"በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ ድንግል እመቤቴ ማርያም ሆይ፣ ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋራ ወደኔ ነይ፡፡ ካንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊልኝ ዘንድ፡፡ ድንግል ሆይ፣ የቃልን ካንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ከአስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ሐዋርያት ጋራ ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ፣ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕታት፣ እርሳቸው ሁለት ልሳን ያለው ሰይፍ የሚታጠቁ ድል የሚነሱ የንጉሥ ሠራዊት ናቸው፡፡ ከርሳቸው ማኅበር ጋራ ደግሞ በረድኤት ወደኔ ነዪ፤ ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ልብሳቸውን ካላሳደፉ፣ ለመንፈስም ማደሪያ ከሆኑ ንጹሓን ደናግል ማኅበር ጋራ ወደኔ ነዪ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!
መንፈሳዊነት ምንድር ነው?
አንድ ሰው መንፈሳዊ የሚባለው ምን ሲያደርግ ነው?
የውሸት መንፈሳዊነትስ አለ?
https://youtu.be/lUYWLWESAuY?si=8rbF5cG073oFbNxx

YouTube
ዲያቆን አቤል ካሳሁን፤"መንፈሳዊነት ምንድነው?"
#subscribe #like #share
ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ።
እግዚአብሔር ያክብርልን!!
©አርጋኖን ሚድያ - Arganon Media -2013|2021

ረቡዕ ነኃሴ 8 አጥቢያ 11 ሰዓት (በኢ/ያ አቆጣጠር) ዘጠነኛ ክፍል ትምህርታችንን እንቀጥላለን። ትምህርቱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላላችሁ ሁሉ ክፍት ነው።
"በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ"
ዕብ 1፥3
ከታች ባስቀመጥነው የzoom link በመጠቀም ይቀላቀሉን!
https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09

👍1
+++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++
ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)
በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10)
ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።
እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ ጋርዶት ቢሆን ኖሮ፣ ሐዋርያቱ "እርሱን ስሙት" የሚለውን ቃል ራሱ ክርስቶስ ለራሱ የተናገረው ሊመስላቸው በቻለ ነበር።
ቅዱስ ጴጥሮስ "አትሙት" ያለው መምህሩን በፍጹም ልቡ ስለሚወደው መሆኑ አያጠራጥርም። ነገር ግን ጴጥሮስ ጌታን የቱንም ያህል ቢወደው፣ ፍቅሩ ግን ከወለደው ከባሕርይ አባቱ ከአብ አይደለም ሊበልጥ ሊነጻጸርም አይችልም። ታዲያ አብ በእርሱ ደስ የሚለው፣ የሚወደው፣ አንድያ ልጁ እንዲሞት ፈቃዱ ከሆነ፣ የአብን ያህል ሊወደው የማችለው አረጋዊው ጴጥሮስ ለምን "አትሙት" እያለ ይቃወማል?!
አብ ምትክ የሌለው ልጁ ወልድ ሰው ሆኖ በክፉዎች እጅ ሲንገላታ እና እስከ መስቀል ሞት ሲደርስ እያየ ዝም ያለው ስለማይወደው አይደለም። ዓለም ያለ ልጁ መከራና ሞት ስለማትድን ነው እንጂ። ከዚህ ምን እንማራለን? ዛሬም ወደ መከራ የምንገባ የጸጋ ልጆቹ የምንሆን እኛ ክርስቲያኖች "እግዚአብሔር እንዲህ ስሆን ዝም ያለኝ ስለማይወደኝ ነው" አንበል። ባገኘን ጥቂት የሥጋ መከራና ሕመም የሚበልጠውን የነፍስ ጤና የምንሸምት ከሆነ እግዚአብሔር ዝም ይላል። ዝም የሚለው መከራችንን ስለማያይ ሳይሆን ከመከራው ጀርባ ያለው ዓላማ ታላቅና የተቀደሰ እንደ ሆነ ስለሚያውቅ ነው።
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ነሐሴ 13፣ 2014 ዓ.ም.
ደብረ ታቦር፣ እስራኤል
ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/AbelKassahunMekuria12
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
👍3
ረቡዕ ነኃሴ 14 አጥቢያ 11 ሰዓት (በኢ/ያ አቆጣጠር) ዐሥረኛ ክፍል ትምህርታችንን እንቀጥላለን። ትምህርቱ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ላላችሁ ሁሉ ክፍት ነው።
“ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል"
ዕብ 1፥4
ከታች ባስቀመጥነው የzoom link በመጠቀም ይቀላቀሉን!
https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09
“ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል"
ዕብ 1፥4
ከታች ባስቀመጥነው የzoom link በመጠቀም ይቀላቀሉን!
https://us02web.zoom.us/j/81873667259?pwd=R2ZGVWVEamhLZU5aVk1PeXhxcGFrdz09
የመነኮሳት መመኪያ፣ የምእመናን ሁሉ አባት፣ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ሐዲስ ሐዋርያ፣ አጋንንትን የሚያሳዱ ጣዖታትን የሚያርዱ፣ እልፍ አእላፋትን በወንጌል መረብ የሚያጠምዱ፣ በምድር ተወልደው እንደ መልአክ የኖሩ ጻድቁ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት ያረፉበት እለት ዛሬ ነው።
እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት የቤታቸውን በር እንደ ተከፈተ ጥለው የወጡትን አባት፣ የገነትን ደጅ ወለል አድርጎ ከፍቶ በታላቅ ክብር የተቀበለበት እለት ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!
አባ ጸሊ በእንቲአነ!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel

❤2🙏1
በቃዴስ በርሃ ምንም በሌለበት፣
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት፣
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምንተስኖት፣
ልባችሁ አይፍራ በፍጹም እመኑት፡፡
https://youtu.be/HYHRBZhO42c?si=FlbfIbfJnZR3AStc

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን | ፈለገ ዮርዳኖስ ሚዲያ
በቦሌ መድኃኔዓለም ፈለገ ዮርዳኖስ ሰ/ት/ቤት በሱባኤ ጉባኤ አንደኛ ዙር ተመራቂ ተማሪዎች የቀረበ መዝሙር::
"ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን
"ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን
እንኳን ወደ አዲሱ ዓመት በሰላም አሸጋገረን!
በዛሬው ቀን መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል አንዱ ጻድቁ ኢዮብ ነው። ኢዮብ ለፈተና ከመጣበት ደዌ የተፈወሰው በዛሬዋ እለት ነው። ይህም በልዩ ልዩ ደዌ ሆነው በዓሉን ለሚያሳልፉ ሁሉ ተስፋ ነው። እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት የሰላም የጤና ያድርግልን!!!
https://youtu.be/RtadI2ocC5E?si=lWiVVmX3eUXQHs0c

መምህር አቤል ካሳሁን ኢዮብ እነደታገሠ ሰምታችኋል ያዕ 5 ፥ 11
✝️✝️✝️የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ በጸሎት ያግዙን✝️✝️✝️አዲሱን የማኅበራችንን የዩቱዩብ ቻናል +++SUBSCRIBE +++ እያደረጋችሁ ትምህርቶችን እና መዝሙሮችን እንዲደርሶት እና ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር በማድረግም ይተባበሩን::
ከዚህ በፊት የተለቀቁ ትምህርቶችንና ዝማሬዎችን ለማግኘት ከስር የሚገኘውን ሊንክ ይጠቀሙ
https://www.youtube.com/channel/UCol_BHX6I…

❤2
የጌታውን እናት የሰላምታ ድምጽ ሰምቶ በማኅጸን በደስታ የዘለለውን (የሰገደውን) ጽንስ፣ በንጉሡ ፊት በክፉት የደነሰችው ልጅ አንገቱን አስቆረጠችው።
ጽንሱ ስለ ሕይወት መምጣት በጠባቡ አዳራሽ በማኅጸን ሲያመሰግን፣ የሄሮድያዳ ልጅ ግን የነቢዩን ሕይወት ስለ ማስጠፋት በሰፊው የንጉሡ አዳራሽ ዘፈነች።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ልጆች በሄሮድያዳ ምክር የማይሄዱበት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ሆነው የሚያድጉበት በጎ ዘመን ያድርግልን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
ጽንሱ ስለ ሕይወት መምጣት በጠባቡ አዳራሽ በማኅጸን ሲያመሰግን፣ የሄሮድያዳ ልጅ ግን የነቢዩን ሕይወት ስለ ማስጠፋት በሰፊው የንጉሡ አዳራሽ ዘፈነች።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ልጆች በሄሮድያዳ ምክር የማይሄዱበት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ሆነው የሚያድጉበት በጎ ዘመን ያድርግልን!!!
ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://www.tg-me.com/Dnabel
https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg
❤3
አይደርስ የለ ተራው ደርሶን ወደ ሕጉ ልንገባ ጥቂት ወይም አንድ ቀን ቀረን። እስከ ዛሬ የብዙ ቃናዎች እድምተኛ ነበርን። እሑድ መስከረም አሥራ ሁለት ግን ሙሽራ ሆነን ልንሰየም ቀጠሮ ይዘናል። እንግዲህ ሁላችሁም ወዳጆቼ በቃናው ሠርግ ቤት በነበረው እና እኛንም ባሳደገን በመልአኩ ቤት ተገኝታችሁ እግዚአብሔር ያደረገልንን ድንቅ ነገር ታዩ ዘንድ በአክብሮት ጥሪዬን አቅርቤያለሁ።
ቦታ፡ አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
ሰዓት፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡ አፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
ሰዓት፡ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ
❤16👍2