በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው?
ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል።
ሰማዕቱ በግፍ የሚደበደቡ የካህናቱን እና የምእመናኑን እንባ ያብስልን!
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ

ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረው ቃል "አንቺ ሴት ስለ ምን ታለቅሻለሽ?" የሚል ነበር። ልባቸው በኀዘን ለተሰበረ እና ዓይኖቻቸው በእንባ ለተሞላ ሁሉ ጌታ ቅርብ ነው። "ለምን ታለቅሳላችሁ?" ብሎ ይጠይቃል። በሰው ኀዘን ያዝናል፣ ልጇን ከሞት እንዳስነሣላት መበለትም "አታልቅሱ" ብሎ ያጽናናል። በመከራ ጊዜ "አምላኬ፣ አምላኬ" ተብሎ በእውነት ሲጠራ ይሰማል። ሁሉን የሚችል አምላክ፣ እርሱ ለኀዘንተኞች መጠጊያ ይሆናል።
ያዘነና የተከዘውን ሰው ቸል የሚል፣ ለሰው ድካም የማይራራ አምላክ የለንም። እንዲህ ስላለውም አምላክ አባቶቻችን አልነገሩንም፣ እኛም አልሰማንም።
+++ ስለሆነው ስለሚሆነውም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን! +++
"ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ"
መዝ 86፥7
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
ያዘነና የተከዘውን ሰው ቸል የሚል፣ ለሰው ድካም የማይራራ አምላክ የለንም። እንዲህ ስላለውም አምላክ አባቶቻችን አልነገሩንም፣ እኛም አልሰማንም።
+++ ስለሆነው ስለሚሆነውም ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን! +++
"ትመልስልኛለህና በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጠራለሁ"
መዝ 86፥7
#አንዲት_ቤተክርስቲያን
#አንድ_ሲኖዶስ
#አንድ_ፓትርያርክ
#ለቅዱስ_ሲኖዱ_እንታዘዛለን!
#አባቶቻችንንም_እናምናለን!
የሩቅ ተመልካች ሆነን በቸልታ የኖርንበት ያለፈው ጊዜ ይቆጨን። ከዚህ በኋላ ለቤተ ክርስቲያን የእውነት ለመኖር ለራሳችን ቃል እንግባ።
#ቤተክርስቲያንን_እወዳታለሁ
#በቤተ_ክርቲያን_እኖራለሁ
#ለቤተ_ክርስቲያን_እኖርላታለሁ

በስደት ውስጥ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የጌታ ቀን ተብላ በምትጠራው በሰንበት ተሰብስበው ሰማእታቱን እየዘከሩ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ነበር።
ታዲያ እኛስ የነገውን ሰንበት ቅዱስ ሲኖዶሱ እንዳዘዘን የቻልን በቅዱስ ቁርባን ያልቻልን ደግሞ ከሥርዓተ ቅዳሴው በመሳተፍ ሰማእታቱን እያሰብን ለምን አናሳልፍም?!
#ሰንበትን_እንደ_መጀመሪያዎቹ_ክርስቲያኖች
"በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ" ራእይ 1፥10

+++ "የመውጊያውን ብረት አንቃወም" +++
ቅዱስ ጳውሎስ ወደሚደነቀው የክርስትና ብርሃን ከመምጣቱ በፊት፣ ለአባቶች ወግ የሚቀና እና የአይሁድን ሥርዓት ከሁሉ ይልቅ አብልጦ የሚጠብቅ ሰው ነበር።(ገላ 1፥14) በክርስቲያኖች አፍ የሚጠራው "ኢየሱስ ክርስቶስ" የሚለው ስም ኦሪታዊው እምነቱን ያጠፋዋል የሚል ስጋት ስለ ነበረበት ክርስቲያኖቹን ያለ ልክ ያሳድዳቸው ነበር። በተለየ እነዚህ የክርስቶስ ተከታዮች በደማስቆ በሰላም እየኖሩ እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ ተቆጣ። እንደሚገድላቸውም እየዛተ በዚያ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ እንዲጽፍለት ሊቀ ካህናቱ ገብቶ ለመነ።(ሐዋ 9፥1-2)
የጠየቀውንም ደብዳቤ እንዳገኘ ጊዜ ሳያጠፋ ወዲያው በፈረስ እግር እየፈጠነ ወደ ደማስቆ ገሰገሰ። ወደ ከተማው መግቢያ ሲቃረብ ግን ያላሰበው ነገር ተከሰተ። ከሰማይ የወጣ አንጸባራቂ ብርሃን አይኑን ወግቶ ጣለው። አስፈሪው ሳውል ከፈረሱ ላይ እንደ ነገሩ ወደቀ። ጌታ ሳውልን ገና በኢየሩሳሌም ሳለ ደቀ መዛሙርቱን ሲያሳድድበት እዚያው በብርሃን መትቶ አልጣለውም። ሳውል በክርስቲያኖቹ መካከል እያለ በብርሃን ቢመታ ኖሮ፣ አይሁድ ክርስቲያኖቹን እንደ አስማተኛ ቆጥረው ይከስሷቸው ነበር። ለዚህም ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ ሌላ ተገቢ ያልሆነ ስም ያወጡለት ነበር። ስለዚህ በደማስቆ ከተማ መግቢያው አፋፍ ላይ በብርሃን መትቶ ጣለው።
የጌታ አመጸኛን የሚስብበት ልዩ የሆነ የፍቅሩን ሰንሰለት ተመልከቱ። በብርሃን መትቶ ከጣለው በኋላ ያናገረው ግን "ስለ ምን ታሳድደኛለህ?" ("ምን አደረግኹ?") በሚል በሚለማመጥ ሰው ቃል ነበር። ልብ በሉ "አንተ ነህ እኔን የምታሳድደው?" አላለውም። ይህ የማስደንገጥና የቁጣ ቃል ነው። ቁጣ ብቻውን ደግሞ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያሠራም።(ያዕ 1፥20) ቢያሠራም የውዴታ አይደለም። ጌታ ግን ለአሳዳጁ ሳውል ያለውን ፍቅር በሚገልጥና ልብን በሚመረምር ቃል "ለምን ታሳድደኛለህ?" ሲል ጠየቀው።
በዚህ ፍቅሩም ምስኪን በጎቹን ለማጥቃት በአደገኛ ተኩላ ተመስሎ ሲበር የመጣውን፣ ከደማስቆ ደጃፍ ከከተማው በር አቅራቢያ ሲደርስ ተኩላነቱን አስጥሎ ከጎቹ መካከል እንደ አንዱ አደረገው። "ለምን ታሳድደኛለህ?" በሚለው ቃል ገዳዩ ሳውልን ጥሎ፣ በጎቹን የሚጠብቅና ስለ እነርሱም ሲል የሚሞት "እረኛው ጳውሎስ"ን አስነሣው።
ሳውል የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያሳድድ የነበረው ከክፋት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ከነበረው ቅናት የተነሣ ነው። አሳዳጅነቱም የእውነት ጠላት ከመሆን ያይደለ፣ አምላክን አገለግላለሁ ከሚል የዋሕ አሳቡ የተወለደ ነበር። ስለዚህ የየዋሐን ሰዎች የክፋት ጽዋ ስትሞላ ተገስጸው ይማሩበታል እንጂ አይጠፉበትምና፣ እግዚአብሔር የዋሑ ሳውልን መገሰጽን ገሰጸው፤ ለሞት ግን አሳልፎ አልሰጠውም ።
ሳውል "ለምን ታሳድደኛለህ?" የሚለውን ድምጽ በሰማ ጊዜ፣ "ጌታ ሆይ ማን ነህ?" ሲል ጠየቀ። ጌታም "አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" አለው። የአንድ ሕዋስ መታመም ለአካሉም ጭምር ይተርፋል። እጅ በስለት ቢወጋ አፍ ደግሞ ይጮሃል። ምእመናንም የክርስቶስ አካል በተባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ያሉ ሕዋሳት ስለሆኑ፣ እነርሱን ማሳደድ ክርስቶስን ማሳደድ ነው። ስለዚህም መድኃኒታችን ራሱን በክርስቲያኖች ቦታ አስገብቶ "የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ" አለው።
"የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" የሚለውን ቃል ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ልክ እንደ እንቆቅልሽ ያለ ንግግር እንደ ሆነ ጽፈዋል። "የመውጊያ ብረት" የሚለውን የኢትዮጵያ ሊቃውንት "ሰይፍ" ብለው ተርጉመውታል። ኃይለ ቃሉን ሲያብራሩትም "ሰይፍን የረገጠ ሰው እርሱ ይጎዳል እንጂ ሰይፋ ምንም አይሆንም። አንተም ከእንግዲህ ወዲህ ምእመናንን ብታሳድድ ለእነርሱ ስደቱ ክብር ስለሆነ ይጠቀሙበታል። አንተ ግን ሳትጎዳበት አትቀርም" ሲለው ነው ይሉናል። ግሩም ትርጓሜ!
ከዚህ በተጨማሪ "የመውጊያ ብረት" ፈረስ የሚጋልብ ወይም በሬ የሚጠብቅ ሰው የሚገለገልበት መሣሪያ ነው። ገበሬዎችና ፈረስ ጋላቢዎች ፈረሱ ፍጥነት ሲቀንስባቸው፣ በሬውም አልሄድም ብሎ ሲለግምባቸው ሁለቱንም "በመውጊያው ብረት" እየወጉ ያነቁበታል። ቃለ እግዚአብሔርም የመውጊያ ብረት ነው። ሳውል ቀድሞ በቅዱስ እስጢፋኖስ በኩል የሰማውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ብሎ ነበር። የቆመበትን አይሁዳዊነት ለቅቆ ወደ ክርስትናው እንዲሻገር የሚያነቃውን የመውጊያ ብረት ተቃውሞ ነበር። ስለዚህም ጌታችን አሁን "የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ሲል አስጠነቀቀው።
ከቆምንበት የኃጢአተኞች መንገድ፣ ከተቀመጥንበት የዋዘኞች ወንበር ቀስቅሶ የሚያነቃንን "የመውጊውን ብረት" ቃለ እግዚአብሔር አንቃወም። ልባችን አይደንድን፣ የቤተክርስቲያንን ድምጽ እንስማ።
"የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል"
ዕብ 4፥12
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com

በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፉት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፣ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ።(ምሳ 16፥32)
ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ ለሰውነትህ ጾም አስተምረው። "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።
ጌታ ወደ እስራኤል የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር።(ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።
መልካም ዐቢይ ጾም ይሁንልን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel

+++‹በተአምሩ አይደለም በቃሉ ድል ነሣው እንጂ!›+++
በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ያለ አምላካችን በባሕረ ዮርዳኖስ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ ፣አብም በደመና ከመሰከረለት በኋላ የመልካም ሥራዎች ሁሉ መጀመሪያ የሆነችውን ጾም ይጾም ዘንድ ወደ ቆሮንቶስ በረሃ ሄደ፡፡ በኋለኛው ዘመን በፍቅሩ ሲነዱ ‹ከሀገር ምድረ በዳ ፣ከዘመድ ባዳ› ይሻለናል ብለው በበረሃ ለሚንከራተቱ መናንያን በር ይከፍት ዘንድ በሰው ልጆች ፍቅር ጥማት የታመመ እርሱ የውኃ ምንጭ ልምላሜ ወደ ሌለበት በረሃ ገሰገሰ፡፡ ይህንንም ሲያደርግ ማንም አላስገደደውም፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ በሆነች በገዛ ፈቃዱ ወደ ገዳም ወረደ እንጂ፡፡
በዚያም በረሃ ለአርባ ቀናት ጾመ፡፡ አምላካችን ለምን አርባ ቀን ብቻ ጾመ? ወደ ሃምሳ ፣ወደ ስልሳ ቀናት ለምን አላሳደገውም? ካልን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክንያቱን ይናገራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ትልቁን ጾም የጾሙት እነ ሙሴ አነ ኤልያስ አርባ ቀን ያህል ነበር፡፡ ስለዚህ አምላካችን እነርሱ ከጾሙት ቀን አትርፎ ለሃምሳ ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆኑ ቀናት ቢጾም ኖሮ ‹አይ ይህስ የሰውነት ጠባዕይ ፣ባሕርይ ቢጠፋለት ነው› ብለው ሰውነቱን የሚጠራጠሩ ይኖራሉና ‹ለአጽድቆተ ትስብዕት› (በእውነት የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ያስረዳ ዘንድ) ሲል እንደ ቀደምት አበው እንደ ሙሴ እንደ ኤልያስ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ጾመ፡፡ በእርግጥ ሌሎች ነቢያት እና የብሉይ ኪዳን ጻድቃን ቢጾሙ ኃይል ብርታት የሚሆናቸው፤ የሚያጸናቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ ግን በገዛ ሥልጣኑ ያለ ማንም አጋዥነት ይህን ጾም ጾሞታል፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም የሙሴን ሕይወት ተርጉሞ ባስተማረበት ድርሳኑ ሙሴ በሲና ተራራ አርባ ዕለታት እንዴት ያለ ምግብ ሊቆይ ቻለ? ብሎ ይጠይቃል፡፡ እውነትም ያለ ምግብ ከሰባት ቀናት ያለ ውኃ ደግሞ ከሦስት ቀናት በላይ መሰንበት የማይችል የሰው ልጅ እንዴት አርባ ቀናት ያለምንም ሥጋዊ መብልና መጠጥ ሊቆይ ቻለ? የሚለው ጥያቄ እኛንም ያሳስበናል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ግን መልሱን እዚያው ሳይርቅ ይነግረናል፡፡ ምን የሚል ይመስላችኋል…? ረሃብ እና ጥምን የሚያስረሳ ሥጋዊ ድካምንም ሁሉ የሚያርቅ ‹የእግዚአብሔርን ፊት አይቷልና!!!›፡፡ በእርግጥም በጽድቅ የፈጣሪውን ፊት በመመልከት ክብሩን ሲያይ የማይጠግብ ማንም የለምና ፤ ሙሴ የፈጣሪውን ፊት እያየ ከገባባት ተደሞ እና መንፈሳዊ ጥጋብ እንዴት ሥጋዊ ረሃብ ፣ሥጋዊ ጥም ቀስቅሶ ሊያነቃው ይችላል? (መዝ 07.05) ታዲያ ሙሴ ገጸ አምላኩን ተመልክቶ ረሃብ ከጠፋለት ‹እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው› መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በገዛ ሥልጣኑ አርባ ቀን አርባ ሌሊት መጾሙ ምን ያስደንቃል?
ቀድሞ ሔዋንን ብቻዋን አግኝቶ በፈተናው መረብ ጠልፎ የጣላት ሰይጣን አሁንም አምላካችንን በበርሃ ብቻውን ቢያየው የለመደውን ድል ፍለጋ ወደ እርሱ በፈተና ቀረበ፡፡ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊው እንደሚነግረን ጌታችን የተፈተነው በአርባኛው ቀን ብቻ ሳይሆን አርባውን ቀን በሰይጣን እየተፈተነ ነው የሰነበተው (ማር 1.03)፡፡ መጻሕፍት በአርባኛው ቀን የተፈተናቸውን ፈተናዎች ብቻ ይዘው መገኘታቸው በሚበልጠው ለመናገር ነው እንጂ እነዚህን ብቻ ነው የተፈተነው ማለታቸው አይደለም፡፡ በፈተና የሚያልፉ ክርስቲያኖች በደል ሳይገኝበት ‹በነገር ሁሉ የተፈተነ› እና በድካማቸው የሚራራላቸው አምላክ እንዳላቸው አውቀው ይጽናኑ ዘንድ እርሱ በበጎ ለሚፈተኑ ሁሉ በኩር ሆነ (ዕብ 4:15)፡፡
አምላካችን የተፈተነው ከተጠመቀ በኋላ ነበር፡፡ ይህ ለእኛ ምን ያስተምረናል? ምዕመናን ሁል ጊዜ የእግዚአብሔርን ኃይል ፣ልጅነትን በጥምቀት ከተቀበሉ በኋላ የሚያስተናግዱት የፈተና ሕይወት እንዳለ ነው፡፡ ሰይጣን ደስ የሚሰኝበት ምንም አይነት የጽድቅ ሥራ ባለመኖሩ ፣የፈተና ወጥመዱን የሚዘረጋው ፈቃዱን ለሚፈጽሙ ደካሞች ሳይሆን በጥምቀት የእግዚአብሔርን ልጅነት ላገኙ እና የዲያቢሎስን ክፋት በመልካም ተጋድሎ ለሚቃወሙት ጽኑዓን ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹ኃይልን የምንታጠቀው እኮ ለመዋጋት ነው እንጂ ለመቀመጥ አይደለም› ይለናል፤ እውነት ነው፡፡ እግዚአብሔር በጥምቀት መንፈሳዊውን ኃይል የሚያስታጥቀን ከጠላት ዘንድ ፋታ የሌለው ውጊያ ስላለብን አይደለምን? ታዲያ ለምን ለፈተና ሁል ጊዜ እንግዶች እንሆናለን?
አምላካችን በወንጌል በምሳሌ እንዳስተማረው ኢየሩሳሌም ከተባለች ልዕልና ኢያሪኮ ወደ ተሰኘች ትሕትና አንድ ሰው የተባለ አዳም ሲወርድ በመንገድ አጋንንት አግኝተው ፈትነው ፣ልጅነቱን ቀምተው ፣በኃጢአት ቁስል አቁስለው በሞትና በሕይወት መካከል ጥለውት እንደሄዱ ፤ የአዳምና የሔዋንን እዳ ለመክፈል ሰው የሆነ ክርስቶስም ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ሲወርዱ በሚያገኙት የቆሮንቶስ በረሃ አዳምን ያቆሰሉትን አጋንንት ድል ነስቶለታል (ሉቃ 10)፡፡
መድኃኒታችን በሰይጣን ለቀረበበት ለእያንዳንዱ ፈተናዎች የሰጣቸውን ምላሾች አንስተን እንማር ብንል ብዙ ቁም ነገር የሚገኝበት ቢሆንም ዛሬ ግን በዚህ ጽሑፍ አናነሣቸውም፡፡ ነገር ግን ሦስቱንም ፈተናዎች ድል የነሣበትን አንድ መንፈሳዊ ጥበብ ፍለጋ እስኪ ደጅ እንጥና፡፡ ታሪኩ ተሟልቶ የቀረበበትን የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራትን ስታነቡ ሦስቱም ፈተናዎች ጋር የሚገኝ ተመሳሳይ መልስ አላገኛችሁም? ‹ተብሎ ተጽፏል› የሚል አገኛችሁ አይደል፡፡ አምላካችን ሰይጣን በፈተነው ጊዜ ሰይጣንን ድል የነሣው በተአምራት ወይም አሁን እኛ ልንገልጸው በማንችለው መንገድ ኃይሉን ተጠቅሞ አይደለም፡፡ ሰይጣንን ድል የነሣው ተጽፎ በተቀመጠ ቃለ እግዚአብሔር ነው፡፡ ለምን ይመስላችኋል ? በእውነት ሰይጣንን በተአምራት ድል ቢነሣው ኖሮ በዛሬ ዘመን ያለን ደካሞች የሰይጣንን ፈተና ላለመቃወም ምክንያት ባገኘን ነበር፡፡ ‹እርሱን በተአምር ካልሆነ በምን ያሸንፉታል ፤ እኔ ደግሞ ይህ ጸጋ የለኝም› ብለን ተሳንፈን እና ተስፋ ቆርጠን በተቀመጥን ነበር፡፡ ነገር ግን የሰይጣንን ፈተና ከእኛ ቆርጦ ለመጣል አምላካችን የሰጠን በዋዛ የማይገኘውን ሰይፍ ተአምር ሳይሆን ፤ ለሁሉ በጸጋ የተሰጠውንና በየቤታችን የምናኘውን የቃሉን ሰይፍ ነው፡፡ ይህንን ሰይፍ እንጠቀምበት፡፡ አፋችን በዚህ ሰይፍ ይሞላ! እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹አፈ ሰይፍ› ፣‹አፈ መጥባሕት› እንሁን!!!
መልካም የጾም ጊዜ ይሁንልን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
(በድጋሚ የተለጠፈ)

👍1
+++ ሌላ ቆሮንቶስ ከዚህ አለ! +++
ክብር ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሰይጣንን ወግቶ ድል የነሣው በቆሮንቶስ በረሃ ነበር። እንደ አይሁድ ትውፊት ከሆነ ሰይጣንና የክፋት መናፍስቱ ከእጽዋት የተራቆተ በረሃማን ስፍራ ለማደሪያነት ይመርጣሉ። በርግጥም ሕያዋን የሆኑ ጻድቃንን፣ ከውኃ ዳር እንደ ተተከለ ዛፍ የለመለሙ እና ፍሬያማ የሆኑ ቅዱሳንን የማይወድ ሰይጣን፣ ለማደሪያነት የውኃ ምንጭ እና ልምላሜ የሌለበትን በረሃ ይመርጣል ቢባል የሚደንቅ ነገር አይደለም። ይህም በመሆኑ መድኃኒታችን ሰይጣንን አጎሳቁሎ እና አዋርዶ ያሸሸው ሰልጥኖ ከሚኖርበት በረሃ ገብቶ ነው። ዛሬም የቅድስና ምንጭ የደረቀበት፣ ከበጎ ምግባር ተራቁቶ ገላጣ መሬት በመሆን ለሰይጣን ምቹ ማደሪያ የሆነ ሌላ በረሃ በዚህ አለ። ይህም በረሃ ሃይማኖት የሰለለበት፣ የመልካምነት ፍሬም ደርቆ የረገፈበት የእኛ ሰውነት ነው። በቆሮንቶስ በረሃ የነበረውን ፈታኝ ድል የነሣ ጌታ፣ በእያንዳንዳችን ሰውነት መሽገው የተቀመጡትን መናፍስት "ከኋላቸው ሂዱ" ብሎ ገስጾ ከእኛ ያርቅልን።
መልካም የጾም ጊዜ ይሁንልን!

በቱርክ ሀታይ በተፈጠረው ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ከድጋይ ፍርስራሽ ውስጥ ከ5 ቀናት ወይም ከ128 ሰዓታት በኋላ በሕይወት የተገኘችውን (የተገኘውን) የሁለት ወር ሕፃን ተመልከቱ።
ጌታችን ለሰይጣን "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" ሲል የተናገረውን ቃል የቤተ ክርስቲያን ሊቃውን ሲተረጉሙ:- "እግዚአብሔር ኑር ያለው ይኖራል፤ እግዚአብሔር ሙት ያለው ደግሞ ይሞታል" ይላሉ። እውነት ነው፤ እግዚአብሔር ኑር ሲል እንዲህም ያኖራል!

🙏1
+++ የማርያም መንገድ +++
ድሮ በልጅነት ከባልንጀሮች ጋር
በየጎዳናው ላይ ስንበር ስንባረር
አባራሪው ደርሶ መንገዱን ከዘጋ
ከግራና ከቀኝ ማምለጫ ካሳጣ
ተባራሪ ምስኪን መንገድ የጠበበው
በጭንቁ 'ሚጠራት አንዲት ዋስ አለችው
የእርሷን ስም ካነሣ የጠበበ ይሰፋል
የተዘጋው ሁሉ መንገድ ይከፈታል
ቀን በጎደለበት ባገኘው መከራ
በጨነቀው ስዱድ ስሟ የሚጠራ
ማርያም እርሷ ነች ሁሉን 'ምታራራ።
እናታችን እመቤታችን ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት እለት እንኳን በሰላም አደረሰን። ጭንቅ እና መከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ ከክፋ ቀን ሁሉ የምንወጣበትን "የማርያም መንገድ" የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
ድሮ በልጅነት ከባልንጀሮች ጋር
በየጎዳናው ላይ ስንበር ስንባረር
አባራሪው ደርሶ መንገዱን ከዘጋ
ከግራና ከቀኝ ማምለጫ ካሳጣ
ተባራሪ ምስኪን መንገድ የጠበበው
በጭንቁ 'ሚጠራት አንዲት ዋስ አለችው
የእርሷን ስም ካነሣ የጠበበ ይሰፋል
የተዘጋው ሁሉ መንገድ ይከፈታል
ቀን በጎደለበት ባገኘው መከራ
በጨነቀው ስዱድ ስሟ የሚጠራ
ማርያም እርሷ ነች ሁሉን 'ምታራራ።
እናታችን እመቤታችን ድንግል ማርያም የምሕረት ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት እለት እንኳን በሰላም አደረሰን። ጭንቅ እና መከራ በተሞላ ዓለም ውስጥ ከክፋ ቀን ሁሉ የምንወጣበትን "የማርያም መንገድ" የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
በገነተ አበው (Paradise of the fathers) እንደ ተጻፈ፣ አንድ መነኩሴ ታርዞ በብርድ ይሰቃይ ለነበረ ምስኪን የለበሰውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ አውልቆ ሰጠው። ከጥቂት ጊዜ በኋላም በገዳም ሆኖ የሰፋቸውን ሰሌኖች ለመሸጥና የእለት ምግቡን ገዝቶ ለመመለስ ወደ ገበያ ሲወጣ፣ በመንገድ ዳር የቆመች አንዲት ዘማ ያን ለምስኪኑ ሰው የሰጠውን የመነኩሴ መጎናጸፊያ ለብሳው ያያታል። ባየው ነገር የተደናገጠው መነኩሴ "የምድር መላእክት የሚለብሱትን ይህን የክብር ልብስ በከንቱ ቦታ እንዲውል አደረግኹት" እያለ ማልቀስና መቆጨት ጀመረ። ሲያዝንም ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ "አይዞህ አትዘን፤ መጎናጸፊያህን ለዚያ ምስኪን በሰጠህበት ቅጽበት ከእጅህ ተቀብሎ የለበሰው ክርስቶስ ነው። ከዚያ በኋላ ለሆነው ሁሉ አንተ ተጠያቂ አይደለህም" ሲል አጽናናው።
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ጠጥቶ ሊሰክር ወይም ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። ያ የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
ተርቦ እና ተቸግሮ ለምታገኘው ምስኪን ያለ ምንም መመራመር ከእጅህ ያለውን ስጠው። እርሱ በሰጠኸው ገንዘብ ረሃቡን ከማስታገስ ይልቅ ጠጥቶ ሊሰክር ወይም ሌላ አጉል ነገር ሊያደርግበት ይችላል። ያ የአንተ ድርሻ አይደለም። አንተን የሚያስጠይቅህ ተመጽዋቹ ከምጽዋቱ በኋላ የገባበት ስካር ሳይሆን፣ አንተ ሳትመጸውተው በፊት የነበረበት ረሃብ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
+++ ልብስህን ማን ወሰደው? +++
በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም "ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ 'ታርዤ አልብሳችሁኛልና' ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ እንዴት አልፌው እሄዳለኹ?" ብሎ ፈጥኖ ልብሱን በማውለቅ ይለብሰው ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ያዘ እርቃኑን በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው።
ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት የሚወስዱትን አንድ ምስኪን ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡
ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ የምጽዋትን ታላቅነት ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከወደቀበት የሕግ እርግማን የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና።
በዚህ ጾም የተራቡት ወገኖቻችንን ከእነርሱ ጋር እንደ ተራቡ ሆነን የምናስብበት ወቅት ነው።
#ቦረናን_እናስብ

በዓመት ለተወሰኑ ቀናት ከእያንዳንዱ የአገሪቱ ዜጋ ጋር የሚገናኝና ጥያቄዎቻቸውን በግለሰብ ደረጃ የሚመልስ መንግሥት ቢገኝ ምን ያህል ሊወደድ እንደሚችል አስቡት? ሕዝቡም በዚህ ደረጃ ቅርብ ሆኖ የሚጨነቅለትና ጥያቄዎቹን የሚሰማለት ደግ ንጉሥ በማግኘቱ ይህን ባሰበ ቁጥር አንዳች የደስታና የኩራት ስሜት ሰውነቱን ውርር ሳያደርገው አይቀርም።
ሰማይና ምድርን የፈጠረው፣ ዓለሙን የሚመግብና የሚያስተዳድረው ታላቁ ንጉሥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንድንገናኝና ጥያቄዎቻችንን እንድናቀርብ በዓመት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ሰጠን? ምድራውያን ነገሥታት ቢገዙ የሚታየውን ዓለም ያውም ደግሞ በተራራ እና በወንዝ ተቆራርሶ፣ በግዛት ታጥሮ የተሰጣቸውን ኩርማን መሬትና በዚያ የሚኖሩትን ሕዝብ ነው። እንዲህም ሆኖ ግን ሥራ ስለሚበዛባቸው ከጊዜያቸው አጣበው በዓመት አንድ ወይም ሁለት ቀን እያንዳንዱን ዜጋ ቢያገኙ እጅግ ታላቅ ጀብዱ ሆኖ ይነገርላቸዋል።
በእውነት እንደ እግዚአብሔር ያለ "ሥራ ብዙ" ማን ነው? መድኃኒታችን በወንጌል "አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል፡ እኔም ደግሞ እሠራለሁ" እንዳለ እርሱ እኮ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሲያስተዳድር ዕረፍት አያውቅም፤ ድካምም የለበትም።(ዮሐ 5፥17) ይሁን እንጂ ከእኛ ጋር ለመገናኘት ግን የወር ወይም የቀናት ቀጠሮ አይሰጠንም። ዛሬስ አይታሰብም ባይሆን ነገ ሞክሩ ብሎ አይመልሰንም። ወደ እርሱ የሚመጡትን ሁሉ ለመቀበል እጆቹ ዘወትር የተዘረጉ ናቸው። "ትናንት አላናገርኩህም? ዛሬ ምን ቀረህ?" ብሎ አያሳቅቅም፤ አይሰለችም። በዚህ ቀንና በዚህ ሰዓት ብቻ እገኛለሁ አይልም። ብንችል ሳናቋርጥ አብረነው ብንሆንና ብናነጋግረው ደስ ይለዋል።(1ኛ ተሰ 5፥17) በእርሱም ዘንድ የተቆለፈ በር የለም። እንደውም ወደ ልባችን እልፍኝ እስክናስገባው ከውጭ ሆኖ እኛን ደጅ ይጠናል። ያንኳኳል፤ ክፈቱልኝ ይላል።(ራእይ 3፥20) ሲከፈትለትም ምስኪኑን ቤት አይቶ አይጸየፍም። የልባችንን እልፍኝ ያሰናዳዋል። ለእራትም አብሮን ይቀመጣል።
ታዲያ እንዲህ ያለ ቸር ጌታ እያለን እንዴት ዝም ይባላል? እንግዲህስ ከተኛንበት የስንፍና አልጋ እንነሣ። ንጉሡን እናነጋግረው። ወደ እርሱ ስላቀረበን እናመስግነው፣ የልባችንንም ኃዘን እንንገረው።
ተንሥኡ ለጸሎት!
"በማታና በጥዋት በቀትርም እናገራለሁ...ቃሌንም ይሰማኛል" መዝ 55፥17

+++‹አውጡ› እንጂ ‹ውጡ› አላለም+++
ሁሉ የሚቻለው፣ የሚሳነውም የሌለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና መንደር በታደመበት ሰርግ ቤት ውኃውን በተወደደው በእናቱ ምልጃ ወደ ወይንነት ከለወጠ፣ ሐዋርያቱም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ካመኑበት በኋላ ከእናቱ እና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፡፡ በዚያም ለአሥራ አንድ ቀናት ያህል ተቀመጡ፡፡ ወቅቱ የእስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት መውጣት የሚታሰብበት የፋሲካ በዓል የደረሰበት በመሆኑ ብዙ ሰዎች ይህንን ታላቅ በዓል ለማክበር መቅደስ ወደ ታነጸባት ቅድስቲቱ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር፡፡ አምላካችንም እርሱ እግዚአ በዓላት (የበዓላት ጌታ) ሆኖ ሳለ በዓልን ለማክበር በትሕትና ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡
ራሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር በማይዋሽ ቃሉ "የተቀደሰ ጉባዔ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ የእግዚአብሔር በዓላት እነዚህ ናቸው" ሲል ለሙሴ እንደነገረው በዓላት የእግዚአብሔር ገንዘቦች ናቸው (ዘሌዋ 23፡2)፡፡ በበዓላት የሚከረው እግዚአብሔር እግዚአብሔር ሲሆን፣ የሚከናወነው ደግሞ አንዱ የአምላክ ፈቃድ በመሆኑ "ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያብራል" (ሮሜ 14፡6)፡፡ በዮሐንስ ወንጌል የተጠቀሰው የ‹ፋሲካ በዓል›ም የእግዚአብሔር ንብረት እንደሆነ ‹እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው› ተብሎ የተቀመጠው የኦሪት ጽሕፈት ምስክር ነው (ዘጸ 12፡11)፡፡ ታዲያ ቅዱስ ዮሐንስ ‹የአይሁድ ፋሲካ› በማለት አይሁድን የበዓሉ ባለቤት አድርጎ ለምን ጠራቸው ? የዚህ ምክንያት በወቅቱ የነበሩት አይሁድ በበዓለ ፋሲካ አምላካቸውን ከማክበር ይልቅ እነርሱ የሚከብሩበትን ተግባር በመፈጸም ተጠምደው ስለሚውሉ፣ እግዚአብሔር ከአዘዘው እና ከፈቃዱ ርቀው ስለሚያከብሩት በዓልነቱን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአይሁድ ሰጥቶ ይናገራል፡፡ በርግጥም የእርሱ ገንዘብ በሆኑት በዓላቶቹ የገዛ ፈቃዳቸውን እየፈጸሙ ለሚያስቀይሙት አይሁድ እግዚአብሔር ‹መባችሁን በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል ልታገሳቸውም ደክሜያለሁ› ሲል በነቢዩ አድሮ ይገስጻቸዋል (ኢሳ 1፡14)፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ አገልግሎቱን ከጀመረ በኋላ እስከ ተሰቀለበት ጊዜ ድረስ አራት የፋሲካ በዓላት የተከበሩ ሲሆን ይህም በዓል የመጀመሪያው ፋሲካ ነው፡፡
መቅደሱን ላነጸ ሰሎሞን ‹በፊቴ የጸለይኸውን ጸሎትህንና ልመናህን ሰምቻለሁ፣ ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ፣ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናሉ› ብሎ ቃል የገባ እግዚአብሔር በዘመን መካከል በሥጋ በተገለጠበት ወራት የፋሲካን በዓል ለማክበር በመቅደሱ ተገኘ (1ኛ ነገ 9፡3)፡፡ በዓላትን ለማክበር የእግዚአብሔር መቅደሱ ወደ አለበት የማይገሰግሱ፣ ለጸሎትም ‹ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች› ወዳላት ቅዱስ ስፍራ መምጣት የማይፈልጉ ወገኖች በየትኛው በሐዋርያቱም ሆነ በጌታ ባልተሰበከ ወንጌል ስተው ይሆን ? ስለ ሕንጻ መቅደስ አስፈላጊነት ራሱ ጌታችን በመቅደስ መገኙትን አብነት ከማድረግ የተሻለ ከዚህ የሚበልጥ ምን ምስክር ሊጠቀስ ይችላል? ፡፡ የሰውነታችን ‹መቅደስ› መሰኘት ሕንጻ መቅደስን ያስቀረው ይመስል ‹እኛ ነን የእግዚአብሔር መቅደሶች!› ይሉናል፡፡ ነገር ግን መድኃኒታችን ሰውነቱን ‹መቅደስ› ያለው በሕንጻ ቤተ መቅደስ ውስጥ ተገኝቶ መሆኑን ይዘነጉታል፡፡
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ጌታችን የፋሲካ በዓል ወደሚከበርበት መቅደስ በገባ ጊዜ በሕንጻ መቅደሱ ካሉት በአንደኛው ክፍል የተመለከተው ድርጊት ቅንዓትን የሚያጭር ነበር፡፡ የመንፈስ ብልጽግና በሚታደልባት ቅድስት ስፍራ ሥጋዊ ብዕልን ለማካበት የሚተራመሱ ብዙ ነጋድያን ሞልተዉባት ነበር፡፡ መቅደሱንም እንዲያገለግሉ የተሾሙ የኦሪት ካህናት ኃላፊነታቸውን ቸል በማለት ትርፍ በሚገኝበት ንግድ ራሳቸውን ጠምደው ነበር፡፡ የክፋት ሁሉ ሥር በሆነው በገንዘብ ፍቅር ልባቸው ስለታወረም ከሃይማኖት ተሳስተው በወቅቱ የነበሩት ብዙ እረኞች የወይን ቦታ የተባለ የእግዚአብሔርን መቅደስ አጥፍተውት ነበር (1ኛ ጢሞ 6፡10 ፣ኤር 12፡10)፡፡ ስለዚህም ‹የሌዊን ልጆች የሚያጠራ› የቤቱ ባለቤት እርሱ ቤቱን ሊያጸዳ ወደ መቅደስ ገባ (ሚል 3፡3)፡፡
እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አምላካችን ‹አንጽሖተ ቤተ መቅደስ› ያደረገው ሁለት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያው አሁን እየተመለከትነው ባለነው ወንጌል እና ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሰው አገልግሎቱን በወጠነባት የመጀመሪያዪቱ ፋሲካ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የስቅለቱ መቃራቢያና የሥራው መገባደጃ በሆነው በአራተኛው ፋሲካ ነው (ማቴ 21፡12 ፣ሉቃ 19፡45)፡፡ ይህ ምን ያስተምረናል? የእግዚአብሔር የሥራው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ ቤቱን ማጽዳት
የዲያቆን አቤል ካሳሁን መኩሪያ ትምህርቶች እና መጣጥፎች, [3/8/20, 9:34 PM]
መሆኑን ነው፡፡ ብዙዎች ራሳቸውን ‹ከባለቤቱ ያወቁ› ሲያደርጉ ‹እግዚአብሔርማ ቤቱን ማጽዳት ትቷል!› ይላሉ፡፡ ይህ ሐሳብ ግን መጠን ካለፈ ድፍረት እና የእግዚአብሔርን ሥራ ካለመረዳት የሚመጣ ጎጂነት ያለው ቁጭት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንን በሰላም የሚመራ አምላክ የሥራው መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የክብሩ ማረፊያ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅና ማጽዳት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ ላሉት ሰዎች እለወጥበታለሁ በማለት ቢሰሙን ‹አትታበዩ በኩራትም አትናገሩ እግዚአብሔር (ከእናንተ ይልቅ ለቤቱ) አዋቂ ነውና!!!› ብለን የምክርን ቃል እንለግሳቸዋለን፡፡
ጌታችን ከዚህ በፊት መቅደስ ውስጥ የንግድ ተግባር ይከናወን እንደ ነበር በመቅደስ ተገኝቶ አይቶ ይሆን? ብለን ብንጠይቅ አዎን! ነው መልሳችን፡፡ ጌታ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በነበረ ጊዜ ከእናቱ ከእመቤታችንና ከዮሴፍ ጋር ፋሲካን ለማክበር እንደ በዓሉ ልማድ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደሱ ወጥተው ነበር፡፡ በዓሉንም አክብረው ሲፈጽሙ እናቱ ድንግል እና ዮሴፍ ከመንገደኞች ጋር ይከተላቸው የነበረ ስለመሰላቸው ጥለውት የአንድ ቀን ያህል መንገድ ሄዱ፡፡ የዚያን ጊዜ ብላቴናው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአይሁድ መምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውና ሲጠይቅ ሦስት ቀን ያህል በመቅደስ ከርሞ ነበር (ሉቃ 2፡46)፡፡ ስለዚህ የለመደባቸውን ንግድ በመቅደሱ ሲያደርጉ ጌታ በአሥራ ሁለት ዓመቱ ወደ መቅደስ በወጣ ጊዜ እንደ ተመለከተ እናስተውላለን፡፡ ነገር ግን በዚያን ወቅት ጅራፍ አንሥቶ አልገሰጻቸውም ነበር፡፡ ይኸውም አንደኛ ለእግዚአብሔር የሥራ ጊዜ እንዳለው የሚያመለክት ሲሆን ሌላው ደግሞ በወቅቱ የአሥራ ሁለት ዓመት ብላቴና በመሆኑ አይሁድ ላይ የአደባባይ ግሳጼን ቢያነሣ ‹ልጅነት ነው እንዲህ የሚያስደርገው› ሲሉ ባልተቀበሉት ነበር፡፡ ስለዚህ ጌታችን የአሥራ ሁለት ዓመት ብላቴና ሳለ በመቅደስ ያገኛቸውን መምህራን ጠየቀ እንጂ ጅራፍ አላነሣም፡፡ ምን ብሎ ጠይቋቸው ይሆን ? ‹በእግዚአብሔር ቤት ለትርፍ መነገድ ይገባልን? በሕግስ ስለ መቅደስ ክብር ተጻፈው ምንድር ነው ? እንዴትስ ታነቡታላችሁ ?› ብሎ ጠይቋቸው ይሆን?

ለአገልግሎት ሙሉ ሰው በሚሰኝበት በሠላሳ ዘመኑ ግን አምላካችን በመቅደሱ በተገኘ ጊዜ እንደ ልጅነቱ ጥያቄን አልጠየቀም፡፡ ወደ ለሊቀ ካህናቱ ገብቶ ለውጥ የማያመጣ አቤቱታን አላቀረበም (ዘኁል 4፡23)፡፡ ቸል ሲሉ የሚሳሳቱ እንደሆኑ የልባቸውን ክፋት ያውቃልና ጅራፍን ገምዶ በሬና በጎቻቸውን እየገረፈ ከመቅደስ እንዲያወጡ አደረጋቸው፡፡ ጅራፍ የሚችሉትን በሬዎችና በጎች ሲገርፍ ጅራፉን የማይቋቋሙ ርግቦችን ግን ከዚህ አንሡ ማለቱ እግዚአብሔር ሁሉን በአቅሙ የሚቀጣ እና ልንቋቋመው ከምንችለው በላይ የሆነን መከራ በሰውነታችን የማያመጣ ርኅሩኅ የሆነ አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡ በዚያውም ላይ ‹የፋሲካ በግ› ከተባለው ከእውነተኛው መሥዋዕት ከእርሱ መምጣት በኋላ በሬ እና በግ የእንስሳትስ መሥዋዕት በመቅደስ ምን ያደርጋሉ ? የሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት እርሱ መሆኑን በምሥጢር ሲያመለክት የኦሪት መሥዋዕቶች ከመቅደሱ እንዲወጡ አደረገ፡፡
ኃጢአትን የሚጸየፍ የኃጢአተኛውን ሞት ግን የማይፈልግ አምላካችን በመቅደስ ይነግዱ የነበሩትን ሰዎች የሚነግዱትን ንብረት ከመቅደሱ እንዲያወጡ ነው እንጂ፣ እነርሱ ራሳቸው ከመቅደሱ እንዲወጡ አላደረገም፡፡ ‹አውጡ› እንጂ ‹ውጡ!› አላላቸውም፡፡ በእውነት ኃጢአተኞች ከእግዚአብሔር ጋር በንስሓ እርቅን ከሚያገኙባት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወዴት ይሄዳሉ ? የአምላካቸውንስ ፊት ከሚያዩበት አጸድ ወዴት ይሸሻሉ? ስለዚህ ሰው ወዳጅ የሆነ ጌታችን ክፉ ሥራችሁን ተዉ ‹አውጡ› አላቸው እንጂ ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ አላዘዛቸውም፡፡ በመሆኑም የአካሉ የቤተ ክርስቲያንም መመሪያ ‹አውጡ› የሚለው ይህ የፈጣሪያችን ቃል ነው፡፡ በኃጢአት በክህደት ውስጥ ላሉ ሁሉ ‹ኃጢአት ፣ክህደታችሁን አውጡ› ትላለች እንጂ ውጡ ብላ ለሞት ለጨለማ አሳልፋ አትሰጣቸውም፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ ሰው ከኃጢአት ጋር ፍጹም ሲተባበር፣ ከሐዲም ክሕደቱ በእርሱ ላይ ሥግው እስኪሆንበት ድረስ እርስ በእርሳቸው ሲጣመሩ፣ ያን ጊዜ ከሐዲውን ከክሕደቱ፣ በደለኛውንም ከበደሉ ለይቶ ማየት ስለሚያስቸግር አበረው ሊቆረጡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን በኃጢአት ሸክም የጎበጡትን ሁሉ ለማሳረፍ እጆቿን ዘርግታ መዳንን ሲወዱ ወደ እርሷ የሚመጡትን ሁሉ የምትቀበል ናት እንጂ፣ እርሷን አንባ የሚያደርግ ኃጢአተኛን የምትገፋ አልፈልግሽም ብሎ የሚያምጽባትንም በኃይል ተጭና የምታስገድድ አይደለችም።
ይቆየን!

"ስላንቺም የተነገረው ፍጹም ምስጋና ሁሉ በምስጋናሽ ባሕር ጥልቅነት ዘንድ እንደ ጠብታ ነው።... የምስጋና ዘውድ በራስሽ ላይ ነው። የጽድቅ ጋሻም አንቺን ይከባል።... ሳላቋርጥ አመሰግንሽ ዘንድ የኪሩቤልን አፍ፣ የሱራፌልን ልሳን ብቀበል፤...የሰሎሞንን ጥበብ ብነሣ፣ የልቡናዬም አጽቅ ቢሰፋ እስከ ባሕር ቢዘረጋም፣ የቃሌም ቡቃያ እስከ ቀላይ ድረስ ቢጠልቅ በዚህ ውዳሴሽን ለመፈጸም አልችልም"
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአፉ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የምስጋና ቃል
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
የፍቅሯ ኃይል ያረፈበት፣ የስሟም አጠራር ከአፉ ከማይጠፋ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገኘ የምስጋና ቃል
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com
ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
+++ "እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር ጉዞ" +++
ጌታችን ስለ በጎ ባልንጀራ ተጠይቆ ለዚያ መልስ እንዲሆን በሰጠው ምሳሌ ላይ ያሉት ሁለቱ ሰዎች (ካህኑና ሌዋዊው) ያስገርማሉ። እነዚህ ሰዎች በመቅደሱ የሚያገለግሉ ሲሆኑ ቆስሎ የወደቀውን ታማሚ ያዩት ካህኑ የመቅደስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ ሌዋዊው ደግሞ ገና ለአገልግሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ ሳይሆን አይቀርም።(ሉቃ 10፥30-35) ከቤተ መቅደስ የወጣውም ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄደውም ያን በሽተኛ አይቶ ገለል ብሎት አለፈ።
ለምን? ከመቅደስ የወጣው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አገልግሎት ጨርሻለሁ ብሎ ስላሰበ፣ ወደ መቅደስ የሚሄደው ደግሞ የወደቀውን ሲረዳ የምስጋና ሰዓቱ እንዳይታጎልበት ሰግቶ እንደ ሆነስ? ማን ያውቃል?!
ብቻ "ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ" በማለት የተናገረውንና ከታማሚው ጋር ያለውን እግዚአብሔር መንገድ ላይ ጥለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ።
እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መሄድ የሚሉት ፈሊጥ ምን ዓይነት ይሆን?
ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ወይም ከቤተ መቅደስ ስንመለስ ስንት ጊዜ እግዚአብሔርን ገለል ብለን አልፈነው ሄድን?