Telegram Web Link
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የልጅነት ጉዳት (childhood trauma)

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወይም እነዚህን መሰል አጉል ልምምዶች በልጅነታችሁ ካሳለፋችሁ፣ ምናልባት አሁን የምትታገሏቸው የስሜት፣ የስነ-ልቦና ወይም ማሕበራቢ ቀውሶች የእዚያ ሰበብና ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡

1. ለእድሜ የማይመጥን ስራን ሰርቶ ማደግ

2. ጨዋታን ተከልክሎ ማደግ

3. በቤተሰብ (በአሳዳጊ) ስድብንና የቃላት ጥቃትን አስተናግዶ ማደግ

4. ከፍተኛ አደጋ አይቶ ማደግ

5. የወሲብ ጥቃትን ወይም ሙከራን አስተናግዶ ማደግ

6. አካላዊ ድብደባን አስተናግዶ ማደግ

7. የጉልበተኛን (bullying) ጥቃት አስተናግዶ ማደግ

እነዚህ የልጅነት ጉዳት (childhood trauma) ልምምዶች አሁን በሚኖረን ስሜት ላይ፣ የፍቅርም ሆነ ማሕበራዊ ግንኙነት ላይ ከፍተኛ የሆነ ተጽእኖ አላቸው፡፡

ያላችሁ አማራጭ በጉዳዩ ላይ በሚገባ በማጥናት፣ በመማርና እርምጃ በመውሰድ መቅረፍ ነው፡፡

ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የምክር እገዛ ያስፈልጋችኋል፡፡

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም አካውንት inbox በማድረግና ፍላጎታችሁን በማሳወቅ የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላቸሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍9335😢5
ፍላጎትን ከፍርሃት የማስበለጥ ስኬት!
👍155
ፍላጎትን ከፍርሃት የማስበለጥ ስኬት!

“እንዲሳካልህ ከፈለክ፣ ካለብህ የመውደቅ ፍርሃት ይልቅ ለስኬት ያለህ ፍላጎት ሊልቅ ይገባዋል” – Bill Cosby

ከልባችን ያልተጸየፍነውን ነገር አንሸሸውም፣ አናሸንፈውም፡፡ በጽኑ ያልፈለግነውንና ያልተከታተልነውን ነገር ደግሞ በፍጹም ልንደርስበትና የእኛ ልናደርገው አንችልም፡፡

የአንድ አንድ ሰው ሕልም በትምህርት አንድ ደረጃ መድረስ ነው፡፡ የሌሎች ሕልም ደግሞ ቤተሰባቸው አሁን ካለበት ችግር ማላቀቅ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ ሁኔታ፣ በስራ፣ በግል ጤንነት፣ እና በሌሎች ሁኔታዎች አንጻር ሰዎች ግብን አውጥተው እዚያ ለመድረስ ይጣጣራሉ፡፡ የእነዚህ ሁኔታዎች መሳካት የአጠቃላይ ሕይወት መሳካት ባይሆንም የስእሉ አካል ስለሆኑ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በዚህ ሰው ሁሉ በሚጋራው አንድ ደረጃ የመድረስ ጉዞ ውስጥ ማንንም የማይምር አንድ ችግር አለ፤ እርሱም የፍርሃት ችግር ነው፡፡ ሁላችንም ቢሆን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የምንፈራቸው ነገሮች አሉን፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ ስኬት የማጣት ፍርሃት፣ ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት፣ ጀምሮ የማቋረጥ ፍርሃት …፡፡ በአጭሩ፣ ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሰው የለም፡፡ ይህንን ሰው ሁሉ የሚጋራውን ፍርሃት የተሰኘውን ተራራ አልፎ ወደ አላማ ለመዝለቅና ወደግባችን ለመድረስ ያለን የውስጥ ፍላጎት ካለብን ስጋትና ፍርሃት በብዙ እጥፍ ሊጠነክር ይገባዋል፡፡

ለመራመድ የተዘጋጃችሁትን እርምጃ አስቡትና ያንን ነገር ለማድረግ ያላችሁን ፍላጎትና በውስጣችሁ የምትፈሩትን ነገር በሚዛን ላይ አስቀምጧቸው፡፡ የትኛው ያመዝናል? ፍርሃቱ ካየለ ወደኋላ ያስቀራችኋል፤ ፍላጎቱ ካየለ ግን ፍርሃትህን አሸንፋችሁ ወደ ግባችሁ እንድትዘልቁ ብርታት ይሆናችኋል፡፡

ፍላጎታችሁን ከፍርሃታችሁ ለማስበለጥ ከፈለጋችሁ ደግሞ ክምትወስዱት እርምጃ የተነሳ የምታገኟቸውን ወሳኝ ለውጦችና ጥቅሞች ማሰብ፣ ማወቅና ማሰላሰል ያስፈልጋል፡፡

ዛሬ መለወጥ፣ ማሻሻልና መድረስ የምትፈልትን ሁኔታ አስቡና ግብን በማውጣት መንቀሳቀስን ጀምሩ፡፡ በጽኑ ያመናችሁበትን ነገር በመከታተል ሊደርስባችሁ ከሚችለው ማንኛው አይነት ችግር ይልቅ ከፍርሃት የተነሳ ባለመንቀሳቀስ የሚመጣባችሁ ችግር የባሰ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍12463🎉7🔥5
ለመላቀቅ መልቀቅ!
👍39
ለመላቀቅ መልቀቅ!

“ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር አንድን ነገር በማግኘታችን ላይ ብቻ ሳይሆን ያንን ነገር በማግኘታችን ምክንያት የምናጣቸውም ሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ጭርም ላይ ሊሆን ይገባዋል”

ይህኛው የትኩረት ምስጢር የገባቸው ሰዎች አንድን ነገር ለመጨበጥ መዘርጋት ቀድሞ የያዙትን ነገር ወደመልቀቅ እንደሚያመጣቸው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህም፣ ለማግኘት የሚጓጉለትን ነገር ለመያዝ ከመዘርጋታቸው በፊት ያንን በማድረጋቸው የሚያጡትን ነገር ቀድመው ያስባሉ፡፡ ትኩረታቸው አዲስ ነገር በማግኘታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ያንን ነገር ለማግኘት በከፈሉት ዋጋ ላይም ጭምር ነው፡፡

የስድስት አመት ልጅ ነው፡፡ የሚኖረው ከአባትና ከእናቱ ጋር እንዲሁም ከሁለት ታላላቅ ወንድሞቹ ጋር ነው፡፡ ይህ ልጅ ከወንድሞቹ ይልቅ ፈጣንና አንዳንዴም ከመስመር ወጣ ያለ ቅልጥፍና ያለው ልጅ ነው፡፡ አንድን ነገር ካየና ከወደደው ያንን ነገር በእጁ የሚያስገባበትን መንገድ በዚህም ሆነ በዚያ ፈልጎ ነገሩን በእጁ ያስገባል፡፡ አንድን ነገር እጁ ለማስገባት ማልቀስ ካለበት ማልቀስን፣ መጣላት ካለበት መጣላትን፣ መስረቅ ካለበት መስረቅን ከመጠቀም የሚመልሰው የለም፡፡ መኝታ ቤቱ ያለው የመጫወቻ ብዛት ይህ ነው አይባልም፡፡ ከየት ለቃቅሞ እንዳመጣው የማይታወቅ ብዙ ነገር ነው ያለው፡፡ አባቱ ይህንን ባህሪውን ያውቃል፣ ሆኖም በተለያየ መልኩ ሊያስተምረው ከመሞከር ውጪ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡

አንድ ቀን ይህ ልጅ የማይረሳውን ትምህርት አገኘ፡፡ ከትምህርት ቤት ተመልሶ ትንሽ ምግብ ከቀማመሰ በኋላ በረንዳው ላይ ይጫወታል፡፡ የጎረቤታቸውን በረንዳና የእነርሱን በረንዳ የሚለየው አንድ ከብረት የተሰራ በሰው ቁመት ልክ የሆነ አጥር ነው፡፡ ይህ ልጅ ቀና ብሎ ሲያይ የጎረቤታቸው ልጅ ሲጫወትባት የነበረች ትንሽ ሳንቲም የምታክል መጫወቻ ያያል፡፡ በተለያዩ ቀለማት ስለምታብረቀርቅ ልቡን ሳበችው፡፡ ዘወር ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ቀና ብሎ ወደ ጎረቤቱ ግቢ ሲያጤን ያ በጣም የሚፈራው ውሻም በአካባቢው የለም፡፡ በቀስታ እጁን በብረት አጥሩ መካከል አሾልኮ ያችን ያጓጓችውን መጫወቻ በእጁ ከጨበጠ በኋላ በቀስታ አጁን ውጣ ቢለው እንዴት ይውጣ፡፡ ሁለት ሶስቴ ከሞከረ በኋላ እምቢ ስላለው መደንገጥ ጀመረ፡፡ ከአሁን ከአሁን ውሻው ይመጣብኛል ብሎ ፈራ፡፡ ብዙ ከታገለ በኋላ አልቦታል፤ ከፍርሃትም የተነሳ እንደ ማልቀስ ቃጥቶታል፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ነበር አባት የደረሰው፡፡ ዘወር ብሎ አባቱ መምጣቱን እንዳየ መለስ ሲል ያ ክፉ የጎረቤትም ውሻ ብቅ አለ፡፡ ልጁ በፍርሃት ማልቀስ ጀመረ፡፡ አባት፣ “ምን ሆነህ ነው?” ልጅ፣ “እጄ አልወጣ ብሎኝ”፡፡

አባት፣ “እጅህ በሁለቱ የብረት አጥሮች መካከል እንዴት ገባና ነው አልወጣ ያለህ?”

ልጅ፣ “መዳፌን ዘርግቼ ነው ያስገባሁት፡፡”

አባት፣ “ታዲያ ለምን መዳፍህን ዘርግተህ ልክ እንዳስገባኸው አታስወጣውም?”፡፡

ልጅ፣ “መዳፌን ከዘረጋሁት የያዝኩት ነገር ስለሚያመልጠኝ መልቀቅ አልፈልግም፡፡”

አባት፣ “ካለህበት ሁኔታ መላቀቅ ከፈለግህ የያዝከውን ነገር መልቀቅ የግድ ነው፡፡ አለዚያ እንደተያዝክ በዚያው መቅረትህ ነው” ብሎት ጥሎት ሄደ፡፡

በዚህ ጊዜ ነበር የውሻው ድምጽ የተሰማው፡፡ ውሻው እየዘለለ ሲመጣ ያየው ይህ ልጅ ምንም ምርጫ ስለሌለው የጨበጠውን ነገር በመልቀቅ ከተያዘበት ነገር ተላቀቀ፡፡

ብዙም ለማይጠቅም ነገር ሌላውን እጨብጣለሁ ብለው እጅግ ወሳኝ የሆነውን የሚጥሉ ሰዎች የትኩረት መዛባት ያጠቃቸው ሰዎች ናቸው፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች በሚፈልጉትና በሚያስፈልጋቸው ነገር መካከል መለየት ያቃታቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የሚፈልጉትን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸውን ይሰዋሉ፡፡ የማያዛልቀውን ለመጨበጥ እስከ ወዲያኛው የሚያዛልቃቸውን ይጥላሉ፡፡

ያዩትንና የተመኙትን ነገር በእጃቸው ለማስገባት ሲሯሯጡ በሂደቱ የሚያጡት ከዚያ የላቀና የተሻለ ነገር አይታያቸውም፡፡ የሚፈልጉትን ያገኛሉ፣ ከዚያ ጋር አብሮ የሚመጣውን ጫና ግን ችላ ስለሚሉ ውለው ሳያድሩ ሲታገሉ ይታያሉ፡፡

አንድን የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ እንከን የማይገኝለት ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም ትኩረታችን ለማግኘት የምንጣጣረው ነገር ላይ ከመሆኑ የተነሳ ሌላ አስፈላጊነቱ የላቀን ነገር የሚያስጥለን ከሆነ መጨረሻው ክስረት ይሆንብናል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በእጃቸው ለማስገባት ብዙ መስዋእትነት የከፈሉለት ነገር እነርሱንው ይይዛቸውና ቀድሞ የነበራቸውን ነጻነት ያሳጣቸዋል፡፡ ነገሩን በእጃቸው ከማስገባታቸው በፊት የነበራቸውን መረጋጋት፣ ጤንነትና አንዳንድ ጊዜም ማጣት እጅግ ዋጋ ያለውን ንብረት አጥተውት ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ አተርፋለሁ ሲሉ ይከስራሉ፤ ከቀድሞው የተሻለ ደረጃ እደርሳለሁ ሲሉ ጭራሽ ይብስባቸዋል፤ ከፍ ወዳለና ወደተሻሻለ ሁኔታ እደርሳለሁ ሲሉ ራሳቸውን ወረድ ብሎ ያገኙታል፡፡

ማናልባት ግራ ከገባህ፣ ሰላምህን ከነሳህ፣ አስሮ ከያዘህና የቀድሞ ደስተኛ ማንነትህን ካጠፋብህ ሁኔታ ለመላቀቅ በመጀመሪያ አንተው መልቀቅ ያለብህ ነገር ይኖር ይሆን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
157👍108🔥6😁2😱2🎉2
ኤቨረስት ሆይ፣ አሸንፍሃለሁ
ራስን የማሻሻል ቁልፍ
👍39
ኤቨረስት ሆይ፣ አሸንፍሃለሁ
ራስን የማሻሻል ቁልፍ


(“25 የስኬት ቁልፎች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

አንድ ሰው ተሸነፈ የሚባለው መቼ ነው? በቃኝ ብሎ ሲያቆም ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ለረጅም ጊዜ የለፉለት ነገር ድል ሲቃረብ ተስፋ በመቁረጥ ጥለውት ይሄዳሉ፡፡ በነበራቸው ጥረት ውስጥ ያዳበሩትን ጥንካሬ አያስተውሉትም፡፡ ብዙ ሞክሮ አለመሳካት ያለማቆም እንጂ የማቆም ምክንያት ሊሆን አይገባውም፣ ምክንያቱም በተሞከረው ሙከራ የመጣው ጥንካሬ፣ የባህሪይ ጽናትና የልምምድ ብስለት ከመሞከራችን በፊት የነበረንን የማሸነፍ ብቃት በብዙ እጥፍ ስለሚጨምረው ነው፡፡ ሞክረን ስንሸነፍ፣ ራሳችንን አሻሽለን እንደገና ብንሞክረው እንደምናሸንፈው ማረጋገጫችን እንደሆነ ማወቅ አንዱ የስኬት ቁልፍ ነው፡፡

ሰር ኤድመንድ ሂለሪ (Sir Edmund Hillary) ለመጀመሪያ ጊዜ የኤቨረስትን ተራራ ጫፍ የረገጠ ሰው ነው፡፡ ይህንን ተራራ በድል ተወጥቶት ጫፍ ከመድረሱ በፊት በነበረው የቀድሞ ሙከራው ቡድኑ ተራራውን መውጣት አቅቶት አንድ ሰው ሞቶባቸው ተመልሰው ነበር፡፡ ከዚያ አሳዛኝ ሙከራቸው ሲመለሱ በለንደን በነበረው ሪሰብሽን ግብዣ ላይ ንግግር እንዲያደርግ ተጋብዞ ነበር፡፡ ቆሞ ንግግር ከሚያደርግበት መድረክ ጀርባ የኤቨረስት ተራራ ምስል በትልቁ ተቀምጧል፡፡ በንግግሩ ወቅት ወደዚህ የተራራ ስእል ዘወር በማለት እንዲህ አለ፣ “ኤቨረስት ሆይ፣ አሁን አሸንፈኸናል፡፡ ነገር ግን ጠብቀኝ እመለስና አሸንፍሃለሁ ምክንያቱም አንተ ያው ነህ፣ እኔ ግን አድጌና በርትቼ እመለሳለሁ”፡፡ እነዚህ ቃላት ከተናገረ በኋላ ነበር የሚያስፈልገውን ዝግጅት አድርጎ ቀድሞ ያሸነፈውን ተራራ ሄዶ ያሸነፈው፡፡

“ታላቁ ክብራችን ያለው ባለመውደቅ ውስጥ አይደለም፣ በወደቅን ጊዜ ሁሉ ተነስተን በመቀጠላችን ውስጥ ነው እንጂ” - Ralph Waldo Emerson

መራመድ እስካለ ድረስ መውደቅ አለ፣ መነገድ እስካለ ድረስ መክሰር አለ፣ መውደድ እስካለ ድረስ መጎዳት አለ፣ መማር እስካለ ድረስ ፈተና መውደቅ አለ … ይህ የማይለወጥ የሕይወት ህግ ነው፡፡ “ምን ይበላሽ ይሆን?” በሚለው ፍርሃት ታስሮ መንቀሳቀስ አለመቻል በሕይወት እያሉ መሞት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ሕይወቴ ያልፍ ይሆናል ብለው ከመፍራታቸው የተነሳ ሕይወትን ሳይጀምሯት ያልፋሉ፡፡ ሕይወት ግን አዳዲስ ነገሮች የሚሞከሩባት፣ ሲሳካ የምንደሰትባት፣ ሳይሳካ ደግሞ ራሳችንን ከወደቅንበት አንስተንና አቧራችንን አራግፈን እንደገና የምንቀጥልባት ጎዳና ነች፡፡

ሕይወት ማለት በዚህ ምድር ላይ “መከሰትና” ምንም ነገር እንዳይደርስብን ራሳችንን መጠበቅ አይደለም፡፡ “ለአደጋ” ሊያጋልጡን የሚችሉትንና ማንነታችንን የሚፈቱትን ነገሮች ከመሞከር ውጪ ሕይወት ባዶ ነች፡፡ ለዚህ እውነታ ልባችንን በመክፈት አዳዲስ “ተራራዎችን” በመውጣት፣ ሰው ያልሞከረውን በመሞከርና በማንነታችን ውስጥ የታመቀውን ድብቅ ብቃት የሚወጣበትን እድል ልንሰጠው የግድ ነው፡፡

1. ማድረግ እንዳለባችሁ እያወቃችሁት ከፍርሃት የተነሳ ያላደረጋችሁት ነገር ምንድን ነው

2. እናንተ በሙሉ ልብ እያመናችሁበት ከሌሎች ሰዎች ግፊት የተነሳ ያመነታችሁበት ነገር ምንድን ነው

3. ከዚህ በፊት ሞክራችሁ ስላልተሳካ ብቻ ድገማችሁ ላለመሞከር ወስናችሁ የተዋችሁት ነገር ምንድን ነው

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍8663🔥7😱1😢1
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

https://www.tg-me.com/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo
👍7530
ገጠመኞችሽ “ሲገጣጠሙ” - ሁለንተናዊ እይታ
👍272
ገጠመኞችሽ “ሲገጣጠሙ” - ሁለንተናዊ እይታ

ከ12ኛ ክፍል በከፍተኛ ውጤት ከተመረቀች በኋላ ለዩነቨርሲቲ ትምህርት ወደክፍለሃገር የተመደበችው ወጣት በዚያ ትምህርቷን ስትከታተል ይህኛው ሶስተኛ አመቷ ነው፡፡ የውጤቷ ልቀት ቀጥሏል፡፡ በዚህ በሶስተኛ አመት የትምህርት ዘመን የነበራትን የጥቂት ቀናት እረፍት በመጠቀም ብዙ መንገድ አቋርጣ ወደቤት መጣች፡፡

ለብቻዋ ያሳደገቻት እናት ብቸኛ ልጇን በማየቷ ብትደሰትም በድንገት በመምጣቷ ደንገጥ ብላለች፡፡ ጥርጣሬዋን ያባሰባት በደስተኝነቷ የምትታወቀው ልጇ ቀዝቀዝ በማለቷ ነው፡፡

ገና እንደተቀመጡ እናት ለልጅ፣ “ያዘንሽ ትመስያለሽ፣ ምን ሆነሽ ነው?” አለቻት፡፡ ቀድማ ጠየቀቻት እንጂ ልጅቷ ያለባትን የስሜት ቀውስ ለመናገር ተዘጋጅታ ነበርና በአንድ ጊዜ ዘረገፈችው፡፡ “በጣም የምወደውና አገባዋለሁ ብዬ ተስፋ ያደረኩት ጓደኛዬ ተወኝ፡፡ ለነገሩ ስህተቱ የእኔው ነው፣ ምን አይነት ሰው ማፍቀር እንዳለብኝ ሳላውቅ በችኮላ ነው የገባሁበት፡፡

ይህ ስህተቴ ሳይበቃ በዚህ አይነት ብስጭት ውስጥ ሆኜ አላጠናም በማለት ማጥናት አቁሜ ነበርና በቅርብ የወሰድኳቸው ፈተናዎቼ ውጤት ጥሩ አይሆኑም ብዬ እፈራለሁ፡፡ ይባስ ብሎ የልቤን የማጫውታት ጓደኛዬ በድንገት ትምህርት ቤቱን ትታ ሄደች” በማለት የሰራቻቸውን ስህተቶችና የገጠማትን ገጠመኞች ሁሉ አጫወተቻት፤ እንደገናም ወደትምህርት ቤት መመለስና ትምህርቷን መቀጠል እንደማትፈልግ ገለጸችላት፡፡

እናት የልጇ ሁኔታ ቢያሳስባትም የብዙ ገጠመኞች ልምድ ስላላት የምክር ብልሃት አላጣችም፡፡ ከጥቂት ዝምታ በኋላ፣ “ለማንኛውም እንኳን በሰላም አገኘሁሽ፣ አሁን ከልጅነትሽ ጀምሮ የምሰራልሽን ያንን በጣም የምትወጂውን ብስኩት ላዘጋጅና እንነጋገራለን” አለቻት፡፡ ልጅቷ ከህጻንነቷ ጀምሮ እናቷ የምትጋግረውን ብስኩት በጣም ስለምትወደውና ስለናፈቃት በነገሩ ተስማምታ በትካዜ ተመስጣ ተቀመጠች፡፡

ወዲያውኑ እናት ዘይት በስኒ ይዛ በመምጣት አቀረበችላትና፣ “ይኸው ጠጪ” አለቻት፡፡ ልጅ ግራ ገባት፡፡ እናት እንደገና ሄደችና እንቁላሎችን ይዛ መጣችና ሰበር ሰበር አድርጋ በሳህን ውስጥ በመጨመር አቀረበችላት፡፡ ልጅ፣ “እናቴ አብዳለች” ብላ አሰበች፡፡ በመቀጠል እናት የተለያዩ ነገሮችን እያቀረበች “ብይ፣ ጠጪ” ማለት ጀመረች፡፡ ጨው … ቅመም … ዱቄት … በየተራ አንስታ እንድትበላቸው ሰጠቻት፡፡ ልጅ፣ “አብደሻል እንዴ? አነዚህን ነገሮች እንዴት እበላቸዋለሁ? አልወዳቸውም፣ አይጣፍጡም እኮ” አለቻት፡፡

አላማዋ እንደተሳካላት ያሰበች እናት ያመጣችውን ነገር ሁሉ ለቃቅማ በመሄድ ደባልቃ ብስኩቱን ከጋገረች በኋላ ይዛላት መጣች፡፡ ልጅ አጣጥማ በላችው፡፡

እናት፡- “አሁን የበላሽው ቅድም የሰጠሁሽን ነገሮች ነው”፡፡

ልጅ፡- “ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?”

እናት፡- “እነዚያን ነገሮች አንድ በአንድ ሳመጣልሽ አልወደድሻቸውም፡፡ በአንድ ላይ ሲደባለቁና ሲበስሉ ግን ጣፈጡሽ፡፡ ሕይወትም እንደዚህ ነው፡፡ ገጠመኞችሽን አንድ በአንድ ስታያቸው አይጣፍጡም፣ እንዲያውም መራራ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ገጠመኞችሽ “ሲገጣጠሙ” እና በአንድ ላይ ሲሆኑ ግን ግሩም ጣእም ይሰጣሉ፡፡ ጣእሙ የሚታወቅሽ ግን የኋላ ኋላ ሲበስሉ ነው፡፡”

በታሪኩ እንደተጠቀሰችው አይነት በኑሮ ውጣ ውረድ ያልበሰለ ማንነት ያለው ሰው እያንዳንዱን ስህተትም ሆነ የሕይወት ገጠመኝ ነጥሎ ለብቻው በማየት ሕይወትን ከዚያ አንጻር የመተርጎም ዝንባሌ አለው፡፡ ስህተትን ሲሰራ ስህተተኛ፣ ሲወድቅ ደግሞ ውዳቂ እንደሆነ ለማመን ይፈጥናል፡፡ መራራ ገጠመኞቹንና ያልተሳኩ ጥረቶቹንም እንዲሁ ራሱን ለማንቋሸሽ ይጠቀምባቸዋል፡፡ የሕይወትን ገጠመኞች አጠራቅሞ ሊኖራቸው የሚችላቸውን አስገራሚና ሁለንተናዊ ስእል ለማየት የሚሞክር አመለካከት የለውም፡፡ እንዲሁ ከአንዱ ገጠመኝ ወደሌላኛው ሲንገላታ ራሱን ያገኘዋል፡፡ ይህ አይነቱ አመለካከት ደግሞ አድካሚና በሆነ ባልሆነ ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርግ አመለካከት ነው፡፡

ሁለንተናዊ እይታ ማለት በሕይወታችን የምንሰራቸው ስህተቶችም ሆኑ የሚገጥሙን አጉል ገጠመኞች ለትልቁ የሕይታችን አላማ ለጥቅም እንዲውሉ የማድረግ አመለካከት ነው፡፡ በሌላ አባባል አንዱን ገጠመኝ ለብቻው ሳይሆን “ገጠመኞችን ገጣጥሞ” ማየት ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ዝም ብለን ውጤቱ መልካም እንዲሆን መጠበቅ ማለት አይደለም፡፡ በሁኔታዎቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ለዘላቂ ህይወታችን ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ መቅደድ ማለት ነው፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደረጃዎች ይህንኑ እንድናደርግ ይጠቅሙናል፡፡

(“እይታ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ ክፍል)

https://www.tg-me.com/Dreyob


https://m.youtube.com/user/naeleyob623
133👍108😱4🎉4
የታሰረው እግሩ ሳይሆን ጭንቅላቱ ነው!
የአመለካከት ቁልፍ
29👍13🎉2😁1
የምንችለውንና የማንችለውን ነገር የሚወስንልን ማን ነው? ለምን ይህንን ብቻ በማድረግ ተገደብን?

እነዚህን ጥያቄዎች ለራሳችን ጠይቀን እውነተኛውን መልስ ብናገኝ ያቃተን ነገር እስካሁን ድረስ ያልሞከርነው ነገር እንደሆነ እንደርስበታለን፡፡ ሰውነታችን አእምሮአችን የነገረውን ለመታዘዝና ለመፈጸም የተዘጋጀ ፍጥረት ነው፡፡ አእምሮዬ ትችላለህ ሲለው ሊሞክር፣ አትችልም ካለው ደግሞ ላይንቀሳቀስ ተገድቦ ይገኛል፡፡

በዚህ እውነታ ውስጥ የኦሎምፒክ ውድድሮች ክብረ-ወሰን የመስበራቸውንም ምስጢር እናገኘዋለን፡፡ የጨከነና ራሱን ያዘጋጀ ሰው ክብረ-ወሰንን እንደሰበረ ይኖራል - የራሱን ክብረ-ወሰን! ይህንን አትዘንጋ - የውስንነታችን የመኖሪያ ስፍራ አእምሮአችን ብቻ ነው!

አንድ ሰው የተለያዩ እንስሶች ለተመልካቾች ትእይንትን ወደሚያሳዩበት ስፍራ ገንዘቡን ከፍሎ ከገባ በኋላ ገና እንደተቀመጠ ያየው ነገር ግር አለው፡፡ ተራራ የሚያክለውን ዝሆን አንድ አጭር ሰው በትንሽ ሰንሰለት እግሩን አስሮ ወዲህና ወዲያ ያደርገዋል፡፡

“እንዴት አንዲት ቀጭን ገመድ ይህንን ግዙፍ እንስሳ ልታስረው ትችላለች?” አንድን ሰው ለመጠየቅ ወሰነ፡፡ ትእይንቱ አልቆ ሰው ሁሉ ሲበታተን ይህንኑ ጥያቄ በውስጡ እያጉላላ ወደ አሰልጣኙ እንደምንም ብሎ ደረሰ፡፡

በውስጡ የጠየቀውን ጥያቄ ለሰውየው በአንደበቱ ጠየቀው፣ “እንዴት አንዲት ቀጭን ሰንሰለት ይህንን ግዙፍ እንስሳ ልታስረው ትችላለች?”

መልሱ አጭርና ግልጽ ነበር፣ “ዝሆኑ ገና ሲወለድ ጀምሮ ነው ይህቺ ሰንሰለት በእግሩ ላይ የታሰረችው፡፡ ገና በለጋነቱ ሲታገላት አላሸነፋትም፡፡ የዝሆኑ ጥንካሬ ግን ይህችን ሰንሰለት መበጠስ ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል፡፡

ዝሆኑ በውስጡ፣ “ይህችን ገመድ በፍጹም አልበጥሳትም” ብሎ ስለሚያስብ እንደታሰረ ይኖራል፡፡ የታሰረው እግሩ ሳይሆን ጭንቅላቱ ነው፡፡

“አይኖችህ አይተው የሚነግሩህን አትመን፡፡ የሚነግሩህ ውስንነትን ነው፡፡ መገንዘብ የምትችለውን ያህል ተገንዘብ፣ የምታውቀውንና የምትችለውን ለይተህ እወቅ፣ ወደከፍታ የምትወጣበትን መንገዱን ታየዋለህ” – Richard Batch

አንድ ሰው ካለበት ወጥቶ መሆን የሚገባውን ለመሆን ከፈለገ የግድ እስከዛሬ ያመነውን ነገር ለጥያቄ ማቅረብ አለበት፡፡ ካለማቋረጥ፣ “ለምን?” ብሎ ካልጠየቀ ባለበት ሁኔታና አመለካከት ታስሮና ሃውልት ሆኖ ይኖራል፡፡

“ሁኔታዬ ለምን እንደዚህ ሆነ?” “ይህንን ነገር ለምን አልችለውም?” “ይህንን ነገር ለምን አመንኩት?” የሚሉትን ጥያቄዎች መጠየቅ አለበት፡፡

ሰዎች የተለያዩ ገደቦችን በፊታችን ሊያስቀምጡብን ይችላሉ፣ ከማሰብና ከመጠየቅ ግን ሊከለክሉን አይችሉም፡፡ መልስ የምታገኘው ስትጠይቅ ነው፡፡

እውነታና ብልሃት ላይ የምትደርሰው ስታስብ ነው፡፡ ዝም ብለህ ሁኔታህን በመቀበልና ከአመታት በፊት የተነገረህን ገደብ አምነህ መኖር ይበቃሃል፡፡

የተሳሳትከውን፣ “ተሳስቼ ነበር” በማለት አዲስ ነገርን ለመሞከር ካልተነሳህ ሁኔታህ አይለወጥም፡፡ ይህንን አስታውስ፣ እስካሁን ያልቻልከው ነገር ያልሞከርከው ነገር ነው፡፡ የገደቡህን ነገሮች እወቃቸው፣ ነገር ግን በፍጹም አትቀበላቸው፡፡ ያመንካቸውን መልእክቶች ደግሞ ለማጣራት ምንጩን ለይተህ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

1. ለራስህ የነገርከው

“ለራስህ የምትነግረው ነገርና የምታሰላስለው ነገር ባለጠጋ ወይም ደኃ፣ የተወደደህ ወይም የተጠላህ፣ ደስተኛ ወይም ኃዘንተኛ፣ ሰዎችን የምትስብ ወይም የምታርቅ፣ ኃይለኛ ወይም ደካማ የማድረግ አቅም አለው” - Ralph Charell

ከሌላ አካል ከምንሰማው ነገር የበለጠ ለራሳችን የምንነግረው ነገር ተጽእኖው እጅግ የላቀ ነው፡፡ ሰው ራሱን “ሊዘጋው” ወይም “አላናግርህም” ሊለው አይችልም - ሁሌ ከራሱ ጋር ነው፡፡ ሰው ሃሳብን ላለማሰብ የማይችል ፍጡር ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ የተስፋ መቁረጥ ወይም የተስፋ ጭላንጭል ምንጭ ሊሆን የሚችል እውነታ ነው፡፡ ተስፋ አስቆራጭ የሚሆንበት ምክንያት ለራሳችን የምንናገረውን መቆጣጠር ካቃተንና በጨለምተኝነት የተሞላን ሰዎች ከሆንን ነው፡፡

2. ሰዎች የነገሩህ

“አንደበታችንን በፈለግነው ጊዜ መክፈትና መዝጋት እንደምንችል፣ ጆሯችንንም እንደዚያ ማድረግ ቢቻል እንዴት ግሩም ነበር?” – Chinese Proverb

ጆሮአችን ምንም እንዳይሰማ ማድረግ አንችልም፣ በጆሮአችን የገባውን መልእክት ግን የማጣራትና የማይጠቅመንን በመጣል ጠቃሚውን ብቻ ማሰላሰል መብቱ የእኛ ነው፡፡ አይናችንም እንዳያይ ማድረግ አንችልም፣ ለምናየው ነገር የምንሰጠውን ምላሽ ግን መቆጣጠር እንችላለን፡፡

3. መገናኛ ብዙሃን የነገረህ

“ሁሉንም ስማ፣ የቱን እንደምታምን ግን በግልህ አመዛዝነህ ድረስበት” - George Eliot

እንደ እውነቱ ከሆነ የምታነብባቸው መጻሕፍትና የምታያቸው ፊልሞች የማንነትህ ነጸብራቆች ናቸው፡፡ ወይ ያንን ነህ፣ ወይም ደግሞ ወደ መሆን ትመጣለህ፡፡ ስለዚህ ወደ ማንነትህ የምታስገባቸውን መልእክቶች የምታጣራ ሰው ሁን!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍14657🔥4🎉2
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
መገፋትን ለጥቅም ማዋል!
(“የመገፋት ሕመም” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ ውስጥ የተወሰደ)

በጓደኝነት፣ በቤተሰብ፣ በፍቅር ግንኑነትና በመሳሰሉት ማሕበራዊ ግንኙነቶች ውስጥ የመገፋትን፣ የመገለልንና ያለመፈለግን ልምምድ በምትቀምስበት ጊዜ የሁኔታውን መልካም ጎን ለማየትና ወደፊት ለመዝለቅ የሚከተሉትን ሃሳቦች እንደመነሻ መጠቀም ትችላለህ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ በሰዎች መገፋትህ ከእነዚያ ከሚገፉህ አላስፈላጊ ሰዎችና ሁኔታዎች የምትለይበትና የምትጠቀምበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ አንዱ ሰው ስለገፋህ ሌላ የተሻለ ሰው፣ አንዱ ተቋም ስላገለለህ ሌላ የተሻለ ተቋም . . . የምታገኝበት ብቸኛ መንገድ ሊሆን እንደሚችል ማስታወስ፡፡

• አንዳንድ ጊዜ በመገፋት ውስጥ በተደጋጋሚ ስታልፍ ምናልባት ካለአግባብ የምትገፋበት አጉል ባህሪይ ሊኖርህ ስሚችል ራስህን እንድትጠይቅና ያንን አጉል ባህሪይ ለመለወጥ የምትችልበትን መንገድ መጀመር፡፡

አዎን! የመገፋትን ልምምድ ወደመልካም መለወጥ ይቻላል!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍13943🎉2
ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር

በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?


(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

1. ያጋጠማችሁ ወቅታዊ አስቸጋሪ ሁኔታ ካለና በራሳችሁ ለመወጣት ስላቃታችሁ እገዛ ከፈለጋችሁ፣

2. የሕይወታችሁን ራእይ ወይም ዓላማ ባለማወቅ ከተወዛገባችሁና አቅጣጫን መያዝ ከፈለጋችሁ፣

3. ካለባችሁ አጉል ልማድ በመውጣት አዲስ ልማድን ማዳበር ካስቸገራችሁና ምክርና ድጋፍ ከፈለጋችሁ፣

4. መመለስ ያቃታችሁ የሕይወት ጥያቄዎች ከበዙባችሁና በአንድ ለአንድ ውይይት የመፍትሄ መንገድ ከፈለጋችሁ፣

5. በራሳችሁ መወጣት ያልቻላችሁት የተያዩ የስሜትና የስነ-ልቦና ጥያቄዎች ውስጥ እንዳላችሁ ከተሰማችሁና ከሁኔታው ለመውጣት ምክር ከፈለጋችሁ፣

ከግል በተጨማሪም ቁጥራችሁ ከአስር ባልበለጠ ሁኔታ በመሰባሰብ የGroup Coaching and Training ጥያቄም ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡

በቴሌግራም

@DrEyobmamo

inbox በማድረግና በፌስቡክ መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን ማሳወቅ ትችላላቸሁ፡፡
49👍39🔥8😁1
የልማድ ምስጢር!
👍5
ውድ የማሕበራዊ ገጾቼ ተከታታዮች!

ከነገ ሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ የልማድን አስፈላጊነት አስመልክቶ ማለዳ በተለመደው ሰዓት (11 ሰዓት) ገና እንደነቃችሁ እና ማታ ከመተኛታችሁ በፊት በ 2 ሰዓት አጫጭር እውነታዎችን አጋራእኋለሁ፡፡

ለመክፈቻ ያህል “የልማድ ምስጢር!” የተሰኘ የመግቢያ ሃሳብ ከዚህ በታች አቀርብላችኋለው፡፡

የተወደዳችሁ ናችሁ የሃገሬ ውዶች!!!

የልማድ ምስጢር!

“ደጋግመን የምናደርገውን ነገር ነን፡፡ ስለሆነም፣ ልቀትና ምርጥነት የአንድ ጊዜ ተግባር ጉዳይ ሳይሆን የልማድ ጉዳይ ነው” - Aristotle

“እኔ የአንተ የዘወትር አጋርህ ነኝ፡፡ ታላቅ የሆንኩ ረዳትህ ነኝ ወይም ደግሞ ከባድ የምባል ሸክምህ፡፡ ወደ ስኬት ልገፋህ እችላለሁ፣ ወይም ደግሞ ወደ ውድቀት ልጎትትህ ብቃት አለኝ፡፡ ሁል ጊዜ እንዳዘዝከኝ ለመሆን ዝግጁ ነኝ፡፡ በየእለቱ ከምታደርጋቸው ነገሮች ገሚሶቹን ለእኔ አሳልፈህ ብትሰጠኝ ባፋጣኝና በትክክለኛው መንገድ አከናውናቸዋለሁ፡፡ ጠንከርና ጨከን ካልክብኝ፣ በቀላሉ ልትገራኝና ልታስተዳደረኝ ትችላለሀ፡፡ አንድ ነገር በምን መልኩ መደረግ እንዳለበት አሳየኝና ትንሽ ካለማመድከኝ በኋላ በፈለከው ጊዜ ሁሉ በፍጥነት አከናውንልሃለሁ፡፡ ታላላቅ የተሰኙ ሰዎች አገልጋይ ነኝ፤ ሆኖም የውድቀትና ያለመሳካትም ምክንያት እኔው ነኝ፡፡ ታላላቅ የሆኑን ሰዎች ታላቅ ወደ መሆን ያመጣኋቸው፤ የወደቁና ያልተሳካላቸውንም ሰዎች ለዚያ ያበቃኋቸው እኔ ነኝ፡፡ ማሽን አይደለሁም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ማሽን የተሰጠኝን ሁሉ ሳላዛባ፣ ልክ እንደሰው ደግሞ በብልህነት እሰራለሁ፡፡ ከፈለክ ለትርፍ ተጠቀምብኝ ካለዚያም ለክስረት ተጠቀምብኝ፣ በእኔ በኩል እንደሆነ ምንም ልዩነት አያመጣም፡፡ ውሰደኝ፣ የራስህ አድርገኝ፣ አሰልጥነኝ፣ ጠንከርና ጨከን በልብኝ እኔም በተራየ አለምን አስገዛልሃለሁ፡፡ ቀለል በልልኝና ችላ በለኝ፣ አጠፋሃለሁ፡፡ ማን ነኝ? እኔ ልማድ እባላለሁ!” – Anonymous

ልማድ ማለት በአንድ ነገር አቅጣጫ ራሳችንን ከማስለመዳችን የተነሳ ያንን ነገር በቀላሉ ማድረግ ስንጀምርና እንደውም ማቆም ሲሳነን ማለት ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ ለጤናማውም ሆነ ለጤና ቢሱ ልማድ የሚሰራ እውነታ ነው፡፡ ልማድ ማለት ካለምንም የውጭ ግፊትና ጉትጎታ ማድረግ የጀመርነውና “የማንነታችን” ክፍል ወደ መሆን የመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ከመልካም ልማድ ውጪ ማንም ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ በሌላ አባባል ወደ ልማድ ባልመጣ መልካም ነገር ወደ ስኬት መምጣት አንችልም፡፡

ብቃትና ጥራት ማለት የተለመደን ነገር ባልተለመደ መልኩ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ መልካምን ልማድ ማዳበር የግድ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ በአንድ ስፖርት ኦሎምፒክ ላይ የሚወዳደሩ ሰዎች በአማካኝ ካለማቋረጥ ለስድስት ዓመታት ሙሉ በአመት ለ310 ቀናት፣ በየቀኑ ለአራት ሰዓታት ልምምድ ያደርጋሉ፡፡ ሌሎች ሰዎች ቀኑን ሙሉ የማይሰሩትን ስራ እነዚህ ስፖርተኞች ጠዋት አንድ ሰዓት ከመሆኑ በፊት ሰርተው ይጨርሳሉ፡፡

አሁን ምንም አይነት የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰን ሰው ተመልከትና ጀርባውን አጥና፤ ለረጅም ጊዜ ደጋግሞ ያደረገውንና የገነባውን አንድ ነገር ታገኛለህ፡፡ በሌላ አባባል፣ አሁን የደረሰበት የላቀ ደረጃ የደረሰው በአጋጣሚ ሳይሆን አንድን መልካም ልማድ አዳብሮና በዚያ ልማድ ዙሪያ ደጋግሞ በመስራትና በመሻሻል ነው፡፡

የንጽህና ልማድ ቤትን፣ አካባቢንና አገርን በንጽህና ልቀው እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ የስራ ልማድ በብልጽግና ልቀን እንድንገኝ ያደርገናል፡፡ የጥናት ልማድ በእውቀት እንድንልቅ መንገዱን ይጠርጋል፡፡ ከማንኛውም ውብ ነገር ጀርባ መልካም ልማድ አለ፡፡ በእኔና በአንተም ኑሮ ስሌቱ ያው ነው፡፡

አንድ ቀን ከእንቅልፋችን ስንነሳ በአንድ ነገር ልቀን አንገኝም፡፡ ከአንድ ግብ አንጻር በየእለቱ የገነባናቸው ልማዶቻችን ናቸው የነገን ልቀታችንን የሚወስኑት፡፡ ልማድ የሕወታችንን አብዛኞዎቹን (ምናልባት ሁሉንም) ነገሮች አቅጣጫ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ጤንነታችንን፣ ኢኮኖሚያችንን፣ ወዳጅነታችንን የኑሮአችንን ጥራትና ሌሎችም ዋና ዋና ነገሮችን ስለሚወስን፤ ልማድ ሲጨመቅ ማንነት ይሆናል፡፡

ክፍል አንድን ነገ ማለዳ በ11 ሰዓት ይጠብቁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
100👍71😱1🎉1
ራእይን ያለማወቅ ምልክቶች እና መዘዞች!

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ወይም እነዚህን መሰል ሁኔታዎች ከታዩባችሁ ሕይወታችሁን አቅጣጫ የሚያስይዘው የራእይ ጉዳይ እንደጠፋባችሁ ጠቋሚ ነው፡፡

1. የውስጥ እርካታ ያለመሰማትና የባዶነት ስሜት

2. ምንም ሳያከናውኑ በእድሜ እየገፉ ስለመሄድ አብዝቶ ማሰብ

3. ይህንንም ያንንም ነገር እየጀመሩ ማቆም

4. ስለወደፊት ሲያስቡ ግራ የመጋባት ስሜት

5. ካለፈው ስህተት ጸጸት አልፎ መሄድ አለመቻል

6. በተለያዩ ገጠመኞች ምክንያት ቶሎ ተስፋ መቁረጥ

7. በሰዎች ሃሳብ ተጽእኖ ስር መውደቅና ከእነሱ ደስተኛነት አንጻር መኖር

ራእይን አለማወቅ መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ከሁሉም የላቀውና የከፋው መዘዝ ግን ይህንና ያንን ነገር ሲያደርጉ እድሜን የማቃጠል እና ጊዜ ካለፈ በኋላ የመባነን ሁኔታ ነው፡፡

ሁል ጊዜ የሌላውን ሃሳብ ሲያስፈጽሙ መኖርና የራስን ዓላማ እና አመለካከት ለመፈጸም ድፍረት ማጣት ሌላኛው መዘዝ ነው፡፡

ጓደኞቻችን፣ የትዳር አጋራችንና የቤተሰብ አባላቶቻችን የራሳቸውን ሕልምና ራእይ እየኖሩ እኛን ግን ሲከለክሉን ዝም ብሎ መቀበልም ሌላው መዘዙ ነው፡፡

ከዚህ ሁኔታ ለመላቀቅ ያላችሁ አማራጭ በጉዳዩ ላይ በሚገባ በማጥናት፣ በመማርና እርምጃ በመውሰድ መቅረፍ ነው፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የምክር እገዛ ያስፈልጋችኋል፡፡

ያንን ለማግኘት ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ጋር በአካል በመገናኘት የግል Counseling, Mentorship, Coaching and Guidance ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

(በውጪ ሃገር ያላችሁም በTelegram and WhatsApp ከዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ፡፡)

ከዚህ በታች ባለው የቴሌግራም አካውንት inbox በማድረግና ፍላጎታችሁን በማሳወቅ የበለጠ መረጃ ማግኘት ትችላላቸሁ፡፡

@DrEyobmamo
👍8725🎉1
በመጀመሪያ!

በመጀመሪያ እናንተ ከራሳች ጋር ሰላም ሁኑ! ያን ጊዜ ከሰዎች ጋርም ሆነ ከሰዎች ውጪ ሰላም ትሆናላችሁ፡፡

በመጀመሪያ የራሳችሁን ዓላማ በማወቅ መስመር ውስጥ ግቡ! ያን ጊዜ የሌላውን ሰው ዓላማ የመደገፍና የማስፈጸም አቅም ታገኛላችሁ፡፡

በመጀመሪያ የራሳችሁን ደካማ ጎን ተመልከቱና ያንን አስተካክሉ! የን ጊዜ የሌላውን ሰው ደካማ ጎን በቅንነት ለማረም ብቃቱን ታገኛላችሁ፡፡

በመጀመሪያ የራሳችሁን ቤተሰብ ተንከባከቡ! ያን ጊዜ የሌላውን ቤተሰብ ለመንከባከብ የሞራል ልእልና ትጎናጸፋላችሁ!

በመጀመሪያ ራሳችሁን ምሩ! ያን ጊዜ ካለምንም የሹመት ስልጣን በመልካም ተጽእኖ ብቻ ብዙዎችን የመምራት ከፍታ ላይ ትወጣላችሁ፡፡

መልካም ምሽት !!!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/https://www.tg-me.com/Dreyob
👍12148🎉1
አስር የልማድ እውነታዎች

ክፍል አንድ - ልማድና ዓላማ

“የየእለት ተግባራችን በሕይወታችን ቀዳሚነት የሰጠነውን ነገር ጠቋሚ ነው” – Mohandas Gandhi

አንድ ሰው ወደ አሰበበትና ወደ አቀደው ደረጃ ለመድረሰ ሊከተላቸው ከሚገባው መመሪያዎች አንዱ የየእለት ተግባሩን ወይም ልማዱን ከዋና ዓላማው አንጻር የመቃኘቱ ጉዳይ ነው፡፡ የምትውልባቸው ቦታዎች፣ የምትመርጣቸው ጓደኞች፣ የምትማረው ትምህርት፣ የምታነባቸው መጻህፍትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች በጥንቃቄ ከዋና ዓላማህ ጋር ሊጣጣሙ ይገባቸዋል፡፡

በሃሳብም ሆነ በተግባር ብዙውን ጊዜህን የምታሳልፍበትን ነገር በሚገባ ብታጤነው በሕይወትህ ቅድሚያ የሰጠኸውን ነገር ይጠቁምሃል፡፡ ይህ ድግግሞሽና ልማድ ደግሞ ውሎና አድሮ ማንነትህን የመቅረጽ ጉልበት አለው፡፡ በሌላ አባባል፣ ሁል ጊዜ ስታደርግ ራስህን የምታገኘው ነገር የሕይወትህን ቅደም-ተከተል ከማሳየቱም ባሻገር ነገ የት እንደምትገኝና ማን እንደምትሆን ይተነብያል፡፡

ስለዚህ፣ መሆን ከምትፈልገው ማንነትና መድረስ ከምትፈልግበት ዓላማ አንጻር ልማድን ማዳበር እጅግ ወሳን ጉዳይ ነው፡፡

ክፍል ሁለትን ማታ በሁለት ሰዓት ይጠብቁ!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍12744😁2🔥1🎉1
እንደገና መጀመር!

በቃ አንዳንድ ጊዜ እንደገና ለመጀመር መቁረጥ የሚገባን ነገር አለ፡፡

• ያለፈው እንዳበቃለት ውስጣችን ሲያውቀው . . .

• ቀድሞ የነበረውን፣ አሁን ግን የሌለው፣ እኛ ግን ልክ እንዳለ አድረገን ለማሰብ በክህደት አለም ውስጥ እንደሆንን ስናውቀው . . .

• ከዜሮ መጀመርም ካለብን ውስጣችን መቁረጥ እንዳለበት የውስጥ መረዳቱ ሲመጣልን . . .

• ያለቀለትን ነገር እንደገና ሕይወት ለመዝራት የሚያስከፍን ዋጋ የማያዛልቀን እንደሆነ በሙከራ ስንደርስበት . . .

• ከምንችለው በላይ አድርገን እንደበቃን ውስጣችን ሲነግረን

. . . እንደገና መጀመር! ከዜሮም ቢሆን!

መልካም ራስን የማየት፣ መልካም ከራስ ጋር የመመካከር፣ መልካም ካለማንም ሰው ጣልቃ ገብነት ከራስ ጋር የመስማማት ምሽት!

https://www.tg-me.com/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
👍9040🔥1😱1🎉1
2025/07/08 22:05:39
Back to Top
HTML Embed Code: