Telegram Web Link
ፍቅር በጣም በቶሎ ነዉ የሚይዘኝ
ጥያቄ፡-

ሰላም ዶክተር፡፡ የ 23 አመት ወጣት ነኝ። ፍቅር በጣም በቶሎ ነዉ የሚይዘኝ ከአብዛኞቹ በቅርቤ ካሉ ሴቶች ፍቅር ይዞኝ ተጎድቻለሁ እየተጎዳሁ ነው።

መልስ፡-

በቅርብህ ከሚገኙ ሴቶች ሁሉ ጋር ወይም ከአብዛኛዎቹ ጋር ፍቅር የያዘህ ከመሰለህ፣ ይህንን ስሜትህን ፍቅር ብለህ ጠራኸው እንጂ የፍቅር ስሜት አይደለም፡፡

ከዚህ በታች ያሰፈርኳቸው ሁኔታዎች ተከስተውብህ እንዳይሆን እስቲ አስብበት፡-

1. አንተ ባለህበት እድሜ ከፍተኛ የሆነ ወሲብ የማድረግ ፍላጎት ሊኖር የሚችልበት እድሜ ስለሆነ ይህንን የተፈጥሮ ሂደትና ወሲብ ለመፈጸም የመፈለግ ስሜት ከፍቅር ስሜት ጋር አምታተኸው ይሆናል፡፡

2. ምናልባት በዚህ እድሜህ ፍቅረኛ የማግኘት ፍላጎትህ የጎላ ስለሆነ ያንን ከመፈለግህ የተነሳ የሚቀርቡህን ሴቶች ሁሉ በዚያ አይን የመመልከትና ፍቅረኛ የማድረግ ጥረትና ዝንባሌ ኖሮህ ሊሆን ይችላል፡፡

3. ምናልባት በሕይወትህ የመገፋት ስሜት ካለህና ተቀባይነትን አጥብቀህ የምትፈልግ ከሆነ ከቀረቡህ ሴቶች ሁሉ ጋር የመቅረብና ተቀባይነት ማግኘት የመፈለግ ዝንባሌ ኖሮህ ሁኔታው ከፍቅር ስሜት ጋር ተምታቶብህ ይሆናል፡፡

4. ምናልባት ፍቅር (Love) ማለት ከተቃራኒ ጾታ ጋር መቀራረብ (Attachment) ብቻ እንደሆነ ጠበብ ያለ ምልከታ ኖሮህ ልክ እንደቀረብካቸው ፍቅር እንደያዘህ እያሰብክ ሳለህ በእነሱ ውስጥ ግን ከቀላል ጓደኝነት ያላለፈ ስሜት ኖሮ በዚያ እየተጎዳህ እንዳይሆን፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ ካገኘሃት ሴት ሁሉ ጋር ፍቅር ስሜት እየተሰማህ ከተጎዳህ ክፍተቱ ያለው አንተ ጋር ነው፡፡ ስለዚህ፣ ለተወሰነ ጊዜ ፍቅረኛ ፍለጋህን ትንሽ ተወት አድርገውና ማንነትህን ማወቅ፣ መቀበልና የፍቅር ግኙነት ምን ማለት እንደሆነ መብሰል ላይ ለመስራት ሞክር፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍19247🔥10
የምትሰሩት ስራ ጉዳይ

በአሁኑ ወቅት በስራ አለም ውስጥ ከተሰማራችሁና የወደፊት የስራ ቆይታችሁ ስኬታማና እድገት ያለበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ስለጉዳዩ ማሰብ ያለባችሁ ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ አእምሯችሁን ተጠቅማችሁ ካላሰባችሁ፣ ነገ ስሜታችሁ መጨነቅና መዛባት ይጀምራል፡፡

በስራው አለም ውስጥ በቆያችሁ ቁጥር በሁለት መልኩ ማደግ አለባችሁ፡- 1) በገንዘብ ብቃት፣ 2) በአእምሮ እድገት

1. የገንዘብ ብቃት

የሚከፈላችሁ ክፍያ አናሳ እንደሆነ ካሰባችሁ፣ ለስራው ካላችሁ ብቃት አንጻር እየተከፈላችሁ ሊሆን ስለሚችል ብቃታችሁን የምትጨምሩበትን መንገድ ፈልጉ፡፡ ብቁ ሆናችሁ መስሪያ ቤቱ የመክፈል ባህሉ ወይም አቅሙ አናሳ ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ፣ የመስሪያ ቤቱን አሰራር ለማስቀየር ከመታገል ወይም ከመነጫነጭ ይልቅ የስራ መስካችሁን መቀየር ቀለል እንደሚል አትዘንጉ፡፡

2. የአእምሮ እድገት

የስራው ጸባይ አእምሮን የሚያሰራ፣ የሚሞግትና የሚያሳድግ ከመሆን ይልቅ ድግግሞሽ የሞላው ከሆነ፣ ምንም እንኳን ገንዘብን ብታኙበትም ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚራመድ የአእምሮ እድገት እንደማይኖራችሁ አትዘንጉ፡፡ በስራው ለመቆየት ከፈለጋችሁ፣ በግላችሁ የምታድጉበትን ሌላ መንገድ መፈለግ አለባችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የሚሞግት፣ አእምሮን የሚያሰራና የሚያሳድጋችሁን ስራ ወደመፈለግ ማዘንበል ወሳኝ ነው፡፡

እድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር ቤተሰብን ከመመስረት የሚመጣ ሃላፊነትና የተለያዩ ፍላጎቶች መጨመር ሁኔታዎች አብረው ስለሚመጡ ካለማቋረጥ የማደጋችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
155👍84🔥9😱2🤩2
የግል ሕልማችሁ ጉዳይ
18👍12🎉2
የግል ሕልማችሁ ጉዳይ

(“የተደራጀ ሕይወት” ከተሰኘው ሰሞኑን ከታተመው አዲስ የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)

የተደራጀ ሕይወት ከመኖር አንጻር ሕልማችን ላይ የመስራታችንን አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተን እንመለከታለን፡፡ በቅድሚያ ግን “የግል ሕልም” ስንል ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ በመስማማት እንጀምር፡፡

“የግል ሕልም ማለት በተለያዩ የግል ሕይወታችን ዘርፎች ስኬታማ እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለመኖር የሚያስችሉንን መርሆች በመከተል የልህቀት ከፍታ ውስጥ የሚከቱንን ሁኔታዎች መገንባት ማለት ነው፡፡”

በዚህ ትርጉም መሰረት በሕልም ላይ ስለመስራት ማሰብ ማለት የራስን ሕይወት መገንባትና ማሻሻል ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ራእይ የሰውን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ሲነካ፣ ሕልም ደግሞ የራስን ሕይወት የመገንባትን፣ የማሳደግንና የመለወጥን ሁኔታ ይነካል፡፡

ይህ ሕልም ብለን የምንጠራው ጉዳይ የራሳችንን ሁለንተናዊ ሕይወት ከማሳደግ ጋር የሚገናኝ ልምምድ ሲሆን፣ ሁኔታው እንዲሁ በሃሳባችን የፈጠርነውን ነገር ሁሉ እንደሚሆን በጭፍንነት የማሰብ ጉዳይ ሳይሆን ተግባራዊ ሂደትን ተከትሎ ስኬታማ ሕይወት ውስጥ የመግባት ጉዳይ ነው፡፡

ሕልሞቻችን ቅዠት ሆነው እንዳይቀሩ መውሰድ ከሚገቡን ወሳኝ እርምጃዎች መካከል የሚከተሉትን ቀላል መርሆች ማስታወስና መለማመድ ይጠቅናል፡፡

1. አልመው - እያንዳንዱ ታላቅ ስኬት የሚጀምረው በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ ሲፈጠር ነው።

2. እመነው - ሕልም ጋር የሚደረሰው ያለምነውን ሕልም ልንደርስበት እንደምንችል በማመን ነው፡፡

3. እየው - ሕልማችንን በገሃዱ አለም ከማየታችን በፊት በአይነ-ህሊናችን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡

4. አጋራው - ሕልማችንን በውስጣችን አምቀን ከምንይዝ ይልቅ ለተገቢ ሰዎች ማጋራት ወደ ስኬት ያስጠጋናል፡፡

5. አቅደው - ያለምነውና አምነን በውስጠ-ህሊናችን ያየነውን ሕልም በእቅድ ደረጃ ማውረድ አለብን፡፡

6. ስራው - ሕልማችንን ካመንነውና ካቀድነው በኋላ ወደ እንቅስቃሴ መግባት ይኖረብናል፡፡

7. አጣጥመው - በሕልም ተጀምሮ ጠንክሮ በመስራት እጃችን የገባውን ውጤት ማጣጣምና መደሰት ያስፈልጋል፡፡

መጽሐፉን በቅናሽ ለማግኘት በ 0947930369

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍10537🤩5🔥2
ምንም አሰባችሁ ምንም፣ ሃሳቡ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም ተሰማችሁ ምንም፣ ስሜቱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም አቀዳችሁ ምንም፣ እቅዱ የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ምንም ወሰናችሁ ምንም፣ ውሳኔው የእናንተው መሆኑን እርግጠኞች ሁኑ!

ከፈጣሪያችሁ ጋር መማከር የመቅደሙ ነገር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በማንም ሰው ሃሳብ እና ሁኔታ ተጽእኖ ስር ከመውደቃችሁ በፊት ከራሳችሁ ጋር ተማከሩ፡፡

Have A Wonderful Afternoon!!!
👍16275
“የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን”
(Writing Skills and Discipline)


ባለፈው ሰኞ የተጀመረው “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline) የተሰኘው ስልጠና ነገ (ኃሙስ) ይቀጥላል፡፡

የመጀመሪያው ክፍል ቢያመልጣችሁም፣ ያለፋችሁን በ note እና በ audio ቅጂ በመከታተል ከነገ ጀምሮ መቀላቀል ፍላጎት ያላችሁ ያንን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

• ርእሱ፡- “የመጻፍ ክህሎት እና ዲሲፕሊን” (Writing Skills and Discipline)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ

@DrEyobmamo
👍4012🎉4🔥1
ራሳችንን ከራሳችን የሚጋርዱ ነገሮች

1. ራስን አለመቀበል

ራስን መቀበል ማለት ዘሬን፣ መልኬን፣ ቁመናየን . . . እና የመሳሰሉትን ልቀይራቸው የማልችላቸውን የማንነቴ አካሎች በመቀበል መደላደል ማለት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ሲታገሉና ሲሸፋፍኑ መኖር ከዋናው ነገር ወደኋላ ይስቀረናል፡

2. ባለፈው ታሪክ መቆለፍ

ያለፈ ታሪክ ማለት ከዛሬ በፊት የነበሩኝን ስኬቶችንና ስህተቶችን የሚያካትት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬታማ ነበርኩ፣ ምንም አያስፈልገኝም ካልን፣ እንዲሁም ደግሞ ስህተተኛ ነበርኩ ስለዚህም ለምንም ነገር አልበቃም ብለን ካሰብን ራስን የማግኘት ትክክለኛ እያታችን ይጋረዳል፡፡

3. ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር

ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማለት ማንነቴን፣ ዓላማዬንና ስኬታማነቴን ሌሎች አቻዎቼ ሆነዋል፣ ደርሰውበታል ብዬ ከማስበው አንጻር መገምገም ማለት ነው፡፡ ይህ ዝንባሌ የራሴ ደረጃና ግብ እንዳይኖረኝ ያግደኛል፡፡

4. የተዛባ የስኬት ልኬት

ስኬት ማለት ማንነትን ማወቅና መቀበል፣ ዓላማን መለየትና ለዚያ መኖር፣ ያለንን ነገር ማሳደግና ለሕብረተሰቡ ጥቅም ማዋል ሆኖ ሳለ፣ ስኬትን ከገንዘብ፣ ከእውቀት፣ ከዝና፣ ከስልጣን . . . ጋር ብቻ ማዛመድ ከራስ ጋር የሚያፋታ እይታ ነው፡፡

5. ወቃሽነት

ወቃሽነት ማለት በዙሪያችን ለሚሆነው ነገር ሁሉ የሚወቀስ ሰው መፈለግና ኃይለኛ አቋሞችን መያዝና ቃላቶችን መናገር ማለት ነው፡፡ ሰዎችን የመውቀስ ልመዳ የእኛን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደማሳበብ አዘቅት ውስጥ ያወርደናል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት እንቅፋቶች ራሳችሁን ያገኛችሁበት ነጥብ ላይ ለመስራትና ለማሻሻል ሞክሩ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
👍17060🎉4🤩1
ማን ነኝ?
👍1510
ማን ነኝ?

ይህንን ጥያቄ ከተወለድክበት እለት አንስቶ ካሳለፍካቸው ሁኔታዎችና ታሪኮች በመነሳት ምን ወደመሆን እንደመጣህ ራስህን ለመመልከት ተጠቀምበት፡፡ አወላለድህ፣ አስተዳደግህ፣ ኖሮህና ሳይኖርህ ያደከው፣ ተደርጎልህና ተደርጎብህ ያደከው . . . ተደምሮ ምን ወደመሆን እንደመጣህ ይሰማሃል?
ይህንን መለስ ብሎ የራስን ማንነት የመጠየቅና የመገምገም ሂደት በፍጹም እውነተኛነትና ድፍረት ልታደርገው ይገባሃል፡፡

እውነተኛነት የሚያስፈልገው አንዳንድ ማሰብ የማንፈልጋቸው ሁኔታዎች ሊኖሩ ስለሚችሉና በክህደት አለም ውስጥ የመደበቅ ፈተና ውስጥ ልንገባ ስለምንችል ነው፡፡ ድፍረት የሚጠይቀው ደግሞ አንዳንድ ታሪኮቻችንና አሁን ያለንባቸው ሁኔታዎች ስናስባቸው አቅም አሳጪ ሊሆኑ ስለሚችሉ ያንን ለመጋፈጥ ራስን የመሞገት ቁርጠኝነት ስለሚጠይቁ ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ቢሆን ሁለንተናውን ተጋፍጦና ከታሪኩ ጋር ተፋጦ፣ እውነቱን አውጥቶና አውርዶ፣ “አሁን የሆንኩትን የሆንኩት ከእነዚህ ሁኔታዎች የተነሳ ነው” በማለት ማሰብ እስከሚጀምር ድረስ መስመር የያዘ የወደፊት አቅጣጫ ውስጥ መግባት ያስቸግረዋል፡፡

- የሚያስፈሩኝ ነገሮች የሚያስፈሩኝ ለምንድ ነው?

- ማሰብ የማልፈልጋቸው ምእራፎቼን ማሰብ የማልፈልገው ለምንድነው?

- ከየትኛው ጤናማ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ መልካም ነገር የበቀለው?

- ከየትኛውስ አስቸጋሪ ታሪኬ የተነሳ ነው አሁን ያለኝ ቀውስ የተከሰተው?

- ዝንባሌዬዎቼና ልገነባባቸው የምችላቸው ጠንካራ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው?

- ላርማቸው፣ ላስተካክላቸውና ልቀርፋቸው እንደሚገባኝ የማስባቸው ደካማ ጎኖቼ ምን ምን ናቸው?

- ከእነዚህ ልምምዶቼና ታሪኮቼ ውስጥ ተደብቆ ያለውን እውነተኛ ማንነቴን እንዴት ፈልፍዬ ላወጣው እችላለሁ?

- ከላይ ካነበብኳቸውና ከመሰል ሂደቶች አንጻር እኔ ማን ነኝ?

እስቲ ይህንን ጥያቄ ቀኑን ውለህ ሌሊቱን እደርበትና፡፡ ከቻልክ የየቀን ማስታወሻ (Diary) ለመጻፍ ሞክር፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍13462🎉6
የሚያነሳሳችሁ (Motivate የሚያደርጋችሁ) ምንድን ነው?

አንድን ማድረግ የምፈልጉትን ነገር ለማድረግ የሚያነሳሳችሁ ነገር ስለማንነታችሁ፣ ስላላችሁ ዲሲፕሊንና ስለ ንጽረተ-ዓለማችሁ ብዙ ይናገርል፡፡

1. የሌሎች ሰዎች አለመሳካት ወይም ወደ ኋላ መቅረት ያነሳሰችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች የመበለጥና የበታችነት ስሜት ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ሌሎች ሰዎች እንዳልተሳካላቸው ሲያዩ ጥሩ ስሜት ሰማቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጽናት የሚከታተሉት የግል ዓላማ እንደሌላቸው አመልካች ነው፡፡

2. አንድ ነገር እንዳይደረስባችሁ መፍራት ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የፍርሃት ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ አንድ ነገር እንደሚደርስባቸው ሲያስቡና ሲፈሩ ምንም ነገር ከማድረግ አይመለሱም፡፡ ፍርሃት ከሌለ መነሳሳቱም አይኖራቸውም፡፡

3. ሰዎች ስለ እናንተ የሚያስቡትና የሚናገሩት ነገር ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች የሰውን አመለካከት ትልቅ ስፍራ የመስጠት ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሌሎች ሰዎች ስለ እነሱ ጥሩ ሃሳብ ሲሰነዝሩ ደስ በመሰኘት ይነሳሳሉ፡፡ መጥፎ ሃሳብ ሲሰነዘርባቸው በዚያ እልህ ምክንያትም ሊነሳሱ ይችላሉ፡፡

4. በፊታችሁ ለመድረስ በውስጠ-ህሊናችሁ ያያችሁት ራእይ፣ ሕልምና ዓላማ ያነሳሳችኋል?

እንደዚህ አይነት ሰዎች ትክክለኛውን የመነሳሳት መንገድ የተገነዘቡ ሰዎች ናቸው፡፡ በዙሪያቸው ምንም ሆነ ምን እነሱ ከታያቸው ራእይና ከያዙት ዓላማ አንጻር ካለማቋረጥ ጉዟቸውን ይቀጥላል፡፡

ራሳችሁን የትኛው ላይ እንዳገኛችሁት በመመልከት ማስተካከያ ብታደርጉ ምን ይመስላችኋል?

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
👍14566🔥3
የትኩረት ጉልበት!

• ችግሩ እያለ፣ ትኩረታችንን ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ ላይ ስናደርግ . . .

• ፍርሃቱ እያለ፣ ትኩረታችንን በጥንቃቄ ወደ ፊት በመራመድ አልፎ መሄድ ላይ ስናደርግ . . .

• የሰዎች ክፋት እያለ፣ ትኩረታችንን ስናስባቸው የሚያበረታቱን ጨዋ ወዳጆቻችን ላይ ስደርግ . . .

• የተለወጠብን ሰው እያለ፣ ትኩረታችንን አብሮነቱ የማይለዋወጠው ሰው ላይ ስናደርግ . . .

• ያልተሳካው ነገር እያለ፣ ትኩረታችንን የተሳካው ላይ እና ወደ ፊትም ሰርተን የምናሳካው ነገር ላይ ስደርግ . . .

• ስህተትና ስህተቱ ያስከተለው ጉዳት እያለ፣ ትኩረታችንን ከስህተቱ ያገኘነው የእድሜ ልክ ትምህርት ላይ ስናደርግ . . .

• በምርጫ ግራ መጋባቱ እያለ፣ ትኩረታችንን ምንም ምርጫ የሌለው ኑሮ ከሚኖሩ ሰዎች የመሻላችን ሁኔታ ላይ ስናደርግ . . .

ኃይላችንን እቆጥባለን፣ ነገን ለመጋፈጥ ጉልበት እናገኛለን፣ በሆነ ባልሆነው ግራ አንጋባም፣ ከልክ ካለፈ የሃሳብ ግልቢያ (overthinking) ረገብ እንላለን፡፡

የትኩረት ለውጥ እናድርግ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
128👍91🔥6😁1🤩1
ከሰዎች ንግግር ይልቅ ለተግባራቸው ቦታ ስጡ!

አንዳንድ ሰዎች የሚናገሯችሁ የፍቅር፣ የአክብሮት፣ የአድናቆትና የናፍቆት ሃሳቦች አስገራሚና አስደማሚ ናቸው፡፡ ተግባራቸው ግን ምን ያህል ተቃራኒ ሆኖ ግራ እያጋባችሁና እየጎዳችሁ እንደሆነ ታውቁታላችሁ፡፡

በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ግራ ከተጋባቸሁ፣ ምላሻችሁንና ውሳኔያችሁን ከንግግራቸው አንጻር ሳይሆን ከተግባራቸው አንጻር እንድታደርጉ ትመከራላችሁ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ደግሞ የሚናገሯችሁ ቃላት ጠንከር ያሉና የሚያቀርቡላችሁ ሃሳቦች ትንሽ ጫን የሚሏችሁ አይነት ናቸው፡፡ በተግባራቸው ግን ሁል ጊዜ ለእናንተ የሚጠቅምንና እናንተን የሚደግፍ ሁኔታን በግልጽ ያሳይዋችኋል፡፡

እነዚህንም ቢሆን ምንም እንኳን የሚናገሯችሁ ንግግሮችና የሚሰጧችሁ ሃሳቦች ጠንከር ቢልባችሁም፣ ከእነሱ ጋር ያላችሁን አቅርቦት ለመወሰን ተግባራቸው ላይ እንድታተኩሩ ትበረታታላችሁ፡፡

መልካም ምሽት!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
147👍82🔥8😱1
ፍርሃት የገዛው ትውልድ!

ይህ ትውልድ ፍርሃት የገዛው ትውልድ ነው፡፡ ፍርሃት የገዛው ትውልድ በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ፍርሃት ያገኘዋል፡፡

ሰዎች አይወዱኝም ብሎ ይፈራል፤ የሚወደው ሰው ሲያገኝ ደግሞ የወደደው ሰው መልሶ እንዳይጠላው ይፈራል፡፡

ተቀባይነት አጣለሁ ብሎ ይፈራል፤ ተቀባይነት የሚሰጠው ሰው ሲያገኝ ደግሞ መልሶ እንዳይገፋው ይፈራል፡፡

ከሰው ጋር መሆን ይፈራል፤ ከሰው ሸሽቶ ብቻውንም ቢሆንም ይፈራል፡፡

የቀረበው ሰው እንዳይጎዳው ይፈራል፤ ሰውየው ከጎዳው ደግሞ እንደገና ላለመጎዳት ሲል ከዚያ ሰው መለየትን ሲያስብ ሰውየውን እጎዳዋለሁ ብሎ ደግሞ ይፈራል፡፡

ሳላገባ ብቻዬን ልቀር ነው ብሎ ይፈራል፤ ካገባሁ ግን እጎዳለሁ ብሎ ስለሚያስብ ማግባትን ይፈራል፡፡

ስለሚፈራ እንቅልፍ አይወስደውም፤ እንቅልፍ ስላልወሰደው ደግሞ ይፈራል፡፡

እንዳይነግድ ክስረትን ይፈራል፤ እንዲሁ ቁጭ እንዳይል ድህነትን ይፈራል፡፡

ደፍሮ ከወጣ አደጋን ይፈራል፤ ፈርቶ ከቀረ ደግሞ ሰዎች ፈሪ ነው ብለው ያስባሉ ብሎ ይፈራል፡፡

ከፍርሃት የተነሳ መሆንና ማድረግ ያለብህን ሳታደርግ አንድ መቶ አመት ከምትኖር ፍርሃትህን ተጋፍጠህና ቀና ብለህ አስር አመት በዓላማ ኖረህ ብታልፍ ይሻልሃል፡፡

ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሕይወት ሊኖር ያለመቻሉን ያህል ፍርሃትን ተጋፍጦ ከመኖር ውጪ ስኬት የለም!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍25498😱11🔥5😢2
“የመገፋት ስስነት”
👍29
“የመገፋት ስስነት”
(“የመገፋት ህመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

በስነ-ልቦናው ቋንቋ “የመገፋት ስስነት” (Rejection Sensitivity) የተሰኘው ሃሳብ ሰዎች በየእለት ኑሯቸው የሚያጋጥማቸውን ጥቃቅን የሰዎች ሁኔታ ከመገፋትና ከመገለል ጋር የማዛመድ ስስነትንና ዝንባሌን የሚያሳይ ጽንሰ-ሃሳባ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ ሰዎች በመገፋት ዙሪያ እጅግ ስስ ከመሆናቸው የተነሳ እንደተገፉ የመሰላቸው ማንኛውም አይነት ሁኔታ ሲመለከቱ የመደናገጥና የመዋረድ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ሰዎች ሲያስጠብቋቸው፣ ስልካቸውን ካልመለሱላቸውና እንደዚህ የመሳሰሉ “አናሳ” የሆኑ ክስተቶች የዝቅተኝትን፣ የመናቅንና የመገለልን ስሜት ያመጣባቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ዝንባሌን አስመልክቶ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል፡፡ ለምሳሌ፣ የዚህ ተጽእኖ ሰለባዎች፣ ሰዎች በፊት ገጽታቸው የሚያሳዩት ሁኔታ እነሱን ያለመቀበልና የመግፋት ምልክት እንዳለው ሲሰማቸው የአንጎል እንቅስቃሴያቸው (Brain Activity) በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪም፣ እነሱን የመግፋት ወይም የማግለል ገጽታ ሊኖረው የሚችልን ማንኛንም እንቀስቃሴም ሆነ ንግግር በንቃትና ሁኔታዎችን በማዛመድ የመመልከትና የመጠባበቅ ዝንባሌ ይታይባቸዋል፡፡

የዚህ ዝንባሌ አንዱ ጫና፣ አድልዎ-ተኮር ምላሽ (Attention Bias) ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ለአስር ሰዎች የፍቅር ጥያቄ አቅርበው ዘጠኙ ተቀብለዋቸው አንዱ ብቻ ፍላጎት እንደሌለው ቢገልጽላቸው፣ እነሱ የሚያተኩሩትና ስሜታቸውን የሚነካው የዘጠኙ እሺታ ሳይሆን የአንዱ እምቢታ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ትኩረትን ከመገፋት አንጻር ብቻ የመቃኘት አድሎአዊ አመለካከት የሚያስከትልባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ በግል ሕይወታቸውም ሆነ በማሕበራዊ ግንኙነታቸው ላይ የሚስከትለው መዘዝ ቀላል አይደለም (ምንጭ፡- verywellmind.com)፡፡

ሁኔታውን ስንጨምቀው፣ በመገፋት ስቃይ ውስጥ ያለፈ ሰው የሰዎችን፣ በተለይም በእነሱ ሕይወት ስፍራ እንዳላቸው የሚሰማቸውን ሰዎች እያንዳንዱን ተግባር በመገመት በመላ-ምት የመኖር ዝንባሌ ያጠቃቸዋል፡፡ ይህ አሉታዊ-ገማችነት ገደብ የሌለው ሃሳብ-ወለድ አለም ውስጥ እንዲዋዥቁና የሌለንና ያልተፈጠረን ነገር በውስጣቸው እንዲያሰላስሉ ያደርጋቸዋል፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች አንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት አለም ውስጥ ከገቡ በኋላ ሲያሰላስሉት ውለው ያደሩት ነገር በእነሱ ውስጥ “የሌለ እውነታ” ሆኖ ይኖራል፡፡ የዚህ ስሜት ውጤት ሰዎች የሚያደርጓቸውንም ሆነ የማያደርጓቸውን ነገሮች እየለቀሙና እየቆጠሩ ካለባቸው “የመገፋት ስስነት” ጋር የማዛመዝ ሁኔታ ነው፡፡

“የመገፋት ስስነት” ያለባቸው ሰዎች የሚሰማቸው ስሜት በእርግጥም ከእውነተኛ የመገፋት ልምምድ የመጣ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን ለመገፋት ስሜት ስስ እንዲሆኑ ከዳረጋቸው ከእውነታ የራቀ እይታም ሊነሳ ይችላል፡፡ መነሻው ያም ሆነ ይህ፣ ሰዎች በዚህ የስሜት ተጽእኖ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላለባቸው የስነ-ልቦና ቀውስ ትክክለኛውን መፍትሄ እንዲፈልጉ ይመከራሉ፡፡

(ከመገፋት ህመም የመላቀቂያውን እውቀት ለማግኘት መጽሐፉ ይነበብ)

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍9148🔥3🎉1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://www.tg-me.com/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo
👍6831🔥7
ነጻ የስልጠና እድል!
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

ለዚህ የቴሌግራም ግሩፕ ተከታታዮቼ በሙሉ፡፡

ቀን - ኃሙስ የካቲት 20

ሰዓት - ማታ ከ2፡30 – 3፡30

የስልጠናው ርእስ - የስሜት ብልህነት (Emotional Intelligence)

ክፍያ - በነጻ!!!

ወዳጆቻችሁም ይህንን telegram channel join በማድረግ እንዲከታተሉ ጋብዟቸው፡፡

በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በዚሁ ቻናል በመግባት ስልጠናውን live መከታተል ትችላላችሁ!
👍31470🤩13🔥12🎉11😱6😁4
2025/07/14 04:11:52
Back to Top
HTML Embed Code: