🏆1
ፋራወች ሆይ የጀነት ናቹህ !
እናንተ ከሀራም ለመጠበቅ ምታደርጉት ጥረት እንደ ፋራ እያስቆጠራቹህ ያላችሁ ወጣቶች ..ሰርክላቹህ ዚናን እንደኖርማል እያየ እፍረትን እንደኋላ ቀርነት ስለቆጠረ ነውርን እንደእርድና ስላየ ራሳችሁን እንደ ጭምት አትዩ ።
በነሱ ምክኒያት የገነባችሁትን መርህ ያደጋችሁበትን እሴት አትቀይሩ ። እነሱ ስሜታቸውን ሲያተርፉ የአላህን ፍቅር ሰውተው ነው ። በምን ስሌት ነው የአላህን ፍቅር የሸጠ ሰው አራዳ ሊሆን ሚችለው?

👍4
Forwarded from Mohammedamin Kassaw
ዛሬያችን አምሮበት ከሆነ በረጅሙ የትላንት መንገድ ውስጥ ስለኛ ብዙ የሆኑ ብዙ ሰዎች ስላሉ ነው ... በዛሬ ውስጥ እነርሱን ከሁሉም ማስቀደሙ ደግሞ የእኛ ትንሹ ሀላፊነት ይሆናል::
@MohammadamminKassaw
@MohammadamminKassaw
.
አንዳንዴ ከዛ ሰው ጋር በጣም መላመዳችሁን ምታቁት ሲለያችሁ ነው ::
መለያየት ሳይመጣ በዙሪያችን ያሉ መልካም ሰዎችን ዋጋቸውን እንወቅ ...በተግባር እናሳያቸው 🙌

👍1
ሴት ልጆቻችሁን በተለይ ደግሞ ታዳጊዎቻችሁን ጠብቁ
ዛሬ የ17/18 አመት ሴት ልጅ ያለው ወዳጄ ለልጁ ስልኳን እንድቀይርላትና የምትፈልገውን ስልክ እንድሰጣት ነግሮኝ ብቻዋን ሱቄ መጥታ ነበር።ሁሉን ነገር ቀድሜ አዘጋጅቼላት ስለነበር ልክ እንደመጣች ፋይሏን እንዳዞርላት ጠየቀችኝ።
እኔም እሺ ብዬ ፋይሏን አዞርላት ጀመር፣ በመሀል
"ምን አሰብሽ?
"መልስሽን በቶሎ አሳውቂኝ"
የሚል መልእክት ሲገባ ተመለከትኩኝ። እኔም መልዕክት አለሽ ትፈልጊዋለሽ? አልኳት።
እሷም "አረ ቆይ አብዲ ይሄን ልጅ አላውቀውም፣ በጣም ብዙ ጊዜ በቴክስት በሳምንት ከ150,000 እስከ 200,000 ብር የሚያስገኝ ስራ ላስገባሽ እያለኝ ነው"አለችኝ።
ምን አይነት ስራ? የት ነው? ምን ብለሽ መለስሽለት? አልኳት
እሷም "ቤት ሁኜ መስራት አልችልም?" አልኩት አለችኝ። "ደግሞ እዚሁ አዲስ አበባ ነው፣ አሪፍ ነበር ቢሳካ አለች"
ምንም የምታውቀው የገባት ነገር የለም።
ደላላውም "ስራው እዚሁ አዲስ አበባ የምነግርሽ ቦታ መጥተሽ ቀኑን ሙሉ ሰውን ማዝናናት ነው ቀላል ስራ ነው ይላታል"
ወዲያውኑ ለአባቷ ደውዬ ሱቅ እንዲመጣ ነገርኩትና ሁሉን ነገር አስረዳሁት፣ አጋጣሚ ሁኖ እሷም ለአባቷ አልተናገረችም ነበር።
ያ ሰው ከተማ ውስጥ ሴት ህፃናትን የወር አበባ እንኳን በቅጡ ያላዩ በየትምህርት ቤቱ እያሰሰ እየደለለ ከቤት እያስወጣ ለእርድ የሚያቀርብ ነው።
ሴት ልጅ ያላችሁ በተለይ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከልጆቻችሁ ጋር ያላችሁን መስተጋብር የጠበቀ አድርጉት፣ ዘመኑ ሰው መሳይ ሰይጣኖች በየቦታው ተኮልኩለው ልጆቻችሁን ሊሰውላችሁ እየጠበቋችሁ ነውና።
© ዐብዲ
||
www.tg-me.com/MuradTadesse