Telegram Web Link
የፓሬቶ መመሪያ
11👍2
የፓሬቶ መመሪያ
(“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በፈረንጆች አቆጣጠር በ1897 ዓ.ም. ቪልፍሬዶ ፓሬቶ የተሰኘ ጣሊያናዊ ኢኮኖሚስት በ19ኛው ክፍለ ዘመን በሃገሩ ውስጥ ያለው የብልጽግና ሁኔታና ሃብት በማን እጅ እንዳለ ጥናት ሲያደርግ አንድን እውነት አገኝ፡፡ አብዛኛው መሬትና የገንዘብ ገቢ ጥቂት በሆኑ ዜጎቿ እጅ እንዳለ ተገነዘበ፡፡ እንደውም ጠለቅ ብሎ ሁኔታውን ሲያጠናው፣ 20 በመቶው የአገሩ ህዝብ 80 በመቶውን የአገሪቱን ሃብት በቁጥጥሩ ስር እንዳደረገና እንደሚያንቀሳቅስ ተረዳ፡፡

ይህን ግኝት የ80 በ20ው መርህ በመባል ይታወቃል፡፡ የሚከተሉትን የዚህ መርህ አመላካቾች ናቸው በመባል የሚታወቁትን ነጥቦች እንመልከት፡፡

• 20 በመቶው ወንጀለኛ 80 በመቶውን ወንጀል ይሰራል፡፡
• 20 በመቶው ሹፌር ለ80 በመቶው የመኪና አደጋ ተጠያቂ ነው፡፡
• 20 በመቶው ባለትዳር 80 በመቶውን ፍቺ ይፈጽማል፡፡
• 20 በመቶው መንገድ 80 በመቶውን መኪና በማስተናገድ ይጨናነቃል፡፡
• 20 በመቶውን ልብሶቻችንን 80 በመቶ ጊዜ እንለብሳቸዋለን፡፡
• 20 በመቶው የመጽሐፍ ክፍል 80 በመቶውን ቁም ነገር ይይዛል፡፡

ይህ የ80 በ20ው የተሰኘው መርህ በሕይወታችን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ተግባራዊ ለማድረግ የሚከተሉትን ሁኔታዎች እናጢን፡፡

የቀን ውሎአችንን አስመልክቶ - 80 በመቶ ጊዜያችንን ዓላማችን ባለበትና ወደ ግባችን በሚያራምደን ነገር ላይ፣ 20በመቶውን ጊዜአችንን ደግሞ ከዚያ ባነሱ ነገሮች ላይ ማሳለፍ፡፡

ሰዎችን አስመልክቶ - 80 በመቶውን ጊዜያችንን ከዓላማችን ጋር ከሚራመዱ፣ ከሚወድዱን፣ ከሚቀበሉንና ከሚደግፉን ሰዎች ጋር፣ 20 በመቶውን ጊዜያችንን ደግሞ ስለ እኛ ብዙም ግድ ከማይላቸው ሰዎች ጋር ማሳለፍ፡፡

የምናነባቸውን መጻሕፍት አስመልክቶ - 80 በመቶው የምናነባቸው መጻሕፍት ከዛሬው ስራችን ጋር የተያያዘን ብቃታችንን የሚያሳድጉልንና መሆንና ማድረግ ከምንፈልጋቸው የወደፊት ራእዮቻችን ጋር የተያያዙ፣ 20 በመቶው መጻሕፍት ደግሞ ለመዝናናትም ሆነ ለተለያዩ መረጃዎችና ለመሳሰሉት የምናነባቸው መጻሕፍት ቢሆኑ ስኬት ይሰፋል፡፡

በቅዳሜና በእሁድ እረፍታችሁ መጽሐፉ ይነበብ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
28👍10
ሰዎች ስኬታማ የሚሆኑት!

አንዳንዶች እደዚህ ሲሉ ይደመጣሉ፡- “ስኬታማና ቢዚ ስሆን ጊዜዬን በሚገባ የማደረጃትን ስልት አዳብራለሁ”፡፡

ሁኔታው ግን የዚያ ተቃራኒ ነው፡፡ ስኬታማና ቢዚ የሆኑ ሰዎች እንደዚያ የሆኑት ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም ስጀመሩ ነው እንጂ ቢዜ ስለሆኑ አይደለም ጊዜያቸውን በትክክል መጠቀም የጀመሩት፡፡

የእነዚህን ሁለት ነገሮች ቅደም ተከተል ማዛባት፣ ፈጽሞ የማይመጣን ነገር ስንጠብቅ ጊዜያችንን እንድናባክን ያደርገናል፡፡

ጊዜያችሁን በሚገባ መጠቀም ስትጀምሩ ስኬታማ እየሆናችሁና ቢዚ እየሆናችሁ መሄዳችሁ አይቀርም፡፡

ስለዚህ፣ ጊዜያችሁን በሚገባ በማደራጀት አሁኑኑ ጀምሩ፣ የቀረው ተከትሎ ይመጣል፡፡

ይህንን ልምምድ ለማዳበር አቅጣጫ የሚያሳያችሁ ስልጠና ስለተዘጋጀ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ሰልጥኑ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
26👍11🔥1
ሁለት አይነት አሰቃቂ ልምምዶች (traumas)

የtrauma ልምምድ፣ ሰዎች በአንድ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፉ የሚከሰት ቀውስ ነው፡፡

አሰቃቂ ልምምዶች (traumas) በሁለት መልኩ ሊከሰቱ ይችላሉ:-

1. የልጅነት አሰቃቂ ልምምዶች (childhood traumas)

ይህ ልምምድ ሰዎች በልጅነታቸው ካሳለፉት አሰቃቂ ሁኔታ የተነሳ የሚከሰት ነው፡፡ አካላዊ ድብደባ፣ ከቃላት የመጣ ስነ-ልቦና ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ እንደ ልጅ ሳይጫወቱና ከባድ ስራ እየሰሩ ማደግና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

2. የዘር አሰቃቂ ልምምዶች (generational traumas)

ይህ ልምምድ አንድ ቤተሰብ ካሳለፋቸው አሰቃቂ ሁኔታዎች የተነሳ የዚያ ልምምድ ተጽእኖ ወደ ልጅ እና ወደ ልጅ-ልጅ ሲተላለፍ የሚከሰት ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በዘር ጥላቻ ውስጥ ያለፈ ቤተሰብ፣ በቤተሰብ ሲወርድ-ሲዋረድ የመጣ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ችግር፣ በወላጆቻችንና ከእነሱም በፊት በነበሩ የቤተሰብ አባላት የምናያቸው የተወሰነ መንገድ ከሄዱ በኋላ ተመልሶ እዚያው የመገኘት ልምምድ እና የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በግል ሕይወታችን እንደዚህ አይነት ልምምዶች ካስተዋል የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ ያንን ካላደረግን፣ ቀውሱ እኛን ለቀውስ ከመዳረግ አልፎ ወደ ትዳራችንና ወደ ልጆቻችን ማለፉ አይቀርም፡፡

መፍትሄ
1. ጸሎት ማድረግ

2. የሰዎችን ድጋፍ ማግኘት

3. ያለፈውን በመጣል የወደፊትን ዓላማና ራእይ ማንሳት

እነዚህን መሰረታዊ ልምምዶች ሞክረን መፍትሄ ማግኘት ካልቻልን፣ ሞያዊ ምክር (therapy) ማግኘት የግድ ነው፡፡

ለሞያዊ ምክር ጥያቄ ለማቅረብ ዶ/ር ኢዮብ ማሞን በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡
49👍15
ጊዜያችንን በትክክል ስንጠቀም!

⏱️ የበለጠ ገንዘብን ለመስራት የሚያስችል አደረጃጀት ይኖረናል፡፡

⏱️ ብዙ ስራ ለማከናወን በቂ ጉልበት ይኖረናል፡፡

⏱️ በትክክለኛው ነገር ላይ የማተኮር ብቃት ይኖረናል፡፡

⏱️ በማይሆን ስፍራና ሁኔታ ላይ ስለማናሳልፍ ስሜታችንን የመቆጠብ እድል ይኖረናል፡፡

ጊዜያችሁን በትክክል ተጠቀማችሁ ማለት ሕይወታችሁን በትክክል ተጠቀማችሁ ማለት ነው፡፡

በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ በቂ የሆነን ስልጠና ለማግኘት መመዝገባችሁን አትርሱ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
24👍2

6👍4
Student Discount!

“ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)
ለተሰኘው ስልጠና ለተማሪዎች የተደረገ ቅናሽ!

በርካታ የ Highschool እና የ University (College) ተማሪዎች ካላችሁ የገንዘብ እጥረት የተነሳ የስልጠናው ክፍያ ቅናሽ እንዲሰጣችሁ በጠየቃችሁት መሰረት ያንን እድል አዘጋጅተንላችኋል፡፡

በተደረገው ቅናሽ ተጠቃሚ ለመሆን ፍላጎታችሁን ከዚህ በታች ባለው የ telegram link ሙሉ ስማችሁንና የምትማሩበትን ትምህርት ቤት ስም መላክና ከቅናሹ ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
16👍5
የማደጊያው መንገድ!
🔥3
የማደጊያው መንገድ!

አንድ ባለሃብት ገበሬ በሚኖርበት ከተማ ውስጥ አንድ ትልቅ ፋብሪካ፣ ከከተማው ወጣ ብሎ ደግሞ አንድ እርሻ አለው፡፡ ይህ ባለሃብት አንድን ሰራተኛ ጥሩ ክፍያና የእድገት እድል ባለው በፋብሪካው ውስጥ ለመቅጠር ሲፈልግ ስራ ፈላጊውን በመጀመሪያ በእርሻው ከቀጠረው በኋላ ለፋብሪካው ብቁ መሆኑን የሚያይበት መንገድ አለው፡፡ በዚህ አሰራሩ መሰረት አንድን ሰው ቀጠረው፡፡

በመጀመሪያ የከብቶቹን ማደሪያ በረት ቀለም እንዲቀባ ስራ ሰጠውና ወደ ሶስት ቀን ሊፈጅበት እንደሚችል ነገረው፡፡ ሰራተኛው ግን አንድ ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡ ያንን የተመለተው ገበሬ በመገረም ሌላ ስራን አዘጋጀለት፡፡

ሁለተኛ የሰጠው ስራ በግቢው ውስጥ የተከመረ እንጨት የመፍለጥ ስራ ነበር፡፡ ይህ እንጨት ብዙ ስለሆነ አራት ቀናት እንደሚፈጅበት ነገረውና ሄደ፡፡ ቅጥረኛውም ገበሬው እስከሚገረም ድረስ በአንድ ቀን ተኩል ፈልጦ ጨረሰው፡፡ ገበሬው አሁንም በመገረም ሌላን ስራ ሰጠው፡፡

ይህኛው ስራ፣ ገበሬው አምርቶ ያከማቸውን መጠነ-ትንሽ የድንች ምርት በሶስት ከፋፍሎ ማስቀመጥ ነበረ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ለዘር የሚሆኑ ድንቾች፣ በሁለተኛ ደረጃ፣ ለከብቶች ምግብነት የሚውሉ ድንቾች፣ ሶስተኛ፣ ለሽያጭ የሚቀርቡ ድንቾችን መለየት ነበር፡፡ ይህ ስራ እጅግ በጣም ትንሽና ቀላል ስለነበረ ግማሽ ቀንም እንደማይፈጅበት ነገረው፡፡

በቀኑ መጨረሻ ላይ ገበሬው ከቀን ስምሪቱ ሲመለስ ይህ ሰራተኛ እንኳን ስራውን ሊጨርስ ቀርቶ ምንም እንዳልጀመረው ደረሰበት፡፡ ገበሬውም ሰራተኛውን፣ “ምነው ስራውን ጭራሹንም አልጀመርከውም” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሰውየውም፣ “እኔ ብዙ ስራ በትጋት መስራት እችላለሁ እንጂ ማሰብ፣ መምረጥና መወሰን ያለበት አይነት ስራ አይመቸኝም ፣ ብዙ ችሎታም የለኝም” አለው፡፡

ባለሃብቱም ለቅጥረኛው፡- “የሰራኸውን አይነት የጉልበት ስራ በመስራት መቀጠል ከፈለክ በዚሁ መልክ መቀጠል ትችላለህ፡፡ ከዚህ የተሻለ የስራ እርከንና የገንዘብ እንድገት ደረጃ ላይ መድረስ ከፈለክ ግን በግል የማሰብን፣ የመምረጥን፣ የመወሰንንና በወሰኑት ነገር ላይ ደግሞ ተግባራዊ ሰው የመሆንን ክህሎት ማዳበር የግድ ነው” አለው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ምንም ያህል አድካሚና ጊዜ የሚፈጅ ስራን ቢሰጣቸው ጠዋት ወጥተው ማታ እስሚገቡ ድረስ ሲለፉ መዋል ችግር የለባቸውም፡፡ ማሰብን፣ ምርጫን፣ ውሳኔንና በድፍረት የመንቀሳቀስን አይነት ስራ የመስራቱ ድፍረቱም ሆነ ክህሎቱን ለማዳበር ግን ብዙም ግድ አይሰጣቸውም፡፡

ለማደግ ከፈለጋችሁ በትጋት የመስራት ልማዳችሁ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚያ ላይ በግል የማሰብን፣ የመምረጥን፣ የመወሰንንና የተግባራዊ እርጃን ክህሎት ማዳበር የግድ ነው፡፡ የዘመኑ የእድገት እድል ያለው ለእነደዚህ አይነት ሰዎች ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
42👍16🔥6
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
Join Our Book Club with Dr. Eyob!

Book Reading Challenge!

📖 ለሕዳር ወር የተመረጠው መጽሐፍ “የመኖር አቅም” (New Book)

📖 መጽሐፍ የማንበቡ challenge የሚጀመረው ሕዳር 1/2018

አሁን በምንኖርበት ዘመን ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ የመኖር አቅምን የሚያሳጡ አስቸጋሪ ገጠመኞች የምንጋፈጥበት ዘመን ነው፡፡

እነዚህ የየእለት ሕይወታችንን አስቸጋሪ የሚያደርጉ ሁኔታዎች፣ በአንድ በኩል ከራሳችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሲነኩ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰዎች ጋር ካለንን ግንኙነት ጋር ይነካካሉ፡፡

እነዚህን ሁለት የግንኙነት ዘርፎች በትክክለኛው መንገድ መያዝ፣ የየእለት ሕይወታችንን በብርታት ለመኖር አቅም እንድናገኝ ያግዘናል፡፡

በእነዚህ የግንኙት ዘርፎች ጥበብ-የለሽ አቀራረብ ሲኖረን ደግሞ የመኖር አቅማችንን እያደከመው ይሄዳል፡፡

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ምእራፎች በእነዚህ በተጠቀሱት የራስ-በራስ እና የሰው-ለሰው የግንኙነት ዘርፎች ዙሪያ አቅም አሳጪ ሁኔታዎች እንድንለይ አቅጣጫ ያሳየናል፡፡ በተጨማሪም፣ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በብርታት ለማለፍ እንድንችል ዘመን-ዘለል መመሪያዎች እናገኛለን፡፡

ይህንን Book Reading Challenge ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Dr. Eyob Mamo
27👍4
አዋቂው መሪ!

ለመሪዎች . . .

(“አመራር A to Z” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

መሪ ሁሉን ነገር ያውቃል ወይም ማወቅ አለበት ብሎ ማመን በፍጹም የማይታለም ነው፡፡ ሆኖም፣ መሪ በሚመራው ተቋም ዙሪያ በቂ እውቀት ቢያዳብር ተጽእኖውን የሰፋ ያደርገዋል፡፡

መሰረታዊ እውቀት የጎደለው መሪ ዘወትር በሌሎች ሰዎች እውቀት ተደግፎ ከመኖሩም በላይ በሚሰራው ስራ ዙሪያ ውጤታማነትን ለመገምገም እንኳ መሰረታዊ ብቃት አይኖረውም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ አይነት መሪዎች ወደ አመራር የሚመጡት ባላቸው ብቃት ሳይሆን በዚያ ስፍራ እንዲከናወን ከተፈለገው ከተቋሙ ዋና ዓላማ ውጪ ከሆነ አጀንዳ የተነሳ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአድሎና ግልጽ ተወዳዳሪነት በሌለበት አሰራር አማካኝነት ወደ አመራር ይመጣሉ፡፡

ስለእውቀትና ተጽእኖ ግንኙነት ካነሳን አይቀር ከጥንታዊ አባባል የተጨመቁትን የሚከተሉትን አራት አይነት ሰዎች አገላለጽ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው፡፡

1. የማያውቅ እና እንደማያውቅ የማያውቅ፡- እንዲህ አይነቱ ሰው ሞኝ ነውና አትከተለው፡፡

2. የማያውቅ እና እንደማያውቅ የሚያውቅ፡- እንዲህ አይነቱ ሰው ያልበሰለ ነውና አስተምረው፡፡

3. የሚያውቅ እና እንደሚያውቅ የማያውቅ፡- እንዲህ አይነቱ ሰው ያንቀላፋ ኃያል ነውና ቀስቅሰው፡፡

4. የሚያውቅ እና እንደሚያውቅ የሚያውቅ፡- እንዲህ አይነቱ ሰው መሪ ነውና ተከተለው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
46👍14🔥5
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
Book Club! With Dr. Eyob

Book Reading Challenge!!!

የንባብ ወር፡- ሕዳር፣ 2018

ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ፡- “የመኖር አቅም” (አዲስ መጽሐፍ)

ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Dr. Eyob Mamo
29👍3🎉1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
Join Our Book Club with Dr. Eyob!

Book Reading Challenge!

📖 ለሕዳር ወር የተመረጠው መጽሐፍ “የመኖር አቅም” (New Book)

📖 መጽሐፍ የማንበቡ challenge የሚጀመረው ሕዳር 1/2018

አሁን በምንኖርበት ዘመን ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ የመኖር አቅምን የሚያሳጡ አስቸጋሪ ገጠመኞች የምንጋፈጥበት ዘመን ነው፡፡

እነዚህ የየእለት ሕይወታችንን አስቸጋሪ የሚያደርጉ ሁኔታዎች፣ በአንድ በኩል ከራሳችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሲነኩ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰዎች ጋር ካለንን ግንኙነት ጋር ይነካካሉ፡፡

እነዚህን ሁለት የግንኙነት ዘርፎች በትክክለኛው መንገድ መያዝ፣ የየእለት ሕይወታችንን በብርታት ለመኖር አቅም እንድናገኝ ያግዘናል፡፡

በእነዚህ የግንኙት ዘርፎች ጥበብ-የለሽ አቀራረብ ሲኖረን ደግሞ የመኖር አቅማችንን እያደከመው ይሄዳል፡፡

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ምእራፎች በእነዚህ በተጠቀሱት የራስ-በራስ እና የሰው-ለሰው የግንኙነት ዘርፎች ዙሪያ አቅም አሳጪ ሁኔታዎች እንድንለይ አቅጣጫ ያሳየናል፡፡ በተጨማሪም፣ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በብርታት ለማለፍ እንድንችል ዘመን-ዘለል መመሪያዎች እናገኛለን፡፡

ይህንን Book Reading Challenge ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡

Dr. Eyob Mamo
18👍9
የተቃርኖ ሱስ!
5👍1
የተቃርኖ ሱስ!

አንዲት ከእድሜዋ ጋር አብሮ የመጣውን የስሜት እብጠትና ንዝረት በቅጡ መያዝ ያቃታት የአስራ አምስት አመት ልጅ (ቲን ኤጀር) ከጓደኞቿ ጋር ወደ አንድ ጫማ ሱቅ ገብታ በጣም የወደደችውን ጫማ ስላገኘችና እጇ ላይ የነበረው ብር በቂ ስለነበር ገዛችው፡፡ ጫማውን ከመውደዷ የተነሳ እቤቷ በመሄድ ነገ ነግቶላት ጫማውን እስከምታደርገው ከመናፈቋ የተነሳ ከትራሷ አጠገብ ነበር ያሳደረችው፡፡

በነጋታው ቤተሰቦቿ ወደ ስራ ከመውጣታቸው በፊት የገዛችውን ጫማ አድርጋው ስላተመለከቱ በምርጫዋና በጫማው ውበት በጣም ስለተደሰቱ እንደወደዱት ነገሯት፡፡

ይህቺ ልጅ ቤተሰቦቿ ገና እንደወጡ ወደ ጫማ ቤቱ በመሄድ ጫማውን መልሱልኝ በማለት ተማጸነች፡፡ የጫማ ሱቁ ባለቤት ያን ያህል የወደደችውን ጫማ ለምን ለመመለስ እንደፈለገች ሲጠይቃት መልሷ፣ “ቤተሰቦቼ ስለወደዱት ጫማው አልፈልገውም” የሚል ነበር፡፡ ምንም እንኳን ጫማውን ብትወደውም ቤተሰቦቿ ሰለወደዱት ብቻ ከእነሱ ለመቃረን ጫማውን ማጣት መረጠች፡፡

አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ አይነት የተቃርኖ ዝንባሌና ሱስ አለባቸወ፡፡ በእሱ ላይ የበላይ የሆነ ሰው የሚፈልገውንና የሚወደውን ነገር በሙሉ ልቅም በማድረግ ተቃራኒውን ማድረግ ይወዳሉ፡፡ አንደዚህ አይነት ሰዎች ልክ የጉርምስና እድሜያቸውን የስሜት መፈንዳትና ንዝረት በቅጡ መያዝ እንዳቃታቸው “ጎረምሶች” “አምጽ!” “አምጽ!” የሚል የውስጥ መነሳሳት አላቸው፡፡

ስልጣን ያላቸው ሰዎች የሚያሳዩትን ጤና-ቢስ ባህሪይም ሆነ ሂደት በቅንነት የመሞገት አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ነገር ልምከራችሁ . . .

ቤተሰብ በሚያስተዳድረው ጣሪያ ስር እስከኖራችሁ፣ የሚያቀርቡትን ምግብ እስከተመገባችሁና ለተለያዩ ፍላጎታችሁ መሟላት ከእጃቸው እስከተቀበላች ድረስ ከእነሱ ሃሳብና ሕግ ጋር ተስማምቶ መኖር ይበጃችኋል፡፡

በአንድ ተቋም ወይም መስሪያ ቤት ሰራተኞች እስከሆናችሁ፣ ገንዘብ እስከተከፈላችሁና ኑሯችሁን የሚደግፍ ጥቅማ ጥቅም እስካገኛችሁ ድረስ ከአስተዳደሩ ሕግና ከአሰራር ሂደቱ ጋር ተስማምቶ መኖር ይበጃችኋል፡፡

በአንድ ሃገር ክልል ውስጥ እስከኖራችሁ፣ የዜግነት መብት እስካላችሁና ሰርቶና አሰርቶ፣ አፍቅሮና ተፈቅሮ መኖር እስከቻላችሁ ድረስ ከሃገሩ ሕግ፣ ስርአትና ደንብ ጋር ተስማምቶ መኖር ይበጃችኋል፡፡

ሁል ጊዜ የሚያቃርነንን ከማሰብና ከማድረግ ይልቅ ሁል ጊዜ የሚያስማማንን ማሰብና መተግበር የብሱል ሰዎች ልምምድ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
62👍4🔥2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
12👍1
በመጀመሪያ ችግሩን ለዩ!

ለመሪዎች . . .

እናንተ በምትመሩት ተቋም፣ ማሕህበርም ሆነ ሌላ መስክ ውስጥ የተሰማሩ ሰራተኞች ተግባራቸውን በተገቢውና ምርታማ በሆነ መልኩ ካልሰሩ እርማት ለመውሰድ ከመሞከራችሁ በፊት በቅድሚያ ችግራቸው ምን እንደሆነ ለመለየት መሞከሩ አስፈላጊ ነው፡፡

ይህንን ማድረግ የሚጠቅማችሁ ለሁሉም አይነት ችግር አንድ አይነት መፍትሄ ለመስጠት ከመሞከር እንድትጠበቁ ነው፡፡

1. የባህሪይ ችግር ያለባቸው ሰዎች

ምንም እንኳን በስራው ስልጡን ቢሆኑም ለመመሪያ አለመታዘዝ፣ መለገም፣ አመጸኝነትና የመሳሰሉት ሁኔታዎችን ስለሚያንጸባርቁ ለስራው እንቅፋት ከመሆን አያልፉም፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች በምክርና በተግሳጽ ካልተመለሱ ለእርማት የሚጠቅም ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

2. የዲሲፕሊን ችግር ያለባቸው ሰዎች

የስራ ችሎታውም ሆነ ጨዋ ባህሪይ ይዘው ሳለ አንድን ነገር ጀምሮ ያለመጨረስና የመሳሰሉት ችግሮች ስላሉባቸው ለስራው እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ለስራው የሚመጥንን ተገቢ ዲሲፕሊን እስከሚያዳብሩ ድረስ ጥብቅ ክትትልና ተጠያቂነት ሊደረግላቸው ይገባል፡፡

3. የክህሎት ችግር ያለባቸው ሰዎች

ጥሩ ባህሪይና ዲሲፐልን ቢኖራቸውም እንኳን ስራውን አስመልክቶ በቂ ችሎታ ስለሌላቸው ምንም ቢታገሉም እንኳን የተዋጣለት ስራ መስራት አይችሉም፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች ለስራው የሚመጥንን ክህሎት እንዲያዳብሩ በስልጠና ሊታገዙ ይገባል፡፡

4. ዓላማውንና የሚሰራውን ስራ ያለመገንዘብ ችግር ያለባቸው

ሰዎች ሲጀምሩ የተቋሙን ዋና ዓላማ ስላልተገነዘቡ የሚተገብሩት ነገር ሁሉ ከመስመር የወጣ ነው፡፡

እንደዚህ አይነት ሰዎች የራእይ ገለጻና ክለሳ ሊሰጣቸውና ራእዩን በሚገባ መገንዘባቸውን የሚያረጋግጥ “የቤት ስራ” ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
29👍11🔥4
የባከነ ጊዜ!

“በአንድ በሚፈስ ወንዝ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ማቋረጥ አትችልም” ይባላል፡፡ እውነት ነው!

ሲተነተን፣ ተራምደህ የገባህበት ወንዝ አልፏል፡፡ ውኃው ቀጥሎ ለሚፈስሰው ውኃ ስፍራውን ለቆ በመሄዱ ምክንያት ተመልሰህ ብታቋርጥ ሌላ ውኃ ነው የምታገኘው፡፡ ፍሰቱ ተመሳሳይ ነው፣ ወንዙ ይዞት የሚመጣው ነገር ግን የተለያየ ነው፡፡

የጊዜያችንም ጉዳይ እንደዚሁ ነው፡፡

⏱️ የሰዓታት፡- በየቀኑ ያሉት ሰዓታት በተመሳሳይ ስም ይጠራሉ፣ ይዘውት የሚመጡትና የሚሄዱት ምርጫ ግን የተለያየ ነው፡፡

⏱️ የቀናት፡- ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉን ቀናትም ተመሳሳይ ናቸው፣ ይዘው መጥተው የሚያሳልፉት እድል ግን ልዩ ልዩ ነው፡፡

⏱️ የወራት፡- የወራቶች መምጣትና መሄድ አንድ አይነት ነው፣ ሆኖም የማይገኝ እድልን ይዘው መጥተው ጥርግ ብለው ይሄሉ፡፡

ጊዜ ሲመጣና ሲሄድ ያለው “አንድ አይነትነት” ያታልላል፡፡ የምንባንነው በወቅቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ የማንችልበት ቀን ከመጣና ኋላ ከቀረን በኋላ ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ በጊዜ ለመንቃት የሚያግዝ ስልጠና ተዘጋጅቷልና ተጠቀሙበት፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
38👍17
ጊዜያችሁን አታባክኑ!

⏱️ የተበላሸ ግንኙነት በይቅርታ ይታደሳል፡፡

⏱️ የከሰረ ገንዘብ በብዙ ጥረትና ትጋት ይመለሳል፡፡

⏱️ የተዛባ ጤንነት በህክምና ይስተካከላል፡፡

⏱️ ያጣነው የስራ እድል በሌላ ስራ ይተካል፡፡

⏱️ የባከነ ጊዜ ግን በምንም አይመለሰም፡፡

ይህንን አንዴ ከባከነ የማይመለስ “ጊዜ” የተሰኘ የፈጣሪ ስጦታ በእውቀት፣ በጥበብና በዲሲፕሊን ለመጠቀም የሚያስችለን ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም ስልቶች” (Effective Time Management Strategies)

ስልጠናው የሚሰጠው፡-
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- ሕዳር 4፣ ሕዳር 11፣ ሕዳር 18፣ ሕዳር 25 – 2018 ዓ/ም (አራት የሕዳር ወር ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ:-
ለስልጠናው ለመመዝገብ በዚህ 👉 @DrEyobmamo user name inbox በማድረግ ፍላጎቶን ሲገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክሎታል፡፡

እናመሰግናለን!
21🔥16👍10
የስሜት ብልህነት ልህቀት
4
2025/10/31 06:32:00
Back to Top
HTML Embed Code: