Telegram Web Link
ምርጥ ተውበት!

የታላቁ ዓሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ...

ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ እናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ እያለ መጠጡን ገፍታ ደፋችባቸው የዛኔ ይህ አላህ በፋጢማ ተው እያለኝ ነው ብለው አሰቡ፣ ከአመት በኃላም ፋጢማ 3አመት ሞላት ከዛም ፋጢማ ሞተች። ከዛም ድጋሚ እንደበፊቱ መጠጣት መስከር ጀመሩ፣ ታዲያ አንድ ቀን ሸይጧን ወሰወሰኝ አሉ ዛሬ ሰክረኸው የማታውቀውን ስካር ነው የምትሰክረው አለኝ እሺ ብዬ መጠጥ መጠጣት ጀመርኩ በጣም ሰክሬ ወደቅኩ አሉ። ከዚያም በህልሜ ቂያማ የቆመ መሰለኝ ፀሀይቱ ጠቁራለች፣ ሰወ ሁሉ አላህ ፊት ተሰብስቧል፣ ባህሩ ይነዳል የሰው ሁላ ስም ሲጠራ ቆየና ማሊክ ኢብኑ ዲናር ና ለሂሳብ ትፈለጋለህ ተባልኩ ከዛም ትልቅ ዘንዶ ማሳደድ ጀመረኝ እሱን ለመሸሽ ስሮጥ አንድ ሽማግሌ አገኘሁ አግዘኝም አልኩት እኔ አቅሜ ደካማ ነው አለኝ ስሮጥ የእሳት ጫፍ ላይ ደረስኩ፣ ዘንዶውን ፈርቼማ እሳት አልገባም ብዬ ተመልሼ ሮጥኩ ድጋሚም ሽማግሌውን አገኘሁ አግዘኝም አልኩት አቅሜ ደካማ ነው እስቲ የምትድን ከሆነ ወደዛ ተራራ ሩጥ አሉኝ። ከዚህም እየሮጥኩ እያለ ከተራራው ላይ ህፃኖች ፋጢማ አባትሽን ዘንዶ ሊበላው ነው ሲሉ ሰማሁ። ለካ በ3 አመቷ የሞተች ልጅ አለችኝ ብዬ ወደ ፋጢማ ሮጥኩ ፋጢማም ዘንዶውን ገፍታ ጣለችው። እኔም ልጄ ሆይ እስቲ ያ ዘንዶ ምንድነው የሚያባረኝ አልኳት እሷም ያ መጥፎ ስራህ ነው አለችኝ እሺ ያ ሽማግሌውስ ያ ጥሩ ስራህ ነው አለችኝ ጥሩ ስራህ ደካማ ሰለሆነ ከመጥፎ ስራህ ሊያስጥልህ አልቻለም አለችኝ። ከዛም 1 የቁርአን አያ ቀራችልኝ።

"እነዛ ምዕመናን ልባቸው ለአላህ ግሳፄ የሚፈራበት ግዜ አልደረሰምን?" የሚለውን አነበበችልኝ። ልክ አኔም ከእንቅልፌ አዎ ግዜው ደርሷል አያልኩ እያለቀስኩ ተነሳሁ ሻወር ወሰድኩ ሱብሂ ወደ መስጂድም ሄድኩ። መስጂድም ኢማሙ ይህንኑ አያ እየቀሩት ነበር አልቅሼ ተመለስኩ ይሉናል ታላቁ ኢማም።

እኝህ ሰው ህዝቡን የሚያስተምሩ ታላቅ ኢማም ሆኑ። ሁሌም መስጂድ አንተ አላህን ያመፅክ ባሪያ ሆይ ወደ ጌታህ ተመለስ ይሉ ነበር።

ጌታችን ሆይ ምህረትህን ለግስን 🤲
👍3
ISLAMIC-QUOTES pinned «ምርጥ ተውበት! የታላቁ ዓሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ... ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ እናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ…»
ከሚግባቡት ከአብሮ አደግ ከቅርብ ሰው ተገናኝቶ እንደመጫወት የልብን እንደማውራት  የሚያስደስት ነገር የለም ሲጀመር ሰዐቱ ራሱ ይፈጥናል አላህ ይጠብቅልኝ ሙሽራዬ ...
👍2
«ከትዕግስት ጋር (የአሏህ) እርዳታ አለ፣ከጭንቅ ጋር ፈረጃ አለ፣ ከችግር ጋር ምቾት አለ።» ውዱ ነቢይ ﷺ
[ ሶሒሑል - ጃሚዕ : 6806 ]
👍5
ማታ ላይ ከመተኛቷ በፊት ስትኳኳል አይተዋት
"ምንድነው በእንቅልፍ ሰዓት እንዲህ የምትቀባቢው?" አሏት።
"አስከሬን እያበጃጀሁ፤ ለገናዦቼ ስራ እያቃለልኩ ነው " አለች አሉ አንዷ እብድ።

አስክሬን ነንና ዉዱዕ አድርገን፣ በልቦናም ንፁህ ሆነን፣ አዝካሮችን አድርገን፣ የምድር ላይ የመጨረሻ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ!!
👍7
"ሁሉም ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት"
[አል-ዒምራን 3:185]

አላህ ኻቲማችንን ያሳምርልን🤲
በአላህን ተስፋ አትቁርጡ ዕለቱን በአላህ ላይ ጥሩ የቂን ኖሮአቹሁ ጀምሩ።"
اللهم بارك لنا في هذا الصباح ووفقنا لكل خير...🌸
ሰባህል ኸይር
@DinisNesiha
በነገራችሁ ላይ እንደዚህ ያሉ ዲኮሮችን ብታዙኝ  ባመረ መልኩ ሰርቼ አስደስታችኋለሁ በተመጣጣኝ ዋጋ ፕሮግራማችሁን ፏ....👌 ማረግ የምትፈልጉ ..አለሁላችሁ Dm
     @H952503
👍2
ከመተኛታችን በፊት የመጨረሻዋ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ ....🙌
«اللَّهُمَّ أسْلَمْتُ نَفْسِي إِلَيْكَ، وَفَوَّضْتُ أَمْرِي إِلَيْكَ، وَوَجَّهْتُ وَجْهِي إِلَيْكَ، وَأَلْجَأْتُ ظَهْرِي إِلَيْكَ، رَغْبَةً وَرَهْبَةً إِلَيْكَ، لَا مَلْجَأَ وَلَا مَنْجَا مِنْكَ إِلَّا إِلَيْكَ، آمَنْتُ بِكِتَابِكَ الَّذِي أَنْزَلْتَ وَبِنَبِيِّكَ الَّذِي أَرْسَلْتَ»
ፋራወች ሆይ የጀነት ናቹህ !

እናንተ ከሀራም ለመጠበቅ ምታደርጉት ጥረት እንደ ፋራ እያስቆጠራቹህ ያላችሁ ወጣቶች ..ሰርክላቹህ ዚናን እንደኖርማል እያየ እፍረትን እንደኋላ ቀርነት ስለቆጠረ ነውርን እንደእርድና ስላየ ራሳችሁን እንደ ጭምት አትዩ ።
በነሱ ምክኒያት የገነባችሁትን መርህ ያደጋችሁበትን እሴት አትቀይሩ ። እነሱ ስሜታቸውን ሲያተርፉ የአላህን ፍቅር ሰውተው ነው ። በምን ስሌት ነው የአላህን ፍቅር የሸጠ ሰው አራዳ ሊሆን ሚችለው?
👍3
Forwarded from Mohammedamin Kassaw
ዛሬያችን አምሮበት ከሆነ በረጅሙ የትላንት መንገድ ውስጥ ስለኛ ብዙ የሆኑ ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው ... በዛሬ ውስጥ እነርሱን ከሁሉም ማስቀደሙ ደግሞ የእኛ ትንሹ ሀላፊነት ይሆናል::

@MohammadamminKassaw
2025/10/25 10:00:40
Back to Top
HTML Embed Code: