Telegram Web Link
የአእምሮ እውቀት (IQ) እና የስሜት ብልህነት (EQ)

ሁለቱም ያስፈልጋችኋል፡፡


1️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) የትምህርት ጥበብ ይሰጣችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) የኑሮ ጥበብ ይሰጣችኋል፡፡

2️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ያሳያችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) ማድረግ ያለባችሁን ነገር እንዴት እንደምታደርጉት የአደራረግ ብልሃት ይሰጣችኋል፡፡

3️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) የመጽሐፍ እውቀት ይሰጣችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) የማህበራዊ ኑሮ እውቀት ይሰጣችኋል፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ለመሰልጠን በርካቶች እየተመዘገቡ ነውና እናንተም አያምልጣችሁ፡፡

ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
48👍33🔥2
ለውጥ የሌለው ይቅርታ!
(ደጋግመው ከሚመጡልኝ ጥያቄዎች መካከል)
👍179
ለውጥ የሌለው ይቅርታ!
(ደጋግመው ከሚመጡልኝ ጥያቄዎች መካከል)

ዶ/ር አንድ ሰው ሁል ጊዜ ይቅርታ እየጠየቀ ነገር ግን ደጋግሞ የሚጎዳን ከሆነ ምን እናድርግ?

ሁል ጊዜ አንድን ተገቢ ያልሆነ ተግባር በመፈጸም እየጎዳችሁና ዘወትር ይቅርታ እየጠየቃችሁ፣ ያንንው ተግባር መልሶ መላልሶ በመደጋገም በተደጋጋሚ የሚጎችሁን ሰው አያያዙን ካላወቃችሁበት ሁል ጊዜ እንደተጎዳችሁ ትኖራላችሁ፡፡

ስለዚህ፣ የሚቀጥለውን ይቅርታ ከመቀበላችሁ በፊት ሊኖራችሁ የሚገባውን ተጨማሪ ምላሽ በሚገባ አስቡበት፡፡

በተለይም የቅርብና የእነሱ የሆኑትን ሰዎች ደጋግመው እየጎዱ አሁንም “ይቅርታ” የሚጠይቁና የማይለወጡ ሰዎች ሁኔታው በዚያ መልክ የሚቀጥል የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሞኞች ናቸው፡፡

ሆኖም፣ ከእነሱ የበለጡት ሞኞች ግን በተመሳሳይ ሰውና በተመሳሳይ ጥፋት ደጋግመው እየተጎዱ፣ እየቆሰሉና ሕይወታቸው እየተመሰቃቀለ ተገቢውን ምላሽ የማይሰጡት ናቸው፡፡

አስር ጥቂት መመሪያዎች

1. ሁል ጊዜ ጥፋት እየሰሩ የሚበድሏችሁን ሰዎች ይቅር ማለት ጥቅሙ ለራሳችሁ እንደሆነ በማወቅ ያንን አድርጉ፡፡

2. ሁል ጊዜ በተመሳሳይ ሰው እና በተመሳሳ ሁኔታ የምትጎዱ ከሆነ ችግሩ ያለው እነሱ ጋር ሳይሆን እናንተው ጋር እንደሆነ እወቁ፡፡

3. ለሰዎቹ ይቅርታ ካደረጋችሁ በኋላ ስህተቱን ደግሞ የሚሰሩ ከሆነ ሊከተል የሚችለውን ምላሻችሁን በተረጋጋ ሁኔታ ግለጹላቸው፡፡

4. ሰዎቹ የማይታረሙ ከሆነ መውሰድ የሚገባችሁትን ማንኛውም ራሳችሁን የመጠበቅ ምላሽ ውሰዱ፡፡

5. የምትሰጡት ምላሽ ከልክ ያለፈና ስሜታዊ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡

6. የምትሰጡትን ምላሽ አንዴ ጀመር አንዴ ቆም ማድረግ የደካማነት ምልክት እንደሆነና ሰዎቹን የበለጠ እንደሚያበረታታቸው አስታውሱ፡፡

7. ሆን ብለው ከሚጎዷችሁ ሰዎች ራስን የመጠበቂያው መንገድ መለየት የሚሆንበት ጊዜ እንዳለ ተቀበሉት፡፡

8. ግንኙነታችሁ እንደ ትዳርና የቅርብ ዝምድና አይነት ሲሆን የመለየትን ምርጫ በብዙ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባችሁ አስቡበት፡፡

9. በሰዎች በጣም እየተጎዳችሁ ከእነሱ መራቅ ካልቻላችሁ ልትላቀቁ የሚገባችሁ የስነ-ልቦና ቀውስ (trauma) ሊኖርባችሁ ስለሚል የምክር እገዛን አግኙ፡፡

10. ማንኛውም ግንኙነት ሰላማችሁን ካስከፈላችሁ ግንኙነቱ እጅግ ውድ ነገር እያስከፈላችሁ እንደሆነ አስታውሱ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
84👍54🎉3
“የልጅነት የስሜት ቀውስ (childhood trauma) ምልክቶቸ ዋነኛው!

"አንድ አስቸጋሪ ሰው ለእኛ ጥሩ እንዲሆን ለማድረግ የመሞከር ከልክ ያለፈ ቻይነት ነው” ይሉናል፣ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ባለሞያዎች፡፡

• አንድ ሰው ለእናንተ ጥሩ እንዳልሆነ እያወቃችሁ አሁንም ያንን ሰው ካለልክ የምትታገሱ ከሆነ፣

• አንድ ለእናንተ ብዙም ግድ የማያሰጠውን ሰው ካለልክ በተስ የምትጠብቁ ከሆነ፣

• ከአንድ ሁል ጊዜ ከሚጎዳችሁ ሰው መለየት ወይም ራሳችሁን መጠበቅ እስከማትች ድረስ ከዚያ ሰው ጋር የምትጣበቁ ከሆነ፣

• ከአንድ ለእናንተ ጥሩ ካልሆነ ሰው ውጪ ሕይወት የማይታያችሁ ከሆነ፣

“የልጅነት የስሜት ቀውስ (childhood trauma) ሰለባ የመሆናችሁ ምልክት ሊሆን ስለሚችል ለሁኔታው ትኩረት ስጡት፡፡

ለዚህና ለመሰል ከስሜት ጋር ለሚገናኙ ሁኔታዎች ብስለት ለማዳበር የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቷል!

ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍6117🤩2🔥1
የትኛውን ትመርጣላችሁ?
“ብርቱ ባህሪ እና ቀለል ያለ ህይወት በአንድ ላይ እንዲኖራችሁ መመኘት አትችሉም። አንዱን ለማዳበርና ለመያዝ ሌላኛውን ስለሚያስከፍላች ማለት ነው”

ብርቱ ባህሪን ስትፈልጉ ያንን ለማዳበር የምትሄዱበት ጎዳና ሕይወትን ከበድ ያደርገዋል፡፡

ቀለል ያለ ሕይወትን ስትልፈልጉ ደግሞ ያንን ቀለል ያለ ሕይወት ላለመልቀቅ ብርቱ ባህሪን ለማዳበር ከበድ ይላል፡፡

የትኛውን ትመርጣላችሁ?

በስሜት ብህነት የመብሰል አስፈላጊነት አንዱ ለብርቱ ባህሪይ ብላችሁ ከበድ ያለን ጎዳና ታግሶ የማለፍ ጥንካሬን ማግኘት ነው፡፡

በዚህ ዙሪያ የተዘጋጀውን ስልጠና አስልከቶ ሰሞኑን የሚለጠፉትን ማስታወቂያዎች ይመልከቱ!

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo


@DrEyobmamo
👍6921🔥1
በቅርቡ ሊሰጥ የተዘጋጀው ስልጠና ከሚዳስሳቸው ነጥቦች የተወሰኑት

1. “ስሜት” ምንድን ነው?

2. “ቀዳማዊ” እና “ተከታይ” ስሜቶች

3. ሶስቱ በስሜት ላይ ተጽእኖ ያላቸው መነሻዎች

4. የስሜት ብልህነት ከአእምሮ ብልህነት ጋር ያለው ልዩነት

5. የስሜት ብልህነትና የአእምሮ ብልህነት ውህደት

6. የስሜት ብልህነት ልህቀት

7. የራስን ስሜት የማወቅ ብልህነት

8. የራስን ስሜት “የማስተዳደር”ብልህነት

9. ከልጅነት የስሜት ቀውስ (childhood trauma) መውጣት

10. የማመዛዘን ብልህነት

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo
👍5924🔥1😁1🎉1
አንዳንድ ሰዎችና ሁኔታዎች ከሕይወታችሁ በመውጣታቸው ምክንያት ቀድሞ የነበራችሁ ሰላማችሁ ከተመለሰላችሁ፣ በእርግጥም እነዚያን ሰዎችና ሁኔታዎች እንዳጣችኋቸው አትቁጠሩት፡፡

የሰላም እንቅልፍ ይሁንላችሁ!
👍19279😢10🎉6
በስሜት ውጣ-ውረድ ውስጥ ከሚያልፉት ሰዎች አንደበት

➡️ አንድ ነገር አቅድና ለመጀመር ከነገ ነገ እያልኩ ሳስተላልፈው በዚያው ይቀራል፡፡

➡️ አንድን ነገር በከፍተኛ ተነሳሽነት እጀምረውና ብዙ ሳልሄድ አቆመዋለሁ፡፡

➡️ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እጀምርና ግንኙነቱን የሚረብሹ አንዳንድ ስሜታዊነቶች ስለምገልጽ ግንኙነቱ አይቀጥልም፡፡

➡️ ካለፈው ስህተቴ አልፎ መሄድ ስለሚያስቸግረኝ በጸጸት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡

➡️ ሰዎች በእኔ እንደተከፉ ካሰብኩኝ እረፍት አጣለሁ፡፡

➡️ ሁል ጊዜ ባላጠፋሁትም ነገር ቢሆን ይቅርታ ስጠይቅ ራሴን አገኘዋለሁ፡፡

➡️ ለብቻዬ ስሆን የሚሰማኝን ስሜት ስለማልወደው ሁል ጊዜ በአካል ወይም በማሕበራዊ ሚዲያ ከሰዎች ጋር ማሳለፍ አለብኝ፡፡

➡️ ከሰዎች ጋር ስሆን ምቾት ስለማይሰጠኝ ደስ ሳይለኝ በብቸኝነት አሳልፋለሁ፡፡

➡️ ከአንድ አሉታዊ ስሜት ለመውጣት ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል፡፡

እነዚህና መሰል የስሜት ሁኔታዎች የሚያታግሏችሁ ከሆነ በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት የመብሰል ሁኔታ ላይ መስራት ይኖርባችኋል፡፡

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበላችሁ ፖስተር ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ በረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ጥያቄያችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍8316🎉4
በጎ አድራጎት የሕይወት ዘይቤ ሲሆን!

አንዲት ሴት በመንገድ ላይ ተቀምጦ እንቁላል የሚሸጥን ሰው አገኘችና፣ “ዋጋው ስንት ነው አለችው፡፡
አንዱን በ50 ሳንቲም (የ Dollar ግማሽ) ነው የምሸጠው” ብሎ መለሰላት፡፡

እሷም፣ “ስድስቱን እንቁላል በሁለት Dollar ከሸጥክ ልግዛህ፣ አለዚያ ትቼህ መሄዴ ነው” አለችው፡፡

የመንገድ ላይ ሻጪውም፣ “ከነጋ ምንም ስላልሸጥኩኝና ገንዘቡን ለህልውናዬ ስለምፈልገው በፈለግሺው ዋጋ ግዢኝ” አላት፡፡

ሁለት Dollar ከፍላ ስድስቱን እንቁላል ይዛ በአሸናፊነት ስሜት ሄደች፡፡

ይህች ሴት በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ከአንድ ጓደኛዋ ጋር አንድ ያማረ ሬስቶራንት ሄዱና ምግብ በማዘዝ የተወሰነውን በልተው ብዙ ተረፋቸው፡፡ በመጨረሻም፣ ሂሳብ ሲመጣ ዋጋው 150 Dollar ነበር፡፡ ሴትዬዋም 200 Dollar ሰጥታው የሬስቶራንቱን ባለቤት መልሱን ለቲፕ እንዲያስቀረው ነገረችው፡፡

የዚህ ታሪክ ጸሃፊ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፡

“ከችግረኞችና አቅም ከሌላቸው ስንገዛ የበላይነትን የምናሳየው፣ ጨከን የምንለውና እስከመጨረሻዋ ሳንቲም ድረስ የምንከራከረው፣ የእኛ ልግስና ለማያስፈልጋቸው ደግሞ ካለልክ ልግስናችንን ለማሳየት የምንሞክረውና ብዙ ገንዘብ የምንረጨው ለምንድን ነው?”

ጸሃፊው፣ ከዚህች ሴት በተቃራኒ፣ አንድን ነገር ከአንድ ችግረኛ ሻጭ ሲገዛ ከተጠየቀው ዋጋ በላይ የከፈለን ሰው አጭር ታሪክም ያጋራል፡፡

ልጆቹ ያደረገውን አይተው፣ “አባ፣ ለምንድን ከተጠየከው መጠን በላይ የከፈልከው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ይህ አይነቱ በጎ አድራጎት የሕይወት ዘይቤዬ ነው” ብሎ መለሰላቸው፡፡

በጎ አድራጎት የታይታ ሳይሆን የሕይወት ዘይቤ ሲሆን!

https://m.youtube.com/user/naeleyob623
174👍72🔥11🎉4😢3🤩1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ስሜታችሁን ትገዙታላችሁ፣ ወይም ደግሞ ስሜታችሁ ይገዛችኋል!

ስሜታችሁን የመግዛታችሁ ምልክቶች

• ስሜቶቻችሁን እንደመጣ ባለመልቀቅ መረጋጋት

• ስሜቶቻችሁን ካለልክ አለማፈን

• ስሜቶቻችሁን በትክክለኛው ሰው፣ ቦታ፣ ጊዜና መጠን መግለጥ

• ካለፉት አጓጓል ስሜታዊነቶች ትምህርት በመውሰድ ራስን ማሻሻል

ስሜታችሁ እናንተን የመግዛቱ ምልክቶች

• ለስሜታችን ጊዜን መስጠት አለመቻልና እንደመጣ መልቀቅ

• ስሜትን ከገለጡ በኋላ መጸጸት፣ ተመልሶ እዚያው መገኘት

• ስሜትን መግለጽ አለመቻልና ለረጅም ጊዜ አምቆ መፈንዳት

• ትክክል እንዳልሆነ የምውታቁትን ስሜታዊነት አሁንም ሲገልጹ ራስን ማግኘትና አለመሻሻል

በዚህ ርእስ ላይ የበለጠ ግንዛቤ በማግኘት ስኬታማ ጉዞ ለመጀመር የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

የስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
51👍42😁2🎉1
በስሜት የበሰለ ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ፡

ሰዎች ተገቢ ያልሆነ ነገር ሲያደርጉበት ለመበቀልና ሰዎቹን ለመጉዳት ከመቸኮል ይልቅ ሰዎቹን ለዚያ ተግባር የዳረጋቸውን ሁኔታ ለመገንዘብ መሞከር ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
95👍54🔥9🎉3😁1
ባይሆን ጥሩ ነበር! ከሆነ ግን . . .

• ባይሆን ጥሩ ነበር! ነገር ግን፣ አንተ እኔ ጋር መደወል ያለህን ፍላጎት ስታቆም፣ እኔም አንተን መጠባበቅ አቆማለሁ፡፡

• ባይሆን ጥሩ ነበር! ነገር ግን፣ አንተ ከእኔ ጋር መገናኘት ያለህን ፍላጎት ስትተው፣ እኔም ጊዜዬን ከአንተ ውጪ የማሳልፍበትን መንገድ እፈጥራለሁ፡፡

• ባይሆን ጥሩ ነበር! ነገር ግን አንተ ከእኔ የተሻለ ሰውና ሁኔታ እንዳገኘህ ስታስብና ዘወር ስትል፣ እኔም ለአንተ የሰጠሁህን ትኩረት ራሴን ለመለወጥና ለማሳደግ ወደ መጠቀም አዞረዋለሁ፡፡

• ባይሆን ጥሩ ነበር! ነገር ግን የገባኸውን ቃል ካጠፍክ፣ መፈጸም ካልፈለክና የራስህን መንገድ መሄድ ከፈለክ፣ እኔም በማንም ሰውና በምንም አይነት ሁኔታ ተሰብሬ አልቀርም የሚለውን ለራሴ የገባሁትን ቃል-ኪዳን በመጠበቅ ትክክለኛውንና ጨዋውን መንገድ በመከተል እሄዳለሁ፡፡

• ባይሆን ጥሩ ነበር! ለእኔ ከነበረህ ከድሮው አቀራረብህ የመቀያየርህ ሁኔታ እውን ከሆነ ግን ራሴን ከማጣው፣ ማንንም ሰውና የትኛውንም ሁኔታ ማጣት ይሻለኛልና ራሴ ላይ ለመስራት ወስኛለሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍18597🔥10🎉4
👍83
ሁለቱ የውስጥ ፍልሚያዎች!

“በሕይወቴ ከተፋለምኳቸው ፍልሚያዎች እጅግ የከፋው ፍልሚያ፣ ውስጤ ትክክል እንደሆነ በሚያውቀው ነገርና ከዚያ በተቃራኒ ስሜቴ እንዳደርገው በሚያነሳሳኝ ነገር መካከል ያደረኩት ፍልሚያ ነው” - ካልታወቀ ምንጭ

እባካችሁ!!! ስሜታችሁ የሚላችሁ ለጊዜው ይቆይላችሁና እውነተኛና ትክክለኛ እንደሆነ ውስጣችሁ የሚያውቀውን መንገድ ተከተሉ፡፡ የሚያዛልቃችሁ እሱ ነውና!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
131👍57😱5🔥2🎉2
የአእምሮ እውቀት (IQ) እና የስሜት ብልህነት (EQ)

ሁለቱም ያስፈልጋችኋል፡፡


1️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) የትምህርት ጥበብ ይሰጣችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) የኑሮ ጥበብ ይሰጣችኋል፡፡

2️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ያሳያችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) ማድረግ ያለባችሁን ነገር እንዴት እንደምታደርጉት የአደራረግ ብልሃት ይሰጣችኋል፡፡

3️⃣ የአእምሮ እውቀት (IQ) የመጽሐፍ እውቀት ይሰጣችኋል፣ የስሜት ብልህነት (EQ) የማህበራዊ ኑሮ እውቀት ይሰጣችኋል፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ለመሰልጠን በርካቶች እየተመዘገቡ ነውና እናንተም አያምልጣችሁ፡፡

ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍8024
የማየው ነገርና የሚሰማኝ ስሜት ግንኙነት!

ደስ የማይል ስሜት ከተሰማችሁ፣ ስሜቱ እንዲመጣ ያደረገ ሃሳብ እንዳሰባች አትጠራጠሩ፡፡ ስለዚህ፣ ሃሳብ ስሜትን ይወልዳልና ስሜትን ለመቆጣጠር ሃሳብ ላይ መስራት የግድ ነው፡፡ ሃሳብ ላይ ለመስራት ደግሞ ሃሳብ ወደ አእምሯችን የሚገባባቸውን በሮች ማጤን ነው፡፡

ከእነዚህ በሮች መካል አይናችን አንዱ ነው፡፡ የምናያቸው ነገሮች በውስጣችን ሃሳብን ይዘራሉ፣ እነዚህ ሃሳቦች ደግሞ ወዲያውም ሆነ ሰንበትበት ብለው ስሜትን ያስከትላሉ፡፡

ለዛሬ የሚከተሉትን ላስታውሳችሁ . . .

• አስፈሪና አሰቃቂ (horror) ፊልሞች ማየት የምታዘውትሩ ከሆነ ፈጠነም ዘገየም የፍርሃት ስሜትና የሌሊት ቅዠቶች ይከተላል

• የተገኘውን ዜና ማየት የምታዘውትሩ ከሆነ እናንተ ብትጨነቁ ምንም ለውጥ በማታመጡት ነገር ሁሉ የመስጋት የመደንገጥ ስሜት ይከተላል

• ወሲብ-ተኮር (Pornography) ፊልሞችን ማየት የምታዘውትሩ ከሆነ ልቅ የሆነ የወሲብ ስሜት ወይም ለትዳር አጋራችሁ የወሲብ ፍላጎት የማጣት ስሜት ይከተላል

• በአካል የማታውቁት ሰው የሚልክላችሁን መልእክትና የእሱን ምስል በማሕበራዊ ሚዲያ ማየት የምታዘውትሩ ከሆነ የመሳብና የትስስር ስሜት ይከተላል

• በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰነዘሩ የግለሰቦች ትችቶች (Comments) ማየት የምታዘውትሩ ከሆነ የተቺነትና የነቃፊነት ስሜት ይከተላል

የምታዩትን ነገር በመቆጣጠር ሃሳባችሁንና ከዚያም ስሜታችሁን ሚዛናዊ በማድረግ ብቃት ማደግ ትችላላችሁ፡፡ ስሜታችሁ ሚዛናዊ ሲሆን ደግሞ ተግባራችሁ መልክ ይይዛል፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍16762🔥6
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
በቅርቡ ሊሰጥ የተዘጋጀው ስልጠና ከሚዳስሳቸው ነጥቦች የተወሰኑት

1. “ስሜት” ምንድን ነው?

2. “ቀዳማዊ” እና “ተከታይ” ስሜቶች

3. ሶስቱ በስሜት ላይ ተጽእኖ ያላቸው መነሻዎች

4. የስሜት ብልህነት ከአእምሮ ብልህነት ጋር ያለው ልዩነት

5. የስሜት ብልህነትና የአእምሮ ብልህነት ውህደት

6. የስሜት ብልህነት ልህቀት

7. የራስን ስሜት የማወቅ ብልህነት

8. የራስን ስሜት “የማስተዳደር”ብልህነት

9. ከልጅነት የስሜት ቀውስ (childhood trauma) መውጣት

10. የማመዛዘን ብልህነት

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo
👍7724
“በነጻ የሚባል ነገር የለም”!
24👍11😁6
“በነጻ የሚባል ነገር የለም”!

ምንም እንኳን አንዳንድ ነገሮችን እንዲሁ በነጻ ብታገኙም ወይም ደግሞ ያገኛችሁ ቢመስላችሁም፣ አጠቃላይ የሕይወታችንን ሂደት ስንመለከተው፣ በነጻ የምናገኛቸው ነገሮች እንደሌሉ እንደርስበታለን፡፡

ማንኛውም ጥራት ያለው ነገር የሆነ ነገር ያስከፍላል፡፡ ማግኘት የምንፈልገውን ነገር በነጻ ስንጠብቅ ባዶ እጃችንን የመቅረታችን እድል የሰፋ ነው፡፡

ማግኘት ለፈለግነው የከበረ ነገር ርካሽ ስንከፍል ደግሞ ርካሽ ነገር የማግኘታችን ሁኔታ የጎላ ነው፡፡

ማግኘት ለፈለግነው መልካም ነገር የሚመጥን ነገር ለመክፈል ዘግጁ ስንሆን ግን አስገራሚ አለም ውስጥ እንገባለን፡፡

ማንኛውን ጠቃሚ ነገር በነጻ ካገኛችሁት . . .

1. የበለጠ ስላልተሰጣችሁ ከመነጫነጭ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

2. በነጻ የሰጧችሁን ባለማመስገን ተጠቅሞ ዘወር ከማለት ተጠበቁ፡፡

3. በነጻ ስለተሰጣችሁ አመስጋኝ መሆንን ልመዱ፡፡

ማንኛውንም ጠቃሚ ነገር በነጻ ካላገኛችሁት . . .

1. ለምን በነጻ እንዳልተሰጣችሁ ከመነጫነጭና ሰዎች ራስ-ወዳድ እንደሆኑ በማሰብ ከመውቀስ ተጠበቁ፡፡

2. የሚከፈል እንደሌላችሁ በማሰብና እድላችሁን በማማረር ባዶ እጅን ከመቀመጥ ተጠበቁ፡፡

3. በተቻላችሁ መጠን መንገድ ፈልጋችሁ የሚከፈለውን ከፍላችሁ ጠቃሚ ነገሮችን በእጃችሁ ማስገባት ላይ ስሩ፡፡

ደግሜ ላስታውሳችሁ! በዚህች ምድር ላይ ነጻ የሚባል ነገር የለም!

• ምንም ነገር ሰዎች በነጻ ሊሰጧችሁ እንደሚገባ አታስቡ፡፡ በዚያ ምትክ፣ ሰርታችሁ ለማግኘት ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

• እናንተ ጋር ያለውን መልካም ነገር ሰዎች እንዲሁ በነጻ ይቀበሉታል ብላችሁ አታስቡ፡፡ በዚያ ፈንታ፣ ተቀባይነትን ለማግኘት መከፈል የሚገባውን የታማኝነትን ዋጋ ክፈሉ፡፡

• ሰዎች እንዲሁ ሊያምኑኝ ይገባል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ይልቁንስ፣ ሰዎች እንዲያምኗችሁ የሚያስችል የማያቋርጥ ታማኝነትን የማዳበር ነገር ላይ ስሩ፡፡

ማንኛውንም ጠቃሚ ነገር ለማግኘት ዋጋ መክፈል እንዳለባችሁ ስታምኑና ለዚያም ስትዘጋጁ፣ አስገራሚ አለም ውስጥ ትገባላችሁ፡፡ ይህ አለም፣ ብርቱዎች፣ ትጉዎችና የዲሲፕሊን ሰዎች ያሉበት አለም ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍12142🎉2
2025/07/13 18:13:18
Back to Top
HTML Embed Code: