ለመባል የበቃች ናት፡፡ እስቲ ታርካቸውን ቀንጨብ አድርጌ ላስቃኛችሁ፡፡ ጢጦስ ከይሁዳ እስከ ሰማሪያ ከገሊላ እስከ ቂሳሪያ የታወቀ ሽፍታ ሲሆን ዳክሪስ የተባለ የራሱ ቢጤ ጓደኛ ነበረው በትውልድ ከቤተ እስራኤል የነበረና በእድሜ ከክርስቶስ ልደት ቀደም ብሎ የነበረና ክርስቶስ ተወልዶ በሄሮድስ ምክንያት ወደ ግብጽ ሲሰደድ በሽፍትነት ሕይወት ውስጥ የነበረ መሆኑን የወንጌላት ትርጓሜና ተዓምረ ኢየሱስ በሚነግሩን መረዳት እንችላለን፡፡ በነዚህ መጽሐፍት እንደተጻፈልን እመቤታቸን፣ ዮሴፍና ሰሎሜ ጌታችንን ይዘው ከገሊላ ተነስተው ወደ ግብጽ ሲሰደዱ ከአንድ በረሃ/ጫካ/ ሲደርሱ እነዚህ ሁለቱ ሽፍቶች ለስድስት ቀናት ያህል ሲፈልጓቸው ከርመው በሰባተኛው ቀን አግኝቷቸው ያላቸውን ልብስና ጫማ ቀምቷቸው ከሄዱ በኋላ በጢጦስ አሳሳቢነት የዘረፏቸውን ንብረት መልሶላቸዋል፡፡ ንብረት መመለሱ ብቻ ሳይሆን ጢጦስ ጌታችንን በትክሻው ተሸክሞት መንገድ እንደሸኘው፣ በመንገድም ሲሄድ ሰይፉ ተሰብሮበት ወደነበረበት እንደመለሰለትና ጢጦስም ይሄንን ተዓምር አይቶ ከነቢያት አንዱ ይሆናል ቢሎ እንደተገረመ ይነገርለታል፡፡ ይሄ ብቻ ሳይሆን ስለማሪያም እንተእፍረት/ባለሽቶዋ ማሪያም/ አንድ መምህር  በጌታችን እግር ላይ ያፈሰሰችው ባለ 300 ዲናር አልባስጥሮስ የተባለ ውዱ ሽቶ ከየትመጣነት ሲናገር ጢጦስ ክርስቶስን ተሸክሞት መንገድ ሸኝቶት ከተመለሰ በኋላ ክርስቶስን ተሸክሞበት የነበረ ትከሻ መዓዛው ቢያውደው ያንን ላቦት ጨምቆ በቢልቃት አኑሮት እንደነበረና በቤተመንግሥት ውስጥ ብቻ የሚገኝ የነበረና ኋላ ለክርስቶስ ለራሱ የቀረበ እንደሆነ ሰምቼው ነበር፡፡ በሉቃስ 23፣42 ላይ ‹‹ዛሬ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ›› የተባለው ቃልም የተገኘው በዚህን ጊዜ የተሰጠው ቃልኪዳን እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ቴክላ ደግሞ በተናሷ እሲያ ኒቆምዲያ በሚትባል ከተማ ከአህዛብ ወገን ተወልዳ ያደገች ሲትሆን በውበት፣ በዝና፣ በሃብት ይሄ ቀረሽ የማትባልና በሁሉም ዘንድ ተወዳጅና ተፈላጊ ወጣት ነበረች፡፡ በከተማው አለ ለሚባል ሰውም ለጋብቻ ተሰጥታ ነበር፡፡ ነገር ግን የቴክላን ሕይወት የቀየረው አንድ ነገር ተፈጠረ ይሄውም ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ በ45 ዓ.ም የመጀመሪያውን ጉዞ ወደ ታናሷ ኢሲያ ባደረገ ጊዜ ኢቆንያ ውስጥ ስፋሮስ በተባለ ቤት ሲያስተምር ቴክላ በወላጆችዋ ቤት ውስጥ ሆና በመስኮት በኩል ተደብቃ የሐዋሪያውን ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ትማር ነበር፡፡ በዚህ በመስኮት ትምህርት ተለውጣ ለጋብቻ የገባችውን ቃል አፍርሳ በድንግልና ለመኖር በመወሰን ሐዋሪያ ቅዱስ ጳውሎስን ተከተለች ይሄን በማድረጓ ከወላጅ እናቷ ሳይቀር ለሌሎች ሴቶች መቀጣጫ እንዲትሆን በቁሟ እንዲትቃጠል ተደርጋለች ግን እግዚአብሔር ከሰማይ ዶፍ አዝንቦ አትርፏታል፡፡ ራቁቷን ለአናብስት ቢትሰጥ ከሰማይ እሳት ከበባት፣ በግንጥና በእባብ ጉድጓድ ቢትጣል እግዚአብሔር በተዓምር አወጣት፣ በሶሪያ ሳለች ወንጌልን በመስበኳ ሕሙማንን በመፈወሷ ሰዎች ሊገሏት ቢያሳድዷት ተራራ ለሁለት ተከፍሎ አሻግሯታል (ያ ቦታ እስካሁን የቅድስት ቴክላ መሿለኪያ  ተብሎ አለ) ብዙ ገቢረ ተዓምራት በማድረጓም የሕሙማን እናት እየተባለችም ትጠራለችና ገነ በመጀመሪያዎቹ የሐዋሪያት ዘመን ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ በማጨት ስለመንግሥተ ሰማያት ስትል በቅንዓተ ክርስትና ከሀገር ወደ ሀገር እየተሰደደች በደረሰችበት ወንጌል እየሰበከች ብዙ ክርስቲያንን ማፍራት ችላለች ብዙ ተጋድሎንም አድርጋለች፡፡ በቤተክርስቲያናችን በመጽሐፈ ስንኪሳር ሃምሌ 25 ትታሰባለች፡፡ እናም ለዚህ ሁሉ ክብር ያበቃት ምንድነው ብዬ ብጠይቅ መልሱ በመስኮት የተማረችው የሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ነው፡፡ ይሄንኑ ጥያቄ ደግሞ ራሴን ስጠይቅ ለስንት ዘመን በመስኮት ያይደለ በበር በኩል ገብቼ፣ በተደላደለ ወንበር ተቀምጬ የቅዱስ ጳውሎስን ትምህረት ብቻ ያይደለ የራሱ የባለቤቱን የክርስቶስን ትምህርት በማቴዎስን ወንጌል፣ በዮሐንስን ወንጌል፣ … እያልኩ ተማርኩ.. ግን የትስደረስኩ? ስል የትም ያልደረስኩ፣ እንደ ወንበዴው ጢጦስ በመቅደሱ ቆሜ ‹‹አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ›› ለማለት እንኳ ያልበቃሁ፤ ጭራሹኑ በመቅደሱ ሞቼ ቀስቃሽ የሚፈልግ ሆኜ ራሴን አገኘሁ፡፡ ይሄንኑ ጥያቄ ይሄንን ለምታነበው ለንተ/ላንቺ ላቅርብ፡፡ ጢጦስ ሽፍታ ነበር የዳዊትን መዝሙር አለነበበም፣ የኢሳይያስን ትንቢት አልሰማም ፣ የነቢያት ትንቢት አልደረሰውም ነገር ግን ለሦስት ሰዓት ያህል ብቻ ከክርስቶስ ጋር ቆይቶ ከአዳም ቀድሞ ገነት የምታስገባውን ሃይማኖት ያዘ፤ አንተስ ስንት ዘመን ከክርስቶስ ጋር ቆየህ? ክርስቶስን መቼ አግኝቼው እንዳትለኝ ከፍያታዊ ዘየማን ጎን በመስቀል የነበረ ክርስቶስ ዛሬም በየቀኑ በቤተመቅደስ ከአጠገብህ አለ አታስተውለው ይሆናል እንጂ አንተም በየቀኑ እንደሱ ‹‹ተዘከረነ እግዝኦ..›› እያልክ በየቀኑ ትጮሃለክ .. እሱስ አምላክነቱ ቢገባው አምኖ ጮሀ…. አንተ ግን በእውነት ገብቶህና አምነህ ነው የምትጮሀው ወይስ እንደኔ የልማድ ሆኖብህ ነው? ይሀው እኔ ስንት ዘመን ጮኩ ግን የልማድ እንጂ በምግባር የተገለጠ ስላልሆነ ወደ ውጪ እንጂ ወደ ውስጥ ያስገባሁት የለም::
እስቲ በአንድነት ሆነን ጢጦስን አንጠይቀው ጢጦስ ሆይ ከነቢያት ሳትሰማ፣ ከመጻሕፍት ሳትረዳ ይሄንን ታላቅ ሃይማኖት የያዝከው በዚያች ሦስት ሰዓት ውስጥ ክርስቶስን እንዴት ብትረዳው ነው? እኛ ይኸው ትንቢተ ነቢያትን እናውቃለን፣ ምሳሌ ኦሪትን እንረዳለን ሦስት ሰዓት ያይደለ ሀያና ሠላሳ ዓመት ቆይተናል በውስጣችን ያኖርነው ክርስቶስ ግን የለም? ምን ብናደርግ ያንተን ሃይማኖት እናገኝ ይሆን? እንበለው… እስቲ እያነበብሽ ከሆነ አንቺንም ልጠይቅሽ ስንት ዘመን በመስኮት ያይደለ በበር ገብተሽ፣ በተደላደለ ወንበር ተቀምጠሽ፣ ወንጌል በአትሮነስ ተዘርግቶ፣ መምህር ከፊትሽ ቆሞ፣ ቃሉን እያነበብሽው፣ በደብተርሽ እየጻፍሽው ተማርሽ? እና ለክርስቶስ ምንሽን ተውሽ? ውበትሽን ተውሽ?፣ ስልጠንሽን ተውሽ? ንብረትሽ ተውሽ? ዝናሽን ተውሽ? ኽረ እንዲሁም እነዚንስ ተይው ያሳሱ ይሆናል? ቀለል ላርግልሽና ውሸትሽን ተውሽ? ሀሜትሽን ተውሽ? ቅናትሽን ተውሽ? ማተለልሽን ተውሽ? ምንሽን ተውሽ?.... አስቲ አንቺም ቅድስት ቴክላን ጠይቂያት ‹‹ቅድስት ቴክላ ሆይ በሲፋሮስ  ቤት አልነበርሽም፣ የሐዋሪያውን ስብከት ሰማሽ እንጂ ሐዋሪያውን ከዚያ በፊት አላየሽውም፣ ቃሉ ሲነበብ ሰማሽ እንጂ አንቺ አለነበብሽውም፣ በጆሮሽ ሰማሽ እንጂ በደብተር አልጻፍሽውም… ጆሮዎችሽ እንዴት የተባረኩ ቢሆኑ ነው ይሄንን ሕያው ቃል ያደመጡ? ልቦናሽ እንዴት ያለ ንዑድ ክቡር ቢሆን ነው ይሄንን ሁሉ ጥለሽ ክርስቶስን ያዥ ያለሽ? ብለሽ ጠይቂያት፡፡ ሲጠቀልለው አንተ/አንቺ/እኔ እንደ ጢጦስ ሽፍታም ብንሆን እንደ ቴክላም ባዕለፀጋም ብንሆን፣ ቃሉን በመስኮትም ተማርን በበር፣ ከክርስቶስ ጋር ሦስት ሰዓትም ቆየን ሠላሳ ዓመት ክርስቶስ ያው ክርስቶስ ነውና ከግብራችን ተመልሰን በክርስቶስ ሕይወት እንኑር! የቅድስ ቴክላ በረከቷ ይደርብን፡፡

ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ
መጋቢት 08/2016 ዓ.ም
ማታ 5፡25

https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
Forwarded from አምደ ተዋህዶ ሚድያ (Te^i|a..Mrsa)
አምደ ተዋህዶ ሰ/ት/ቤት

መንፈሳዊ ጉዞ

መዳረሻ ፡ ምሁር ኢየሱስ ገዳም
የጉዞ ቀን ፡ 28/7/2016 ዓ.ም
የጉዞ ሰዓት ፡ 12:00 am
መነሻ ቦታዎች ፡
1.አለም ባንክ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል
የጉዞ አይነት ፡ አዳር
ክፍያ ፡ 1000.00

ለመመዝገብ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ
http://hawir.abruthtech.com/trip/128
ንዑስ ገጣሚያን🥱
Photo
አብረን እንህድ
ለምወዳቸው የነፍሰ አባቴ ለሥጋ አባታቸው እረፍት ማስታወሻ የቀረበ
Forwarded from ዮቶር ዘራማ
ወይ እኔ.😭

ንግሥናው ክህነቱ
ዘውዱ ታቦቱ
ሆኖለት ቢያየው
ማመን ቢቸግረው
እንዲህ ብሎ ነበር አንዱ ባለ ቅኔ
ወዴት ሂዶ ኖሯል ሰሞነኛው ቄሱ
ታቦት ተሸከመ ዘውዱን ጥሎ ኢያሱ
እስቲ እኔም ልዋሰው ልሁን ባለቅኔ
ወዴት ሂዶ ነበር ከሰሞኑ ኢያሱ
መልአከ ሞት ደፍሮ ከደጁ መድረሱ
ወዴት ሂዶ ነበር ከሰሞኑ ኢያሱ
ነጠላ ዘቅዝቀው እንዲህ መለቀሱ
በያያው ነው እንጂ ኢያሱ ካህኑ
ባይነቃበት እንጂ ዮሐንስ ካህኑ
ሞት የሞተበትን መስቀል ተሸክሞ ስለሚዞር በእጁ
ይገትረው ነበር ያንን መልኣከ ሞት እንዳይደርስ ከደጁ
ይህ እንዴት ይሆናል
ቢፈቅድለት እንጂ
እለፍ ቢለው እንጂ
እንዴት ደፍሮ ይቆማል እርሱ በቆመበት
እንዴት ደፍሮ ያልፋል እርሱ ከዘጋበት
እንደው እኔ ስመስለኝ
እኛ አልገባ ብሎን አለቀስን እንጂ
ነጠላ ዘቅዝቀው ተለበሰ እንጂ
ይህ ለቅሶ አይደለም
እንደው ስላልበቃን ተስኖን ነው እንጂ ማየት ከጸዳሉ
ያኔ እኮ የመጣ መልአከ ሞት ሳይሆን
     ከዓቢያን ሊቃናት አንዳቸው ይሆናሉ
እኔ ግን ስመስለኝ ገብርኤል ይሆናል ተጠርቶ በኢያሱ
መስዋእትን ሲያቀርብ ሊያሳርግ ሲመጣ በሹመት መቅደሱ
አዎ...
አሁንም እላለሁ ይህ ለቅሶ አይደለም የንጉሥ ድግስ ነው
አሁንም እላለሁ ይህ ሀዘን አይደለም የንጉሥ ጥሪ ነው
በቃል አስተምህሮ መች ያበቃልና
በተግባር ማሳየት መምህሩ ኢያሱ ልማዱ ነውና
የእስከ ዛሬን ወንጌል አንዲምታ ትርጉሙን ሊያሳየን ጠርቶን ነው
ምን አይነት ካህን ነው ምን አይነት መምህር
በአባቱ ቀብር ላይ ልጁን የሚያስተምር
አዎ....
አፈር አይማርም
አፈር አይሰማም ቢነግሩትም ያው ነው
አፈር አይፆምም
አፈር እምቢ አያውቅም ቢሰጡት መብላት ነው
አፈር ቃል የለውም
አፈር ነፍስ የለውም ቢያወሩት ዝም ነው
እንግዲህ አንተ ተማር የቆምከው ወንድሜ
ከዚህች ቀን አታልፍም የደለህ ቢመስልህ ሲትኖር ረዥም እድሜ
መማር የሞት ቀን ማልቀስ ወይ እኔ ብሎ
ማሰብ የሞት ቀን ነው ነፍስን ነጻ ማውጣት ስጋን መሬት ጥሎ
መማር በዚህ ቀን ነው ዓለምና አምሮቷን በፆም አጎሳቅሎ
በል ተማር ወንድሜ ወንጌል ከአንአንዲምታው ፊትህ ተዘርግቷል
እንዴት እንደሚኖር፣ እንዴት እንደሚሞት ዛሬ እዚህ ታይቷል
ሀብት ንብረት ጠፊ፣ ውበት ደም ግባቱ፣ ዓለሙም ከንቱ ነው
ትልቁ ብልሃት በሚፈርስ ቤት ሆኖ የማይፈርሰውን ቤት በሰማይ መሥራት ነው
ወዳጄ....
እስቲ ልጠይቅህ
ይሄን ቤት ያንኳኳ የሞት ያልነው መልአክ
ዛሬ በዚህ ሰዓት ወደ አንተ ቤት ቢላክ
ምንድ ነው ያንተ መልስ?
መልአኩ ይመለስ?
ወይ አንተ ትቀደስ?
ትሩፋት ቋጥረሃል?
ሃይማኖት ይዘሃል?
እንደ ወልደ ሩፋኤል በሰማዩ መቅደስ
ሌላ ቤት ሠርተሃል?
ወይስ...
ልክ እንደ ትናንቱ
ጎረቤትህ ሲሞት ወይ እኔ ብለህ ቀብረህ
ወንድምህ ሲወሰድ ደረት ደቀህ ቀብረህ
አንተ ጋ እስኪመጣ በፈረሰ ጎጆ ልትኖር አስብሃል።
አዎ..
እንባ ሞት አይመልስ
ዋ በል ለንተ አልቅስ
እሞታለሁ ሳይሆን እኖራለሁ ብለህ ነፍስህን አታርክስ

ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን
አሜን!!!   

           ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ(ወልደ ኢየሱስ)
           11/08/2016 ዓ.ም
            ምሽት 04:50

https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
ጠረጠርኩህ😭

ባይዝልም ያንተ ትከሻ
ባያሻውም እጅ መንሻ
ጌታዬ ሆይ አደከምኩህ
ጌታዬ ሆይ አሳዘንኩህ
ጌታዬ ሆይ ጠረጠርኩህ
ቢታወር እንጂ አይን
እንዴት ይረሳል ያ ዘመን
በእኔ ጉልበት በእኔ ኃይል
መች ወጥቼ ከዚያች ገደል
በእግሮችህ እየመራህ
ቃል አውጥተህ እየጠራህ
በክንዶችህ ደግፈህ
በትከሻህ ተሸክመህ
ከጭለማ ያወጣህኝ
በዕለ ማዕረግ ያደረከኝ
አንተ መሆንክን እያወኩ
ጠረጠርኩህ
የኔን መስቀል ከኔ አውርጄ
ዳግም አንተን አሸከምኩህ
ጌታዬ ሆይ
ትናንትና
ብዙ ወጥወድ ነበሩብኝ
አንተ ሰብረህ ያሻገርከኝ
ትናንትና
ብዙ ዳገት ነበሩብኝ
አንተ ገፍተህ ያወጣህኝ
ትናንትና
ብዙ ሰልፎች ነበሩብኝ
አንተ ድል ያደረክልኝ
ትናንትና
ብዙ ውድቀት ነበረብኝ
አንተ በእጅህ ከፍ ያረከኝ
ትናንትና
ብዙ ቁስል ነበረብኝ
በደምህ የጠረክልኝ
ትናንትና
ብዙ ደዌ ነበረብኝ
ሥጋህን ሰጥተህ የፈወስከኝ
ዛሬ ግና
ትንሽ ቁስል ብታገኘኝ
ትንሽ ደዌ ብትጎበኘኝ
የትናንቱን ሁሉ ረስቼ
ጠጋኝ ክንድህን ከድቼ
አያወጣኝም ብዬ
በቃ ረስቶኛል ብዬ
በኔ አይን አንተን ስዬ
እምነቴን ከልቤ ጥዬ
ጠረጠርኩህ
ያለ እምነት መረመርኩህ
ጌታዬ ሆይ
ይቅር ትለኛለህ አይደል?
አትተወኝም አይደል?
አዎ... አውቃለሁ
አንተ ክንድህ አይዝልም
ትከሻህም ሰው አይጥልም
ቢረሱህም አንተ አትረሳም
ዳግም ልትጥል አተነሳም
እና አባቴ...
ወደ ኋላ አትመልሰኝ
ወደ ፊት ብቻ አራምደኝ
ጀርባ ጀርባህን እያየሁ
ድምጽህን ብቻ እየሰማሁ
ከእግርህ ዱካ እየረገጥኩ
እጆችህን እየመረኮዝኩ
ልከተልህ
ልጠለልህ
ልታመንህ
ልደገፍህ
እርዳኝ
አጽናኝ
ያለፈውን አትይብኝ
ከሚመጣውም ጠብቀኝ
እኔ ያልኩትን ሳይሆን አንተ ያልከውን ስጠኝ🙏

            ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ
            ሚያዚያ 16/2016 ዓ.ም
            ጠዋት 2:00

https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
ተመስገን🙏

መልክና ውበት ባይኖረኝ
በሰው ፊት ሞገስ ባላገኝ
ጌታዬ ሆይ መልኬ አንተ ነህ
ያቆነጀኝ ወርቀ ደምህ
ጎተራዬ ባዶ ሆኖ ከኪስ ገንዘብ ባይኖረኝም
ቁራሽ እንጀራ አጥቼ አንድም ቀን ርቦኝ አያውቅም
በሰዎች ዘንድ የተዋበ ማጌጫ ልብስ ባይኖረኝም
ለእርቃኔ ሽፋን አጥቼ አንድም ቀን በርዶኝ አያውቅም
በቪላ የተገነባ ቅንጡ ቤት ባይኖረኝም
ማደሪያ ጎጆ አጥቼ በረንዳ አድሬ አላውቅም
ጌታዬ አንተ መልኬ ነህ በአንተ ውበት እደምቃለሁ
ጌታዬ አንተ ልብሴ ነህ በላቦትህ እሞቃለሁ
ጌታዬ አንተ መብሌ ነህ በአንተ ሥጋ እጠግባለሁ
ጌታዬ አንተ ቤቴ ነህ በማደሪያህ እኖራለሁ
ጌታዬ ሆይ
እንዲህ ሆነህ እያኖርከኝ ከንተ ወዴት እሄዳለሁ
በደጀፍህ ተንበርክኬ "ተመስገን" እለሃለሁ

ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ
ሚያዚያ 18/2016
ጠዋት 2:00

https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
ይቺን ያዟት!
Forwarded from አንቀጸ ብርሃን
❤️❤️❤️❤️❤️በነጻ የሚያክም ባለመድኃኒት❤️❤️❤️❤️❤️
ራሴን ፈለጠኝ፣ ሆዴን ቆረጠኝ ብለህ በሥጋ ታመህ ታውቃለህ? ታመህ ካወቅህ ምን ተጠቅመህ ዳንህ? ቅጠል ጨፍጭፈህ ፣ ቅመማትን ቀምመህ ወይስ ሆስፒታል ከባለ መድኃኒት ቤት ህደህ? ከሆነስ ለካርድ ስንት  ከፈልክ? ለላብራቶሪስ? ለመድኃኒትስ…. ስንት ከፈልክ? ክፍያውስ ይሁን ከዚያ በኋላ ግን ዳንኅ? ወይስ ተሻለህ? መቼም መሻልና መዳን እንደሚለያዩ አይጠፋህም፡፡

በመድኃኒት ቤት የሚሸጡ መድኃኒቶች ብዙ ጊዜ የሚያሽሉ እንጂ የሚያድኅኑ እንዳልሆኑ ራሳቸው ባለመድኃኒቶች ፈራጅ ናቸው፡፡ ሰው ሥጋ ለባሽ ተንቀሳቃሽ  በመሆኑ በሥጋ ሲታመም ለማደን ባለመድኃኒት መሻቱ፣ ብዙ ዋጋ መክፈሉ ያለ ነው፡፡ እኔ ግን ዛሬ ላነሳ የፈለኩት በሥጋ ታመን ለሚያሽለን መድኃኒት ይሄን ያህል ዋጋ ካወጣን ከሆስፒታል ሆስፒታል፣ ከጠበል ጠበል ከተመላለስን በነፍሳችን ስንታመም በነጻ ወደሚያክመው ባለመድኃኒት መሄድ ለምን እንፈራለን?፡፡ የነፍስ ህመም እንደ ሥጋ ህመም የራስ መፍለጥ፣ የሆድ መቁረጥ ምልክት ስለሌለው ነው ወይስ ባለመድኃኒቱ ስለሚያስፈራ? ወንድሜ በዝሙት ታመሃል? በስርቆት ታመሃል? በውሸት፣ በሃሜት፣ በትምኪት፣ በትብዒት ታመሃል? ታመህ ከሆነ በእርግጠኝነት ይህ ባለመዳኃኒት ያስፈልግሃል።

ይሄንን ባለ መድኃኒት ግን ታውቀዋለህ? ማነው እሱ? አድራሻውስ የት ነው? ትሉኝ ከሆነ ልንገራችሁ.. የተወለደው በቤተልሔም ከአንዲት ንጽሂት ቅድስት ድንግል ነው፣ ስሙ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ይባላል፣ ለዓለም ሁሉ ብሎ የመጣ ያመነበት ሁሉ ሕይወትን የሚያገኝበት፣ የተጠማው የሚረካበት ምንጭ፣ የተራበው የሚጠግቢበት እንጀራ ነው፡፡ለሚፈልገው የትም የሚገኝ ወሰን የሌለው፣ መዳኃኒቱ የማያልቅበት ሁልጊዜ የሚኖር፣ ዘር ወገን ሳይለይ የሚያክም ፍትሃዊ ባለ መድኃኒት ነው፡፡ አወቃችሁት? የመጽሐፍ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል የሚሰጠውም መድኃኒት ቅጠል በጢሶ ስር ሚሶ ሳይሆን የራሱን ሥጋና ደም ነው፤ የሚዘጋጀውም በቤተመቅደስ ነው እዚያ የሄደ ሁሉ ያገኘዋል፤ ይህ ሥጋውና ደሙ በምንም ዋጋ የማይሸጥ በነጻ የሚታደል ነው ስትቀበለው በመድኃኒት ቤት እንደምትገዘው የሥጋ መድኃኒት የሚያድን ያይደለ የሚያሻል ሳይሆን ከልጅነት እስከ እውቀት ከታመምከው የኃጢአት በሽታ የሚያድን ነው፡፡

ያልኩህ ግን ገብቶሃል? ከገባህ ምን ትጠብቃለህ በዚህ መድኃኒት በነጻ እንዳትታከም የሚከለክልህ ምንድ ነው? ልማድ ነው? እጅህ ከመስረቅ፣ እግርህ ለክፋት ከመሮጥ፣ አይንህ አይቶ ከመዘሞት፣ ጆሮህ ሀሜት ከመስማት፣ አንደበትህ ከመሳደብ አልመለስ አለህ? ወይስ ይህ መድኃኒት የህጻናትና የሽማግሌ ነው የሚል የሰዎች ወሬ? እንግዲህ ልንገርህ ልማድ ካስቸገረህ መድኃኒቱ ራሱ መድኃኒቱ ነው ካንተ የሚጠበቀው በልማድህ በወደቅክ ቁጥር ለንስሃ አባትህ መናዘዝ ነው፤ የሰዎች ወሬ ከሆነ ደግሞ ባለ መድኃኒት የማያሻው ታማሚ የለም በላቸው፡፡

እናም ውድ ወንድሜ እንዳትሞኝ ከዚህ ባለመድኃኒት ቤት ሳትደርስ መልኣከ ሞት እንዳይቀድምህ ተጠንቀቅ! እንዳይረፍድብህ! ዝባ ዝንኬ ሳታበዛ ራስህን ለካህን አሳይና ወደዚህ ባለመድኃኒት ህደህ በነጻ ታከም ይሻልሃል ሳይሆን ትድኅናለህ እሱ በደልን የማይቆጥር ይቅር ባይ የማይበቀል የዋህ ነው፡፡ በል ወደ ባለ መድኃኒቱ ጉዞ ጀምር…… በርታ…. አንተ ብቻ ጉዞ ጀምር እርሱ ያግዘሃል… ለመድኃኒቱ ያብቃህ

                  ታካሚው ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ
                  ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም
ምሽት 1:00                                                                                                                                   https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
አፍቃሪ ፍቅር ነው

ከእውቀት ባህር ጨልፈን
ከልብ አፍላግ ቀድተን
በየአውዱ ብንናገር
ለአዝማናት ብንመሠክር
ቅንጣት እንኳ አንደርስበት
ሽራፊውን አንኖርበት
ጌታችን ሆይ ያንተን ፍቅር

በስቅለትህ እኛ ተረፍን ከመቸንከር
አንተ ስትሞት እኛ ወጣን ከመቃብር
በትንሳኤህ ነጩን ለብሰን ተመላለስን
ከንተ ጋራም እንኖራለን እየዘመርን
አፍቃሪ ሆይ ክበርልን
ብርሃንህን አትውሰድብን🙏

ኦባብ ወልደዮቶር ነኝ
ሚያዚያ 27/2016 ዓ.ም
ቀን 08:30

ውድ የንዑስ ገጣሚያን ቤተሰቦች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ። በትንሳኤው ብርሃን ያመላልሰን🙏🙏🙏

ያጋሩት👆

https://www.tg-me.com/+emQOdn8jgZVlNDM0
ንዑስ ገጣሚያን🥱
https://youtu.be/XjzKwWNKM-g?si=zGHYd6Uz6PmRgzqg
በጣም ደስ የሚል ነፍስን የሚያርስ መዝሙር ዛሬ ደግሞ ሰማዕትነትን የተቀበለበት ቀን ነው።
ተወለድኪ

ተወለድኪ ተወለድኪ
እም እያቄም እም አቡኪ
ተወለድኪ ተወለድኪ
እም ሀና እም እምኪ
ዘበ ህግ አላ በሩካቤ
እያልኩ ልዘምር በፊትሽ ቀርቤ
ጽድቅሽን ተርቤ
በፍቅርሽ ተስቤ
አንቺ ነሽ ገንዘቤ
አንቺ ነሽ ምግቤ
እመ አምላክ ርግቤ
ተወለድኪ እያልኩ በፍቅር ላዜምሽ በፊትሽ ቀርቤ
ተወልድኪ ልበል
አንቺ ያዳም ጠበል
ተወለድኪ እያልኩ ከደጅሽ ልጠለል
በእቅፍሽ ልከለል
በጣቶችሽ ልሳል
ይንካኝ ያንቺ ጸዳል
አንቺ ያዳም ጠበል
የሰማዕታት አክሊል
ተወለድኪ እያልኩ ልምጣ ከሊባኖስ
ማህደረ ሥሉስ
ልምጣ ከልባኖስ
ከአድስቷ መቅደስ
ሀናን ልጠይቃት በእያቄም ልባረክ
ሰላምለኪ እያልኩ በፊትሽ ልንበርከክ
ልንበርከክ በፊትሽ
ከአቅፏ አይቼሽ
እኔ....
ኃጢአት ያሳወረኝ
እውር ስለሆንኩኝ
በእጆችሽ ዳሽኝ
ከቁስሌ ፈውሺኝ
.......
ግና እመቤቴ
ትውልዱ
በስምሽ ሲሄዱ
እንኳን ማርያም ማረችሽ
ማርያም በሽልሙ ታውጣሽ
እያሉ
ይመራረቃሉ።
ዛሬ...
በልደትሽ እለት
ሀናን ስንጠይቃት
በምን እንመርቃት?
        
              ኦባብ ወልደ ዮቶር ነኝ
              ግንቦት 01/2015 ዓ.ም
              ቀን 11:42

እነሆ በዚህ Link ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/DbhH12

ውድ ቤተሰቦቼ እንኳን ለወላዲተ አምላክ ልደት በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏🙏
2024/05/16 06:31:59
Back to Top
HTML Embed Code: