Telegram Web Link
እጮኛው ዶ/ር ትንሳዔ እንዲህ ብላን ነበር!

"በመኖር ውስጥ ያገኘሁት የፈጣሪ ፀጋ የቸረኝ እጮኛዬ ነው ዳኒዬ። ነገዬን ያቀድኩት ከእርሱ ጋር ነው። በወጉ ሽማግሌ ልኮ ያስከበረኝ ፍቅሬ ነው። አሁን ታሞብኝ የህክምና ወጪው ከእሱም ከቤተሰቡም ከእኔም አቅም በላይ ሆነብን።

ባደረገው የአጥንት መቅኔ ባዮፕሲ ምርመራ አኪውት ማይሎይድ ሉኪሚያ (የደም ካንሰር) ተገኝቶበታል፡፡ የኢትዮጵያ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቦርድ ወደ ውጭ አገር ሄዶ የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ እንዲደረግለት ወስኗል።

ወዳጆቼ ሆዬ የነገው ባለቤቴ ፤ የዛሬ እጮኛዬ በሰርጌ ዋዜማ ታሞብኛልና ከታች ባስቀመጥኩት አድራሻ ትተባበሩኝ ዘንድ በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ።”

እኛም ይህንን ልብ የሚነካ ጥሪዋን ተቀብለን ኢትዮጵያዊነት ማለት ከትርፋችን ብቻ ሳይሆን ከጉድለታችን መቆረስ መሆኑን በተግባር አስመስክረን በእናንተ ደግነትና በእግዚአብሔር እርዳታ ወንድማችን የተጠየቀው ገንዘብ ሞልቶለት ከታላቅ እህቱ የተለገሰውን የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላውን በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ ተመልሶ ነበር::

ቤተሰቡ እናንተንና እግዚአብሔርን ለማመስገን: ጥንዶቹም ከዚያ ሁሉ ፈተና ማግስት ተስፋቸው እንደገና አንሰራርቶ ጎጆአቸውን ለመቀለስ እየተዘጋጁ እያለ በሽታው ዳግመኛ እንዳገረሸበትና ዳግመኛ አስቸኳይ የአጥንት መቅኔ ንቅለ ተከላ እንደሚያስፈልገው ተሰማ::

ይህች መንፈሰ ጠንካራና በመከራ ጊዜ የማትከዳ ልበ-ወርቅ እጮኛው ዛሬም በፅናት ከጎኑ ቆማ "እኔ በፍቅሬ ተስፋ አልቆረጥኩም! እናንተም ከጎኔ ቁሙ" ብላ ትጣራለች::

ሼር ማድረግም ማገዝ ነው🙏

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ዳንኤል አጥላባቸው
1000289986107

https://gofund.me/64cfcc91
የቁስል ህክምና ራሱን የቻለ ህክምና እንዴት ሊሆን ቻለ?

የቁስል ህክምና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ራሱን የቻለ ህክምና ነው፡፡ ከነርሶች አንስቶ እስከ ሀኪሞች ድረስ የዚህን ህክምና ልዩ ስልጠና (Speciality)  እየወሰዱ የቁስል ህክምናን ያደርጋሉ፡፡ የቁስል ህክምና እንደ ሰርጀሪ ፤ የአጥንት ህክምና እና የፕላስቲክ ሰርጀሪ ካሉት ልዩ ህክምናዎች ጋር በቅርበት ቢዛመድም ከነዚህ ህክምናዎች ጋር አንድ አይነት አይደለም፡፡

የቁስል ህክምናን ምን ልዩ ያደርገዋል?

የተለያዩ ቁስሎች የተለያየ ህክምና ነው የሚያስፈልጋቸው፡፡ በሀገራችን ሁሉም ቁስሎች በአንድ አይነት መንገድ ሲታከሙ ይስተዋላል፡፡ የቁስል ህክምና እያንዳንዱን ቁስል እንደአይነቱ ለይቶ ያክማል፡፡

ሁሉም ቁስሎች በአንድ አይነት ግብዓት (ማቴሪያል) ነው የሚታከሙት?

አይደለም! ቁስሎች እንደ አይነታቸው በተለያዩ ግብዓቶች ነው የሚታከሙት፡፡ ለቁስሎች በቶሎ ወይም በጭራሽ አለመዳን እንደምክንያት የሚጠቀሰው ለዛ ቁስል ተገቢውን ግብዓት አለመጠቀም ነው፡፡

ዶ/ር ፌቨን ሞገስ
ጠቅላላ ሀኪም ፤ የስቶማ እና ቁስል ህክምና አማካሪ

በዶ/ር ፌቨን ለመታከም ከፈለጉ በ 09-73-40-23-86 ደውለው ቀጠሮ ይያዙ፡፡
ማን ነው የተረዳው (ቁ.3)
የረገጥከው መሬት ያለፍከው መከራ
ቀላል አይባልም እንዲሁ የሚወራ
ጦር ካቆሰለው አካሉን ከጎዳው
የውስጥህን ሕመም ማን ነው የተረዳው?
የትላንት መካሪ አለው የምትል ለሰው
አጣሁኝን ማታውቅ ለሁሉ የምትደርሰው
ተረተህ እጅ ብትሰጥ ጊዜ ጣለህና
ወዳጆችህ ራቁ መሳትክን አዩና
እርግጠኛ ሆነው በእነርሱ ጤንነት
በአንተ መንገዳገድ ስምህን ቀየሩት
በሕመም ላይ ሕመም እየጨማመሩ
ባገኙት አጋጣሚ ሊያጠፉህ መከሩ
ወንድ ነው በማለት ሊረዳህ አልሞከረ
በተሳሳተ እሳቤ ስንቱ ከቤት ቀረ
ፆታን መሰረት አድርገው ምኑም ሳይገባቸው
ብዙዎችን አጣን ቀርበን ሳንረዳቸው

ሊያበረቱህ ሲቻል ሕመምክን አባሱ
እርግማን አድርገው ሲገፉህ ሲያንኳሱ
ቡቱቶህን አይተው ሊያዩህ ተጠየፉ
ፊታቸውን አጥቁረው ተረማምደው አለፉ
መጨረሻው ይህነው ወንድ ሆኖ መታመም?
አዎ...በእኛ ማህበረሰብ የሚረዳህ የለም
እናም ተስፋ አትቁረጥ ፈልግ ራስህን
በሌላ የተኩትን ቀይረው ስምህን።


    ናትናኤል ኃይሌ
የስቶማ እና ቁስል ህክምና

ስቶማ ማለት ከትልቁ ወይም ትንሹ የአንጀት ክፍል ለመፀዳጃነት እንዲውል በሆድ በኩል በቀዶ ህክምና የሚበጅ ቀዳዳ ነው። በሀገራችን ከዚህ ሁኔታ ጋር የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በጉዳዩ ላይ ለማማከር  እና ተያያዥ ችግሮችን ለመቅረፍ ልዩ ስልጠና የወሰዱ የህክምና ባለሞያዎች የሉንም። ዶ/ር ፌቨን ሞገስ በስቶማ እንክብካቤ እና ቁስል ህክምና ላይ ልዩ ስልጠና ወስዳ ላለፉት ሁለት አመታት በመዲናችን አ/አ በመስራት ላይ ትገኛለች።

የስቶማ እንክብካቤ የሚያጠቃልላቸው ቅድመ-ቀዶ ህክምና ማማከር ፣ ከቀዶ ህክምና በኋላ ከስቶማ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ተግዳሮቶችን ለማለፍ የሚደረግ አካላዊ እና ስነልቦናዊ እርዳታዎችን ነው።

ከስቶማ እና ቁስል ህክምና ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ዶ/ር ፌቨን በማዘር ኬር ኦፌስ ፕራክቲስ ዘወትር ማክሰኞ ፣ ሀሙስ እና ቅዳሜ ትገኛለች።

ቀጠሮ ለማስያዝ በ0973402386 ይደውሉ። ክፍለሀገር ላሉ ታካሚዎች የስልክ ማማከር አገልግሎት እንሰጣለን።

ስቶማ መፍትሄ እንጂ ችግር አይደለም።
Narrative Exposure Therapy (NET) is a trauma-focused therapeutic approach designed to help individuals process and integrate traumatic memories through storytelling. By constructing a coherent narrative of their life experiences, clients can confront and reframe their trauma, reducing symptoms of PTSD.

Betel Abrham is a Clinical psychologist with more than a decade of clinical experience who is available every Tuesday and Sunday at 11:00 am-4:00 pm.

📌For more info & booking

📞0953-40-41-42
📞0116-67-69-79
📞0963-26-94-87

📍Figa traffic light 155 m on the way to Goro.

Asheten Psychiatry and Rehabilitation Center
Mark your calendars for October 27 and get ready for an eye-opening Mental Health Awareness event hosted by Ubuntu Psychological Services in collaboration with Why Global and Rotaract club of Lewet!☺️

We’re excited to introduce two outstanding panelists:

• Dr. Dawit Assefa (MD, Psychiatrist)—former CEO of Amanuel Mental Specialized Hospital, past President of the Ethiopian Psychiatric Association, and the brilliant mind behind the novel “YeHulu.”

• Petros Hagos, a senior clinical psychologist at Erq Maed and Lebeza Psychiatry Clinic, with a wealth of experience in guiding mental wellness.

Join us as they take you on a journey to uncover the secrets of resilience and how to thrive through life’s challenges. 🤗

This is one event you won’t want to miss!😌

📅 Date: Sunday, October 27, 2024
Time: Begins at 1:00 PM |7:00LT
📍 Location: Atmosphere, Bole behind Alem Cinema
http://surl.li/bftgdy

Follow Us 👇
Instagram | Facebook | Linkedin | Telegram
#EmbracingChange #MentalHealthAwareness #Resilience
የምስራች --- ምክር ብሉ!
================

የምስራች ሲባል "ምስር " ብሉ ማለት ቀርቶ "ምክር" ብሉ መባል በጀመረበት ወቅት ደፍሬ የምስራች ለምስራቅ ኢትዮጲያ እንዲሁም ለድሬደዋ ነዋሪዎች በሙሉ እላለው፡፡ ምንም እንኳን የአዕምሮ ህመም በምስራቁ የሀገራችን በብዛት ቢታይም ይህንን ያማከለ እና ለአእምሮ ህክምና ታስቦ የተዘጋጀ ህክምና ማዕከል አለመኖሩ ብዙውን የምስራቅ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ እንዲያማትር ሲያስገድደው አስተውለናል፡፡ ይህንን መጉላላት ለመቅረፍ ቤካንሲ ልዩ የአዕምሮ ህክምና ለምስራቅ ሀረርጌ እንዲሁም ድሬደዋ "ምክርም ምስርም ብሉ" ብሎ በተዳረጀ ምልክ ብቁ ከሆኑ የአእምሮ ህክምና እና ስነልቦና ባለሞያዎች ድሬደዋ ላይ ከትሞ ይጠብቆታል፡፡

አድራሻ፡- ኢትዮጲያ ፣ ድሬደዋ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
+251920016898
ማህበራዊ ድህረገፃችንን ተቀላቀሉ
Telegram:- https://www.tg-me.com/Bekansipsyc
Tiktok:- https://www.tiktok.com/@bekansi01?_t=8rf7RzbOksx&_r=1
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=61568832854930
የጭንቀት ህመም ስሜቱ ምን ይመስላል?
==========================
ወንበር ላይ ተቀምጠህ የወንበሩ የጀርባ መደገፊያ ላይ ጀርባህን አስደግፈህ በአንድ እጅህ የጠረጴዛ ጫፍ ይዘህ የወንበሩን የፊት እግሮች ከመሬት ከፍ እያደረግህ ወደ ኋላ ለጠጥ ትላለህ። ለጠጥ ለጠጥ ስትል የሆነች ነጥብ ላይ ስትደርስ ልትወድቅ የሚመስል ልብን ስውር የምታደርግ ቦታ አለች። እሷን ስሜት አወቅሀት? Generalized anxiety disorder (የአጠቃላይ ጭንቀት ህመም) ያለባቸው ሰዎች ሁልጊዜ እንደሱ ነው የሚሰማቸው።

ፈተና ልትገባ ስትል ያለው ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ ሰውነት መወጣጠር፣ ሀሳብ ብትንትን ማለት...ወዘተ እሱን ስሜት አስታወሴከው ? GAD ያለባቸው ሰዎች ቀን በቀን የሚሰማቸው እንደዛ ነው። ይዜ ስሜት Apprehensive expectation ይባላል። 'የሆነ አደጋ ሊደርስ እንደሆነ ታውቆኛል' ስሜት ልንለው እንችላለን።

ይሄ ስሜት ለአንድ ቀን ከሆነ ኖርማል ነው። ለሳምንታት ከዘለቀ አሳሳቢ ነው። ለ6 ወራት እና ከዛ በላይ ከቆየ ግን መታከም ያለበት ህመም ነው።

ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ከባድ የጭንቀት ስሜት ከተሰማችሁ ቀአቅራቢያችሁ ያለ የአእምሮ ሀኪም ጋር ቀርቦ መታየት ጥሩ ነው። GAD ውጤታማ ህክምና አለው!

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
2025/06/27 02:17:57
Back to Top
HTML Embed Code: