Telegram Web Link
“በነጻ የሚባል ነገር የለም”!
24👍11😁6
“በነጻ የሚባል ነገር የለም”!

ምንም እንኳን አንዳንድ ነገሮችን እንዲሁ በነጻ ብታገኙም ወይም ደግሞ ያገኛችሁ ቢመስላችሁም፣ አጠቃላይ የሕይወታችንን ሂደት ስንመለከተው፣ በነጻ የምናገኛቸው ነገሮች እንደሌሉ እንደርስበታለን፡፡

ማንኛውም ጥራት ያለው ነገር የሆነ ነገር ያስከፍላል፡፡ ማግኘት የምንፈልገውን ነገር በነጻ ስንጠብቅ ባዶ እጃችንን የመቅረታችን እድል የሰፋ ነው፡፡

ማግኘት ለፈለግነው የከበረ ነገር ርካሽ ስንከፍል ደግሞ ርካሽ ነገር የማግኘታችን ሁኔታ የጎላ ነው፡፡

ማግኘት ለፈለግነው መልካም ነገር የሚመጥን ነገር ለመክፈል ዘግጁ ስንሆን ግን አስገራሚ አለም ውስጥ እንገባለን፡፡

ማንኛውን ጠቃሚ ነገር በነጻ ካገኛችሁት . . .

1. የበለጠ ስላልተሰጣችሁ ከመነጫነጭ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡

2. በነጻ የሰጧችሁን ባለማመስገን ተጠቅሞ ዘወር ከማለት ተጠበቁ፡፡

3. በነጻ ስለተሰጣችሁ አመስጋኝ መሆንን ልመዱ፡፡

ማንኛውንም ጠቃሚ ነገር በነጻ ካላገኛችሁት . . .

1. ለምን በነጻ እንዳልተሰጣችሁ ከመነጫነጭና ሰዎች ራስ-ወዳድ እንደሆኑ በማሰብ ከመውቀስ ተጠበቁ፡፡

2. የሚከፈል እንደሌላችሁ በማሰብና እድላችሁን በማማረር ባዶ እጅን ከመቀመጥ ተጠበቁ፡፡

3. በተቻላችሁ መጠን መንገድ ፈልጋችሁ የሚከፈለውን ከፍላችሁ ጠቃሚ ነገሮችን በእጃችሁ ማስገባት ላይ ስሩ፡፡

ደግሜ ላስታውሳችሁ! በዚህች ምድር ላይ ነጻ የሚባል ነገር የለም!

• ምንም ነገር ሰዎች በነጻ ሊሰጧችሁ እንደሚገባ አታስቡ፡፡ በዚያ ምትክ፣ ሰርታችሁ ለማግኘት ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡

• እናንተ ጋር ያለውን መልካም ነገር ሰዎች እንዲሁ በነጻ ይቀበሉታል ብላችሁ አታስቡ፡፡ በዚያ ፈንታ፣ ተቀባይነትን ለማግኘት መከፈል የሚገባውን የታማኝነትን ዋጋ ክፈሉ፡፡

• ሰዎች እንዲሁ ሊያምኑኝ ይገባል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ይልቁንስ፣ ሰዎች እንዲያምኗችሁ የሚያስችል የማያቋርጥ ታማኝነትን የማዳበር ነገር ላይ ስሩ፡፡

ማንኛውንም ጠቃሚ ነገር ለማግኘት ዋጋ መክፈል እንዳለባችሁ ስታምኑና ለዚያም ስትዘጋጁ፣ አስገራሚ አለም ውስጥ ትገባላችሁ፡፡ ይህ አለም፣ ብርቱዎች፣ ትጉዎችና የዲሲፕሊን ሰዎች ያሉበት አለም ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍12142🎉2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
በቅርቡ ሊሰጥ የተዘጋጀው ስልጠና ከሚዳስሳቸው ነጥቦች የተወሰኑት

1. “ስሜት” ምንድን ነው?

2. “ቀዳማዊ” እና “ተከታይ” ስሜቶች

3. ሶስቱ በስሜት ላይ ተጽእኖ ያላቸው መነሻዎች

4. የስሜት ብልህነት ከአእምሮ ብልህነት ጋር ያለው ልዩነት

5. የስሜት ብልህነትና የአእምሮ ብልህነት ውህደት

6. የስሜት ብልህነት ልህቀት

7. የራስን ስሜት የማወቅ ብልህነት

8. የራስን ስሜት “የማስተዳደር”ብልህነት

9. ከልጅነት የስሜት ቀውስ (childhood trauma) መውጣት

10. የማመዛዘን ብልህነት

ለበለጠ መረጃ ከዚህ በታች ባለው link inbox ያድርጉ

@DrEyobmamo
👍5018😁2
ከስሜት ቀውስ ጋር የሚታገሉ ሰዎች . . .
👍174
ከስሜት ቀውስ ጋር የሚታገሉ ሰዎች . . .

➡️ እርዳታ እየፈለጉ እንኳን እርዳታ መጠየቅ ስለሚያስቸግራቸው ሁል ጊዜ ሁኔታቸው በራሳቸው ለመፍታት ይታገላሉ፡፡

➡️ ፈታ የማለት (relax የማድረግ) ስሜት ስለሌላቸው ሁል ጊዜ የሆነ ነገር እንደጎደለ አይነት ስሜት ይዘው በተጠንቀቅ ነው የሚኖሩት፡፡

➡️ ላጠፉትም ላላጠፉትም ነገር ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አላቸው፡፡

➡️ ከሰዎች ጋር ካሳለፉ ወይም ከተነጋገሩ በኋላ ሁኔታውን በሃሳባቸው በማውጣትና በማውረድ “ምነው እንዲህ ባልኩኝ” እና “ምነው እንዲህ ባላልኩኝ” የሚሉት ነገር ብዙ ነው፡፡

➡️ እነሱ በውል ምክንያቱን አያውቁትም እንጂ ገና ለገና ሰዎች ይገፉኛል በማለት ቀድሞኑ ሲቀርቧቸው ራሳቸውን ክፍት ማድረግ ያታግላቸዋል፡፡

➡️ ሁል ጊዜ ከሰዎች መደነቅንና ጎሽ መባልን (approval and validation) ይፈልጋሉ፡፡

➡️ በምንም ሁኔታ ውስጥ ሰዎችን ቅር ማሰኘት ስለማይፈልጉ ሰዎች ለሚሰማቸው ስሜት እነሱ ሃላፊነትን የመውሰድ ዝንባሌ አላቸው፡፡

እንደዚህና እነዚህን መሰል የስሜት መዛባቶች ከታዩባችሁ መፍትሄው በስሜት ብልህነት በሚገባ የመብሰልን ጉዞ መጀመር ነው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ ለመሰልጠን በርካቶች እየተመዘገቡ ነውና እናንተም አያምልጣችሁ፡፡

ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገል መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
81👍63😁3🔥1
በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!
👍261
በዜሮ የተባዛው አገልግሎት!

አንድ ንጉስ አስር አመት ሙሉ በታማኝነት ያገለገለው አገልጋዩ እንዲት ስህተት ስለሰራ ብቻ ቅጣትን አስተላለፈበት፡፡

በንጉሱ ሕግ መሰረት ማንኛውም ስህተት የሰራ አገልጋይ በኃይለኛነታቸውና በተናካሽነታቸው የታወቁት የንጉሱ ውሾች ወደሚኖሩበት ግቢ ለቅጣት ታልፎ ይሰጣል፡፡

ይህንን የንጉሱን ውሳኔ የሰማው ታማኝ አገልጋይ በሁኔታው በጣም አዘነ፡፡ እሱን ያሳዘነው የተላለፈው ቅጣት ሳይሆን፣ ለአስር አመታት ካለምንም ስህተት አገልግሎ፣ አንዲት ስህተት ብቻ ስለተገኘችበት የንጉሱ መጨከን ነው፡፡

ይህ አገልጋይ ቁጭ ብሎ፣ “ይህንን ቅጣት አስቀረሁትም፣ አላስቀረሁት ንጉሱ ግን ይህንን ጥሩ ያልሆነ ልምምድ የሚያቆምበትን አንዲት ትምህርት ባስተምረው ደስ ይለኛል” ብሎ አሰበና አንድ ብልሃት መጣለት፡፡

ንጉሱንም፣ “ቅጣቱን እቀበላለሁ፣ ቅጣቱ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን አስር ቀን ይሰጠኝና ከዚያ በኋላ በፈቃዴ ለቅጣቱ እመጣለሁ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ንጉሱም ፈቀደለት፡፡

በእነዚህ አስር ቀናት ለውሾቹ የሚሆንን ምግብ አዘጋጅቶ እነሱ ያሉበት ግቢ በመሄድና ቀስ ብሎ በመቅረብ እያበላቸው፣ እየተንከባከባቸውና እያሻሻቸው በሚገባ ካገለገላቸው በኋላ በአስረኛው ቀን ወደ ንጉሱ መጣ፡፡

ፍርዱ አልቀረለትም ነበረና ወደውሾቹ ግቢ እንዲጣል ትዝዛዝ ተላለፈበትና ተጣለ፡፡ ውሾቹ ለአስር ቀን የተንከባከባቸውንና ያገለገላቸውን ይህንን ሰው ምንም ነገር አላደረጉትም ነበር፡፡

ንጉሱም ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተ ሁኔታ በመሆኑ ተገርሞ አስጠራውና የተፈጠረውን ጠየቀው፡፡

አገልጋዮም፣ “ንጉስ ሆይ፣ እርሶን አስር አመት በታማኝነት አገልግዬ አንዲት ጥፋት ስለተገኘብኝ ብቻ ያ ሁሉ ታማኝነቴና አገልግሎቴ ተረሳና ምህረትም አላገኘሁም፡፡ እነዚህ ውሾች ግን ለአስር ቀናት ብቻ ስላገለገልኳቸው ምንም እንኳን ጥፋተኛ ሆኜ ለእነሱ ታልፌ ብሰጥም ያንን አገልግሎቴን ባለመርሳት ምንም አላደረጉኝም” አለው ይባላል፡፡

ንጉሱ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህንን ባህሪውን ለማረም ክፍት ወደመሆን እንደመጣ ይነገራል፡፡

ሰዎች ያሳዩንን የብዙ ዓመታት ታማኝነትና አገልግሎት በአንዲት ስህተት ምክንያት በዜሮ አናባዛው፡፡ ይቅርታን እንልመድ! ለሰዎች ሁለተኛ እድልን መስጠትን እንልመድ! ውለታ ቢሶች አንሁን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍17197🔥8😁3
በስሜት ብልህነት ከመብሰሌ በፊት . . .

➡️ ስህተት ስሰራ ራሴን በጣም እወቅስ ነበር፡፡ አሁን ግን፣ ከእያንዳንዱ ስህተት ትምህርትን ማግኘትንና ስህተቱን አለመድገምን ተለማምጃለሁ፡፡

➡️ ራሴን ከሌሎች ጋር በማነጻጸር ተስፋ እቆርጥ ነበር፡፡ አሁን ግን፣ የራሴ ማንነት በመቀበልና ለራሴ ባወጣሁት ግብ ላይ በማተኮር መኖርን ተለማምጃለሁ፡፡

➡️ ሰዎች የሚናገሩኝ አሉታዊ ነገር እየረበሸኝ ከእኔ ጋር ብዙ ጊዜ ይቆይ ነበር፡፡ አሁን ግን፣ ሰዎች የራሳቸው የሆነ አመለካከት፣ የስሜት ብስለትና ባህሪይ ስላላቸው የፈለጉትን ማሰብና መናገር እንደሚችሉ መብት ሰጥቻቸው ራሴን በማሳደግ ላይ ማተኮርን ተለማምጃለሁ፡፡

➡️ ቀን የሆነውን ነገር እያብሰለሰልኩኝ እንቅልፍ በማጣት አመሽ ነበር፡፡ አሁን ግን፣ መለወጥ በምችላቸውና በማልችላቸው በመለየት፣ መለወጥ የማልችለውን መተው፣ መለወጥ ለምችለው ነገር ደግሞ ለነገ እቅድ በማውጣት በሰላም መተኛትን ተለማምጃለሁ፡፡

➡️ አንድ ነገር ቶሎ ካልተሳካ አቋርጠው ነበር፡፡ አሁን ግን፣ የጀመርኩት ነገር ትክክለኛ እንደሆነ ካረጋገጥኩ በኋላ እስከጥጉ የመቀጠልን ዲሲፕሊን ማዳበርን ተለማምጃለሁ፡፡

እነዚህ የተጠቀሱትና መሰል ልምምዶች አንድ ሰው በስሜት ብልህነት እያደገ ሲሄድ የሚያዳብራች ልምምዶች ናቸው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ በሚገባ ለመብሰልና ብዙዎች ያመጡት አይነት ለውጥ ለማምጣት ከፈለጋችሁ የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

ለመረጃው ከዚህ ጽሑፍ ጋር የተለጠፈውን ፖስተር ይመልከቱ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል

@DrEyobmamo
👍10048🔥10🎉3😱1
👍25
ሁለቱ ዲሲፕሊን የማጣት ችግሮች!
👍16
ሁለቱ ዲሲፕሊን የማጣት ችግሮች!

1. አልፈልገውም እኮ! . . . ግን አደርገዋለሁ!

ብዙ ሰዎች ማድረግ የማይገባቸውን ነገር በሚገባ ያውቁታል፣ ያንንም ነገር ማድረግ አይፈልጉም፡፡ ሆኖም ያንንው ነገር ደጋግመው ሲያደርጉት ራሳቸውን ያገኙታል፡፡

ይህ ሁኔታ መነሻው ከተለያዩ ነገሮች ጋር የሚገናኝ ቢሆንም፣ መሰረታዊው ችግር ግን ዲሲፕሊን ካለማዳበር ጋር የተነካካ ነው፡፡

ይህ የዲሲፕሊን ዘርፍ፣ “ያለማድረግ ዲሲፕሊን” ይባላል፤ አንድን ማድረግ የማይገባንን ነገር ያለማድረግን ዲሲፕሊን ማዳበር ማለት ነው፡፡

ይህንን አይነቱን ዲሲፕሊን ማዳበር ካልተጠበቁ አጉል ውጤቶች (unintended consequences) ይጠብቀናል፡፡

የማትፈልጉትን ተገቢ ያልሆነ ነገር ለማቆም ከፈለጋችሁ፣ ከፍተኛ የሆነን ዲሲፕሊን ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በስሜት ብልህነት የመብሰል ዘርፍ ነው፡፡

2. እፈልገዋለሁ እኮ! . . . ግን አላደርገውም!

ከላይ ከተጠቀሰው በተቃራኒ፣ ብዙ ሰዎች ማድረግ የሚገባቸውን ነገር በሚገባ ያውቁታል፣ ያንንም ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ፣ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ጀመር ቢያደርጉትም መልሰው ሲተውት ራሳቸውን ያገኙታል፡፡

ይህም ቢሆን መነሻው ከተለያዩ ነገሮች ጋር የሚገናኝ ቢሆንም፣ መሰረታዊው ችግር ግን ዲሲፕሊን ካለማዳበር ጋር የተነካካ ነው፡፡

ይህ የዲሲፕሊን ዘርፍ፣ “የማድረግ ዲሲፕሊን” ይባላል፤ አንድን ማድረግ የሚገባንን ነገር ካለማቋረጥ የማድረግን ዲሲፕሊን ማዳበር ማለት ነው፡፡

ይህንን አይነቱን ዲሲፕሊን ማዳበር በሕይወታችን የምንጠብቃቸውን መልካም ውጤቶች ከማጣት ይጠብቀናል፡፡

የምትፈልጉትን መልካም ነገር ለመጀመርና ካለማቋረጥ ለመቀጠል ከፈለጋችሁ፣ ከፍተኛ የሆነን ዲሲፕሊን ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በስሜት ብልህነት የመብሰል ዘርፍ ነው፡፡

በዚህ ርእስ ላይ በሚገባ ለመብሰልና ብዙዎች ያመጡት አይነት ለውጥ ለማምጣት ከፈለጋችሁ የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

ለመረጃው ከዚህ ጽሑፍ ጋር የተለጠፈውን ፖስተር ይመልከቱ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል::

@DrEyobmamo
👍9417😢3
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://www.tg-me.com/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo
👍8228
ሰላም የሞላበት ቀን እንዲሆንላችሁ!

(“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተቀነጨበ ሃሳብ)

1. “ሁል ጊዜ አንተው ያመንክበትን ሕይወት መኖርህን እርግጠኛ ሁን፡፡”

2. “ልክህን እወቅ፣ ለስራህና ለሕይወትህ መርህና ገደብ ይኑርህ፡፡”

3. “ማንነትህን፣ ኑሮህንም ሆነ የሰራሃቸውን ስህተቶች አሻሽላቸው እንጂ አትፈርባቸው፡፡”

4. “ከወዳጆችህ ጋር ነጻ የሆነን ግንኙነት መስርት፣ ግልጽነትና የቀረበ ወዳጅነት ቢጎዳህም ከጉዳቱ ጥቅሙ ይበልጣልና በፍጹም አትሽሽ፡፡”

5. በመጨረሻ፣ ሁል ጊዜ ደስተኛ መሆንን ምረጥ፡፡ የሕይወት ቀንደኛ ዓላማዎች ከሚባሉት ውጤቶች መካከል ደስተኛነት አንዱ ነውና፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍8944😁1
የተስፋ ጉልበት!

አንድ ጊዜ በአይጦች የተደረገ አንድ የሙከራ ጥናት እንዲህ ሲል ይነበባል፡፡

አይጦቹን አንድ በአንድ በየተራ ውኃ ውስጥ ይከቷቸውና ዝም ብለው ሲመለከቷቸው አብዛኛዎቹ አይጦች ለአስራ አምስት ደቂቃ ለመዋኘት እየታገሉና እየቀዘፉ ከቆዩ በኋላ በመጨረሻ ተስፋ በመቁረጥ ጥረታቸውን በማቆም መስጠም ይጀምራሉ፡፡

እነዚህን አይጦች ወዲያው ያወጧቸውና የተወሰነ ጊዜ እረፍት ከሰጧቸው በኋላ መልሰው ተመሳሳይ ውኃ ውስጥ ሲጨምሯቸው ለሰዓታት ተስፋ ባለመቁረጥ በመዋኘት ለመውጣት ይታገላሉ፡፡

በመጀመሪያው ልምምዳቸውና በሁለተኛው ልምምዳቸው መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ የደረሱበት ድምዳሜ ይህ ነበር፡፡

የመጀመሪያው ልምምዳቸው ምንም ተስፋ የማይታይበት የመጀመሪያቸው ነበርና ተስፋ ቆርጠው መስጠም ጀመሩ፡፡

ሁለተኛው ልምዳቸው ግን ቀደም ካለው አስቸጋሪ ሁኔታ ወጥተው ስለነበረና የተስፋ ጭላንጭል ስለተመለከቱ ከዚህኛውም እንደሚወጡ ያገኙት ተስፋ የበለጠ እንዲታገሉ አበረታታቸው፡፡

ከታሪኩ የምናገኘው ትምህርት (Moral of the story)

1. ከዚህ በፊት የማንዘልቀው መስሎን የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለፍነው አንዘንጋ፡፡

2. ያንን ሁኔታ ካለፍን አሁንም ያለንበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እናልፈዋለን፡፡

3. በአስቸጋሪ ልምምድ ውስጥ አልፈው በሚሄዱትና በሚሰጥሙት መከካለ ያለው ልዩነት “ተስፋ” ይባላል፡፡

4. በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

በርቱ የምወዳችሁ የሃገሬ ሰዎች!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
129👍69😢1
የስሜት ውጣውረድ የሚያታግላቸው ሰዎች አንዲህ ይላሉ . . .

• አንድ ነገር አቅድና ለመጀመር ከነገ ነገ እያልኩ ሳስተላልፈው በዚያው ይቀራል፡፡

• አንድን ነገር በከፍተኛ ተነሳሽነት እጀምረውና ብዙ ሳልሄድ አቆመዋለሁ፡፡

• ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እጀምርና ግንኙነቱን የሚረብሹ አንዳንድ ስሜታዊነቶች ስለምገልጽ ግንኙነቱ አይቀጥልም፡፡

• ካለፈው ስህተቴ አልፎ መሄድ ስለሚያስቸግረኝ በጸጸት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡

• ሰዎች በእኔ እንደተከፉ ካሰብኩኝ እረፍት አጣለሁ፡፡

• ሁል ጊዜ ባላጠፋሁትም ነገር ቢሆን ይቅርታ ስጠይቅ ራሴን አገኘዋለሁ፡፡

• ለብቻዬ ስሆን የሚሰማኝን ስሜት ስለማልወደው ሁል ጊዜ በአካል ወይም በማሕበራዊ ሚዲያ ከሰዎች ጋር ማሳለፍ አለብኝ፡፡

• ከሰዎች ጋር ስሆን ምቾት ስለማይሰጠኝ ደስ ሳይለኝ በብቸኝነት አሳልፋለሁ፡፡

• ከአንድ አሉታዊ ስሜት ለመውጣት ብዙ ጊዜ ይፈጅብኛል፡፡

እነዚህና መሰል የስሜት ሁኔታዎች የሚያታግሏችሁ ከሆነ በስሜት እና በማሕበራዊ ብልህነት የመብሰል ሁኔታ ላይ መስራት ይኖርባችኋል፡፡

ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበላችሁ ፖስተር ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ በረጃ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ inbox በማድረግ ጥያቄያችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍10523
36👍11
የመገፋት ፍርሃት (ክፍል አንድ)
20👍13
የመገፋት ፍርሃት (ክፍል አንድ)

(“የመገፋት ሕመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ አዲስ መጽሐፍ የተቀነጨበ)

ሁላችንም ቢሆን በመጠኑም ቢሆን መገፋትን የመፍራት ዘር በውስጣችን መኖሩ የሚካድ አይደለም፡፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ የስሜት ቀውስ ውስጥ የሚገኝ ወይም ደግሞ ከዚህ በፊት መገፋትን የቀመሰ ሰው ተገቢውን የመፍትሄ እርምጃ እስከሚወስድ ድረስ እድሜ ልኩን መገፋትን በመፍራት ሊነዳ ይችላል፡፡

በዚህ ውጥረት ውስጥ የማለፉን ሁኔታ በሚገባ ያሰበበት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ “በሕይወቴ ያለው ዋናው የምርጫ ግራ መጋባት፣ የአንድ ህብረተሰብ አካል ለመሆን ባለኝ ጥልቅ የውስጥ ፍላጎቴ (Desire to belong) እና በተቃራኒው ያንን ለማድረግ ባለኝ ፍርሃትና ጥርጣሬ (My suspicion of belonging) መካከል ነው”፡፡

ሰው ከማሕበራዊ ሂደት ጋር የተሳሰረ ማንነት ስላለው በሌላው ሰው መወደድ፣ ተቀባይነት ማግኘትና የአንድ ሕብረተሰብ አባልና አካል የመሆን ጥልቅ ፍላጎት አለው፡፡ ሆኖም፣ በዚህ ጤናማና ተፈጥሯዊ ፍላጎት ላይ ጣልቃ የሚገባ አስቸጋሪ ሁኔታ አለ፡፡

ሰዎች አብሮነትንና ተቀባይነትን የመፈለጋቸውን ያህል በዚያው መጠን መገፋትንና መገለልን አይፈልጉም፡፡ ይህ መገፋትንና መገለልን ያለመፈለጋቸው ተፈጥሯዊ ባህሪይ በሚዛናዊነት ካልተያዘ ለበርካታ የስነ-ልቦና፣ የስሜትና የማሕበራዊ ቀውሶች ይዳርጋቸዋል፡፡

ይህ መስመሩን የሳተ ዝንባሌ ቀስ በቀስ እያደገ በመሄድ መገፋትን ወደመፍራት ዝቅታ ስለሚያወርደን ከብዙ እንቅስቃሴዎቻችን መገታት እንጀምራን፡፡ የመገፋት ፍርሃት በሰዎች የየእለት ግንኙነት ውስጥ ታላቅ አሉታዊ ተጽእኖ የሚያመጣ ስሜት ነው፡፡ መገፋትን፣ መገለልንና እምቢ መባልን ስለማንፈልግ ቀድሞውኑ አይኖቻችንን ጨፍነንና እውነታን ክደን ነገሮችን መሸሽ እንጀምራለን፡፡

ለምሳሌ፣ አንዳንድ ሰዎች ስራ በመፈለግ ከከረሙ በኋላ የስራ ቃለ-መጠይቅ (Interview) የሚያደርጉበት ቀን ሲመጣ “ተቀባይነት ባጣስ” በሚል ፍርሃት ወደፊት መቀጠል ስለሚያስቸግራቸው ምክንያት ፈልገው ያስተላልፉታል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የንግድ ልውውጥ፣ የፍቅር ጥያቄ፣ አዳዲስ ሰዎችን መተዋወቅና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ላይ ራሳቸውን ሲያገኙት ገና ለገና ተቀባይነት አጣና እገፋለሁ በማለት የመፍራት ዝንባሌ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ፍርሃት ደግሞ የሕይወትን ሁለንተናዊ ጣእም ከማጣጣም የሚገታን ጉዳይ ነው፡፡

በሚቀጥለው ጽሑፌ አንድ የመገፋት ፍርሃት ያለበት ሰው የሚያሳያውን ባህሪያት ይዤ እስክመለስ ምናልባት ገና ለገና ሰዎች ይገፉኛል ወይም ተቀባይነትን አጣለሁ በሚል ፍርሃት ከአንዳንድ ወሳኝ እንቅስቃሴዎች እየተገታችሁ እንዳይሆን ራሳችሁን መመልከትና በጉዳዩ ማሰብ መጀመር ትችላላችሁ፡፡

ይቀጥላል . . .
87👍69🔥2😁2😱1
Certificate of Participation!

ከመጋቢት 25 እስከ ሚያዚያ 23
ለአምስት ተከታታይ ኃሙሶች ለሚሰጠው ስልጠና ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት ያገኛሉ ወይ የሚል ጥያቄ ያላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡

መልሱ፣ አዎን! ነው፡፡ ለሰልጣኞች ከዚህ መልእክት ጋር ለ sample የቀረበው ዓይነት የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የተሳትፎ ምስክር ወረቀት ለተሳታፊዎች የሚላከው በ soft copy መሆኑንና በ hard copy እንደማንሰጥ የታወቀ ይሁን፡፡

ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ 16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል::

@DrEyobmamo
👍4925😱3
መቆጣጠር የምትችሉት እና የማትችሉት!

በሕይወታችሁ የሚከናወኑ አስቸጋሪ ነገሮችን በብዙ መንገድ በማየት መስመር ማስያዝ ትችላላችሁ፡፡ ስኬታማ ከሚባሉት መንገዶች አንዱ፣ መለወጥ (መቆጣጠር) በምትችሉት እና መለወጥ (መቆጣጠር) በማትችሉት መካከል የመለየት ሁኔታ ነው፡፡

በዙሪያችሁ ከእናንተ አቅም ውጪ የሆኑ ሁኔታዎች፣ የሰዎች ንግግሮች እና ተግባሮች አሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች በፍጹመ መቆጣጠር አትችሉም፡፡ ስለሆነም፣ ትኩረታችሁንና ጉልበታችሁን (your energy) ከእነሱ ላይ መለስ አድርጉና መቆጣጠር በምትችሉት ነገር ላይ አድርጉ፡፡

መቆጣጠር የምትችሉት ዋነኛ ነገር የራሳችሁን ስሜት በመገንዘብ፣ በምን መልኩ መቆጣጠር እንደመትችሉ በማሰብ ትክክለኛውን ስሜት መግለጽ ነው፡፡

ይህንን ግንዛቤ በሚገባ ለማዳበርና በስሜት ብልህነት ለመብሰል የሚያስችላችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡


ስልጠው ርእስ፡- “የስሜት ብልህነት” (Emotional Intelligence)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ቀናት፡- መጋቢት 25፣ ሚያዚያ 2፣ ሚያዚያ 9፣ ሚያዚያ 16 እና ሚያዚያ 23 (ለአምስት ኃሙስ ምሽቶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የምዝገባ መረጃ፡- መረጃውን ለመቀበል ከዚህ በታች ባለው የ telegram link inbox በማድረግ ፍላጎቶትን ሲገልጹ መረጃው ይላክሎታል::

@DrEyobmamo
👍6328
2025/07/11 21:48:48
Back to Top
HTML Embed Code: