Telegram Web Link
ያሉን አማራጮች!

ብትወዱም ባትወዱም . . .
አንዳንድ ሰዎች በእናንተ ላይ የተለያየ ጤና-ቢስ ሃሳብ ማሰባቸውም ሆነ የተለያዩ ነገሮችን ማውራታቸው አይቀርም፡፡ ያላችሁ አማራጭ፡- ቀድሞውኑ ሰዎች ስለ እናንተ ምን እንዳሰቡና ምን እንዳወሩ ለማወቅ ከመሞከር መቆጠብ ነው፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ሳትፈልጉት እናንተ ጋር ስለሚደርሰው የሰዎች አሳብና ወሬ ያላችሁ አማራጭ ራሳችሁን ማጠንከር ነው፡፡

ብትወዱም ባትወዱም . . .
በሚቀጥሉት ቀናት ሕይወት አንዳንድ ደስ የማይሉ ነገሮችንና ገጠመኞችን ማቀበሏ አይቀርም፡፡ ያላችሁ አማራጭ፡- ገና ለገና ምን ይመጣ ይሆን ብላችሁ ከመጨነቅ መጠበቅ ነው፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ለሚመጣው ነገር ሁሉ ራሳችሁን በማዘጋጀት ብርቱ መሆን ነው፡፡

ብትወዱም ባትወዱም . . .
አንዳንድ የጀመራችኋቸው ነገሮች እንደጠበቃችኋቸው ላይሄዱ ይችላሉ፡፡ ያላችሁ አማራጭ ገና ለገና ባይሳካስ ብላችሁ አዳዲስ ነገር ከመጀመር አለመገታት ነው፡፡ ይህንን ካደረጋችሁ በኋላ ሁታዎች ባልጠበቃችሁት መንገድ ከሄዱ ግን የመጠባበቂያ እቅድ (plan B) ማዘጋጀታችሁን አትርሱ፡፡

እውነታው፡-

1. ሰዎች ስለእናንተ ከሚያስቡትና ከሚያወሩት በላይ ናችሁ!

2. ሁኔታዎች ከሚያቀብሏችሁ መጥፎ ገጠመኞች በላይ ናችሁ!

3. ከተሳካውም ሆነ ካልተሳካው ሁኔታ በላይ ናችሁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
77👍51🔥4
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ችግራችሁን ለዩት!

አንድን ነገር ለመጀመር ብዙ ካሰባችሁ በኋላ፣ ነገር ግን ሳትጀምሩት በዚያው የሚቀር ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “በሃሳብ መጥገብ” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ብዙ ነገር ለመጀመር ያስቡና አንዱንም ሳይጀምሩት ወደ ሌላ ሃሳብ ይዞራሉ፡፡

አንድን ነገር ለመጀመር ምንም ችግር ከሌለባችሁና ከጀመራችሁት በኋላ ግን የማትቀጥሉት ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “የመነቃቃት ሱስ” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች በሰሙትና ባዩት ነገር ለመነሳሳትና ለመነቃቃት ችግር የሌለባቸውና ከጀመሩ በኋላ ካለማቋረጥ የሚያነቃቃቸው ነገር ካላገኙ ይተውታል፡፡

አንድን ነገር ጀምራችሁ፣ ቀጥላችሁና ጨርሳችሁት ሳለ፣ የጨረሳችሁት ነገር ዝርክርክ ያለና ከታሰበበት የጥራት ደረጃ የወረደ ከሆነ፣ ይህ ሁኔታ “የልህቀት ጉድለት” ይባላል፡፡ ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች አንድን ነገር መጨረሳቸውን እንጂ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የመጨረስ ነገር ትዝም አይላቸው፡፡

በእነዚህና በተመሳሳይ ሁኔታዎች የምቸገሩ ከሆነ በቅርቡ ሊሰጥ የተዘጋጀው ስልጠና ይመለከታችኋል፡፡

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍4139😁1🤩1
ለምንድን ነው?

አንድን ያሰብኩትን ነገር ለመጀመር የሚያስቸግረኝ ለምንድን ነው?

የጀመርኳቸውን ነገሮች መቀጠል የሚያስቸግረኝ ለምንድን ነው?

የጀመርኩትን ነገር መቀጠል ችግር ባይኖርብኝም ስጨርሰው ግን ያሰብኩት ጥራት ማግኘት የሚያስቸግረኝ ለምንድን ነው?

እነዚህና መሰል ጥያቄዎች ጀምሮ በመጨረስ ሂደት ውስጥ ቢያንስ አንድ ነገር እንደጎደለ ጠቋሚዎች ናቸው፡፡

ያሰበውን ነገር የማይጀምር ሰው እንዲሁም የጀመረውን ደግሞ የማያጠናቅቅ ሰው የዚህ ችግሩ ውጤት የሚገባው ጊዜው ካለፈና ሁኔታዎች ለመቀልበስ አሰቸጋሪ ከሆኑ በኋላ ነው፡፡ ልክ ችግሩ ሲገባውና ከሁኔታው ሲባንን ብዙ እድሎችንና ምርጫዎች እንዳባከነ ይገባዋል፡፡ ስለዚህ በጊዜ ነቃ ለማለት የተዘጋጀላችሁን ስልጠና ውሰዱ፡፡

ርዕሱ፡ “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍4816😱2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
🎓 የስልጠና እድል!

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን”
በ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

📅 የስልጠና ቀናት: ሚያዚያ 27 , 30 ፣ ግንቦት 4 , 7
🕒 ሰዓት: ከምሽቱ 2፡30 - 4፡30
💻 ስልጠናው የሚካሄደው: በቴሌግራም / Live

📥 ስልጠናውን መሳትፈ ከፈለጉ በዚህ 👉 @DrEyobmamo ፍላጎትዎን ይግለጹ!
22👍13
የመገደድ ስሜት
10👍3
የመገደድ ስሜት

ውስጣችን ካለማቋረጥ ይናገረናል፡፡ ውስጣችንን ማድመጥ ግን የእኛ ሃላፊነት ነው፡፡ ስህተት ስንሰራ ህሊናችን እንደሚናገረንና እንዲሁም ሲያመን፣ ሲርበንና ሲጠማን አካላችን እንደሚናገረን ሁሉ ውስጥጣችን ከሚነግረን በርካታ ጠቃሚ ነገሮች አንዱ በሰዎች የመገደድን ስሜትህን ነው፡፡

በሰዎች የመገደድን ስሜት ማድመጥ ማለት ከማንነታችን የሚያወጣንን የሰዎች ግፊት መለየት ማለት ነው፡፡ በአካባቢያችን የሚገኙ ሰዎች የማናምንበትን ነገር እንድናደርግ፣ የማንፈልገውን ውሳኔ እንድንወስንና ምቾት ወደማይሰማን የሕይወት ቀጠና ውስጥ እንድንገባ ካለማቋረጥ ግፊት ያደርጉብናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሚጫኑንና የሚያስገድዱን ለእኛ መልካም የሰሩ እየመሰላቸው ሲሆን፣ ሌሎች ግን እኛን የመቆጣጠር ዝንባሌ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህች አለም ላይ ስትኖር ራስህን ከአስገዳጅና ከተቆጣጣሪ ሰዎች ነጻ ማውጣት ከቻልክ የድሎችን ሁሉ ድሎች ተጎናጽፈሃል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜህን ካባከንክ በኋላ የባነንክባቸውን ሁኔታዎች መለስ ብለህ ብታጤናቸው በሰዎች ግፊት ምክንያት ካደረካቸው ወይም ከማድረግ ከተቆጠብክባቸው ሁኔታዎች ጋር ተዛምደው ታገኛቸዋለህ፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመዳን ከፈለግን፣ ምንም አሰብን ምንም ሃሳቡ ከውስጣችን የወጣ ወይም ውስጣችን ያመነበት መሆን አለበት፡፡ ስለዚህም፣ በሰዎች ከመገደድ አዙሪት ነጻ ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች አሉ፡፡

1. የሕይወት መመሪያ ይኑረን
የሕይወታችንን መመሪያ በመለየትና በማወቅ ያንን ማዳበርና በዚያ እውቀት መደላደል አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ራሳችንን ካልመራን የመጣው ሰውና ገጠመኝ ይመራናል፡፡ ራሳችንን ስንመራ ግን ሁሉን የምንመዝን እንሆናለን፡፡

2. ገደባችንን እንወቅ
ለሰዎች ብለን የት ድረስ መሄድ እንዳለብን ለይተን እንወቅ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ ማድመጥም ሆነ ለሰዎች ስንል ዋጋ መክፈል ታላቅ ብስለትና ጨዋት የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ያንን ማድረግ ያለብን ግን በመገደድ ስሜት ሳይሆን ውስጣችን ስላመነበትና ያንን ለማድረግ ስለወሰንን መሆን አለበት፡፡

3. ለሰዎች ገደብን እናብጅላቸው
ያላመንንበትን ነገር ካለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እምቢ ማለትን መልመድ መልካም ልማድ ነው፡፡ የሰው ስሜት ላለመጉዳትና ክፉ መስሎ ላለመታየት ለሁሉም ነገር እሺ ማለት ማንነታችንን እንደሚሸረሽረውና ዘመናችንን በከንቱ እንደሚበላው አንርሳ፡፡

ከፈዘዝንበትና ከደነዘዝንበት ሁኔታ እንነሳና እንውጣ! ለማን ሰውና ለምን አይነት ሁኔታ እሺ እንደምንል ለይተን እንወቅ! የራሳችንን ጉዞ ከሰዎች እጅ እናውጣና ወደራሳችን እጅ እናስገባ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍7750
ግራ የገባችሁ ነገር!

• ያላችሁበት ሁኔታ መለወጥ እንዳለበት እያወቃችሁ መንቀሳቀስ ካቃታችሁ . . .

• ስራችሁም ሆነ ሌሎች ተግባሮቻችሁ ድግግሞሽ ሆነው ሰልችቷችሁ እንኳን ወደ አዲስ ነገር መግባት ዳገት ከሆነባችሁ . . .

• አንድን ነገር ለመጀመር ስታስቡ ገና የማይሆበትና የማይሳካበት ሁኔታ የሚጎላባችሁ ከሆነ . . .

• በተለያዩ ጊዜያት የጀመራችኋቸውን ነገሮች መለስ ብላችሁ ስታስታውሷቸው አብዛኛዎቹ እንዳልቀጠሉ ከደረሳችሁበት . . .

እዚህንና መሰል ሁኔታዎቻችሁን ስታስቡ ለምን እንደዚያ እንደሚሆን ግራ የሚገባችሁ ከሆነ የመንቂያው ጊዜ አሁን ነው፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ያላችሁን ምልከታ የሚያሰፋላችሁ ወሳኝ ስልጠና የፊታችን ሰኞ ይጀምራል፡፡

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍5615😢4
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች “ጀምሮ የመጨረስ” ጥያቄ!

የማከናውናቸው ተግባሮችና ስራዎች በርካታ በመሆናቸው፣ እነዚህን ተግባሮች ለመጀመር እንዴት መነሳሳቱን (motivation) እንደማገኝ፣ እንዲሁም በምን አይነት ዲሲፕሊን እንደምቀጥልና እንደምጨርስ ከልምምዴ በመነሳት እንዳጋራቸው የሚጠይቁኝ ተከታታዮች በርካታ ናቸው፡፡

እነዚህ ጥያቄዎች ሲጨመቁ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፡-

1. አንድን ያሰቡትን ነገር መጀመር እንዴት ይቻላል? (ይህ የmotivation ጥያቄ ነው)

2. አንድን የጀመሩትን ነገር እንዴት ካለማቋረጥ መቀጠል ይቻላል? (ይህ የdiscipline ጥያቄ ነው)

3. አንድን የቀጠሉትን ነገር ታስቦ በተጀመረበት ጥራትና ብቃት እንዴት መጨረስ ይቻላል? (ይህ የfocus ጥያቄ ነው)

ከእነዚህ ተያያዥ ጥያቄዎች በመነሳት . . .

“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”) የተሰኝ ለአራት ቀናት ብቻ የሚቆይ አጭር ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

• ርእሱ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍2824
የእንድርድረት ሕግ!
7👍1
የእንድርድረት ሕግ!

አንድ ነገር በተጀመረበት ፍጥነት እስከመጨረሻው እንዲቀጥልና እንዲጠናቀቅ ካስፈለገ ካለማቋረጥ “ሊነካካ” እና እንዲደረደር የሚያደርገውን አቅም መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ ይህንን የእንድርድረት ሕግ ተግባራዊ በማድረግ ስኬት ውስጥ እንዳንገባ የሚያደረጉን አጉል ልማዶች አሉ፡፡

1. ነገርን እያሰቡ ገና ሳይጀምሩ የመተው ልማድ

አስፈላጊ እንደሆኑ የምታውቋቸውን ነገሮች የተለያዩ ምክንያቶች እያበዛችሁ የማትጀምሯቸው ከሆነ መጨረሻው ኋላ ቀርነት ነው፡፡ እናንተ ስትወላውሉ ሌሎች ስንቱን ነገር ጀምረው ይዘው ወደ ስኬት ቀጠና እንዘለቁ ላስታውሳችሁ፡፡

2. የተጀመረን ነገር እያቆሙ እንደገና የመጀመር ልማድ

ከዚህ በፊት አምናችሁባቸው የጀመራችኋቸውን ነገሮች በቀጣይነት ካላንቀሳቀሳችኋቸውና ያዝ ለቀቅ የምታደርጓቸው ከሆነ መጨረሻችሁ ዝለት ነው፡፡ የተጀመረ ነገር በቀጣይነት ካተንቀሳቀሰና ከቆመ በኋላ እንደገና ሲጀመር አሰልቺ ይሆል፡፡

3. ጀምራችሁ ያቆማችኋቸው ነገሮች

ያተጀመረ ነገር የመቀጠል እድሉ ዜሮ ነው፤ ያልቀጠለ ነገር ደግሞ የመጠናቀቁ እድል ባዶ ነው፡፡ ሰለሆነም፣ አንድን የጀመርነውን ነገር በምንም አይነት ውጥረት ውስጥ ብናልፍም ቀጣይነቱን ማረጋገጥ የግድ ነው፡፡

በዚህ አስፈላጊ እውነታ ዙሪያ መመሪያ የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

ርዕሱ፡
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍4713🔥1
ይቅርታን መጠየቅ ለምን ያስቸግረናል?
👍17
ይቅርታን መጠየቅ ለምን ያስቸግረናል?

“ይቅርታ ያለፈውን ነገር አይለውጠውም፣ የነገውን ግን የላቀና ያማረ ያደርገዋል” - Paul Boese

በአለም ላይ በጉልበታማነታቸው ከታወቁ የሰው-ለሰው ግንኙነቶች መካከል አንዱ የይቅርታ ኃይል ነው፡፡ ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ያንን ይቅርታ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆነው ሰው ትክክለኛውን ምላሽ ሲያገኝ የሚፈጠረው ኃይል ግለሰቦቹን ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰብን የመፈወስ ጉልበት አለው፡፡ ይህም ሆነ አንዳንድ ሰዎች ይቅርታ መጠየቅ ይከብዳቸዋል፡፡ ለምን?

1. ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት

አንዳንድ ሰዎች ይቅርታን ሲጠይቁ ያኛው ወገን ጥያቄቸው ባለመቀበል “የሚያሳፍራቸው” ስለሚመስላቸው ከዚያ ተግባር ይገታሉ፡፡ ይህ ብዙ ሰዎች የሚታገሉት ስሜት ነው፡፡ ይህንን የስሜት ጫና ለማለፍ ግን ሃላፊነታችን ላይ ማተኮር አስፈላጊ ነው፡፡ የእኛ ሃላፊነት ላጠፋነው ጥፋት ይቅርታን የመጠየቅ ሃላፊነት እንጂ ሰዎች ይቅርታችንን እንዲቀበሉ የማስገደድ አይደለም፡፡ ትኩረታችንን በእኛ ሃላፊነት ላይ ብቻ ስናደርግ ለይቅርታ የተነሳሳ ልቦና ይኖረናል፡፡

2. የኋላ ኋላ ብቅ የሚል ሰበብን ፍርሃት

“ዛሬ ስህተቴ ነው ብዬ አምኜ የተቀበልኩት ነገር ነገ ማስረጃ ይሆንብኛል” ብለው የሚሰጉ ሰዎች አሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች ይቅርታን እንዳይጠይቁ እንቅፋት የሚሆንባቸው ስህተታቸውን የማመናቸውን ሁኔታ ተጠቅሞ ሌላኛው ወገን የክስንና የበላይነት ስፍራ ይይዝብኛል ብለው ስለሚሰጉ ነው፡፡ እዚህ ላይ ማስታወስ ያለብን ግን ይቅርታ የገደለውን ስህተት ማንም ሰው እንደገና ሕይወት ሊዘራበት እንደማይችል ነው፡፡ ቢሞክርም እንኳ ብዙም ሳይቆይ ሃሳቡ መሞቱ አይቀርም፡፡

3. ተሸናፊ ሆኖ የመታየት ስጋት

ይቅርታ መጠየቅን እንደደካማነትና እንደተሸናፊነት የሚያዩ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም፣ ምንም እንኳ ስህተተኛ እንደሆኑ ቢያውቁትና ሁኔታዎች ሁሉ የሚጠቁሙት ወደ እነርሱ ስህተተኛነት ቢሆንም፣ ሁኔታውን ወጥረው በመያዝ ሸፋፍነው ለማለፍ ይጣጣራሉ፡፡ ይህ የአልሸነፍም ባይነትና እንደተሸናፊ መስሎ የመታየት ፍርሃት ለጉዞአቸው ታላቅ ጠንቅ ነው፡፡

4. ተስፋ መቁረጥ

አንዳንድ ሰዎች ቶሎ ተስፋ ቆራጮች ናቸው፡፡ አንድ ችግር እንደተከሰተ ነገሮች ሁሉ እንዳከተመላቸው የማሰብና በነገሮች ላይ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ አላቸው፡፡ ይህ ሁኔታ የሚመጣው፣ ይቅርታ ቢጠየቅም ባይጠየቅም ግንኙነቱን ለማደስ ጊዜው አልፎአል ብሎ ከማሰብ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምንም ያህል ይቅርታ ብንጠይቃቸው እንኳን ነገር ከነከሱ አይለቁምነቀ ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ለይቅርታ እድልን መስጠት ጠቃሚ ነው፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍7730
አምስት ቀን ብቻ ቀረው!!!

ቀላል እውነት . . .

• ማንኛውም አስፈላጊ ነገር ቆርጣችሁ ካልወሰናችሁ በስተቀር አትጀምሩትም!

• ማንኛውንም ነገር ካልጀመራችሁት የመጨረሱ እድል ዜሮ ነው!

• ማንኛውም ተጀምሮ እንዲጨረስ ደግሞ አንዴ ከተጀመረ በኋላ መቋረጥ የለበትም!

ይህ አመለካከት የስኬታማ ሰዎች ልምምድ ነው፡፡

በዚህ እውነታ ዙሪያ ራሳችሁን እንድታሰለጥኑ መንገዱን የሚመላክታችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

ርዕሱ፡ “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍3116😱1
“ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

➡️ ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

➡️ የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)፡፡

➡️ የስልጠናው ክፍያ፡- አምስት መቶ ብር (500 ብር) ብቻ!

የምዝገባ መረጃ

ለስልጠናው ለመመዝገብ ከዚህ በታች በተቀመጠው የክፍያ መረጃ መሰረት ክፍያውን በመክፈል፣ screenshot በማንሳት inbox ማድረግ ይኖርቦታል፡፡

ክፍያውን ከከፈሉ በኋላ ለዚህ ስልጠኛ ተመዝጋቢዎች ብቻ ወደሚዘጋጅ ቴሌግራም ግሩም እንቀላቅሎታለን፡፡

ከዚያም ስልጠናው እስከሚደርስ ድረስ በግሩፑ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች እና መመሪያዎችን እየተከታተሉ ይጠብቃሉ፡፡

ንግድ ባንክ
Eyob Mamo
Account # 1000614499056

ቴሌብር
Dr. Eyob
ስልክ ቁጥር 0945087238

እናመሰግናለን!
👍255😢3🔥2
ጀምረን የመጨረሳችን ጉዳይ!

ያሰብነውን ነገር የማንጀምረው ለምንድን ነው?

የጀመርነውንስ ነገር የማንጨርሰው ለምንድን ነው?

• ምናልባት አንድን ነገር የምንጀምርበትን ዋና ዓላማ አላወቅነውም ይሆናል!

• ምናልባት ዓላማችንን አውቀን ሳለን የዲሲፐልን ጉድለት ይኖርብን ይሆናል!

• ምናልባት ደግሞ የመጀመር፣ የመቀጠልና ጥጉ ድረስ የመውሰድ ክህሎት ይጎድለን ይሆናል!

• ምናልባት ከራሳችን ጋር ወይም ከሰዎች ጋር የማያስማማ አጉል ባህሪይ አስቸግሮን ይሆናል!

ማንኛውም ሰው አንድን ነገር ካለምክንያት መጀመር አያስቸግረውም!

ማንኛውም ሰው አንድን የጀመረውን ነገር ካለምክንያት መቀጠልና መጨረስ አያስቸግረውም!

በዚህ እውነታ ዙሪያ በመሰልጠን ጀምራችሁ የምትጨርሱ ሰዎች ለመሆን ከፈለጋችሁ ይሀቺ አጭር ስልጠና አያምልጣችሁ፡፡

• የስልጠናው ርእስ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

• ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮበ ማሞ፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

• ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

• የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30፡፡

ለስልጠናው ፍላጎት ካላችሁ ከዚህ በታች ባለው link inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ::

@DrEyobmamo
👍3310🎉1
አስተዳደጋችሁ !!!
👍13
አስተዳደጋችሁ !!!

የመጀመሪያዎቹ አምስት አመታቶቻችን (Formative age) ወደፊት በዙሪያችንና በሕይታችን ላይ ያለንን ንጽረተ-ዓለም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የመቅረጽ ጉልበት አላቸው ይባላል፡፡ በለጋነት እድሜያችን ያሳለፍናቸውን የአስተዳደግ ሁኔታዎች መለስ ብሎ ማየትና መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

የአስተዳደግን ሁኔታ ማወቅ ማለት ባደግንበት ቤት ውስጥ ምን አይነት “መንፈስ” ጠጥተን እንዳደግን መለየት ማለት ነው፡፡ በልጅነትህ ስታየውና ስትሰማው ያደከው ሁኔታ በአንተ ላይ ታላቅ የሆነ ተጽእኖ አለው፡፡ በተለይ ከወላጅ ቤተሰቦችህ ወይም ካሳደጉህ ሰዎች ጋር ያሳለፍካቸው የለጋነት ዘመኖችህ በማንነትህ ላይ ትልቅ ስፍራ አላቸው፡፡

በሃገራችን ውስጥ ብዙ ሰዎች የልጅነት ትዝታቸውን ማሰብ አይፈልጉም፡፡ ያን ጊዜ የደረሰባቸው፣ የሆኑትና እያዩ ያደጉት ሁኔታ በአእሮአቸው ውስጥ ተጋግሮ ማድረግና መሆን የሚችሉት ነገር ላይ ገደብ ጥሎባቸዋል፡፡ ከዚህ ሁኔታ አልፎ ለመሄድ ግን ቁርጥ ውሳኔንና እርምጃን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡

የአስተዳደግህን ሁኔታ ለማወቅ የሚከተሉትን ነጥቦች ማሰብ ትችላለህ፡-

1. ቤተሰቦቼ ከእኔ ጋር

ቤተሰቦቼ በግሌ ምን ሲነግሩኝ፣ ምን ሲያደርጉልኝ ወይም ሲያደርጉብኝ አደግሁ? ቤተሰቦቼ ከእኔ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በዙሪያዬ ባለው አለም ላይ ለሚኖረኝ አመለካከት ታላቅ ተጽአኖ አለው፡፡ ስለዚህ ምናልባት አሁን ያለኝ የስሜትም ሆነ የአመለካከት ቀውስ ከዚያ ይገናኝ እንደሆነ በማሰብ ተገቢውን የእርማት እርመጃ መውሰድ ሊያስፈልገኝ ይችላል፡፡

2. ቤተሰቦቼ እርስ በርሳቸው

ቤተሰቦቼ እርስ በርሳቸው በምን ሁኔታ ሲስተናገዱ አይቼ አደግሁ? ወላጆቼ እርስ በርሳቸው ሲከባበሩ አይቼ አደኩ ወይስ ሲበዳደሉ? ይህ ሁኔታ በወደፊቴ ላይ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ስፍራ አለው፡፡ ከዚህ አይነቱ ተጽእኖ ነጻ ያልዉ ሰዎች በወደፊት ባላቸው የፍቅር ግንኙነት ላይ ይህ ነው የማይባል ጫና ሊኖርባቸው ይችላል፡፡

3. ቤተሰቦቼ ከኑሮአቸው ጋር

ቤተሰቦቼ የኑሮን ተግዳሮትም ሆነ በረከት በምን መልኩ ሲያስተናግዱ አይቼ አደግሁ? ወላጆቼ ችግር ሲጋፋቸውም ሆነ ምቾት ሲመጣ ይሰጡት ለእነዚህ አይቀሬ የሕይወት ክስተቶች የነበራቸው ምላሽ በእይታዬ ላይ ወሳኝ የሆነን ነገር ይቀርጻል፡፡ በሕይወት ዘመናችን አንዳንዴ በችግር ሌላ ጊዜ ደግሞ በምቾት እናልፋለን፡፡ እነዚህን የኑሮ “ፍርርቆች” አያያዜ የወደፊቴን መወሰኑ አይቀርም፡፡

የልጅነት ትውስታዎቻችሁ ጣፋጭና በእናንተ ላይ ያስከተለውም ተጽእኖም መልካም ከሆነ በዚያ ላይ እንድትገነቡና እያደጋችሁ እንድትሄዱ ትመከራላችሁ፡፡

ከዚህ በተቃራኒ የልጅነታችሁ ትውስታዎች አስቸጋሪ እና ደስ የማያሰኙ ከሆኑ ከዚህ trauma እስከምትላቀቁ ድረስ በስሜታችሁ፣ በማሕበራ ግንኙነታችሁም ሆነ በፍቅር ግንኙነታችሁ (ትዳርን ጨምሮ) ቀውስን እንደሚፈጥር በመገንዘብ አስፈላጊውን እርዳታ እንድታገኙ ትመከራላችሁ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍6325
አራት ቀን ብቻ ቀራችሁ!

➡️ የስልጠናው ርእሰ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን”
(“The art and discipline of starting and finishing”)

➡️ ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

➡️ የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)፡፡

➡️ የስልጠናው ክፍያ፡- አምስት መቶ ብር (500 ብር) ብቻ!

የምዝገባ መረጃ

ለስልጠናው ለመመዝገብ ከዚህ በታች በተቀመጠው የክፍያ መረጃ መሰረት ክፍያውን በመክፈል፣ screenshot በማንሳት inbox ማድረግ ይኖርቦታል፡፡

ክፍያውን ከከፈሉ በኋላ ለዚህ ስልጠኛ ተመዝጋቢዎች ብቻ ወደሚዘጋጅ ቴሌግራም ግሩም እንቀላቅሎታለን፡፡

ከዚያም ስልጠናው እስከሚደርስ ድረስ በግሩፑ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች እና መመሪያዎችን እየተከታተሉ ይጠብቃሉ፡፡

ንግድ ባንክ
Eyob Mamo
Account # 1000614499056

ቴሌብር
Dr. Eyob
ስልክ ቁጥር 0945087238

እናመሰግናለን!
👍205😁1
ሕይወት ተጀምሯል!
👍13
ሕይወት ተጀምሯል!

ምንም አይነት የእኛ ተሳትፎ ሳይጨመርበት በፈጣሪ ፈቃድና በወላጆቻችን ተሳትፎ ሕይወታችን ተጀምሯል፡፡

ይህ የተጀመረ ሕይወት ብዙ እድሎች እና አደራዎችን ይዞ ይመጣል፡፡ እነዚህን እድሎችና አደራዎች በሚገባ በማሰብ፣ በማቀድ፣ በመጀመርና በጥሩ ሁኔታ በማጠናቀቅ መምራት የእኛ ድርሻ ነው፡፡

በሕብረሰቡ መካከል ቀደም ብለው በሚታዩትና ኋላ በቀሩት መካከል ያለው ልዩነት እዚህ ላይ ነው፡፡ ስኬታማዎቹ ያሰቡትን ነገር በቁርጠኝነት ይጀምራሉ፣ የጀመሩትን ደግሞ ካለማቋረጥ ይቀጥላሉ፡፡

ለሕይወታችን እድገት የሚሆኑ ነገሮችን እንዳንጀምር የሚያደርጉን እንቅፋቶች ምን ምን ናቸው? እነዚህን እንቅፋቶችስ እንዴት እንለፋቸው?

አንዳንድ ነገሮችን እየጀመርን እንድናቆም የሚያደርጉን እንቅፋቶች ምን ምን ናቸው? እነዚህን እንቅፋቶችስ እንዴት እንለፋቸው?

ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁ ስልጠና እነዚህንና መሰል ጥያቄዎቻችሁን ይመልሱላችኋል፡፡

➡️ የስልጠናው ርእሰ፡- “ጀምሮ የመጨረስ ጥበብ እና ዲሲፕሊን” (“The art and discipline of starting and finishing”)

➡️ ስልጠናው የሚሰጠው፡- በሁለት ተከታታይ ሳምንቶች ለአራት ምሽቶች ብቻ በመስጠት የሚጠናቀቅ፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ telegram (online live) የሚሰጥ ይሆናል፡፡

➡️ ስልጠናው የሚሰጥበት ቀን፡- ሚያዚያ 27 (ሰኞ)፣ ሚያዚያ 30 (ኃሙስ)፣ ግንቦት 4 (ሰኞ) እና ግንቦት 7 (ኃሙስ)፡፡

➡️ የስልጠናው ሰዓት፡- በሁሉም ቀናት ከምሽቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)፡፡

➡️ የስልጠናው ክፍያ፡- አምስት መቶ ብር (500 ብር) ብቻ!

የምዝገባ መረጃ

ለስልጠናው ለመመዝገብ ከዚህ በታች በተቀመጠው የክፍያ መረጃ መሰረት ክፍያውን በመክፈል፣ screenshot በማንሳት inbox ማድረግ ይኖርቦታል፡፡

ክፍያውን ከከፈሉ በኋላ ለዚህ ስልጠኛ ተመዝጋቢዎች ብቻ ወደሚዘጋጅ ቴሌግራም ግሩም እንቀላቅሎታለን፡፡

ከዚያም ስልጠናው እስከሚደርስ ድረስ በግሩፑ የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች እና መመሪያዎችን እየተከታተሉ ይጠብቃሉ፡፡

ንግድ ባንክ
Eyob Mamo
Account # 1000614499056

ቴሌብር
Dr. Eyob
ስልክ ቁጥር 0945087238

እናመሰግናለን!
👍4310😁1🎉1
2025/07/09 16:36:15
Back to Top
HTML Embed Code: