የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በድሬዳዋ ትምህርት ቤቶች የግምገማና የውይይት መድረኮች ተካሄዱ
ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ስኬታማ ለማድረግና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የውይይት መድረኮችን አካሄዱ።
የመልካ ጀብዱ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም የትምህርት ቤት ማሻሻያ ዕቅድ ላይ ከመምህራንና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ሰፊ ግምገማ አድርጓል። በዚሁ መድረክ ላይ በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርትና አስተዳደር ሥራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራን የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
በተመሳሳይ የሀፈት ኢሳ ትምህርት ቤትም በትምህርት አሰጣጥ ሂደት የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ዘላቂ መፍትሄ ለማስቀመጥ ያለመ ውይይት ከተማሪ ወላጆች ጋር አካሂዷል። ውይይቱ ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ክትትል በማጠናከርና ከትምህርት ቤቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማሳደግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በመድረኮቹ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ የትምህርት ስራ ዋነኛ አላማ እውቀትና ክህሎትን ከማስታጠቅ ባለፈ በስነ ምግባር የታነጹ ዜጎችን መፍጠር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። "የትውልድ ግንባታ የሚሳካው አካዳሚያዊ ብቃትን ከመልካም ስነ ምግባር ጋር ማዋሃድ ስንችል ነው" ያሉት ኃላፊው ይህን ግብ ለማሳካት የመምህራን፣ የወላጆችና የማህበረሰቡ የተቀናጀ ርብርብ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

❤8
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት የግል ባለሀብቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ ገልጿል።
ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም -- ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ለ2018 የትምህርት ዘመን ከ13 ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 1,800 አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪ ልጆች ከ2.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገዙ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ተደራሽነቱን ለማስፋት የግል ባለሀብቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። “ይህ ድጋፍ የነገ ተስፋዎቻችን ያለምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የፈጠረ የልማት እርምጃ ነው” ብለው በትምህርት ጥራት ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ስላለው ልዩ ትርጉም አለው" ሲሉ አቶ ሱልጣን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም የናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ "ቋሚ አጋር" በመሆን ለትምህርት ልማት እያበረከተ ላለው አስተዋጽዖ በአስተዳደሩ ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
የናሽናል ሲሚንት አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሊዮ ጄሼንግ በበኩላቸው እንደተናገሩት በባለፈው አመት የተደረገውን ድጋፍ በማስቀጠል በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ዘንድሮም ማድረጋችን ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ እና የነገው ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በቂ የተማረ ኃይል እንዲኖር ለማስቻል ናሽናል ሲሚንት አ.ማ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም በመርሐ ግብሩ ላይም በክብር እንግዶቹ አማካኝነት የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፉን ለተማሪዎች ተበርክቷል።

❤12👍1