Telegram Web Link
“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline) የተሰኘው ስልጠና በትናንትና ኃሙስ ምሽት እለት ተጀምሯል፡፡

በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

ከነበረብን የኔትወርክ ችግር ውጪ ስኬታማ ነበር፡፡

በኔትወርክ ምክንያት ሃሳቡ ላመለጣቸው በ audio እና በ pdf ቡድኑ ውስጥ ፖስት ይደረጋል፡፡

መመዝገብና ከሚቀጥለው ኃሙስ መቀጠል የምትፈልጉ ያመለጣችሁን የስልጠና ክፍል በaudio እና በ pdf ታገኛላችሁ፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Money Management Skills and Discipline)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሰኔ 19, ሰኔ 26፣ ሐምሌ 3, ሐምሌ 10 እና ሐምሌ 17 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ ለማግኘት በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox ማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ክፍለ-ጊዜ ላመለጣችሁ!

“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
የተሰኘው የአምስት ኃሙሶች ስልጠና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስኬታማ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

ትናንት ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) ማካካሻ በመውሰድ ለመቀላቀል በርካቶች በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጥያቄ መሰረት ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ጠንቃቃ አመኔታ!

የጥንት አባባል፡-

“ከማን ጋር እንደምትገነቡ ተጠንቀቁ፣ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች መሰረቱን ለመጣል ይጠቀሙባችሁና የግንባታውን እና የአጨራረሱን ሂደት ከሌላ ሰው ጋር ያደርጉታል”

ይህ አባባል “ጠርጣራ” ሳይሆን “ጠንቃቃ” እንድንሆን እንዳስታወሰን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የመጀመሪያው ክፍለ-ጊዜ ላመለጣችሁ!

“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” የተሰኘው የአምስት ኃሙሶች ስልጠና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስኬታማ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

ትናንት ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) ማካካሻ በመውሰድ ለመቀላቀል በርካቶች በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጥያቄ መሰረት ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
በሙዳችሁ አትመሩ!

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ስራ በመስራት በሕይወታችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ከሰዎች ጋር ሰላም እየሆናችሁ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ጤናማ አድርጋችሁ ማቆየት አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ስፖርት እየሰራችሁ ጤናማ አካል ልትገነቡ አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ እያነበባችሁ ራሳችሁን ማሻሻል አትችሉም፡፡

• ስሜታችሁ (ሙዳችሁ) ጥሩ የሆነ ቀን ብቻ ዓላማችሁን በመከተል ራእይና ሕልማችሁን ማሳካት አትችሉም፡፡

ጥሩ ቢሰማችሁም ባይሰማችሁም መሰራት ያለባቸው ስራዎች አሉ!

ብትነቃቁም ባትነቃቁም መከናወን ያለባቸው ተግባሮች አሉ!

ብትጓጉም ባትጓጉም መጓዝ ያለባችሁ ጎዳናዎች አሉ!

ጥሩ ሙድ ላይ ብትሆኑም ባትሆኑም መጠበቅ ያለባቸው የሰው-ለሰው ግንኙቶች አሉ!

ቀጣይነት ይኑራችሁ!

መልካም ቅዳሜ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የመጀመሪያው ክፍለ-ጊዜ ላመለጣችሁ!

“የገንዘብ አስተዳደር ክህሎት እና ዲሲፕሊን” የተሰኘው የአምስት ኃሙሶች ስልጠና ትናንትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በስኬታማ ሁኔታ ተጀምሯል፡፡

ባለፈው ሃሙስ ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) ማካካሻ በመውሰድ ለመቀላቀል በርካቶች በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በዚህ ጥያቄ መሰረት ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ስልጠናው ላመለጣችሁ!

ባለፈው ኃሙስ ሰኔ 19 የተጀመረውን ስልጠና ዋና ሃሳብ የሚዳስስ እና ሰፊ የጥያቄና መልስ ያካተተ ክፍለ ጊዜ በፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 24 ምሽት ይሰጣል፡፡

ይህ ክፍለ-ጊዜ ተመዝግበው በወቅቱ በኔትወርክ ምክንያት በሚገባ ላልተከታተሉትም የሚጠቅም ነው፡፡

በተጨማሪም ሳትመዘገቡ ያለፈው ስልጠና ያመለጣችሁ ከማክሰኞ በፊት ምዝገባን በማድረግ የማካካሻውን ክፍለ-ጊዜ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

ለስልጠናው ስትመዘገቡና የቴሌግራም ቡድኑን ስትቀላቀሉ ባለፈው ሃሙስ ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) በግሩፑ ውስጥ በቋሚነት ተቀምጦ ታገኛላችሁ፡፡

ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ጊዜ የለኝም!

• የምወዳቸው ሰዎች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ሰዎችን የምጠላበት ጊዜ የለኝም!

• የሚወዱኝ ሰዎች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ለሚጠሉኝ ሰዎች ጊዜ የለኝም!

• የምሰራው ስራ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ለስንፍና ጊዜ የለኝም!

• ለሰዎች የማስተላልፈው ጠቃሚ መልእክት ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ተራ ወሬ ለማውራት ጊዜ የለኝም!

• ያለብኝ ሃገሬንና ሕዝቡን የማገዝ ሃላፊነት ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ለጸብ ጊዜ የለኝም!

• የምመለከታቸው፣ የማዳምጣቸውና የማነባቸው ጠቃሚ ነገሮች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ለተራውና ለወረደው ነገር ጊዜ የለኝም!

• ባለኝ መጠንና አቅም ለሰዎች የመስጠት እድሌ ብዙ ስለሆነ ለሌብነት ጊዜ የለኝም!

• ወደ ራእዬ አቅጣጫ የሚያነሳሱኝ የየእለት ግቦቼ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ለድብርት ጊዜ የለኝም!

• ቤተሰቦቼንም ሆነ ሕብረተሰቤን ለማገልገል ያለኝ ፍላጎት ብዙ ስለሆነ ለበላይነትና ለአጉል ጉልበተኛነት ጊዜ የለኝም!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ስልጠናው ላመለጣችሁ!

ባለፈው ኃሙስ ሰኔ 19 የተጀመረውን ስልጠና ዋና ሃሳብ የሚዳስስ እና ሰፊ የጥያቄና መልስ ያካተተ ክፍለ ጊዜ በፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 24 ምሽት ይሰጣል፡፡

ይህ ክፍለ-ጊዜ ተመዝግበው በወቅቱ በኔትወርክ ምክንያት በሚገባ ላልተከታተሉትም የሚጠቅም ነው፡፡

በተጨማሪም ሳትመዘገቡ ያለፈው ስልጠና ያመለጣችሁ ከማክሰኞ በፊት ምዝገባን በማድረግ የማካካሻውን ክፍለ-ጊዜ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

ለስልጠናው ስትመዘገቡና የቴሌግራም ቡድኑን ስትቀላቀሉ ባለፈው ሃሙስ ያለፋቸውን ስልጠና በ audio እና note (Manual) በግሩፑ ውስጥ በቋሚነት ተቀምጦ ታገኛላችሁ፡፡

ይህንን እድል በመጠቀም ለመቀላቀል የምትፈልጉ በዚህ 👉🏼 @DrEyobmamo የቴሌግራም user name inbox በማድረግ ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
ተረጋጉ!

ስትበሳጩና ስሜታዊ ምላሽ ስትሰጡ ያንን እንድታደርጉ ያደረጓችሁ ሰዎች እና ሁኔታዎች በእናንተ ላይ ኃይልን ስለሚያገኙ በቁጥጥራቸው ስር ያደርጓችኋል፡፡

ሁሉም ነገር ስሜታዊ ምላሽ አያስፈልገውም፡፡

የሰዎች ንግግር ከውስጣችሁ አልወጣ እያለ ከተቸገራችሁ . . . ለሰዎች ንግግርና ሁኔታ ሁሉ ምላሽ የመስጠት መነሳሳት ካላችሁ . . . ኃይላችሁን እያስቀማችሁ ነው፡፡

• ዝምታ ኃይል ነው!

• ከአንዳንድ ሁኔታዎች ዘወር ማለትም ኃይል ነው!

• ስሜትን ወዲያው ከመግለጽ ቆጠብ ስትሉም ኃይል ነው!

ስትረጋጉ እና ከስሜታዊነት ይልቅ በምክንያታዊነት ምላሽ ስትሰጡ ኃይላችሁን በራሳችሁ ቁጥጥር ስር ታደርጋላችሁ፡፡

መረጋጋት የአቅመ ቢስነት ምልክት ሳይሆን የብስለትና የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡

ተረጋጉ! የስሜታችሁን ቁልፍ ለማንም ሰውና ለምንም ሁኔታ አሳልፋችሁ አትስጡ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ልጆችሁን 24 ሰዓት ተመልከቷቸው!
ልጆችሁን 24 ሰዓት ተመልከቷቸው!

ለወላጆች . . .

ልጆቻችሁ ከተወለዱበት ቀን አንስቶ
መዳህና መራመድ እስከሚችሉበት እድሜ ድረስ በራሳቸው ምንም ነገር ለማድረግ የሚችል አቅም ስለሌላቸው 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ መዳህና መራመድ ወደመጀመር ሲሸጋገሩ በድንገት ከፊታችሁ ሊሰወሩና ለአደገኛ ነገር ሊጋለጡ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ማድመጥ፣ መገንዘብና መናገር ሲጀምሩ የተለያዩ አይነት ሃሳቦች ሊያስተናግዱና የአመለካከት ብክለት ውስጥ ሊገቡ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ኤሌክተትሮኒክሶችን ማብራትና ማጥፋት ወደመልመድ ደረጃ ሲደርሱ በተለያየ አይነት ዘመን አመጣሽ ነገር ተጽእኖ ውስጥ ሊወድቁ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ጓደኛ ማበጀትና ከሌሎች ልጆች ጋር መገናኘት ሲጀምሩ የተለያዩ አይነት አጉል ባህሪዮችን ሊወርሱ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ትምህርት ቤት መሄድ ሲጀምሩ ለተበላሸና ልቅ ለሆነ የትምህርት ፍልስፍና እና ስርአት ሊጋለጡ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ለጆቻችሁ መሀከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲደርሱ ለአቻ ግፊትና ለጉልበተኞች (bullies) ስለሚጋለጡና ወደማፈልጉት የስሜት ውጥረት ውስጥ ስሚገቡ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ወደ ጉርምስና እድሜ ክልል ውስጥ ሲገቡ ከሚከተለው የተፈጥሮ ሆርሞን ለውጥ የተነሳ ለተለየ ስሜታዊ ምላሽና አጉል ልማድ ሊጋለጡ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

ልጆቻችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡና በራሳቸው መንቀሳቀስ ሲጀምሩ ለተለያዩ አይነት ተስፋ አስቆራጭ ጫናዎችና አሳሳች ፍልስፍናዎች ሊጋለጡ ስለሚችሉ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው፡፡

በአጭሩ ልጆችሁ አድገው ራሳቸውን እስከሚችሉ ድረስ 24 ሰዓት ተመልከቷቸው!!!

24
ሰዓት መመልከት ማለት ለእድሜያቸውና ላሉበት ሁኔታ የሚመጥን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ማለት ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
2025/06/29 15:42:42
Back to Top
HTML Embed Code: