በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ የትምህርት ተቋማት 18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር ሥነ ሥርዓት በምስል
👏3👍2
Dire Dawa Administration Education Office communication
Photo
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተወሰደ እርምጃ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ታሸጉ
ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም. - የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ዘመቻውን አጠናክሮ በመቀጠል በወረዳ 01 ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሂላል ሞዴል ት/ቤት እና ሱቡሉ ሰላም ት/ቤት ላይ የማሸግ እርምጃ ወሰደ።
ቢሮው እርምጃው ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን በመግታት ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ስርዓት ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት አካል መሆኑን ገልጿል።
በማሸግ ሂደቱ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊው አቶ ሱልጣን አልይ ከሚመለከታቸው የጥራት ማረጋገጥ ባለሙያዎችና የወረዳ አመራሮች ጋር በመሆን ስራውን በበላይነት መርተዋል።
ኃላፊው በቦታው ተገኝተው እንደተናገሩት "የትምህርት ጥራት የልጆቻችን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስን በመሆኑ በዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖርም።" በማለት የአስተዳደሩን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
በመጨረሻም ወላጆችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ልጆቻቸውን ህጋዊ ፈቃድ ወዳላቸው ትምህርት ቤቶች ብቻ በመላክ ከጥራት ጉድለት እንዲጠብቁ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

😁4❤3