Telegram Web Link
Live stream started
Live stream finished (54 minutes)
የእርገት/የጰራቅሊጦስ በዓልን ጌታችን በተወለደበት፣ ባስተማረበት፣ በተሰቀለበት፣ ከሙታንም በተነሳበት በኢየሩሳሌም ያክብሩ።

ምዝገባ እየተጠናቀቀ ነው!

ይደውሉልን!

+251 9 05 95 95 95
+251 9 03 95 95 95
+251 9 11 23 56 79

ካዛንችስ ፓላስ ፓርኪንግ (አንድነት ፓርክ) ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ብቅ ብለው ዝርዝር መረጃ ይውሰዱ፣

ድል አስጎብኚና የጉዞ ወኪል
30👍11🔥1
ከመላእክት ጋር አብረን የምንዘምርበትን የዜማ ሥርዓት ለሠራልን፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የወረደውን የምስጋና ማዕድ ለእኛ እንደሚገባ አድርጎ ላደረሰ ታማኝ መጋቢ፣ ለዘማሪው፣ ለተርጓሚው፣ ለባለ ቅኔው ለቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።

-የአንደበት አመጽ ጸጋን አስገፍፎ እንዴት የመልአክነትን ክብር እንደሚያሳጣ በሳጥናኤል አየን!

-የአንደበት ፍሬ እንዴት እንደሚያከብር እና ምድራዊ መልአክ እንደሚያደርግ ደግሞ በቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ተመለከትን!

አቤቱ የያሬድን ልሳን ስጠኝ!

ዲያቆን አቤል ካሣሁን
[email protected]
https://www.tg-me.com/Dnabel
248👍25🙏12🔥6🥰3
ሰላም ክቡራን፣

የዕብራውያን መልእክት ሐተታ ትምህርታችንን ከተወሰኑ የዕረፍት ጊዜያት በኋላ እንደ አዲስ ከትምህርቱ ሂደት ማሻሻያ ጋር የምንጀምር ይሆናል። እስከዚያው ግን እስከ ዛሬ በነበረን ቆይታ ያላችሁን አስተያየት በcomment መስጫ ቦታው ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

ቸር ያገናኘን!
👍65🥰18
"ትዕቢተኛ ከሚያደርግህ ስኬት ይልቅ፣ ትሑት የሚያደርግህ ስህተት ይሻላል"
309👍21👏10🔥9
"በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን" ኤፌ 2፥6-7

እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን!
231🙏27👍6🔥2
+++ "እመቤታችን ከጌታ ዕርገት በኋላ" +++

መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅዱስ መስቀሉ ላይ ባፈሰሰው ክቡር ደሙ የመሠረታትን ቤተ ክርስቲያን ለሐዋርያቱ አደራ ሰጥቷል፡፡ በመጀመሪያው ምዕት ዓመት በነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የጌታ እናቱ እመቤታችን የነበራት ድርሻ ትልቅ ነበር፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ እመቤታችን በሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት ሳለች፣ የሐዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ራስ እና ፈጻሚ የሆነው ክርስቶስ የተገኘባትን እርሷን ለማየት ከሁሉም የዓለም ክፍላት የሚመጡ ሰዎች ብዙ ነበሩ፡፡ ድንግልም ወደ እርሷ የመጡትን ሁሉ እየባረከች፣ ያዘኑትንም እያጽናናች፣ በንስሓ ሕይወት እንዲኖሩ በመምከር ተስፋና ደስታን እየሞላች ትሸኛቸው ነበር፡፡ በርግጥም እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በምድር ላይ ለመገለጡ፣ እንደ ሕፃናት ጥቂት በጥቂት ለማደጉና በመጨረሻም ለፈጸመው የቤዛነት ሥራው ሁሉ እናቱና አገልጋዩ ከምትሆን ከእመቤታችን የበለጠ ምስክር ከየት ሊመጣ? እርሷን ለማየት ባይጓጉ ነበር የሚደንቀን፡፡

ከሰባ ሁለቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱስ ሉቃስም ወንጌሉን ሲጽፍ በሕይወቷ ውስጥ የተፈጸሙ እርሷ ብቻ የምታውቃቸውንና ብቻዋን ሆና የሰማቻቸውን እንደ ብሥራት ያሉ ታሪኮችን በመንገር እረድታዋለች፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ በቃልም በመጽሐፍም አይሁድን ተከራክሮ ድል ባደረጋቸው ጊዜ፣ ተቆጥተው ድንጋይ ሲያነሡበትና ሲከቡት ከሩቅ በማየቷ የሰማዕትነት ሥራውን በጽናት ይፈጽም ዘንድ በጸሎቷ እንዳበረታችው በጥንታውያን የታሪክ መዛግብት ሰፍሮ እናገኛለን፡፡

እመቤታችንን የማየት ዕድል ካገኙት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስ እርሷን ባየ ጊዜ ሐዋርያቱ ሰው መሆኗን ባይነግሩት ኖሮ አምላክ መስላው እንደ ነበር ጽፏል፡፡ የፊቷን ደም ግባትና ሰላም፣ በእርሷም ላይ ይንጸባረቅ የነበረውን የቅድስና ብርሃን አይቶ በልጇ የማያምን እንደ ሌለም መስክሯል፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙርና የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ የነበረው ቅዱስ አግናጥዮስም ለመምህሩ (ቅዱስ ዮሐንስ) በላከለት መልእክት፣ ክርስቲያኖች በሚሳደዱበት በዚያ ዘመን የእግዚአብሔር እናቱ እመቤታችን በስደቱ ደስተኛ እንደ ሆነች፣ በመከራዎችም ውስጥ ሆና እንደማታጉረመርምና እርሷንም ይነቅፉ በነበሩ ሰዎች እንዳልተቆጣች ይናገራል፡፡

እመቤታችን በልጇ ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ታሪኮች የተፈጸሙባቸውን ስፍራዎች መጎብኘት ትወድ ነበር፡፡ የልደቱን ነገር፣ የእረኞችና የመላክቱን ዝማሬ፣ የጥበበኞቹን ስጦታ አስባ ቤተልሔም ትሄዳለች፡፡ ከሁሉም በላይ ግን መከራ ወደ ተቀበለበት ስፍራ መሄድ ታዘወትራለች፡፡ በዚያም የተቀበላቸውን ሕማማት፣ የደረሰበትን ተዋርዶ እና መከዳቱን እያሰበች ታነባለች፡፡ ‹ይህ ልጄ የተገረፈበት፣ ይህ የእሾህ አክሊል የተቀዳጀበት፣ ይህ ደግሞ መስቀል ተሸክሞ የሄደበት፣ ይህ የተሰቀለበት ነው› ትላለች፡፡ ወደ መቃብሩ ስፍራ ስትመጣ ግን በልዩ ደስታ እየተሞላች ‹‹ይህ በሦስተኛው ቀን ከሞት የተነሣበት ቦታ ነው›› ትል ነበር፡፡

በተሰጣት ቃል ኪዳን እኛ ኃጥአን የሆንን ልጆቿን ታስምረን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
223🙏21❤‍🔥3👍3🔥3🥰2😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?!በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡

ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምእመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
163🙏10👍8👏1
አዳም "አትብላ" ለሚለው የመጀመሪያ ድምጽ ቢታዘዝ ኖሮ፣ "አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ" የሚለውን ሁለተኛውን ድምጽ ባልሰማ ነበር።

"ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍና (pig philosophy) እንተው።

"ነገ እንሞታለንና እንጹም!"

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
322🙏40🥰15😢4👏3
በመንገድ እየሄድህ ሳለ በድልድይ ስር ስታልፍ ድንገት ከላይ የሚንጠባጠብ የቆሸሸ ውኃ ቢነካህ ሁኔታው ሊያናድድህ ይችላል። ነገር ግን ያ ቦታ እንደሚያፈስ እያወቅህ ተመላልሰህበት ከበሰበስህ ግን ጥፋቱ የአንተ እንጂ የማንም አይደለም። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚለው አንዳንዴ ልክ እንደዚያ ጠብታ ሰይጣን ወደ ኅሊናህ ሊያስገባ የሚሞክረው ነፍስህን የሚያቆሽሽ ክፉ ሐሳብ ይኖራል። አንዴ የነካህ ክፉ ሐሳብ ግን ተመላልሶ እንዲያቆሽሽህ ከፈቀድህ ተወቃሹ አንተ እንጂ ሰይጣን አይሆንም።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
277🙏25👍16🔥3
“በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።”
ዳን 10:21

እንኳን አደረሰን!
327🙏23🥰10
“ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ”

ኢሳይያስ 57:15
206🙏11👏8
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ኃምሌ አምስት ቅዱሱ ሰማዕትነት በተቀበለበት እለት እጃችሁ ትገባለች!!!
396🔥15👏12👍11❤‍🔥7🙏4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅዱስ ጳውሎስ እና ደማስቆ!
127👍7
2025/07/14 00:29:32
Back to Top
HTML Embed Code: