Telegram Web Link
ወይ ፍቱት ወይ አስፈቱት!

የአብዛኛዎቻችን ችግር የማይፈታው ከችግራችን ግዝፈት የተነሳ ሳይሆን ችግር እንዳለብን አምነን እና ከራሳችን ጋር እውነተኛ ሆነን እርዳታን ለማግኘት ፈቃደኛ ባለመሆናችን ነው፡፡

“ችግሬ አንድ ቀን በራሱ ይሄዳል” ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፡፡

ችግራችሁን ፍቱት!

እናንተ መፍታት ካቃታችሁ ደግሞ እርዳታ ጠይቁና አስፈቱት!

ዛሬ እርዳታን ለማግኘት ከምትከፍሉት ጊዜ፣ ገንዘብና የመሳሰሉት ማንኛውም አይነት ክፍያዎች በበለጠ ሁኔታ ያልተፈታው ችግራችሁ የኋላ ኋላ ብቅ ብሎ ያስከፍላችኋል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ከኃዘን ድባብ ውጡ!

አሁን ላላችሁበት ሁኔታ የእናንተ የትናንትና ምርጫና ውሳኔያች መዋጮ ኖረውም አልኖረውም፣ ሙሉ ሃላፊነቱን ካልወሰዳችሁ፣ በኃዘን ድባብ ውስጥ ስለምትኖሩ ወደ ኋላ ትንሸራተታላችሁ፡፡ “ዛሬን እንደዚህ የሆንኩት ከእገሌ የተነሳ ነው” ብለን ማሰባችን፣ መናገራችንና ሰውን መውቀሳችን ከሃላፊነት አያድነንም፡፡

ዛሬ ላለንበት ሁኔታ ሙሉ ሃላፊነት መውሰድ ስንጀምር ነገ ወደየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ጥርት አድርገን ማየት እንጀምራለን፡፡

የትናንትናችንን በመራራነትና በወቃሽነት ስሜት ማሰብ የሚያስከትለው የኃዘን ድባብ የነገውን የማየት አቅማችንን ይጋርደዋል፡፡

ለትናንትናው ስህተት መድሃኒቱ የነገ ራእይ ነው፡፡ የነገን ራእይ ለማየት ደግሞ ዛሬ ላለንበት ሁኔታ ሙሉ ሃላፊነትን በመውሰድ ካለብን ኃዘን መላቀቅ የግድ ነው፡፡

አዲስ ምልከታ፣ አዲስ እቅድ፣ አዲስ ጅማሬ፣ አዲስ ግንኙነት፣ አዲስ ሃሳብ . . . ያዙ! ካለፈው ተማሩ! ያለፈውን ተው! የወደፊት ሕይወታችሁ ያለው ነገ ላይ ስለሆነ ነገን ናፍቁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
እስቲ ሰዎችን ተዋቸው!

በከተማ፣ በመንደር፣ በሰፈር፣ በጉርብትናም ሆነ በስራ . . . አካባቢያችሁ ያሉ ሰዎች በማንነታቸው፣ በመልክ በቁመናቸው፣ በዘራቸው፣ በኃይማኖታቸው፣ በኢኮኖሚ ደረጃቸውና በመሳሰሉት ምክንያት በእናንተ በምንም መልኩና በማንኛውም መጠን አድሎ፣ መገለልና መገፋት ከደረሰባቸው፣ ከተገፉ፣ ከተጎዱ፣ ከፈሩ፣ ከሰጉ . . . ቀናችሁ ያልተሳካ፣ የወደፊታችሁም የጨለመ እንደሆነ ለማስታወስ እወዳለሁ፡፡

እስቲ ሰዎችን ተዋቸው! ይኑሩበት!


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ጥገኝነት

ጥገኝት ማለት በራሳችን ለመቆም ካለመቻላችን ወይም ካለመፈለጋችን የተነሳ በሰዎች ላይ ተደግፈን ስንኖር ማለት ነው፡፡ ለጊዜውና አንድን አስቸጋሪ ሁኔታ እሰከምናልፍ ድረስ በሰው ላይ ጥገኛ መሆን ችግር የሌለውናሁሉም ሰው የሚልፍበት የሕይወት እውነታ ነው፡፡ ነገር ግን ጥገኛ የምንሆንባቸውን ሁኔታዎች መለየት፣ ለምን በሰዎች ላይ ጥገኛ ለመሆን እንደተገደድን መገንዘብና እስከመቼ በዚህ ሁኔታ እንደምንኖር አስበንበት ከሁኔታው የመላቀቅ እቅድ ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡

የሰው ጥገኛ ሆኖ በራሱ ላይ ያለውን ግምት ትክክለኛና ሚዛናዊ አድርጎ ለማቆየት የሚችል ሰው ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ጥገኝነት በራሳችን ላይ ያለንን ግምት ስለሚያወርደው ማለት ነው፡፡ ጥገኝነት መራራ ያደርገናል፣ እኛን ለሚጎዱ ሰዎች አጋልጦ ይሰጠናል፣ የራሳች የሆነ ነገር እንድንገነባ አይፈቅድልንም፡፡

ከላይ እንደጠቀስነው አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኳን ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ ለተወሰነ ጊዜ የሰው ጥገኛ ብንሆንም ከዚያ የመውጣት ፍላጎቱ፣ እቅዱና ጥረቱ ሲኖረው ውስጣችንን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡

ሁል ጊዜ ልንሰራባቸው የሚገቡን የጥገኝነት አይነቶች፡-

1. የገንዘብ ጥገኝነት፡- ራስን ችሎ ለመኖር ካለመፈለግ ወይም ካለመቻል ራስን ወደመቻል ለመሻጋገር እንስራ፡፡

2. የስሜት ጥገኝነት፡- በሰዎች ላይ የስሜት ጥገኛ ከመሆናችን የተነሳ እንደ እነሱ ወቅታዊ ሁኔታ የሚዘባረቀውን ስሜታችን በማስተካከል የራሳችን ስሜት የምንቆጣጠረው ራሳችን ወደመሆን እንደግ፡፡

3. የእውቀት ጥገኝነት፡- ሁልጊዜ ሰዎችን በመጠየቅና ከእነሱ በምናገኘው መልስ ላይ ብቻ በመደገፍ ከመኖር በራሳችን እውቀትን ወደመቅሰምና በእውቀት ወደመሻሻል ደረጃ ለመድረስ እንስራ፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
ሃሳብን ወደ ተግባር መለወጥ

አንድን ያመንንበት ሃሳብ ወደ ተግባር ለመለወጥና ስኬታማ ለመሆን ከፈለግን የሚከተሉት ሶስት መሰረታዊ ልምምዶች ያስፈልጉናል፡፡

1. እውቀት

ለመተግባር በፈለግነው ማንኛውም ጽንሰ-ሃሳብ አንጻር በቂ እውቀት ማዳበር በምንም ነገር ሊተካ የማይችል ልምምድ ነው፡፡ ካለእውቀት የሚጀመር ነገር ረጅም ርቀት ለመሄድ ካለመቻሉም ባሻገር አንድ እርምጃ ለመራመድ እንኳን እውቀቱን በጨበጡ ሰዎች ላይ የምንደገፍ ያደርገናል፡፡

2. እምነት

በአንድ ማከናወን በፈለግነው ነገር ላይ በቂ ወይም ለመነሻ የሚሆን እውቀት ካዳበርን በኋላ ወደፊት ለመገስገስ ከፈለግን የምንጀምረው ነገር እንደሚሰራ በሙሉ ልባችን ልናምን ይገባናል፡፡ እንደሚሳካም ሆነ ወደፊት እንደምንገሰግስ ልባችን ያላመነበትን ነገር መጀመር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ፣ ቢጀመርም እንኳን ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡

3. እርምጃ

ማድረግ የፈለግነውን ነገር አወቅነውም አላወቅነውም፣ እንደሚሰራ አመንንበትም አላመንበት፣ የመጨረሻው የውጤታማነት ምስጢር ያለው በዚያ ነገር ላይ እርምጃ በመውሰዳችን ላይ ነው፡፡ እርምጃና ተግባራዊነት የሌለው እውቀትም ሆነ እምነት የትም አይደርስም፡፡

በቂ እውቀት! ጽኑ እምነት! የማያዳግም እርምጃ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
መፍራትን አትፍራው!

እንደ ፍርሃት፣ ድንጋጤና ስጋት አይነት ስሜቶች ሰው ከአደጋ እንዲጠነቀቅ ከፈጣሪው የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በአግባቡ ልንጠቀምባቸውና ከአደጋ ልንጠበቅባቸው ሲገባን ለአንዳንድ ሰዎች የኑሮ ዘይቤ ሆነዋል፡፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ የመክሰር ፍርሃት፣ ያለመወደድ ፍርሃት፣ ብቻ የመቅረት ፍርሃት፣ … ጣጣችን ብዙ ነው፡፡

በፍርሃት ስንወረስ፣ ሕይወታችንን በራእይ መምራት እናቆምና ለፍርሃት ምላሽ በመስጠት መምራት እንጀምራለን፡፡ ከአንዱ ራእይ ወደሌላኛው በማለፍ ሕይወትን “ልናጠቃት” ሲገባን የመጣው ሁሉ የኑሮ ገጠመኝ የሚያጠቃን ቋሚ ኢላማዎች እንሆናለን፡፡ ቆመን ለመጣው ወይም የመጣ ለመሰለን ጥቃት ምላሽ በመስጠት ጊዜአችንን እናባክናለን፡፡ ይህ ሲሆን የቆመ ኢላማ ሆንን ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ከአንዱ ግብ ወደሌላኛው በአላማ የምንንቀሳቀስ ሰዎች ስንሆን አይኖቻችን ከችግሩ ላይ ይነሱና መፍትሄው ላይ ማረፍ ይጀምራሉ፡፡

የፍርሃትህ ጥልቀት አእምሮህ የፈቀደለት ያህል ነው” - Unknown Source

ፍርሃት በሕይወትህ ብቅ ጥልቅ ማለቱ አያስፈራህ፡፡ በዚያ ፍርሃት ምክንያት ግን መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ እንዳትታሰር ፍራ፡፡ ማንኛውም ሁኔታ አንተን የማስፈራራት ሙከራ የማድረግ ሙሉ መብት አለው፡፡ አንተ ካልፈቀድክለት ግን ሊያስፈራራህ አይችልም፡፡

ትፈራለህ፣ ፈሪ ግን አይደለህም፡፡ “በፍጹም አልፈራም” ብለህ ካሰብክና ከተናገርክ ከፍርሃት የተደበቅህ ሰው እንደሆንክ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አባባል፣ የፍርሃት ስሜት እንዳይመጣ መከልከል አትችልም፣ ይህንን ስሜት ለማስተናገድ የተፈጠረ ማንነት ስላለህ፡፡ ሆኖም፣ የፍርሃትን ጥልቀትና በአንተ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጉዳት የመወሰን ሙሉ መብትም ሆነ ብቃት አለህ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የስልጠና እድል!

With Dr. Eyob Mamo

ከሃገር ቤት ውጪ ለምትገኙ ሁሉ የተዘጋጀ በ Zoom የሚሰጥ የስልጠና እድል፡፡

ራእይ . . .

• የተፈጠርንነትን የሕይወት ትርጉም የምናገኝበት . . .

• ከተሰላቸንበት የሕይወት ዑደት የምንወጣበትና ወደ ዓላማችን አቅጣጫን የምንይዝበት . . .

• ለራሳችን ብቻ ከመኖር ባሻገር በሌሎች ላይ ተጽእኖ የማምጣት መትረፍረፍ ውስጥ የምንገባበት . . .

. . . ብቸኛው መንገድ!

በማስወቂያ ፖስተሩ ላይ ባለው መረጃው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ! አያምልጣችሁ!


https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ከኢትዮጵያ ውጪ ለምትኖሩ በዚህ ሊንክ ግቡና ተመዝገቡ ክፍያውንም እዛው ላይ እንዴት እንደምትከፍሉ ይነግራል::

ኢትዬጽያ ለምትኖሩ ይህ ስልጠና የሚሰጥበት ሰአት ለናንተ ሌሊት ስለሚሆን ላይመች ይችላል::

https://forms.gle/NkcpF5jQwrUVVf47A
ያስቸገረኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር!

ተወልዶ ካደገበት ሃገሩ በተፈጠሩ ማሕበራዊ ቀውሶች ምክንያት ወደሌላ ሃገር በስደት ለመሄድ የቆረጠ አንድ ሰው ረጅም፣ አድካሚና አስፈሪ የሆነን በረሃ ለቀናት በእግሩ በመሄድ ካቋረጠ በኋላ እጅግ ደክሞና ዝሎ ነበር፡፡ በመጨረሻም በደረሰበት አንዲት ከተማ ውስጥ በተሰጠው እርዳታ ትንሽ አገገመ፡፡

የዚህን ሰው ጉዞ የሰማና ለሕብረተሰቡ ለማቅረብ የፈለገ አንድ ጋዜጠኛ አገኘውና አንድን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ “ተጉዘህ የመጣኸው በረሃ ብዙ ሰው የማይደፍረው በረሃ ነው፡፡ ለመሆኑ በመንገድህ ላይ በጣም የጎዳህና ያስቸገረህ ውኃ ጥም ነበር? ምግብ ማጣት ነበር? አውሬ ነበር? ሽፍቶች ነበሩ? ወይስ . . . ?

የዚህ ስደተኛ መልስ ለጋዜጤኛው ያልተጠበቀ ነበር፡፡ በዚህ አደገኛ በረሃ አቋርጬ ስመጣ በጣም ያስቸገሩኝ የጠቀስካቸው ትልልቅ ነገሮች አልነበሩም፡፡ ጉዞየን በጣም አድካሚና አስቸጋሪ ያደረገብኝ በእርምጃዬ ወቅት ጫማዬ ውስጥ እየገባ የሚቆረቁረኝና አላራምድ ያለኝ ጥቃቅኑ አሸዋ ነበር፡፡

የሕይወት ጉዞም እንዲሁ ነው! አብዛኛውን ጊዜ የሚያስቸግረን፣ የሚቆረቁረን፣ አላራምድ የሚለንና ከዓላማችን የሚጎትተን ችግር ትልልቁ አይደለም፡፡ በየቀኑ የሚያጋጥሙን ጥቃቅን “አሸዋዎች” ናቸው፡፡ ትንንሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ባህሪይ፣ ትንንሽና አናሳ ወሬን የሚያወሩ ሰዎች ሁኔታ፣ ትንንሽና ስሜትን የሚነካኩ የየቀን ገጠመኞች . . . ጉዟችንን አዳጋችና አድካሚ ያደርጉታል፡፡

“በትንንሽ” ሰዎችና ሁኔታዎች ሳትበገሩ ትልቁ የሕይወት ስእልና ዓላማችሁ ላይ በማተኮር ወደፊት መገስገስን ያወቃችሁበት ጊዜ ዋናውን የሕይወት ድል የተጎናጸፋችሁበት ጊዜ ነው፡፡

በርቱ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
በጥራት ማደግ!

ሁለት አይነት እድገቶችና ትልቅነቶች አሉ፡፡ አንደኛው ውጫዊ እድገትና ትልቅነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” ነው፡፡

1. ውጫዊ እድገትና ትልቅነት

ሰዎች በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በዝና፣ በስልጣን እና በመሳሰሉት ነገሮች ሲያድጉ፣ “ውጫዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ምንም እንኳን በራሱ ምንም ችግር ባይኖረውና እንዲያውም ለጥቅም የሚውል ቢሆንም ብቻውን ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

2. “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት”

ሰዎች በመልካም ስብእና፣ በጤናማ አመለካከት፣ በስሜት ብልህነት፣ በራእይ እና በጥበብ ሲያድጉ፣ “ውስጣዊ እድገትና ትልቅነት” አገኙ እንለዋለን፡፡ ይህ እድገትና ትልቅነት ከማንኛውም ነገር በፊት ሊቀድም የሚገባው የእድገትና የትልቅነት ዘርፍ ነው፡፡

አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ውጫዊ እድገትንና ትልቅንን እያስመሰዘገ ውስጣዊ እድገት ሲጎድለው ከራሱ ሕይወት ጀምሮ እስከ ቤተሰቡ፣ የስራ ስምሪቱና በሃገር ደረጃ የሚያስከትለው ቀውስ ይህ ነው አይባለም፡፡

የገንዘብ አቅሙን ለማይረባ ነገርና ለሕገ-ወጥ ተግባር የሚጠቀም ማነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን?

በዝናውና በታዋቂነቱ የሚኩራራውና ሰውን የሚንቀው ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን?

በስልጣኑ ተጠቅሞ ሰውን የሚደቁስና እንደፈለገ የሚሆን ማን ነው? በውጪ አድጎ ውስጡ ግን ቀጭጮ የቀረው አደለምን?

በመጀመሪያ በውስጣችን እንደግ!

ከሁሉም በፊት በጥራትና በብቃት ትልቅ እንሁን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ብቁ ናችሁ!

ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!

እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን የዓለም መጨረሻ ነው ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሰው እናንተን የመቀበልና የመውደድ ብቃቱ ወይም ፍላጎቱ የለውም ማለት ነው እንጂ እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡

እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!

አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ፡፡

በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች!

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ሕልሜን ላጫውታችሁ
ሕልሜን ላጫውታችሁ

አንድን ሕልም አለምኩ፡፡ አንድን በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተፈላጊነት ያለውን ጥበበኛ አዛውንት ያገኘሁት ይመስለኛል፡፡ ይህ ጥበበኛ ሰው ምንም አይነት ጥያቄ ከብዶት አያውም፣ ለማንኛውም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ መፍትሄ በመስጠት የታወቀ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ቢያንስ ከአንድ አመት በፊት ቀጠሮ በማስያዝ ከአለም ዙሪያ ወደእርሱ የሚመጡት፡፡ ጠቢቡ አስተርጓሚ አያስፈልገውም፡፡ የአለምን ሁሉ ቋንቋ ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ፈገግተኛ፣ የደስ ደስ ያለውና ከአጠገቡ መለየትን የማያስመኝ መረጋጋት ያለው ሰው ነው፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላውቀውም ካለምንም ቀጠሮ ለብቻዬ ጠቢቡን የማግኘት እድል ያገኘሁ ይመስለኛል - በሕልሜ፡፡

ሁኔታው ድንገተኛ ስለሆነብኝ ይመስለኛል፣ ምንም እንኳን ጊዜ ቢሰጠኝ ብዙ የምጠይቃቸው ጥያቄዎች ቢኖሩኝም የምለውን አጣሁ፡፡ ሰዎች ከአለም ዙሪያ በብዙ ትግል የሚያገኙትን ይህንን ጠቢብ የማግኘት እድል አግኝቼ ምንም ነገር ሳላገኝ ሄጄ በኋላ እንዳይጸጽተኝ የመጣልኝን ሁሉ ለመጠየቅ ወሰንኩ፡፡ እንዲህ ስል ጠየኩት፣ “ሰዎች ወደአንተ ይዘው ለሚመጡት ጥያቄ በሙሉ ለመፍትሄ የሚሆንን ምክር የመለገስ ጥበብ እንዳለህ ዝናህን ሰምቻለሁ፡፡ እስቲ እስካሁን ድረስ ለመምከር ወይም መፍትሄ ለመስጠት ከባድ ሆኖ ያገኘኸውን ቀንደኛ ሁኔታ ንገረኝ” አልኩት፡፡

አንዴ እኔን፣ አንድ ጊዜ ደግሞ መሬት መሬት ከቃኘ በኋላ፣ እንደገና ወደ እኔ ከዚያም ልክ አንድ አዲስ ሃሳብ ሰማዩ ላይ የሚያነብ እስኪመስልበት ድረስ ወደላይ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ አለኝ፡-

“ፈጣሪ አድሎኝ ለብዙ ሰዎች መፍትሄ የሚሆኑ ምክሮች የመለገስ ብቃት አለኝ፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ፡፡ ምክር ፍለጋ ወደእኔ የሚመጡት በአብዛኛው በወጣትነትና በመካከለኛው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ድረስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን አማክሬአለሁ፡፡ እስካሁን የሰጠኸኝ ምክር አልሰራልኝም በማለት የተመለሰ ሰው አላጋጠመኝም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ሁለት ነው፡፡ አንደኛው በወጣትና በጎልማሳ እድሜአቸው ላይ የሚገኙት ሰዎች ምክሩን ተግባራዊ አድርገው መፍትሄ በማግኘታቸው ምክንያት ወደ እኔ አይመለሱም፡፡ ከዚህ ለየት የሚለው ሁኔታ ግን እንደ እኔ እድሜያቸው እጅግ የገፋ አዛውንቶች ይዘው የሚመጡት ጥያቄ ነው፡፡ የእነዚህ ሰዎች ጥያቄ በአብዛኛው የጸጸት ጥያቄ ነው፡፡”

ጠቢቡ ንግግሩን ቀጠለ፡- “ያሳለፏቸውን አመታቶቻቸው መቼ መጥተው መቼ እንደሄዱ ማሰብ እስከሚያስቸግራቸው ድረስ ግር የሚላቸው አዛውንት ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁን መለስ ብለው ሲያስቡት ሕይወታቸውን ወደማይፈልጉበት አቅጣጫ እንዲሄድ ያደረገውንና አሁን የሚጸጸቱበትን ውጤት ያስከተለባቸውን የመነሻ ችግር በሚገባ ያውቁታል፡፡ በወቅቱ እርምጃ ወስደው ሊያርሟቸው የሚገቡ ቀላል የሚመስሉ ሁኔታዎች ዛሬ ምንም ቢጸጸቱ እንኳን ሊቀለብሱት የማችሉትን ሰበብ አጠራቅሞ አገኙት፡፡”

ጠቢቡ ፍላጎቴን አይቶ የኋላ ኋላ እንዳልጸጸት ምን ማድረግ እንዳለብኝ ምክርን ለገሰኝ፡፡ የሰጠኝ ምክሮች ከብዙ አዛውንት የጸጸት ሁኔታ በመነሳት በብዙ ሰዎች የሚንጸባረቁትን የጸጸት መንስኤዎች በመጭመቅ እንደሆነ ገምቻለሁ፡፡ ወዲያውኑ ከእንቅልፌ ባነንኩኝና ሳልረሳቸው ጠቢቡ በምክሩ የጠቆመኝን የሚከተሉትን መመሪያዎች መዘገብኳቸው፡፡

1. “ሁል ጊዜ አንተው ያመንክበትን ሕይወት መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡”

2. “ልክህን እወቅ፣ ለስራህና ለሕይወትህ መርህና ገደብ ይኑርህ፡፡”

3. “ማንነትህን፣ ኑሮህንም ሆነ የሰራሃቸውን ስህተቶች አሻሽላቸው እንጂ አትፈርባቸው፡፡”

4. “ከወዳጆችህ ጋር ነጻ የሆነን ግንኙነት መስርት፣ ግልጽነትና የቀረበ ወዳጅነት ቢጎዳህም ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣልና በፍጹም አትሽሽ፡፡”

5. በመጨረሻ፣ ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆንን ምረጥ፡፡ የሕይወት ቀንደኛ ዓላማዎች ከሚባሉት ውጤቶች መካከል ደስተኛነት አንዱ ነውና፡፡

(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
ችግሩ እናንተ ጋር ባይሆንስ !?

ሰዎች በእናንተ ላይ የሚያንጸባርቁት ባህሪይ የእናንተን ሁኔታ ከማንጸባረቁ ይልቅ የሚያሳየው የእነሱኑ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ መገንዘብ በሄድንበት ሁሉ ሰዎች የሚሰጡንን መስተግዶና የሚሳዩንን ባህሪይ እየተከታተልን ከመደናበር ይጠብቀናል፡፡

በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ሰዎች የሚያሳዩአችሁን አጉል ባህሪይ እያያችሁ ሁኔታው የእናንተን ማንነት መተርጎሚያ ከማድረግ ልቦናችሁን ጠብቁ፡፡

ጥቂት የመንደርደሪያ ሀሳቦች . . .

ሰዎች ከጠሏችሁ
የግድ የምታስጠሉ ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሰዎቹ በጥላቻ የተሞሉ አይነት ሰዎች ስለሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ከናቋችሁ የግድ መናቅ የሚገባችሁ አይነት ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን የመናቅ ችግር ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ካገለሏችሁ የግድ እንድትገለሉ የሚያደርጋችሁ ማንነት ስላላችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን በተለያየ ምክንያት ማግለል የለመደ ባህሪይ ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

በአጭሩ ሰዎች ለእናንተ የሚያሳዩትን ባህሪ በመመልከት ብቻ ከዚያ አንጻር ለማንነታችሁ ትርጉምና ፍቺ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ በዚያ ምትክ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ሊያዛባ የሚችል አጉል ባህሪይ ካለባች እሱ ላይ ካለማቋረጥ በመስራት የሰዎችን የግል አመለካከትና አጉል በህሪይ ለራሳቸው ተውላቸው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
የአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”)

ከሰዎች ጋር ያላችሁ ግንኙት የስነ-ልቦና፣ የስሜት እና አንዳንዴም አካላዊ ጉዳት እያከተለባችሁ ምንም ማድረግ እንዳልቻላችሁ ከተሰማችሁ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን የአሰቃቂ ሁኔታ ትስስር (“Trauma Bonding”) ምልክቶችን በሚገባ መገንዘብና ለመፍትሄው ተከታይ የቲክቶክ መልችክቶቼን መከታተል አትዘንጉ፡፡

1. ሰዎቹ እንደ ልማዳቸው ይጎዱናል

2. እኛም በሁኔታው እንጎዳና ከእነሱ ስለመለየት ወይም ጠንካራ ሆኖ ስለመመከት ማሰብ እንጀምራለን

3. ሰዎቹ ብዙም ሳይቆዩ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ሆነው በጥሩ ሁኔታ ይቀርቡናል

4. እኛም ሰዎቹ የተለወወጡ ወይም የተጸጸቱ መስሎን መለስ እንላለን

5. ሰዎቹ ለተወሰነ ጊዜ በአስገራሚ ሁኔታ ጥሩ ሆነው በማሳለፍ ያዘናጉናል

6. እኛም ከተወሰነ የእፎይታ ጊዜ በኋላ ራሳችንን ተጋላጭ አድርገን በማቅረብ ነገሩን ተወት እናደርገዋለን

7. ሰዎቹ በቁጥር አንድ ላይ የተጠቀሰውን የጉዳት ሁኔታ በመድገም ዑደቱን ይቀጥላሉ፡፡

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ የ Counseling, Coaching and Mentorship አገልግሎቶች ከፈለጋችሁ ለመረጃው

@DrEyobmamo

ቴሌግራም inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
2024/05/28 18:59:53
Back to Top
HTML Embed Code: